October 5, 2023
12 mins read

ይጋብዟል እንግዳ እንደ መልካም ሞላ!

በአማራ ባህል ለድግስ እንግዳ የጠራ ሰው ተእንግዳው ፊት ጠርጎ አይበላም፡፡ እንዲያስተምር እንግዳ የጠራ ጋዜጠኛም ተእንግዳው የበለጠ ወይም እኩል አያዋራም፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

 

ለአያሌ ዓመታት ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚደረጉ ቃለ መጠይቆችን አልፎ አልፎ ስመልከት ጋባዡ ጋዜጠኛ ከተጋበዘው እንግዳ የበለጠ ወይም እኩል ሲናገር ሳይ ስግጥጥ ያደርገኝና “ለድግስ ጋብዞ ተፊት ተፊቱ እየጠለፉ መብላት” እልና መመልከቱን አቆማለሁ፡፡  ከተጋባዥ እንግዳ ፊት ለፊት እየጠለፈች የማትልፍና ባህሏን የጠበቀች ወይዘሮ መልካም ሞላ የምትባል ጋዜጠኛ ሰሞኑን አየሁ፡፡ ወይዘሮ መልካሞ ሞላን አላውቃትም፡፡ የጋዜጠኝነት ሙያዋን ያየሁት በቅርቡ ሥራውን በጀመረውና እጅግ አስፈላጊ በሆነው የአማራ ዜናና መረጃ ማሰራጫ ማእከል በሚባለው የሕዝብ መገናኛ አውታር ነው፡፡

የጋዜጠኝነት ሙያም ሆነ ሌላ ትምህርት መማሯን አላውቅም፡፡ የጋዜጠኝነት ሙያ ትማርም አትማርም በእኔ እምነት ወይዘሮ መልካምን ጥሩ እንግዳ አስተናጋጅ እንድትሆን ያዘጋጃት የአማራ ባህልን ተመግባ በማደጓና ካጠለቀችው ማተብ ጋር አስራ በመያዟ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና አላማም የአማራን ባህል አጥብቆ መያዝ ለጋዜጠኝነትም፣ ለጀግንነትም ሆነ ለሌላ ሙያ ወደር የሌለው ጥቅም እንዳለው ለማስገንዘብ ነው፡፡

አማራ እንግዳ በማስተናገድ ፀጋው አቻ እንደሌለው እንኳን ወዳጆቹ ሊያጠፉት የከጀሉት ሁሉ የሚያምኑት ነው፡፡ አማራ ሰውን መለኮት በአምሳሉ ሰራው ብሎ ስለሚያምን ሰውን ሁሉ በእግዚአብሔር አምሳል የሚያይ ሕዝብ ነው፡፡ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ስለሚያይም የእግዚአብሔር እንግዳ ሲመጣ እርሱ ባዘቦት በልቶት የማያውቀውን ድግስ ደግሶ አብልቶ፣ የክት ብልኮውን አልብሶ፣ አልጋውን ለቆ እርሱ መሬት ተኝቶ የሚያሳድር ሕዝብ ነው፡፡

በአለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን የእግዚአብሔር እንግዳ መስሎ የመጣ የልዋጭ ነጋዴ እቤቱ አድሮ እየሰለለ ለጥቃት የዳረገውም ይኸንን በጎ ባህሉን እንደ ድክመት ቆጥሮ ነው፡፡ ነቁባቸው እንጅ የበፊቶቹ ፋሽሽቶች እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ፋኖዎችን “በማርያም ይዘናችኋል!” እያሉ ሊያታልሉ የሞከሩት ይኸንን ባህል አጥንተው ነው፡። የዛሬዎች ጭራቅ ፋሽሽቶችም ሊያምኑበት ቀርቶ በማያውቁት ሽምግልናና እርቅ ስም የሚያታልሉት ይኸንን የመለኮት በረከት የተላበሰ ባህል እንደ ድክመት ቆጥረውት ነው፡፡ ይህ መለኮታዊ ባህሉ የሳጣጥናኤል መንገዶች በሚከተሉ ጭራቆች ስላስጠቃው አማራ የእግዜር እንግዳ ነኝ፣ ሽማግሌ ነኝ፣ አስታራቂ ነኝ እያለ የበግ ለምድ ለብሶ የሚመጣውን ፎግልና ቀበሮ ሁሉ በሚገባ አንጠርጥሮ መፈተሽ እንዳለበት የደረሰበት መከራ ትምህርት ነው፡፡

ለወደፊቱ አማራ ወደ ቤቱ የሚጋብዘውን እንግዳ አንጠርጥሮ የማወቅ ግዴታ እንዳለበት መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ የእግዜር እንግዳ፣ ሽማግሌና አስታራቂ መስሎ ጭራውን እያወራጨ፣ ጢሙን እያፍተለተለ፣ ቆቡን ደፍቶ ወይም መስቀሉን ጨብጦ የሚንጦለጦልን የዲያብሎስ መልእክተኛ መቀበል የለበትም፡፡ እውነተኛ የእግዜር እንግዳ ወይም ተጋባዥ እንግዳ ተቤቱ ሲመጣ ግን ተእንግዳው ፊት እየጠለፈ አይበላም፡፡ እንግዳው ሲናገርም አያቋርጠውም፡፡ የመናገር እድሉን ለእንግዳው ይሰጥና መግቢያ ሲያገኝ የሚጠይቀውን ጥያቄ ወይም አስተያዬት ለእንግዳው ያቀርባል፡፡ ወይዘሮ መልካም ስታደርግ ያየሁት ይኸንን ነው፡፡ ይህ ደሞ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የአማራ ባህል ነው፡፡

የአማራን ባህል በትክክል መከተል ጥሩ እንግዳ አስተናጋጅ ጋዜጠኛ እንደሚያደርግ ሁሉ ሽለላውን፣ ቀረርቶውን፣ ፊከራውንና የጀግንነት ዜማዎች አዘውትሮ ገና ከእናት ማህፀን ሳሉ ጀምሮ መስማትም ጥቃት የሚጎፈንነው ወኔ የተላበሰ ፋኖ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሴቶች እህቶቻችን ሲያረግዙ ጀምረው ልጆቻቸውን በሽለላ፣ በቀረርቶ፣ በፊከራና በጀግንነት ዜማዎች መጥመቅ ይኖርባቸዋል፡፡

ዓለም ከተፈጥረች ጀምሮ የሰው ልጅ ክፋትና ተንኮል አልቀነሰም፡፡ ይኸንን ያህል ዘመን ያልተቀየረች ዓለም ወደ ፊት የተሻለች ትሆናለች ብሎ የሚያስብ ሞኝ አብዮት አህመድን ሙሴ መጣ ብሎ ከተከተውለው ዘልዛላም አይሻልም፡፡ ሰው በሰማይ ተሽክርካሪዎች በሮ ተጨረቃና ማርስ ቢያርፍም የሰው ልጅ ክፋት ከክርስቶስ ልደት በፊትም ሆነ በኋላ ከነበረው ከፋ እንጅ አልተሻለም፡፡

በዚህች የሰው ክፋት ማእበል በሚያናውጣት ዓለም አማራ ነፃነቱን፣ አገሩንና ቅርሱን በሚገባ ጠብቆ የኖረው ሃይማኖቱንና ባህሉን እንደ ወይዘሮ መልካም በማተቡ አስሮ ጸንቶ በመኖሩ ነው፡፡ ካልተረገመና ባህሉን እንደ ቆሻሻ ታልጣለ በቀር በአማራ ባህል ተነቅሮና ተጠምቆ ያደገ ጤነኛ ሰው በፍጡም ባንዳ አይሆንም፡፡ በዚህ ወቅት የአማራ ባንዳ በዝቶ መታየቱ የሚያመለክተው አንድም በአማራ ባህል ያላደጉ ጉዶች አማራ መስለው መቅረባቸውን ሁለትም የአማራ ባህል መሸርሸሩን ነው፡፡ ስለዚህ መፍትሔው የአማራ ባህልን መሸርሸር ማስቆምና የተሸረሸረውንም ጠግኖ ለእውነተኛ እግዜአብሔር እንግዳ እንደ ፍራሽ የተመቸ ለወራሪ ደሞ ሰደድ እሳት የሆነ ተከታታይ ትውልድ ማፍራት ነው፡፡

ይኸንን ለማድረግ ደሞ እንደ ወይዘሮ መልካም ባንዳነትን፣ አድርባይነትንና ሆዳምነት ተጠይፎ ሃይማኖትንና ባህልን በቃል ኪዳን  ማተብ አስሮ እንዲጠፋ ለግማሽ ክፍለ-ዘመን ከፍተኛ ሴራ የተሰራበትን ማህበረሰብ ማገልገል ነው፡፡

አፈርነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ እንዳለው የተሸከምነው ሥጋ ነገ አፈር የሚሆን ገል ነው፡፡ እንደ ገል አፈር መሆንን ባንዳውም፣ በጥቅም የሚገዛውም፣ ወገኑ ሲጨፈጨፍ ምን አገባኝ እያለ ዝም ብሎ እንደ አሳማ ሲጎሰጉስ የሚኖረውም የማያመልጠው ነው፡፡ ለዘላለም የሚኖረው ሥራችን ነው፡፡ ሥራችን ደሞ ቅድመ ዓያቶቻችን ለብዙ ሺ ዓመታት ባክበቱት የነፃነት፣ የፍትህና የመንፈስ ልእልና ሥርዓት ቢመራ መልካም ነው፡፡

ጋዜጠኛም ሆነ መሐንዲስ፣ ሐኪም፣ ጠበቃ፣ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ወዘተፈ ተውጭ መበደር የሚገባው ያልቸገረውን ባህል ሳይሆን ያጠረውን ሳይንስ ወይም ጥበብ ብቻ ነው፡፡ አማራ ነፃነትና ክብር ያጎናፀፈውን ባህል አውልቆ የባዕድ ባህልን ሲወርስ ባርነትንና ክብረ ቢስነትን ተራሱ ገላ ላይ ብቻ ሳይሆን ተተኪው ትውልድ ሰውነት ላይም እንደለበደ ይቁጠረው፡፡ ይህ እንግዳ የሚያስተናግድን የጋዜጠኝነትን ሙያም የሚጨምር ነው፡፡ ለድግስ እንግዳ ስንጋብዝ ተፊት ተፊቱ እየሞጨለፍን እንደማንበላው ሁሉ  እውቀትን እዲያጋራን እንግዳ ስንጋብዝም ተተጋበዘው እንግዳ የበለጠ ድስኩር በመደስኮር ጊዜ በከንቱ ባናጠፋ ጥሩ ነው፡፡ እንደ ባህላችን ጊዜውን ብዙ ለሚያውቀው የተጋበዘ እንግዳ እንስጠው፡፡ እስካሁን እንዳየሁት ወይዘሮ መልካም በማድረግ ላይ ያለችው ይኸንን ነው፡፡ ይህ ሙያዋን በባህሏ ግምጃ ሸፍና የመያዟ ሥርዓትም ይጋብዟል እንግዳ እንደ መልካም ሞላ! የሚያሰኝ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ለናሙና ያህል እነዚህን የእንግዳ ግብዣዎች ይመለከቱ፡-

 

ABC TV እንግዳ:- አገዛዙ ያራከሰው ሽምግልና እና ድርድር ||/ አሰፋ ነጋሽ || ቅዳሜ ሐምሌ 29, 2015 – YouTube

ABC TV እንግዳ:-|| የሰብዓዊ መብት ተጠያቂነት የጎደለበት ጦርነት ||/ ፍፁም አቻምየለህ | ማክሰኞ መስከረም 22,2016 – YouTube

መስከረም ሁለት  አስራ ስድስት ..

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop