October 7, 2023
6 mins read

የሰላም ዋጋው በእውነት ስንት ነው?  – ሙናች ከአባይ ማዶ ፊላው ስር  ገሳ ለብሶ እየቆዘመ 

abiy Killer
በፕሮስታንት ጠንቋይ የሚመራው ጨካኙ እርኩስ መንፈስ ያደረበት ፋሺሽቱ ደም መጣጭ አብይ አህመድ አሊ
በፕሮስታንት ጠንቋይ የሚመራው ጨካኙ እርኩስ መንፈስ ያደረበት ፋሺሽቱ ደም መጣጭ አብይ አህመድ አሊ

በምድራችን ሰዎች ሲገናኙ “እንደምን አደራችሁ፣ እንደምን ዋላችሁና እንደምን አመሻችሁ” የሚባባሉት የሰላምታ ትክክለኛ ትርጉም ለብዙዎቻችን በደንብ የገባን እና የተረዳነው አይመስልም::

ጨለማን ተገን አድርጎ ንብረትን ብቻ ሳይሆን የሰውን ነፍስ ሳይቀር የሚዘርፈው ሌባ ወንብዴ የሚነግሥበትን እይታ አልቦ ጊዜን ምንም ሳንሆን አልፈን ብርሃን ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን፣ ሲደክም የዋለው ሥጋችን ያለስጋት ተዘልሎ በጤና እንቅልፍ ጠግቦ መነሳት መቻል ‘እንደምን አደራችሁ’ የሚለው ጥያቄ ቀላል የልማድ ጥያቄ ብቻ አይደለም! በተኛንበት ሰዓት ዘራፊና ገዳይ የነገሠበት ጊዜ ስለሆነ ጭምር እንጂ!
አብዛኛው ሰው የለመደውና የሚያውቀው ነገር ይቀልበታል! ሲርቀውና ሲያጣው ግን በጸጸት ዋጋ ከፍሎ ሳይቀር ሊያገኘው ይሻል “በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል” የሚለው አባባል ይህን ሃሳቤን የሚገልጽልኝ ይመስለኛል::
ትምህርቴን ጨርሼ ሥራ በያዝኩበት ትንሽ ዓመታት ውስጥ ሰሜን ኢትዮጵያን እስከ ምጽዋ ወደብ፣ ምስራቅ ኢትዮጵያን እስከ ጅጅጋ፣ ደቡብ ኢትዮጵያን እስከ ሲዳሞ አዋሳ ላንጋኖ አርባ ምንጭ፣ ምእራብ ኢትዮጵያን መተከል ጉብላክና አጋሮን ድረስ ያለምንም ስጋት ተዘልዬ በደስታ ጎብኝቻለሁ ዛሬ ግን አይደለም ከአዲስ አበባ ከተማችን መውጣትም ሆነ መግባት ይቅርና ከቤትህ ጠዋት ወተህ ማታ መዳረሻ ማደሪያህ የት እንደሚሆን አንተም ሆንክ ቤተሰብ ጭራሽ ማወቅ አይችልም::
ትናንት በአገሪቱ ሙሉ ስፋትና ወርድ በደስታ እና በሰላም የፈነጨንባት ምድር ዛሬ ክቡር የሆነው ሰው በተገኘበት እንደ በግ ግልገል ተይዞ እየታሰረ የገንዘብ ማግኛ ዋና ምንጭ ሆኖ ስናይ ትናንት ለነበረው የጋራ አንድነትና ሰላማችን የሰጠነውን ዋጋ እና በሕዝባችን መካከል ዛሬ ላለው ሰላም የምንሰጠው ዋጋ ምን ያህል ነው? ብለን መጠየቅ ግድ ይላል::
ዛሬ በእውነት ተወልደን ሳንሰበር እየዘለልን ባደግንባት የጋራ አገራችን ውስጥ ያለው የሕይወት ትርጉም ምንድነው? እያንዳንዱ ሰው አስቦና አቅዶ ላልሆነው ማንነቱ ይህን ያህል መከራና ስቃይ ማየት እና መገደል አለበት? በዚህ እልህ አስጨራሽ ጥላቻና መሳደድ በእውነት አሸናፊና ተሸናፊ ይኖር ይሆን? እሺ እንደ ወያኔ ጊዜ ወይም ወቅት የሰጠው ወይም በለስ የቀናው አንዱ ወገን ያሸንፍ እንበል! የዛሬ ተሸናፊና ተገዳይ ነገ ዝም ብሎ አሜን በማለት የሚቀበል ልብ ያለው ይመስላችሁዋል?
አይደለም ተሰዳጅና ተገዳይ ይቅርና ገዳይና አሳዳጅ ሳይቀር በሠራው የጥል እና የክፋት ሥራው ሰላም አግኝቶ የተደላደለ ኑሮ ጨርሶ መኖር አይችልም! ሰው ተብሎ ሊጠራበት የተሰጠው ሕሊናው ካልደነዘዘ በስተቀር!
ስለዚህ ለተነሳንበት የሰላም ዋጋው ስንት ነው? ጥያቄ የእኔ የትንሽዋ አእምሮ መልስ አንተ ለሌሎች፣ ሌሎች ላንተ፣ እያንዳንዱ ለሁሉ፣ ሁሉም ለእያንዳንዱ ያለው ምልከታ እና አቀባበል ነውና ሁሉም የራሱን ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣ! እንብሰል! እንደግ! አንዱ ለሌላው የሰላም ኑሮ ወሳኝ አጋር መሆኑን አውቆ ዛሬ ባለበት ላይ ሆኖ ነገን አሻግሮ በማየት ለትውልድ(ለልጆቹ)መልካም የሆነ ሌጋሲ ያቁም? ጥያቄ ነው!
ከዚህ በተረፈ የዛሬ ባለዕድል ጉልበተኛ ነገ እንደ ዛሬው TPLF ፀሐይ ልትጠልቅብህና ጨለማ ሊወርስህ እንደምትችል ረጋ ብለህ ካላሰብክ “የመውጊያው ብረት በአንተ ላይ ይብሳልና” እንደባለ አእምሮ ሰው ቆም ብለን እናስብ? ኑሮ ዛሬ ብቻ አይደለምና::
እመኑኝ አሸናፊና ተሸናፊ ፈጽሞ አይኖርም!
          ለጋራ ሰላምና እድገት
 ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር የግድ ነው!
ሁሉም ለዚህ ዓላማ በጋራ ይሥራ፣!
ከታላቅ አክብሮት ጋር
ሙናች
ከአባይ ማዶ
ፊላው ስር
ገሳ ለብሶ
እየቆዘመ

1 Comment

  1. የቀበጡ እልት ሞት አይገኝም አለ። አርፎ ድፍን ጦብያን የሚመግበውን ህዝብ ነካክተው ነካክተው አዉሬ አደረጉት። አያት ቅድመ አያቶቹ በአጥንትና በደም ያቆዩትን አገር ሰበርናቸው ብለው ተዘባነኑ ቅድመ አያቶቻቸው የቆረቆሩትን ከተማ አትገቡበትም ተባሉ አያት ቅድመ አያቱ ባጸኑት ምድር ልቀቁ ተባሉ እንኳን ሰው እግዚሃሩም ገደብ አለው። ያ የግፍ ጽዋ ሞልቶ ፈስሶ ያየነው ሆነ ይህ ጅምሩ እንጅ መጨረሻው አይደለም አሁንም አገራዊና ታሪካዊ ሃላፊነት ያለበት ይህ ህዝብ ስለሆነ ሃገር ያጸናል፤እኩልነት ያስከብራል፤ዳር ድምበርን ከጠላት ይጠብቃል፤አናሳ ብሄሮችን እስከዛሬ ጠብቆ እንዳቆየ አሁንም ይከላከላቸዋል። ፋኖ ይደገፍ ፋኖ ማንንም አይበድልም ተማመኑ የትግሬን ትርክት ሰምታችሁ አትደናገጡ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

DJ 59t9t9gi
Previous Story

ወሳኙ የፋኖና የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል። ኅልውናን ከማዳን እስከ ሐገር ግንባታ።

186335
Next Story

በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሆነው ምንድን ነው? | ሚሊሻው ካደ፤ ቋራና ደንቢያ | ለምን እኛ ብቻ እናንተስ ለምን አትሞቱም |

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop