የአብይ አህመድ አገዛዝ የጀመረውን አማራን የማንበርከክ ወረራ የተሳካ ለማድረግ፣ የመከላከያ እና የሲቪል አመራሩን በከሃዲነትና በታማኝነት መስፈርት እየለካ የኢተርኔት አገልግሎት የዘጋባቸውና የለቀቀላቸው መሆኑ የሚቀጥለው የስም ዝርዝር ያሳየናል። ለአንባቢ ግልጽ ማድረግ የሚያስፈልገው ኢንተርኔት በአማራ ክልል አልተዘጋም። የኢንተርኔት አገልግሎት የማያገኙ ቦታዎችና ግለሰቦች ተመርጠው እንዲዘጉ ነው የተደረገው። አገዛዙ ከፈለገ በአማራ ክልል በየትኛውም ቦታ ኢንተርኔት ከፍቶ ለአንድ ሰው መክፈት ይችላል። የደህነንት ሰዎችና አንዳንድ ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኙት በዚህ ምክንያት ነው። ይህን ማድረግ በመቻሉ፤
ለፋኖ መረጃ ይሰጣሉ በሚል ፍራቻ ከመከላከያ ኢንተርኔት የተዘጋባቸው
ሌ/ጀ አሰፋ ቸኮል
ሜ/ጀ ሙላለም ታደስ
ታማኝ ናቸው በሚል ምክንያት ከመከላከያ ኢንተርኔት የተከፈተላቸው
ብ/ጄ ዘውዱ ሰጥአርጌ
ብ/ጀ ማርየ በየነ
ሻለቃ ደግስው ዶሻ
ኮነኔል ተስፋየ ኤፍሬም
ኮነኔል ዳዊት እንዳለ
የተፈቀደላቸው የወረራው አሰተባባሪዎችና የክልል አመራሮች
ደሳለኝ ጣሰው ምክትል ፐሬዝደንትና የክልሉ አሰተዳደር ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አሁን ባህር ዳር ያለ
ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን የክልሉ ፖሊስ አዛዥ አሁን ባህር ዳር ያለ
ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ የክልሉ የማረሚያቤቶች ሀላፌ
ኮሚሽነር ደጀኔ ለምነው
ኮ/ል ባምላኩ አባይ
ኮ/ል ማሩ
ጧሂር ሙሐመድ የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ
ወ/ሮ ፈንቱ ተስፈየ አፈ ጉባኤ
ሲሳይ ዳምጤ
ዘላለም ልጅዓለም
የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ድረስ ሳህሉአቶ ብርሃኑ ጎሽም የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኅላፊ
ዶክተር መንገሻ ፈንታው የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኅላፊ
በሌላ በኩል
ኢዜማ የሚባለው ፓርቲ የድርጁትን ሊቀመንበር የዶ/ር ጫኔን መታፈን በሚመለከት ከጥቂት ቀናት በፊት ያወጣው መረጃ አስገራሚ ሆኖ ያገኘነው ብዙዎች ነበር። ዶ/ር ጫኔ “የታርጋ ቁጥር በሌለው፣ የፍርድቤት መያዣ ትእዛዝ በሌላቸው የጸጥታ አከላት በቁጥጥር ስር ውሏል” ብሎን ነበር። መኪናው ታርጋ ከሌለው፣ አጋቾቹ የፍርድ ቤት ማዘዣ ከሌላቸው እንዴት “የጸጥታ አካላት” የሚል ስም ኢዜማ ሰጣቸው የሚል ጥያቄ መግለጫውን ያነበበው ሁሉ ጠይቆ ነበር።
መግለጫ መሆን የነበረበት “ማነንታቸው ባልታወቀ ታርጋ በሌለው መኪና አፋኞች ታፍኗል፣ የት እንደደረሰ ለማወቅ ጥረት እናደርጋለን” ነበር። በግሌ ያንን መግለጫ ባነበብኩበት እለት ግልጽ የሆነልኝ ዶ/ጫኔ ከመታፈኑ በፊት አገዛዙ፣ ዶ/ር ጫኔ እንደሚያስረው፣ ለምንስ እንደሚያስረው አስቀድሞ ለኢዜማ አመራራ ተናግሮ እንደነበርና ከኢዜማ አረንጓዴ መብራት በርቶለት እንደነበር ነው። ኢዜማ ጉዳዩን ለማጣራት ኮሚቴ አቁሚያለሁ ያለው ጉዳይ የፖለቲካ እቃ እቃ ጨዋታ እንደሆነ ገብቶኝ ነበር። ዶ/ር ጫኔ በኢዜማ የተሸጠና ጉዳይ ያበቃለት እንደሆነ ያወቅሁት በዛን እለት ነበር። በዛሬው እለት ኢዜማ ያወጣው መግለጫ ያረጋገጠው ይህንኑ ነው።
በዛሬው እለት በኢዜማ የወጣው መግለጫ ዶ/ር ጫኔ በአመጽ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሳተፍ የነበረ የድርጅቱን መርህ የጣሰ ግለሰብ ነው የሚል ነው። ዶ/ጫኔ ፍርድ ቤት ሳይፈርደበት በገዛ ድርጅቱ ወንጀለኛ መሆኑ ተወስኖበት ለብልጽግና ጅቦች ተወርውሯል። አንድ ሰው ጥፋተኛነቱ በፍርድ ቤት ሳይረጋገጥ ወንጀለኛ እንዳይባል እታገላለሁ ሲል የነበረ ድርጅት በገዛ አባሉ ላይ ከፍትህ ሂደት በፊት ብያኔ ሰጥቶ ተገኝቷል። እሱ ብቻ አይደለም፣ ዶ/ር ጫኔን ወንጀለኛ ለማድረግ አገዛዙ ለዲጂታል ቅጥረኛ ሰራዊቱ ያሰራጨው የድምጽ ቅጅ እውነትኛ እንኳን ቢሆን ይህ ቅጅ በፍርድ ቤት ትእዛዝ የተደረገ ካልሆነ በየትኛውም የፍትህ ሂደት ተቀባይነት እንደሌለው እየታወቀ፣ ኢዜማ የዶ/ር ጫኔ የድምጽ ቅጅ፣ በማን ትእዛዝ ተቀዳ፣ ማን ቀዳው የሚል ጥያቄ ሳያነሳ፣ አገዛዙስ የዶ/ር ጫኔ ጉዳይ ለፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ለማህበራዊ ሚድያ በማሰራጭት ህገወጥ ተግባር ለምን ፈጸመ የሚሉ ጥያቄዎች ከማንሳት ይልቅ፣ ቀላሉን እና ከአገዛዙ ጋር ይበልጥ የሚያቀራርበውን እርምጃ ውስዷል። ለተጨማሪ ሹመትና ስጦታ የሚያበቃውን ዶ/ር ጫኔ ማውገዝ መርጥዋል። “በተፎካካሪ” ፖለቲካ ድርጅቶች ታሪክ የድርጅቱን አመራራ ተሸቀዳድሞ ወንጀለኛ የሚል ብያኔ ስጥቶ አንድ ግፈኛ አመራራ ለሚወስደብት ማንኛውም እርምጃ ቡራኬ በመስጠት ኢዜማ የመጀመሪያው ድርጅት ሆኗል።
የሚገርመው ግን የ/ዶር ጫኔ ድምጽ የቀዳው አካል 24ሰአት ሙሉ እነዚህን ዶ/ር ጫኔን ለጅቦች አሳለፈው የሰጡትን የኢዜማ አመራሮች የስልክ ምልልስ ሲቀዳ እንደሚውል፣ ይህ አካል ከግለሰቦች ውጭ፣ ይህን ተግባሩን የሚቆጣጠረው፣የሚያስቆመው ምንም አይነት መንግስታዊ አካል እንደሌለ አለማወቃቸው ነው።
ምስሎቹ የጄነራል ቸኮል አሰፋ እና የዶ/ጫኔ ከበደ ናቸው