October 12, 2023
7 mins read

ንግግር ሌላ ፤ ተግባር ሌላ

F7IDyi3X0AEtIWP

ብዙዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተለያየ አስተያየት ሲሰጡ ይደመጣል ወይም ይሰማል ፡፡ የሚገርመዉ ግን አዉቃለሁ ባዮች በዉጭም በዉስጥም ያሉ የአዋቂ ዘባራቂዎች መሆናቸዉ ደግሞ ለየት ያለ እንዲሆን ያደርገዋል ፡፡

በተለይም በሰሜን  ምዕራብ ኢትዮጵያ እነደ ጊዜዉ “ዓማራ ክፍለ ግዛት አስተዳደር ” ስላለዉ ጦርነት ከቅርብ ርቀት እና ከሩቅ ሆነዉ ይኸ ቢሆን ይኸ ባይሆን ሲሉ መስማት በዕዉነት ሠዉ ለሆነ ያማል ፡፡

ህዝብ ላለፉት ሶስት ዓመታት በጦርነት ባጂቶ እንደገና በጦርነት ወላፈን ሲገረፍ ከዚህ ጋ ተያይዞ ድህነት ፣ ርኃብ፣ በሽታ፣ ቸነፈር፣ ስደት  እና ሞት በየቤቱ በሆነበት ጊዜ ይህን ሁላ ተቋቁሞ አልሞት ባይ ተጋዳይ ሲዋደቅ በቦታ የሌለ የትግሉን መሪ መጨበጥ እና መዘወር የሚፈልግ ጣት መቀሰር ለማቆም ካለፉት የኢትዮጵያ የቀደመ ታሪክ  አለመማር የሚያስተዛዝብ ነዉ ፡፡

መንግስት ይህን ቢያደርግ፤ ያኘዉ ያን ቢያደርግ እያለ በቁስል ላይ ጨዉ መጨመር ከንቱ ህልም ከመሆኑ በላይ የምቀኛ ፖለቲካ አካሄድ ምኞት ምልክት ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል እና አስኳል መሆኑን በመካድ በየትኛዉም የአገሪቷ ታሪክ በተነሱ እና በተከናወኑ የለዉጥ ጥያቄዎች የተዘጋጀ እና የበቃ መሪ የለዉም ለማለት እና እኛ እናዉቅለታለን ባዮች  የስልጣን ጥመኞች በህዝብ መስዋዕት መርካትን ዛሬም ደጋግመዉ ያልማሉ ፡፡

መሪነት በተግባር የተፈተነ ፤በመከራ እና በወሳኝ ገዜ ከህዝብ ፊት የሚገኝ እንጂ በመልካም ንግግር እና ምኞት የሚገኝ አይደለም ፡፡ ፖለቲካ በኢትዮጵያ መጧሪያ እና የእድሜ ልክ መጠቀሚያ ወይም መገልገያ አድርጎ መዉሰድ ዛሬም የብልጠት የፖለቲካ አካሄድ የወረቀት አርበኞች ያልዳነ በሽታ ነዉ ፡፡

“የማታ አፍ ደራን ይወጋል ” እንዲሉ አበዉ ጥቀም ማነፍነፍ እና የሚሰሩትን መጥለፍ የምቀኝነት አባዜ እንጂ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለዓለም የሚሆኑ መሪዎች ማበርከት በሚችል የኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ  ብዙዎችን አበርክቷል ፡፡

በዚህ የ21ኛዉ ክ/ዘመን መባቻ ቀርቶ ከግማሽ ምዕተ ዓመት አስቀድሞ የኡጋንዳዉ ሞሶቮኒ፣ የእኛ ትህነግ/ኢህዴግ፣ የኤርትራዉ ሻቢያ……… የፖለቲካ እና የተዋጊ ክንፍ የመደቡት የዘመናችን የዕኛ አገር የወረቀት አርበኞች አለመሆናቸዉን ለሚያዉቅ ዞትር አዋቂ ነን ባይ ዘባራቂወች አገር እና ህዝብ በሰጠቻዉ ወረቀት በህዝባቸዉ እና በአገራቸዉ ላይ ንቀት ሲያሳዩ የስተዋላሉ ፡፡

የያዙት ወረቀት አገር ለማገልገል ሳይሆን ለመገልገል መሆኑን ገልብጠዉ በማንበብ ዛሬም በነገረ ስራ አገር ካልመራን የማለት የጥቅመኝነት እና የምቀኝነት አባዜ እንደተበተባቸዉ ይገኛሉ ፡፡

ያኔ በአስራ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ስድስት የለዉጥ አብዮት ህዝብ በከፈለዉ መስዋዕትነት የተገኘዉን ድል በወረቀት ለመለወጥ ከዕዉነት እና ከዕዉቀት ይልቅ አገር በወረቀት ካልተመራች ብሎ  ክችች ያለ ትዉልድ ዛሬም በነበረበት ይገኛል ፡፡

ነገር ግን በተግባር የተፈተነዉ የጊዜዉ የለዉጥ አራማጂ አካል የጦር ኃይል አባላት በብሄራዊ ልማት ማለትም በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በፍትኃ ተጠቃሚነት፣ ድህነት እና ማይምነትን ለመቀነስ….ከፍተኛ ጥረት እና ዉጤት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎችን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ማዕከላዊ መንግስት አስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አስጠብቆ ለህዝብ አስረክቧል ፡፡

በአስራ ሠባት ዓመት የተሰሩ ብሄራዊ ልማቶች ከአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት አስከ ዛሬ በፀረ ኢትዮጵያዉያን አፍርሶ መጨረስ እንዳልተቻለ ተግባር ከንግግር ጋር ምንም አይነት አንድነት ሆነ ዕዉነትነት እንደሌለዉ የሚያሳይ ነዉ ፡፡

የመከራ እና የጭንቅ ጊዜ በንግግር በአገር እና በወገን ጉዳይ ዳር ተመልካች ፣መኃል ሰፋሪ ሆነ ገለልተኛ መሆን ከንግግር የማይዘልቅ መዘባረቅ ነዉ እና የአገር እና ህዝብ ጉዳይ ያገባኛል ባይ  በማንኛዉም መመዘኛ ሲታይ ንግግር ተግባር ሆኖ ሊቆጠር አይችልም ፤ ኢትዮጵያም ሆነበ ኢትዮጵያዉያን የሚናገረዉን የሚኖር ፤ የሚኖረዉን የሚመሰክር በተግባር የሚገለጥ ማንት እንጂ የማይኖረዉን የሚዘባርቅ ፤የሚናገር ዕጦት የለባትም  ፡፡

 

 

 

“አንድነት ኃይል ነዉ !”

 

Allen!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop