December 19, 2023
23 mins read

ኦነግ፣ የሞተና የበሰበሰ ድርጅቱና፣ ጸያፍ፣ ናዚዛዊ ፣ አደገኛው አስተሳሰቡ

393727061 10230813036500235 143759728525390040 n 1 1

ግርማ ካሳ

ኦነግን በተመለከተ ሰዎች የተለያዩ አመለካከቶች አሏቸው፡፡ ለኔ ኦነግ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው ድርጅቱ ወይም ድርጅቶቹ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አስተሳሰቡ፣ የፖለቲካ ፍልስፍናው ነው፡፡ እነ አብይ አህመድ ኦነግ ናቸው ስንል፣ ኦነግ የተባለው ድርጅት ውስጥ ያሉ ናቸው ማለታችን አይደለም፡፡ የኦነግ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው ማለታችን እንጂ፡፡ እነ ጃል መሮና እነ ሺመለስ አብዲሳ አንድ ናቸው ስንል፣ በአንድ ድርጅት ውስጥ ያሉ ናቸው ማለታችን አይደለም፡፡ ለስልጣን ይኸው እየተገዳደሉ አይደለም እንዴ ? ነገር ግን ሁለቱም አንድ አይነት ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው ማለታችን ነው፡፡

የኦነግን አመሰራረት ከሜጫና ቱሉም ማህበር ጋር፣ የኦሮሞ ብሄረተኞች ያገናኛሉ፡ ያ በጣም የተሳሳተ ነው፡፡ ምንም አይገናኙም፡፡ የሜጫና ቱሉማ ማሀበር በዋናነት ገበሬው የመሬት ባለቤት እንዲሆን፣ በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ፣ በኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎቶች እንዲሰጡ፣ የኦሮሞ ቅርስ፣ ባህልን ማሳደግ እንዲቻል የሚታገል፣ ኦሮሞን ለመጥቀም፣ ለ እኩልነት የሚሰራ የነበረ ማህበር እንደሆነ ነው የሰማሁት፡፡ የሜጫና ቱሉማ ማህበር ጥያቄዎች፣ በወቅቱ መመለስ የነበረባቸው የሁሉም ዜጎች ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

እዚህ ማህበር ውስጥ እውቁ ጀነራል ታደሰ ብሩም እንደነበሩበት ይነገራል፡፡ ጀነራል ታደሰ ኢትዮጵያን ያገለገሉ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱ ትልቅ ሰው ነበሩ፡፡ ኔልሰን ማንዴራልና ጓዶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጡ ጊዜ ስልጠና የሰጧቸው እነ ጀነራል ታደሰ ብሩ ነበሩ፡፡ ጀነራል ታደሰን አሳንሰው ፣ የኦሮሞ ብሄረተኛ አድርገው ለማቅረብ ለማቅረብ የሚሞክሩ ማፈር ነው ያላባቸው፡፡ ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ እንደ ጀነራል ጃጋም ኬሎና ሌሎች ፣ የኢትዮጵያ ጀግና ነበሩ፡፡

በ1959 ዓ/ም በጃንሆይ ዘመን፣ ሜጫና ቱሉም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ አመራሮቹም ይበታተናሉ፡፡ ጀነራል ታደሰ የቁም እስረኛ ይሆናሉ፡፡ በኋላ በገለምሶ አካባቢ ይታሰራሉ፡፡ የሜጫና ቱሉማ አንዱ አመራር፣ አቶ ሁሴን ሶራ ወደ ሶማሊያ ይሄዳል፡፡ በሶማሊያ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ( ENLF – Ethiopian National Liberation Front) የሚል ያቋቁማል፡፡ ትንሽ እንቆየ፣ ኢትዮጵያ ጠሎች እየበዙ፣ የነ ሲያድ ባሬ ተጽኖ ተጨምሮበት፣ ኢትዮጵያ የሚለውን በኦሮሞ ቀይረው፣ የኦሮሞ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር፣ ONLF- Oromo National Liberation Front) የሚል ድርጅት ይፈጠራል፡፡ (እዚህ ጋር አሁን ONLF ከሚባለው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ጋር እንዳንደባልቀው፡፡ ያኔ የኦጋዴን ነጻ አውጭ የሚባል አልነበረም፡፡ የምእራብ ሶማሎያ ነጻ አውጭ የሚባል እንጂ፡፡ ) አቶ ሁሴን ሶራ የ ONLF ዋና ጸሃፊ ሆነ፡፡ ዋና ጸሃፊ ማለት መሪ ማለት ነበር፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ የኢሰፓ ዋና ጸሃፊ እንደነበሩት፡፡

393727061 10230813036500235 143759728525390040 n 1 1 393729756 10230813036340231 8043973150951966196 n 1 1 393740349 10230813036460234 421082359206778696 n 1 1

አቶ ሁሴን ግንባራቸውን ከሶማሊያ ወደ ሃረርጌ ለማስገባት ሞከሩ፡፡ የሶማሌ ፖሊስ ችግር እንዳይፈጠር በሚል አከላከላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሞከሩ፡፡ ተሳካላቸው፡፡ አብዱል ክሪም ሃጂ ኢብራሂም በሚባለውና ጃራ አባገዳ የሚል የጦር ስም በነበረው፣ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የሙስሊም አክራሪ መሪነት በሃረርጌ መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ሆኖም እንቅስቃሴያቸው ተደርሶበት እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ ተበታተኑ፡፡ እነ ጃራም ሸሹ፡፡ ሁሴን ሶራ በየመን አድርጎ ወደ ቤህሩት ሄደ፡፡ በ1960 አካባቢ ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ የመጀመሪያው በኦሮሞ ስም የተደረገ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ከጅማሬው የከሸፈው የትጥቅ ትግል፡፡ሙሉ ለሙሉ የሃረርጌ ሰዎችን ብቻ ያቀፈ፡፡

እስከ 1966 ድረስ፣ በውጭ አገር ከሚደረጉ ስብሰባዎችና፣ ውይይቶች በቀር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት፣ በኦሮሞ ስም ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ድርጅት አልነበረም፡፡ በየካቲት 1966 አብዮቱ ሲፈነዳ፣ ስልጣን የያዘው ደርግ በውስጥ ትልቅ ችግር ውስጥ ስለነበረ፣ በባሮ ቱምሳ አቀነባባሪነት በሚስጥር በአዲስ አበባ ስብሰባ ተደረገ፡፡ እነ ሁሴን ሶራ ከቤህሩት፣ ሌላ ደገሞ ሃሰን ኢብራሄም የሚባል፣ በየመን የኦሮሞ አክቲቪስቶችን ቤቱ ሲሰበስብ የነበረ፣ ከየመን መጥተው በስብሰባው ተካፈሉ፡፡ አሁን የሚታወቁ እነ ሌንጮ ለታ፣ ገላሳ ዲልቦ ዲማ ነግዎ የመሳሰሉትም እንደዚሁ፡፡ ያኔ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (OLF) በሃረርጌ ኦሮሞዎችና በወለጋ ኦሮሞዎች በይፋ ተመሰረተ፡፡ የወታደራዊ ዊንጉም በሃረርጌ ገለምሶ አካባቢ፣ ጨርጨር ተራራች ላይ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት OLA፣ ተባለ፡፡ ሃሰን ኢብራሄም ፣ የትግል ስሙ ኤሌሞ ቂልጦ የኦላ መሪ ተደረገ፡፡

ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ አብዮቱ ሲፈነዳ ተፈቱ፡፡ እዚህ ጋር ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው፣ እነ ባሮ ቱምሳ በሚስጥር የጠሩት ስብሰባ ላይ አልነበሩበትም፡፡ ኦነግ ከሚባለው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸው፡፡ ሳይጋበዙ፣ ሳይጠየቁ ቀርተው አይመስለኝም፡፡ እነ ጀነራል ታደሰ ኢትዮጵያዊነታቸው ከኦሮሞነታቸው ጋር ስለማይጋጭባቸው፣ የጸረ ኢትዮጵያ ቡድን አካል የመሆን ፍላጎት ስለሌላቸው፣ ስለሌላቸው ብቻ ሳይሆን ይታገሉትም ስለነበር እንጂ፡፡

በወቅቱ ደርግ ጀነራል ታደሰ የአገር አስተዳደር ሚኒስቴርነት እንዲሆኑ ሁለት ጊዜ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ ጀነራሉ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ፣ ደርጎች ጥርስ ነክሰውባቸው፣ ያው ነፍሰ ገዳዮችና ዱርዬ ስለነበሩ፣ እነ ጀነራል አማን አንዶምን፣ ልጅ እንዳልካቸውን እንደረሸኑት፣ ጀነራል ታደሰ ብሩንም ገደሏቸው፡፡ የርሳቸውም መገደል ከኦሮሞነታቸው ጋር ምንም አይጋናኝም፡፡

እነ ኤሌሞ ቂልጡ ፣ ኦላዎች፣ በጨርጨር ተራሮች እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ በባለስልጣናት ላይ ጥቃት ፈጸሙ፡፡ ደርግ ጦር ሰራዊት ልኮ፣ የአጸፋ ምላሽ ሰጣቸው፡፡ ተደመሰሱ፡፡ ኤሌሞ ቂልጡም ተገደለ፡፡ ኦነጎች ከጅምራቸው ከፍተኛ ውዥንብር ውስጥ ወደቁ፡፡ ያለቻቸው ትንሿ ጦር ተበታተነች፡፡

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፣ ያ አልበቃ ብሎ፣ ሌላ ትልቅ ችግር ኦነጎች አጋጠማቸው፡፡ ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ለመውረር በዝግጅት ላይ እያለ፣ ቆቱዎች (የሃረር ኦሮሞዎች) እንዲያግዟቸው፣ ኦነጎችን ማግባባት ጀመረ፡፡ አብዛኛውን ኦጋዴን ወደ ሶማሊያ የቀላቀለ ካርታ አሳያቸው፡፡ ያኔ እነ ባሮ ቱምሳ ተቃወሙ፡፡ ወለጋዎቹ፡፡ ሃረሮቹ እነ ጃራ አባ ገዳ ከሲያድ ባሪ ጎን ቆሙ፡፡ በኦነጎች መካከል ትልቅ መከፋፈል ተፈጠረ፡፡ እነ ጃራ አባገዳ ፣ ባሮ ቱምሳን ሃረርጌ ላይ ገደሉት፡፡ ከባሮ ቱምሳ ጋር የነበሩ የኦነግ ሰዎች፣ ከሞት የተረፉት፣ ሃረርጌን ጥው፣ ወደ ቦረና ሄዱ፡፡ በሃረርጌ እስላማዊ ኦነግ፣ የነ ጃራ ኦነግ ብቻ ቀረ፡፡ ያው ብዙዎቹ የወለጋ ሰዎች ስለሆኑ፣ ከቦረና የተወሰነ ኃይል ወደ ምእራብ ወለጋ ሄደ፡፡ አብዛኛው ከፍተኛ አመራርም ከአገር ለቆ ጠፋ፡፡ ቦረና ኬኒያ ድንበር፣ ወለጋ ሱዳን ድንበር አካባቢ ፣ በየጫካ እንደ ሽፍታ ውርውር ከማለት በቀር፣ ከ1970 እስከ 1983 ዓ/ም ኦነግ የሚባል ያን ያህል ተሰምቶ አያውቅም ነበር፡፡በበርሊን፣ ሜኒሶታ፣ ግብጽ .. የኦነግ ጽ/ቤቶች አሏቸው፡፡ በውጭ ይጽፋሉ፣ ይታገላሉ፣ ይጮሃሉ፡፡ ግን አገር ቤት ሜዳ ላይ ብናኞች ነበሩ፡፡

ህወህትና ሻእቢያ ደርግን ለማዳከም በወለጋ በኩል፣ የኦነግ ሰራዊት መስለው ፣ ካሉት የኦነግ ጥቂት ሽፍታዎች ጋር በመሆን፣ በደርግ ዘመን መጨረሻ ሰሞን፣ በአሶሳ ከ200 በላይ ዜጎች በአንድ ቤት አድርገው አቃጠሉ፡፡ እንግዲህ ኦነግ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በብዙ ህዝብ ዘንድ የተሰማው የአሶሳውን እልቂት ተከትሎ ነው፡፡ በእልቂትና በጭፍጨፋ ነው ኦነግ ለመጀመሪያ ጊዜ በገሃድ የታወቀው፡፡

ህወሃት ለአዲስ አበባ፣ ሻእቢያ ለአስመራ ሲቀርቡ፣ ኦነግም በለስ እየቀናት መጣ፡፡ ህወሃቶችና ሻእቢያዎች የአንድነት ኃይል የሚሏቸውን ለማዳከም፣ ኦሮሞን ከሌላው መለየትና የኦሮሞ ብሄረተኝነትን ማጠናከር ብቸኛ አማራጭ አድርገው ወሰዱት፡፡ ያኔ እማራ ምናምን አይባል ነበር፡፡ ለዚህ ስትራቲጂያቸው ኦነግ ስላሰፈለጋቸው ኦነግ ከነርሱ ጋር አብሮ መቀመጥ ጀመረ፡፡ አብዛኛው ኦነግ የሚፈልገውን ፣ ኦሮሚያ የሚል ክልል ተሰጠው፡፡ የላቲኑን ፊደል እንዲጠቀም ተፈቀደለት፡፡

ህወሃቶች ኦነግ ላይ እምነት ስለሌላችው፣ በአንድ በኩል ኦነግን እየተለማመጡ፣ በሌላ በኩል በብዛት የአርሲ ሰዎች የበዙበትን ኦህዴድን ማጠናከር ጀመሩ፡፡ ከሁለት አመት በኋላ፣ ኦነጎችን በካልቾ ብለው፣ አዋርደው ካባረሩ በኋላ ፣ ኦሮሚያ ብለው የሸነሸኑትን፣ ኦህዴድ እንዲያስተዳደር አደረጉ፡፡ እነርሱ ከበላይ ኦህዴዶችን እየተቆጣጠሩ፡፡

ኦነግ እንደ ድርጅት ከየውጭ አገራር ተለቃቅሞ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የገባው፡፡ ሁለት አመት በአገር ቤት ሲንቀሳቀስ ፣ የቀድሞ ኦሮሞ የሆኑ የተበተኑ የደርግ ወታደሮች ሰብስቦ ጦር አለኝ ማለት ጀምሮም ነበር፡፡ ሆኖም በቀላሉ ህወሃቶች ጦሩን የኦነግን ጦር በተኑት፡፡ አመራሮቹም እነ ሌንጮ ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡ እነ አብይ አህመድ ስልጣን እስኪይዙ ድረስ ኦነግ በውጭ የሚጮህ ብቻ ድርጅት ሆኖ ቀጠለ፡፡ የትጥቅ ትግል አድርጋለሁ እያለ በወያኔ ዘመን አንዲተ ቀበሌ ተቆጣጥሮ አያውቅም ነበር፡፡ አመራሮቹ የተወሰኑት በተሰነይ ፍየል ጠባቂ፣ የተቀሩት አንዲ በርሊን፣ ሌላ ጊዜ ሚኔሶታ የሚንከራተቱ ሆኑ፡፡ እርስ በርስ ተከፋፈሉ፡፡ እነ ሊንጮ ለታ፣ ዲማ ነግዎ ኦነግ ለቀው ወጡ፡፡

እነ አብይ አህመድ ስልጣን ሲይዙ፣ ልጅ ወያኔ አዲስ አበባ ስትገባ እንደሆነው አሁን የኦነግ መሪዎች ተለቃቅመው ወደ አገር ቤት ገቡ፡፡ አስመራ አለን ይሉት የነበረውም ጦራቸው ወደ አገር ቤት ገባ፡፡ አንዳንድ አመራሮቻቸው ስልጣን አገኙ፡፡ እነ ዳዎድ ኢብሳ ያለው ሁኔታ አልተመቻቸውም፡፡ በኦነግና በብልጽግና መካከል እንደገና ጠበ ተፈጠረ፡፡ መዓከላዊ መንግስቱ ደካማ ስለነበረም፣ የኦነግ ወታደራዊ ዊንግ ኦላ፣ በተለይም በወለጋና በጉጂ ጫካ ገብቶ መታገል ጀመረ፡፡ አሁን ኦላ በብዙ ቦታ ውጊያ እያደረገ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይኸው አምስት አመት ሆነ እየተዋጋን ነው ማለት ከጀመሩ፣ የሚጨበጥ ውጤት ያመጡበት ሁኔታ የለም፡፡

ኦነግ እንደ ድርጅት እዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም፣ አንድ የተፈጠረ ግን ትልቅ አደገኛ ነገር ነበር፡፡ ኦነግ ከአገር ቤት በነ አቶ ስዬ አብርሃ ሲባረር፣ የኦነግ ፖለቲካን፣ የኦነግን አስተሳሰብ ግን ኦህዴዶች በኦሮሞ ክልል ሙሉ ለሙሉ ተግብረዉታል፡፡ እነ ዳዎድ ኢብሳ፣ ሌንጮ ለታ ባይገዙም፣ በነርሱ ርዮት አለም ነበር ኦህዴዶች ሲገዙ የነበሩት፡፡

ወያኔ አዲስ አበበ ከገባች 32 ዓመት ሆነ፡፡ ያኔ 8 አመት የነበረ ሰው፣ አሁን 40 አመት ይሆናል፡፡ ምን ማለት ነው ከ40 አመት በታች ያሉ ኦሮሞዎች በኦነግ አስተሳሰብ ነው ያደጉት ማለት ነው፡፡ የቁቤ ትውልድ የምንላቸው፡፡

ይህ የኦነግ አስተሳሰብ ደግሞ በጥላቻ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ አስተሳሰብ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሰንደቅ፣ የኢትዮጵያ ፊደል፣ ኢትዮጵያን የሚያሳይ ማናቸውን ነገር የሚጠላ አስተሳሰብ፡፡ አማራ ኢትዮጵያ የሚል ስለሆነ፣ የኦነግ ፖለቲካ አማራን በመጥላት ላይ ያተኮረ ፖለቲካ ነው፡፡

የነ ጀነራል ታደሰ ብሩ ሜጫና ቱሉም አጀንዳ ኦሮሞን በመጥቀም ፣ ኦሮሞን empower በማድረግ ላይ የተመሰረተ PRO OROMO አጀንዳ ነበር፡፡ የኦነግ አጀንዳ ግን ኢትዮጵያዊ የሆነን ነገር በመጥላት ፣ በተለይም አማራ፣ አማርኛ በመጸየፍ ላይ ያተኮረ፣ ANTI AMHARA፣ ANTI ETHIOPIA የጥላቻ አጀንዳ ነው፡፡

ይህ የኦነግ አስተሳሰብን አጀንዳው ያደረገ የቁቤ ትውልድን ፣ ራሳቸው የቀድሞ የኦነግ አመራሮች፣ እነ ሌንጮ ለታ ፣ ዲማ ነግዎ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት ነገር አልሆነም፡፡ እነርሱ ቀላል መስሏቸው፣ በጀርመን ሚሺነሪዎች ሆይ ሆይ ተብለው፣ የቀሰቀሱት እሳት፣ መልሶ ኦሮሞን እያቀጠለው መሆኑን እያዩ ፍርሃት ውስጥ የወደቁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

ይህ የኦነግ አስተሳሰብ ስር ሰዶ፣ ጭፍጨፋዎችን ፣ መፈናቅሎችን፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች፣ ጦርነቶች ቀስቅሷል፡፡ ይህ የኦነግ የዘርና የጥላቻ ፖለቲካ የኦሮሞ ማህበረሰብ በቀጥታ ከሌላው ማህበረሰባት ጋር እንዲጋጭ፣ እንዲካረር፣ ደም እንዲፋሰስ፣ በሌሎች ማህበረሰባት እንዲጠላ፣ እንዲፈራ፣ እንደ ጭራቅ እንዲታይ እያደረገ ነው፡፡ የኦነግ አስተሳሰብና ፖለቲካ፣ አብሮነት፣ እክሉነት፣ መቻቻል፣ ፍቅር፣ አንድነት የሚሉትን ቃላቶች አያውቅም፡፡ የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ የሆኑ ብዙ ወጣቶችም፣ እራሳቸውንም፣ አገርን ገደል ውስጥ እየከተቱ ነው፡፡

የኦሮሞ ልሂቃን፣ ነገሮችን እናገናዝባለን የሚሉ ፣ በርግጥም የህዝብ ጥቅም የሚአስቀድሞ ቆም ብለ ማሰብና ነገሮችን ማስተካከል አለባቸው፡፡ የተበላሸ አይምሮ እንዲፈወስ መስራት አለባቸው፡፡ የኦነግ አስተሳሰብ ናዚዛዊ፣ ሰይጣናዊና ክፉ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ በቶሎ መውጣት ባይቻልም፣ መውጣት እንዲቻል ማስተማር መጀመር አለበት፡፡

አገር ለሁሉም ትበቃለች፡፡ የነርሱ መብት እንዲከበር እንደሚፈልጉት የሌላውን መብት ማክበር መቻል አለባቸው፡፡ እነርሱ ከማንም አናንስም እንደሚሉት፣ ከሌላው እነርሱ እንደማይበልጡ ማወቅ አለባቸው፡፡ እነርሱ ራሳቸው ከደቡብ ባሌ መጥተው ሰፋሪና ወራሪ እንደነበሩት፣ ሌላው መጤ፣ ወራሪ የማለት አምስት ሳንቲም መብት የለቸውም፡፡

ተከባብረን እንኑር፡፡ ከኦነግ ፖለቲካ፣ ከኦነግ አስተሳሰብ ስካራቸው ሰከን ያድርጉ፡፡ ይሄ ኦሮሚያ ክልል ታግለው ያመጡት አይደለም፡፡ ህወሃት ጠፍጥፎ የሰራላቸው አፓርታይዳዊ ክልል ነው፡፡ ህወሃት እስኪመጣ ድረስ በታሪክ ኦሮሚያ የሚባል ኖሮ አያውቅም፡፡ በመሆኑ ይህ ዘረኛ ክልል ምፍረስ አለበት፡፡ አምራዎች፣ ጉራጌዎች፣ ሶማሌዎች ሌሎች በብዛት የሚኖርባቸውን አካባቢዎች የኦሮሞ ነው በሚል ፌዝ፣ ኦሮሚያ ያውስጥ አጠቃለው ፣ ሌላው እየገፉ የሚኖሩበት ጊዘ አክቷሟል፡፡ ይሄን ማወቅ አለባቸው፡፡ ክልሉ አይፈርሱም፣ ደም እንፋሰሳለን ካሉ፣ እንግዲህ ለዚያም ይዘጋጁ፡፡

2 Comments

  1. ብሄርተኞች የዝቅተኛነት መንፈስ የሚያንገላታቸው በውጭና በውስጥ ሃይሎች እየተደገፉና የራሳቸውን ኑሮ እያሳመሩ ነጻ እናወጣሃለን በሚሉት ህዝብስም የሚነግድ ሙቶች ናቸው። እነ አሉላ አባ ነጋ፤ እነ ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሄር በበቀሉበት የትግራይ ምድር የገበሬ ቤት አቃጥለው የሚፎክሩ የዘር ሰካራሞችና ደም አፍሳሾች ይራወጡበታል። እንደ ደራሲና ገጣሚ ሰለሞን ዴሬሳ፤ እንደ ጸጋዬ ገ/መድህን በወጡበት የወለጋ ምድር በኦሮሞ ህዝብ ስም ሰው በላ ጭራቆች በሰው ደም ምድሪቱን አጨቅየተዋታል። መለስ ብሎ ታሪክን በሙሉ ዓይኑ ለፈተሸ በኤርትራም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ያኔም ሆነ ዛሬ እሣት የሚለኩስት እነማን እንደሆኑ እስከ ምክንያቱ ግልጽ ሆኖ ይታየዋል። ከመሞት በላይ ከመኖር በታች የሚኖረውን ህዝባችን የእለት እለት ሰቆቃና ፍትህ ማጣት እንደ መፋለም የምድር አውሬ ይመስል በቋንቋውና በዘሩ እየወገነ ሲገዳደል መዋሉ የዛሬው አርቲፊሻል ታሪካችን ካለፍንባቸው ታሪኮች እንደማይለይ ያሳያል። አፍራሽ አፍራሽን እየተካው ይኸው በደንበር ገተር ፓለቲካ ይባስ ተብሎ የገሌ ክልል የገሌ ቋንቋ የገሌ ሃይማኖት እያልን እንተራመሳለን። አኞ ፓለቲካ፤ ለማኘክ የማይቻል፤ ልዋጥ ቢሉት የማይዋጥ አክ እንትፍ መባል ያለበት የብሄር ፓለቲካ። ድንቄም ነጻነት። በነጻነት ስም ባርነት ” የእንስሳት አብዪትን” ያንቡ። ፍትጊያችን ጆርጅ ኦርዌላዊ ነውና!
    ሲጀመር ከለለ ማለት – አጥር አበጀ፤ አትድረሱብኝ አለ፤ ማለት ነው። ይህ የክልል ፓለቲካ ወያኔ እኛው በተጣለልን የፓለቲካ አጥንት ስንፋጅ እነርሱ እስከ ዘለቄታ ለመኖር ከጣሊያን ወራሪ ሃይል ኮርጀው የፈጠሩት ብልሃት ነው። ችግሩ ተኮረጀም፤ ፎርጅድም ሆነ ድምሩ ዜሮ መሆኑ ነው። ኑሮውና የዘሩ ፓለቲካ አፍዞናል። ሞትን ተላምደናል። በራችን አንኳኩቶ የእኛን ቤተሰብ እስካልነካ ድረስ ለብሄርተኞችና ለሆዳሞች ዓለሙ ሁሉ ጸጥ እረጭ ያለ ነው። ኦሮሞ አማራን በማፈናቀሉና በመግደሉ የሚያተርፈው አንዳች ነገር የለም። አሁን ትርፍ መስሎ የታያቸው በሰፈሩት መስፈሪያ ያው ራሱ ነጻ አወጣሃለሁ የሚለው የደም ሰካራም በወረፋ አፈር ይመልስባቸዋል። ፓለቲካ እንደዚያ ነው። ከታሪክ ማህደር ላስረዳ። ወያኔና ሻቢያ በጥምረት ያኔ የደርግ ሰራዊት እየተባለ የሚጠራውን አንድ ቦታ ላይ ክፉኛ ይመቱታል። ታዲያ የተረፉት ነጭ ጨርቅ መሳይ ነገር አንጠልጥለው እጅ ይሰጣሉ። እንዲሰለፉ ይታዘዛሉ። እንደ ተሰለፉ በላያቸው ላይ ታንክ በመንዳት ይገድሏቸዋል። ሌላም ብዙ ግፍ ራሳቸው በስፍራው የነበሩ የሻቢያና የወያኔ ተዋጊዎች አጫውተውናል። የዚህ ጉዳይ ዋና ሃሳቡ ግን ወያኔና ሻቢያ ድባ በማያበቅል ባድሜ ሳቢያ ሲፋለሙ እነዚያ ደም አፍሳሾች ከወያኔም ከሻቢያም በኩል ቀዳሚዎቹ ሟቾች ነበሩ። እንዲህ ነው የሃበሻ ፓለቲካ በወረፋ መገዳደል፤ መጠፋፋት ነው። ከባዶ ላይ ዘግኖ እንካችሁ የሚል የጠባብ ብሄርተኞች ፓለቲካ ለማንም ለምንም አይጠቅምም።
    ኦነግ በታሪኩ ለኦሮሞ ህዝብ አንድም ነገር ያደረገው የለም። ያው አውቀናል ተምረናል የሚሉት ግን ልክ እንደ ወያኔና ሻቢያ ውጭ ሃገር በየሰበቡ በመውጣት በስሙ በኦሮሞ ህዝብ ነግደውበታል። ለአዝማድ ዘመዳቸው መጠለያ አመቻችተዋል። በኦሮሞ ህዝብ ስም በተለመ ገንዘብ ከብረውበታል። ለዚህ ነው ሻቢያ/ወያኔ/ኦነግ በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ አንድ ናቸው የምንለው። አፍራሾችና ከፋፋይ ሃይሎች ናቸው። ግን ባንረዳው በደምብ ባይገባን እንጂ የሃበሻ ፓለቲካ Political Pawn በሚያጫውቱንና በሚጫወቱብን የውጭ ሃሎች የሚዘወር ነው። ልክ እንደ ሻቢያና ወያኔ የኦነግ ፓለቲከኞችም የቀደሙት ያለሙት ሳይሞላ፤ በህይወት ያሉት ጥርሳቸው ወልቆ፤ አይናቸው ፈዞ ምንም ነገር ለህዝባችን የሚሉትን ሳያሳኩ ለአዲሱ ትውልድ ጥላቻና የደነቆረ ዘረኝነትን አጋብተውበታል። ይህ እግዚኦ ያሰኛል። ግን ለማን? እሱስ ቢሆን የሃበሻን ምድር ረስቷት የለ? ወቸው ጉድ እስቲ እንሰንብት መጭው ዓመት ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ለሃበሻ ምድር? በቃኝ!

  2. የኦሮሞ ማህበረሰብም ሆነ የሌሎቹ የኢትዮጲያ ማህበረሰቦች ጥያቄ ባግባቡ መከነወን የማያባራውን መተላለቅ ያስቆማል::በጥላቻ መፈራረጅ ባለፉ ነገስታትና ፖለቲከኞች ስህተት የዘመኑ ትውልድን ለጥላቻ የሚዳረጉ ትርክቶችን ማስተላለፍ ለማናቸንም የማይተቅም ኢትዮጲያን ለከፋ መበታተን ስደት የሚዳርግ ስለሆነ የመብት ጥያቄዎችን ባግባቡ በመመለስ ያለፉ ስህ ተቶችን አንድገም ትውልድ ከቀጣይ መካራና መተላለቅ ይረፍ::
    ከመጀመሪያው በአለም አቀፍ ደረጃ የተከበረች ሃገር ንጉሱ አሜሪካንን ሲጎበኙ ፕርዚዳንቱ የሌሎች ሃገሮች መሪዎችን ቤተምንግስት ከሚቀበለው በተለየ በኤየር ማረፊያ ለመቅበል ልዩ ድንጋገ የወጣባት የእንግሊዝ ንግስት በከፍተኛ ክብር ልኡላኑ ሚንስትሮቹ አጎንብሰው የተቀበሉዋቸው ንጉስ በእድሜ መገፋት የራሳቸው ዘምዶች ራስ እምሩ በቅርቡም የተወሳው የ ልኡል ራስ አስራተ ካሳ ጭምር የዘውድ ስር ኤቱን ለምልክት በማደርግ በእንግሊዝ ስልት ከማደረግ በፍጹም ሞናርኪ ለመቀጠል ሲሞክሩ የወሎ ድርቅ ያባባሰው የህዝባችን ቁጣ የደርግ ወታደሮች ሊያስወግዷቸው በቁ:: ንጉሱን የተካቸው አምባገነን መነግስቱ ሃይለማርያም በማርስኪስት ፍልስፍና በምእራባዊያን የጥላቻ ቃሉ ሃገራችን ድሮም የኣፈሪካ የጥቁር ነጻነት ምስሌ መሆንዋ በሚያናጃቸው ክፉ መራባዊያን ሃገር ከፋፋይ ታጥቂዎች ህዝባችን ስም ከፍተኛ የጥላቻ ፖልቲካ ቀጥለው ዛሬ የከፈ ደረጃ መድረሱ ይታወቅል::የመጀመሪያው የሽምቅ ተዋጊ የእርትራዎቹ ጀብሃና ሻቢያ በወልደኣአብ ወልደማርያም የትግራይ ትግሪኛ ንቅናቄ የተጀመረውን ያስፋፉት ንጉሱ በተወዳጅነት በአንድነት ማሀበሩ ግፊት የፌደሬሽን ህጉ ተጥሶ በሆታ አርትራ በመቀላቀሏ ሲሆን ያ ትግል ወደከፋ ጥላቻ ደርሶ ባርነት ወይስ ነጻነት በሚል ሪፈርንደም ባብዛናው የኤርትራዊያን ምርጫ ኤርትራ ለመለየ በቃች::
    የኦሮሞው ባህላዊ ሜቻና ቱለማ የንጉሱን መፈንቀለ መንግስት በመከተው በጄንራል ታደሰ ብሩና ባልደረቦቹ ሲካሄድ በንጉሱ ወዳጅ መሳይ ክፉ ጠቁዋሚዎቹ በቁም እስር ስቆዩ ሌላው መሪ መቶኤለቃ መዘምር ሲኒማ ቤት በማቃጠል የትግሉ ተቀባይነትን ለማስፈን ሲሞክር ተይዞ በስቅላት ተቀጣ:: በዚህ ወቅት በኦሮሞ ሜቻና ቱለማ የነበሩ በሶማሌ የኢትዮጲያ የትግል ድርጅት የጀመሩት በነበረው የሶማሌ የመስፋፋት ፖልሲ ኦቦሶማሌ በሚል ሲያድ ባሬ ያደራጃቸው ዋቆ ጉቱን የመሰሉት በባሌ ገበሬዎች ትግል በጄንራል ጃገማ ኬሎ ተማርኮ ምህረ ተደርጎለት ቪላ ቤት በንጉስ የተሰጠው ቆይቶ የሶማሌ ሲያድ ባሬ ኢትዮጲያ ሲወርር የምእራብ ሶማሌ ጀመራል ሆኖ ሃገራችንንችን ከድቶ ተዋጋን:: በኢትዮጲያ ስም የነበረው የኦሮሞ ትግል የኦሮሞ ሲሆን በሃገር ቤት በነአቶ አሰፋ ጫቦና በሮ ቱምሳ ይላሄድ የነበረው ሃገራዊ የኢትዮጲያ ጭቁን ህዝቦች ድርጅትን ባሮ በመለየት ኦነግን ቢያዋቅርም ክርስቲያን በመሆኑ ያባሌና የሃረር የኦሮሞ ትግል መሪዎች ገደሉት ትግሉን ወንድሙ ቄስ ጉዲና ቱምሳ በብተከርቲያን ውስጥ ቀጥሎ ሌንጮ ለታና ወንድሙን ዮንስ ለታን ነጋሶ ጊዳዳን በመመልመል ኦነግ ከመፍረስ ተርፎ ትግሉን ቀጥሎ በደርግና በውያኔ አንዳች ሃይል የሌልው ለዘምናት መረት ሳይዝ በሽምቅ ውጊ ብቻ የቆየ በነለማ መገርሳ ሹዋ ሹዋ ከኤርትራ በረሃ ትቁን ሳይፈታ ገብቶ የዛሬው ሁለተኛ መንግስት ስልጣን ይዞ በታጥቂዎቹ ከወሎ ሰፋሪዎች ጀምሮ ዘራቸው አማራ የሆኑትን ለይቶ በወለጋ በአርሲ በቤንሻንጉል በማረድ ባንኮችን በመዘረፍ ሾፌሮችና ባለሃብቶችን በማገት በባንክ ብዙ መቶሺ ብር በማስገባት ላይ ይገኛል;: የብልጽግናው መንስግት ጋር ድርድር ጀምሮ ጃል መሮ የሽመልስ አብዲሳ ምክትልነትን በመናቅ ትግሉን ቀጥሎ የህዝባችን ጭፍጨፋ ቀጥሏል;L:
    ይህን ሁሉ በማየት መጀመሪያ የተደርጉት የመሪዎች ስህተት ሳይደገሙ ብዙሃን የህዝባችን አካል የሆነው ኦሮሞን ባግባቡ በሚያስከብር መልኩ ሌልቹንም የኢትዮጲያ ማሀበርስቦች በዲሞክራሲ ያካተተ ለሃገሩ ኢትዮጲያ ያለምንም ማምነታት የተዋደቀው ኢትዮፒያና አምራ ልዩነት እስከማይታይበት ድረስ የተዋደቀውን አምራን በነገስታቱና በምንግስቱ ሃይለማርያም ጥፋት መኮነን ቆሞ የሁሉም የኢትዮፒያ ህዝቦች ድሮ የመላው ኢትዮፒያ ሶሻሻሊስ ንቅናቄ የመላው ኢትዮጲያ የገብረዎች ማሀበር የሰረተኞች ማሀበር የወጣች ማህበር የሚል የኣንድንተ ራእይ ስያሜ በሰጠው በሃይሌ ፊዳ መርህ በመከባበር በመቀባበል ሃገራችንን ከውድቀት ማንሳት ከባሰ ጥፋት ማትረፍ የሁሉም ቅን ኢትዮጲያዊ ሃላፊነትና ግደታ መሆን ይኖርበታል ::
    ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

411969850 748999773924616 8882494238832183547 n
Previous Story

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው “ዝማምነሽ ታወር” ሕንጻ ከወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በሥጦታ ተበረከተለት

187745
Next Story

የአፍሪካ ልማት ባንክ ሰራተኞቹን ሊያስወጣ ነው፥ የጎጃም ፋኖ ለእነ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረበ፥ ተጋድሎው ቀጥሏል፥ የአርሲው ግድያ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop