November 7, 2023
16 mins read

አማራ ሆይ የመጣብህ ፈተና የከፋ ነውና መከፋፈልን ትተህ “ድርና ማግ ሁን”

362279578 877222194248616 8394952406458389026 n 1 1 1

በ16ኛው ምዕተ ዓመት በኦሮሞ ፣ በግራኝ መሃመድ እና በቅርቡ ሕውሃት አማራን ድምጥማጡን ለማጥፋት እና ዕርስቱን ለመንጥቅ  ከተደረጉት ወረራዎች የዘንድሮው የአያቶቻቸውን የወራሪነት ውርስ ያጠለቁት እና የተላባሱት የኦሮሙማው ብልፅግና ዐይን ያወጣ ድፍረት እና ጦርነት እጅጉን የከፋ ፣ በኢትዮጵያ ሆነ በዓለም ታሪክ ሊረሳ ፣ ይቅር ሊባል የማይገባው እና መላው የአማራ ህዝብ “ድር እና ማግ” ሆኖ ሊመክተው የሚገባ ክስተት ነው ።

ይህን ቅጥ ያጣ ፣ መርህ አልባ እና አጉራ ዘለል ወረራ የአማራ ሕዝብ ከአያት ቅድመ አያቶቹ በወረሰው መሪ ተቋሙ “ፋኖ “ ስር ተዋቅሮ ይህን ገዳይ ፣ ደፋሪ እና ተስፋፊ ቡድን እየለበለበው እና አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ይገኝል።

ይህን መሰሉን ወረራ ለዘመናት የአማራ ሕዝብ እየተጋፈጠ ፣ የግፈኞችን ሴራ እየመከተ ፣ ህይወቱን እና ደሙን ግብሮ ለድል ቢበቃም ላለፉት አምሳ ዓመታት በላይ የሥልጣን ባለቤት ሳይሆን መንበረ የስልጣን ዕርካቡን ለማይመለከታቸው መሰሬ ፣ ሴረኞች እና ለድል አጥቢያ አርበኞች አሳልፎ ሲሰጥ ኑሯል።

ይህ ከሆነበት ዋነኝው ምክንያቶች መካከል አንደኛ እና ዋነኛው ከእራሱ አብራክ በወጡ “ከእኛ በላይ አማራነት ለአሳር” በሚሉ ፣ የአማራነታቸውን የታሪክ ዳፋ በወጉ ባልተረዱ የዋህ አማራዊያን እና በስመ አማራ ተብየዎች በሚከወኑ አሉታዩ የሆኑ ድርጊቶች እና ተፅእን ነው።

ሌላው ደግሞ ሴረኞች በጫኑበት አጓጉል ትርክት ፣ አስተሳሰብ እና አመለካከት እርስ በእርስ አማራ በሽሙጥ ፣ በአሽሙር ፣ በንግግር እና “አንተ እንዲህ ነህ ፣ እሱ እንዲህ ነው” እንዲባባል ፣ እንዲሸራረድ ፣ ያልተገቡ መገለጫ ስሞችን እንዲለዋወጥ ሆን ተብሎ በመደረጉ አማራው እርስ በእርሱ እንዳይተማመን እና የጎሪጥ እንዲተያይ ለረዥም ዘመናት ሲደረግ ቆይቷል።

የአማራ ህዝብ መነሻ ፣ አሻራ እና መሰረት በሆኑት በጎንደር ፣ በሽዋ ፣ በጎጃም እና በወሎ ሕዝቦች መካከል የመራራቅ ፣ የመናረት ፣ የአለመተሳሰብ እና  የባዕድነት ስሜት ሆን ተብሎ ባአሻጥር እንዲዳብር ፣ እንዲነሳሳ እና እንዲዛራ በመደረጉ እና እየተደረገም በመሆኑ ለዘመናት ከአያት ቅድመ አያቶቹ ሲወርድ ሲዋረድ ጨብጦት የነበረው የአማራው ኃያል ክንዱ እንዲዝል እና የሥልጣን ባለቤት ውርስ ውቅሩ ደምጥማጡ እንዲጠፋ ሲደረግ ቆይቷል።

ከሁሉም በላይ መንግስታት “እነዚህ ናቸው ያንተ መሪዎች” ብሎ “በስማ በለው” አማራ ያልሆኑ እንደ ብአሕዲን እና የኦሮሞ ልፅግናዎች ውላጅ የሆኑ ባለስልጣኖችን ፣ ጭቃ ሹሞችን እና የስራ ኃላፊዎችን እየሰየመ ይሾምበት ስለነበር የአማራ እድገቱ ፣ ህልውናው እና ማንነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው።

እግዚአብሔር መጀመሪያ አዳም እና ሔዋንን በልጅ በእየሱስ ክርስቶስ ገፅ እና አምሳል በአራቱ ወንዞች የኢትዮጵያን የአባይን ምንጭ የኤደንን ወንዝ አካቶ የሰውን ልጅ ፈጠረ።  ከዚያም “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት” ዘፍ.1:28 ብሎ  በቃሉ ባዘዘው መሰረት የአምላክ የተስፋ ቃል እውን ይሆን ዘንድ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ጣራ ነክቶ ወደ ስምንት ቢሊዮን አካባቢ ደርሰናል።

ይህን ያልንበት ምክንያት አምላክ ሰውን ፈጠረ እንጂ ነገድን ( በአሁኑ አጠራር ብሔርን) አልፈጠረም። ሰው አብሮ በመኖር ማህበራዊ ፣ ባህላዊ ፣ ኢኮኖማያዊ ፣ መሰላሰልን እና መሰባሰብ ገቢርን እያዳበረ ነገድን (ብሔርን) መሰረተ ፣ አደራጀ።

በነገድ ( ብሔር ) የተሰባሰቡ ማህበረሰቦች ደግሞ ተግባብተው ስሉጥ የሆነ ሕይወት ይኖር ዘንድ በእግዚአብሔር ተራዳይነት የሱ ፈቃድ ሆነና የሰው ልጅ አፉን ከፈቶ ይናገር ዘንድ ቋንቋን ቸረው።

እንግዲህ ይህን እውነታ መሰረት አድርገን ስናይ አማራ ፣ ትግሬ ፣ ኦሮሞ ፣ ሱማሌ፣ ጉራጌ ፣ ሃዲያ ፣ ወላይታ ፣ ስልጤ ፣ ሐረሬ ወ.ዘ.ተ. የተባሉ ነገዶች (ብሔሮች) እና የተለያዩ ቋንቋዎች የሰው ልጅ ከተፈጠረ ከረጅም ዘመናት በኋላ የተዋቀሩ ፣ የተሰሩ እና የተገነቡ የማንነት ውቅሮች እንጂ ስንፈጠር ሆነ ስንወለድ እንደ ዐይን ፣ ጀሮ ፣ አፍንጫ ፣ የራስ ቅል እና ወ.ዘ.ተ. አካላችን ብሔር ፣ ነገድ እና የቋንቋ ልዩነት ማንነቶቻችን በአምላክ እግዚአብሔር የተቸረን እና የተበረከተልን አብረውን የተፈጠሩ ስጦታዎች እና በረከቶች አይደሉም።

ነገር ግን ዋናው ሊታወቅ የሚገባው የትኛው ነገድ ነው ቀድሞ እራሱን በማንነት አደራጅቶ ለሃገረ ግንባታ ፣ እድገት እና ለውጥ ትልቁን ሚና የተጫወተው ? የሚለው ጥያቄ መልስ ሊቀመጥለት የግድ የሚል ይሆናል።

ታሪክ እንዳስቀመጠው የአማራ ታሪክ ከእየሱስ ክርስቶስ መወለድ 360 ምዕት ዓመት በፊት ጀምሮ በድሮ ስሟ “አቢሲንያ” ከዚያም በአባታችን “ ኢትዮጺስ” አማካኝነት “ኢትዮጵያ “ ተብላ ከተሰየመች በኋላም ቢሆን በሃገር ግንባታው ፣ ከወራሪ በመከላከል እና ደንበር በማስጠበቅ በኩል ታላቁን ሚና የተጫወተው የአማራ ነገድ መሆኑ አሌ የማይባል ጉዳይ ነው።

አማራ ከሁሎችም ነገዶች በፊት የተገነባ ፣ የተደራጀ እና ለአክሱም ስልጣኔም ታላቁን አስተዋፅኦ ያበረከተ ነገድ ነው። ቀደምት እና ሰፊ የቆዳ ስፋት የነበራትን  የአበሻ ምድር አቢሲኒያን የአሁኗን ኢትዮጵያን ከአረቦች ፣ ከህንድ ናፓታወች ፣ ከሩቅ ምስራቅ ወ.ዘ.ተ. ጋር ሰፊ የንግድ ልውውጥ እንዲኖራት ከማድረግ ባሻገር ደሙን እፍሶ እና አጥንቱን ከስክሶ ከአምሳ ዓመት በፊት የነበረችውን ዕፁብ ድንቅ የሆነች ኢትዮጵያን ከነሙሉ ቁመናዋ እድትቀጥል አድርጎ ያቆየ የአማራ ነገድ ነው።

አክሱም ላይ ገኖ የነበረው የአማራ ነገድ የመሪነት ፣ የወታደራዊ እና የአስተዳደር የበላይነቱ እየደከመ እና የአረቦች ኃይል እየበረታ ሲመጣ በምዕራብ በኩል በስናር ( በአሁኗ ሱዳን) በገባው የአማራ (ኢምራይት) ፣ በደቡብ በኩል ፣ ነባር ወደሆኑት አማራዊያን ወገኖቹ አማራ ሳይንት ፣ ቡግና ፣ የከለው አማራ ነገዶች ወደ ሆኑት ወልቃይት ፣ ጠገዴ ፣ ጠለምት እና እራያ በኩል ስልጣኔዎን ይዞ በመጓዝ የአማራነት ባህሉን እያስፋፋ መላ ኢትዮጵያን ገናና አድርጎ ያስረከበ ታላቅ ነገድ ነው።

ከላይ የታተተውን የአማራ ነገድ ታሪክ ለጊዜው ገታ እናድርግና  “አማራ ሆይ መከፋፈልን ትተህ ‘ድርና ማግ ሁነህ’ ቁም” በሚለው ዋና ርዕሳችን ላይ እናተኩር።

ኢትዮጵያዊያን ብሔር ብሔረሰቦች የተለያዩ አግባብ ያልሆኑ ተለጣፊ ስሞች እየተሰጣቸው ለዘመናት ቢዘልቁም ይህ አካሄድ ብዙም ጉዳት ያላደረሰ እና ማህበረሰቡም ቦታ ስላልሰጠው እየሳቀ በፈገግታ አሳልፎታል።

ከሕውሃት ሥልጣን መያዝ በኋላ ግን የአንድ ብሔር አባላትን ያልተላበሱትን የብሔር ማንነት በመለጠፍ ለማሸማቀቅ ፣ ከነገዳቸው ፣ ከማንነታቸው እንዲርቁ እና የሚወክላቸውን ብሔር በእውቀታቸው ፣ በሙያቸው ፣ በገንዘብ እና በተቻለው ሁሉ እንዳይደግፉ ትልቅ ስራ ተሰርቷል።

የአማራ ምድር (ክልል ለማለት-አማራን አይመጥንምና) አቃፊ እና የመላ ብሔር ብሔረሰቦች መናህሪያ ነው። ከዚህ ባሻገር የደሙ ክፋይ የሆኑ ግን በተለያየ ምክንያት ፣ የሕውሃት ፣ የኦነግ እና የኦሮሞ ብልፅግና አሻጥረኞችና መሰሪዎች ሰለባ እንዲሆኑ በመደረጉ እና እነዚህ ህዝቦች የብሔር ማንነት ሊሰጧቸው በመሞከሩ ማለትም በአማራ ምድር በሚኖሩት እንደ “ቅማንት” ፣ ይሁዲዎች ፣ አገዎች ፣ አርጎባዎች እና  ወ.ዘ.ተ. ባሉ ማህበረሰቦች ላይ በተሰሩት ደባዎች እና ሻጥሮች ምክንያት ማህበረሰቦቹ ከአማራ ወንድሙ ሕዝብ ጋር በሰላም ተቃቅፈው እና ተዋድረው እንዳይኖሩ ብዙ አፀያፊ ፣ አለያይ እና የጥላቻ ድር እና መቃቀር እንዲፈጠር ሆን ተብሎ ተሰርቶበታል ።

የሚያሳዝነው ደግሞ የህውሃት ፣ የኦሮሞ ብልፅግና እና የኦነግ ቡድን ተላላኪዎች አማራ በመምስል በአማራ አደረጃጀት ውስጥ ሰርገው በመግባት አማራዊያንን ለመከፋፈል እና ይህን ፅዩፍ ተልዕኮ ለመፈፅም እና ለማስፈፀም ብሎም የጋራ ትግሉ እንዲስተጓጎል ከዚያም አልፎ የአማራውን ሕዝብ  በዕቡዕ ፣ በሴረኝነት እና በደባ መርዛቸውን በመርጨት ለማቃቃር ያልሄዱበት እርቀት የለም።

አማራ በጎንደር ከትግራይ እና ከኤርትራ ጎጃም ከኦሮሞ ፣ ወሎ ከትግራይ እና ከአፋር እንዲሁም ሽዋ ከኦሮሞ ጋር ይዋሰናል።

አማራ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች መዋሰኑ እና አብሮ ከወንድም ሕዝቦች ጋር አቃፊ ሆኖ መኖሩን እንደ ክፍተት በመቁጠር ጎንደሬ አማራውን ትግሬ ፣ ኤርትራዊ ፣ ቅማንት ፣ ጎጃሜውን ኦሮሞ ፣ ወሎየውን ትግሬ እና ኦሮሞ ፣ ሸዋውን አማራ እና ኦሮሞ እያሉ የሌለበትን ማንነት እየሰጡ የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል እና እርስ በርሱ የጎሪጥ እንዲተያይ ፣ የህወሃት ፣ የኦሮሞ ብልፅግና እና የኦነግ ሰለባ እንዲሆን እንዲሁም ከትግሉ እንዲሸሽ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።

ይህን ሰይጣናዊ የባንዳ ፣ የተላላኪነት እና የመሰሬነት አካሄድ ተሸክመው እና የአማራ ካባ ለብሰው የሚንቀሳቀሱትን እና የሚሽሎኮለኩትን አሸክቶችን “ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል” ልንላቸው ይገባል።

በተለይ ይህን የተንኮል እና ኋላ ቀር አጀንዳ ተሸክመው በዲያስፖራው አደረጃጀት የሚንቀሳቀሱ አማራ መሰል እስስቶችን ፣ ከፋፋዮችን፣ዘራፊዎችን እና ሴረኞችን በቃችሁ ልንላቸው ይገባል። የአማራነትን ሆደ ሰፊነት ፣ ልበ ሙሉነት ፣አቃፊነት ፣ ስሉጥ ማንነት ፣ የታሪክ ባለቤትነትን ለመናድ የሚሯሯጡትን ግለሰቦች ሆነ ቡድኖች ብዙ እርቀት ሳይሄዱ እንዲጋለጡ ፣ እርቃናቸውን እንዲቀሩ እኛ አማሮች“ ድር እና ማግ ሁነን” ልናወግዛቸው የሚገባ ይሆናል እንላለን።  በጋራ ክንዳችን እኛ አማሮች የድል ባለቤት እንሆናለን ፣ አንጠራጠርም።

 

ተዘራ አሰጉ

 

ከምድረ እንግሊዝ ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

186957
Previous Story

የአማራን መሬት በጦርነት እወስዳለሁ” ጄነራሉ | “ትግሉን የሚጎትቱ ኃይሎችን አንታገስም” | አሁናዊ የፋኖ መብረቃዊ ድሎች በሁሉም ግንባር

186972
Next Story

የችሎት ዜና! “ከኦህዴድ መንግስት ፍትሕ አንጠብቅም” The Voice of Amhara

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop