የሀገርን ትንሣኤ ለማፋጠን ፋኖን ከሠርጎ ገቦች ሤራ መጠበቅ – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 ፋኖየሚወራውና መሬት ላይ ያለው እውነት እየተለያየብኝ ስጨነቅ የታዘበ አንድ ወዳጄ የአማራ ፋኖ ትግል በገንዘብ በተገዙ ፋኖን መሳይ ፋኖዎች በአንዳንድ ቦታዎች እክል እየደረሰበት መሆኑን ጠቆም አደረገኝ፡፡ መጠርጠር ጥሩ ነው፡፡ “የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ቤት ደጃፍ ታዬ” የመባሉ ነገር በጥጃው ላይ የሚኖረንን ተስፋ ያጨልመዋል፤ እናም ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ በርግጥም በአማራ ፋኖ ዙሪያ የምሰማው እውነት ከሆነ ነፃነት መምጣቱ የማይቀር ቢሆንም የሚወስድብን ጊዜና የሚፈጀው የመስዋዕትነት መጠን ያሳስባል፡፡ የሰው ነፍስ ቀላል አይደለም፡፡ ኦነግሸኔ አሁን በአማራው አካባቢ በተለይ እያደረገው ያለው ጅምላ ጭፍጨፋና ሌላ ሌላ ሊነገር የሚዘገንን ግፍና በደል ሰው ነኝ የሚልን ፍጡር እንቅልፍ ሊያሲይዝ አይችልም፡፡ በወለጋና በሻሸመኔ እንሰማው የነበረው አማራ ላይ የሚደርስ ሰቆቃ ጊዜውን ጠብቆ አማራው ጓዳና ሣሎን ገብቷል፡፡ በጠራራ ፀሐይ ዜጎች በየአደባባዩ እየተረሸኑ ነው፡፡ የነገ ፋኖ ናችሁ በሚል ሕጻናት ሳይቀሩ በየተገኙበት ይገደላሉ፡፡ አሳሳቢና አስጨናቂ ጊዜ ላይ ነን፡፡ በአዲስ አበባ ግን በአገር አማን ሕይወት እንደወትሮው ቀጥላለች፡፡ እንደሚባለው ገንዘብ የማይሠራው ነገር የለምና ከነአባባሉም “ገንዘብ የተሸከመች አህያ የማትደረማምሰው ምሽግ የለም” እንዲሉ ነውና ይህን ትግል በገንዘብ የጠለፉ ኃይሎች እስካሉ ድረስ የአማራ ኅልውና እንደሰውኛ አስተሳሰብ ትልቅ አደጋ ላይ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ገንዘብ የፈለገውን ያህል ገብጋባ ቢያደርግ ለጭራቁ አቢይና ኦነግ ሸኔ አድሮ አማራን የሚሸጥ አማራ ወይንም በአማራ ስም ተመሳስሎ የገባ ወገን ወንጀሉና ኃጢኣቱ ከሰባት ትውልድም በላይ የሚተላለፍ ትልቅ በደል ነው፡፡ ለአንዲት እንጀራ ተብሎ በ70 እና በ80 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ የአማራን ትግል ለማኮላሸት ፋኖን ሳይቀር መከፋፈልና ማገዳደል ይቅር የማይባል ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡

“ሽልም ከሆነ ይገፋል፤ ቂጣም ከሆነ ይጠፋል” ይባላልና ይሄ ከፍ ሲል የሰነዘርኩት ሥጋት እውነትነት ካለው እየቆዬን በግልጽ የምናየው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህልም ሆኖ እንደጤዛ እንዲረግፍ እንደጉምም እንዲተን ጸሎቴና ምኞቴ ነው፡፡ ለማንኛውም ከተለያዩ ገፆች የቃረምኳቸውን አስተያየቶች ከዚህ ቀጥዬ ላስቀምጥና የሚመለከታቸው ወገኖች እንዲያስቡበት አደራ በማለት ጅምሬን ልቋጭ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃቅ መስዋዕትነት ከተራራ ይልቅ ትከብዳለች፣ የሸረኛ ሞት ከላባም ትቀላለች! - ሚኪ

* * *

ይቅርታ ይደረግልኝና ባንዳ አማራን ከመማር ይልቅ ኦነጎችን አስተምሮ ወደመጡበት አካባቢያቸው በሠላም መሸኘት ብዙ ጥቅም አለው፡፡ የገዛ ወገኑን ለገንዘብና ለመናኛ ሥልጣን የሸጠ ከርሣም አማራ ግን አንዴ አይደለም አሥሬ በመግ*ል መቀጣጫ ማድረግ ነው፡፡ የገዛ ወገኑን ለብልት ቆራጭና በአማራ ጥላቻ ላበደ ኦሮሙማ አሣልፎ የሚሰጥ ይሁዳ ጥንቱንም ባይወለድ ይሻለው ነበር፡፡

ስለአማራ የቀን ጅቦች ብዙ ይሰማል፡፡ ፋኖን መስለው በውስጡ በመሰግሰግ ብዙ ኪሣራ እያደረሱና ትግሉን እየቀለበሱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ስለዚህ አማራ ከኦነግ ጋር የሚያደርገውን ውጊያ ጋብ አድርጎ በቅድሚያ ውስጡን ቢያጠራ በአጭር ጊዜ ስኬታማ ይሆናል፡፡ ወንድም እህቱን ለጭራቅ እየሸጠ ላይበላው በራሱና በዘመዶቹ ስም በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ባንኮችና ግለሰቦች ረብጣ ብር በአቢይ ሸኔ የሚቀመጥለት ፋኖ በአመራርና በጦር ሜዳ ተሠልፎ የአማራን ዕልቂት በሚያፋጥንበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ትንሣኤ እንዳማረን ይቀራል ባልልም በጣም ሊዘገይና መስዋዕትነቱም ከትርፉ ኪሣራው ሊበልጥ ይችላል፡፡ አማራ ሆዳም አማራን ካላስወገደ በጥቃቅን ድሎች ሆን ተብሎ እንድንደሰት እየተደረገ የአማራ ዘር እንደምናየው በአጭር ጊዜ ከራሱ ክልል ጭምር ይጸዳል፡፡ ከዚያ በኋላ ኦነግሸኔን የተባበሩ ባንዳ አማሮች ተራቸው ይደርስና የሸኔ ቁርስ ይሆናሉ – ሊያውም ሙሉ ሌሊቱን የሸኔው መንጋ እየተፈራረቀ አስገድዶ ከደፈራቸውና ከተጫወተባቸው በኋላ፡፡ ወይ መረገም እናንተዬ!! ምን ቀን ላይ ጣለኝ???

 

* * *

አንድ ትልቅ ችግር ልናገር፡፡

ኦሮሙማ ለማንም ነፍስ አይጨነቅም፡፡ ለሰው ነፍስ የሚጨነቅ ሰው ነው፡፡ እነሱ ግን የሰው ጠባይ የለባቸውም፡፡ ለምሣሌ “አንድ መቶ ሺህ ኦሮሞ ምርኮኛ እንልቀቅላችሁና አንድ ፋኖ ምርኮኛ ልቀቁልን” ቢባሉ “ስትፈልጉ ቀቅላችሁ ብሏቸው እንጂ ፋኗችሁን ዐይናችሁ እያዬ እንረሽነዋለን” እንደሚሉ ከኔ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እነሱ የሚደሰቱት አንድ ፋኖ ገድለው የአማራ ጥላቻቸው የፈጠረባቸውን ቂም በቀል መወጣትና 60 እና 70 ወይ 80 ሚሊዮን አማራን ማስከፋት እንጂ የመቶ ሺህ ኦሮሞ ሕይወት በአንድ አማራ ለውጠው መላውን የኦሮሞ ማኅበረሰብ ማስደሰት አይደለም፡፡ ይህም intrinsic (ተፈጥሯዊ?) የኦነጋውያን ጠባይ አቢይንና ሽመልስን ጨምሮ የሁሉም አክራሪ ቄሮና ቄሪት የወል ጠባይ ነው፡፡ ከነዚህ ሰዎች የማያውቁትን ምሕረትና ርህራሄ መጠበቅ ከጅልነት ያለፈ ዕብደት ነው፡፡ ለነዚህ የሰው ግማሾች ያደረ አማራ ታዲያ ከነሱም በከፋ ትልቁ ጠላት ነውና ቀድሞ ማጥፋት ሆዳም ባንዳን መሆን አለበት፡፡ ከዋና ጠላት የከፋ ተመሣስሎ የሚገኝን ክፉ ወረርሽኝ ሳያስወግዱ የውጪ ጠላትን ለማሸነፍ መሞከር በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ሊመዘገብ የሚገባው በዓይነቱ አዲስ የሆነ ገልቱነት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የአማራው ትግል ክለሣና ውይይት እንደሚያሻው ሳልጠቁም ይቺን አስተያየት ብጨርስ ይቆጨኛል፡፡ ግን የሀገራችን አድሮ ቃሪያነት ሲበዛ ይገርማል፡፡ ምን ይሻለን ይሆን? መሞቱን እንኳን ሳያውቅ በኑሮም በጥይትም እያለቀ ያለ ብቸኛው ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይመስለኛል፡፡ በቻፓቲ ዋጋ ላይ የተደረገ የአሥር ሣንቲም ጭማሬ የሆሲኒ ሙባረክን መንግሥት አፈር ከመሬት ሲደባልቅ በአንድ ኪሎ ነጭ ጤፍ ላይ የተጨመረ ብር 140 ግን የአቢይን ሰይጣናዊ መንግሥት ማነቃነቅ ቀርቶ ዝምቡን እሽሽሽ ሲል አይታይም፡፡ በአፄዎቹ ዘመን እንደነበረው ዘና ፈታ ያለ ሕይወት ለመምራት ከ500 ሽህ ብር በላይ የወር ገቢ ሊኖርህ ሲገባ ከትራንስፖርት የማያልፍ 2000 ብር የሚከፈል ሕዝብ የምታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በደርግ ዘመን ባለሃምሣ ብር የወር ደሞዝተኛ የራሱን ቤት መሥራት እንዳልቻለ ሁሉ የዛሬ የብር 20 ሽህ ደሞዝ ቤት መሥራቱ ይቅርና በረንዳ እየታደረ ሥጋንና አትክልትን ለማይጨምር ቱሪማንቱሪ ምግብም አይበቃም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም አማራ ሆይ ከዳግም ክህደት ተጠንቀቅ! - አገሬ አዲስ

ይህ ወደዞምቤነት የለወጠን ማኅበረሰብኣዊ አፍዝ አደንግዝ መቼ እንደሚለቀን አላውቅም፡፡ መሪ ነኝ ባዩ ሰውዬ ደግሞ የሰው ደም ካልጠጣና በሰው ደም ባሕር ካልዋኘ እንቅልፍ አይወስደውም፡፡ ዓለም እስካሁን ያላየችው ሀሰተኛና አስመሳይ እንዲሁም ወደር የለሽ ጨካኝ ሰው ነው የገጠመን፡፡ ድህነትን ማስፋፋት፣ በመናፈሻ ሰበብ ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው በሚሊዮኖች ማፈናቀል፣ በዘራቸው ሳቢያ ለፍተው ጥረው ግረው የሠሩትን ቤት በግሬደር መደርመስ፣ ቤቴን አታፍርሱ የሚልን በጥይት መቁላት፣ ከተሞችን በሰካራምና በዕብድ፣ በለማኝና በበረንዳ አዳሪ ማጥለቅለቅ፣ የሴቴኒዝምን እምነት ተከታዮች ማብዛት፣ ቀደምት የእምነት ተቋማትንና ተከታዮቻቸውን ድራሻውን ማጥፋት፣ በየቀኑ ሰዎችን በሰበብ አስባቡ ማሰርና መግደል፣ ሕዝብን በኑሮ ውድነት የእሳት ጅራፍ መግረፍ፤ ፍቅርሲዝምና ሰላሚዝም እንዲሁም የማርያም ሲሰተሪዝም (ለዚህችኛዋ ነጥብ እመት ስንዱን ያስቧል) የመሳሰሉ አስቂኝ መጤ እምነቶች እንዲበራከቱና ትውልዱን እንዲያሽመደምዱ ማድረግ፣ ሕንጻዎችንና አጥሮችን ማደስን የመሳሰሉ መንግሥታዊ የተቋራጭ ሥራዎችን ያለ አንዳች ጨረታ ሥልጣኑን ተመክቶ ለጓደኞቹና እወክለዋለሁ ለሚለው ነገድ አባላት በከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጡ ማዘዝ፣ ወዘተ … የዚህ በአጋንንት መንፈስ የሚመራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና ዋና መገለጫ ጠባዮቹ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ጉድ ችሎ የሚኖር ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ዓለም ምን ይታዘበን ግን? ይገርማል!! “ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል” እንደሚባለው ሆኖ እንጂ ኢትዮጵያ አሁን አለች ማለት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ ብዙ ቦታ መደበኛ ሥራ ቆሞ ሠራተኛው ለላንቲካው ገብቶ እንደሚወጣ ነው የሚነገረው፡፡ ማንም ስለምንም ግድ የለውም፡፡ ጉቦውና ሙስናው አይነሳ፡፡ እጅህን ካልዘረጋህ ሌላው ቀርቶ ካህናት እንኳን እቤትህ መጥተው የሞተ ዘመድህን አስከሬን አይፈቱልህም – በኔው ስለደረሰ ይህን በደምብ አውቀዋለሁ፡፡ በጥቅሉ ሀገር ባለቤት አልባ ሆናለች፡፡ ግዴላችሁም የሃይማኖት አባቶቸ ባይኖሩንም በየግላችን ሱባኤ እንግባ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንዴት ለዚህ በቃን?--ገዥዎቻችንስ እናውቃቸውለን ወይ?

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share