ከዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት የተሰጠ መግለጫ

August 16, 2023

 

Amhara
#image_title

ንፁሐንን በድሮን፣ በጦር አውሮፕላኖች እና በከባድ መሳሪያዎች በመጨፍጨፍ የአማራ ህዝብ እና ፋኖ የጀመረውን የህልውና እና የስርዓት ለውጥ ትግል መቀልበስ አይቻልም

ዘረኛውና ፋሽስቱ አብይ አህመድ በምዕራብ ጎጃም በፍኖተ ሰላም ከተማ ከቤተክርስቲያን በመመለስ ላይ በነበሩ ምእመናን ላይ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ከ300 በላይ ንፁሐንን በግፍ ጨፍጭፏል፣ ብዙወችንም ቁስለኞች አድርጓል። እንደዚሁም ተመሳሳይ በምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከተማ፣ በምስራቅ ጎጃም በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ ኳስ ሜዳ ላይ እንዲሁም በየላምገጅ ቀበሌም በድሮን ጥቃት ብዙ ንፁሐንን እና አርሶ አደሮችን ጎድቷል፣ ገድሏል። እንዲሁም በደብርሃን፣ ሸዋሮቢት፣ ጎንደር፣ ባህርዳርና፣ ቆቦ በድሮን፣ በጦር አውሮፕላን እና ሄሊኮፕተር፣ በታንክ፣ መድፍ እና ዙ-23 ከባድ መሳሪያወችን በመተኮስ በሽህወች የሚቆጠሩ ንፁሐንን ጨፍጭፏል፣ ቁስለኛም አድርጓል። በቅርሶችና በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ይገኛል።

ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ዘረኛውና ፋሽስቱ አብይ አህመድ ከላይ በተጠቀሱ ቦታወችና በሌሎች ከተሞች በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ (genocide) በጥብቅ ያወግዛል። ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ዘግናኝ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እንዲያወግዙ ጥሪ እናቀርባለን። የአማራ ህዝብ በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከ30 ዓመታት በላይ የደረሰበት መጠነ ሰፊ ሰቆቃ አልበቃ ብሎት ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ግፉ በተባበሰ መልኩ ቀጥሎ ህዝቡ በመኖርና በመሞት መካከል ውስጥ ይገኛል። በአብይ አህመድና ግብረ አበሮቹ እየደረሰበት ያለው ግፍ አንገፍግፎት እና የሚጠይቃቸው ጥያቄወች ሊመለሱ የሚችሉት በሰላሚው ትግል ሳይሆን የስርዓት ለውጥ በማምጣት መሆኑን አምኖበት ቆርጦ ስለተነሳ ድሮን በመጠቀም ንፁሐንን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ በማሰር ወይንም በሽምግልናና ድርድር ሰበብ በማታለል ወደ ኋላ የሚመለስ ትግል እንድማይኖር መታወቅ አለበት።

ይህ አማራው የጀመረው የህልውና ትግል የሚደመደመው ይህን አስከፊና ሰው በላ ስርዓት ከስሩ ነቅሎ በማፈራረስ የህግ የበላይነትን፣ ሰላም፣ ፍትህ፣ እና እኩልነትን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን በማረጋገጥ ብቻ ይሆናል። የአብይ አህመድ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች አማራው ወደ ስልጣን ከመጣ የብሄረሰቦችን መብት ይደፈጥጣል፣ በራስ መተዳደርን ይከለክላል፣ የሃይማኖቶችን ነፃነት ይገድባል፣ ቋንቋና ባህላቸውን እንዳያሳድጉ ይከለክላል ብለው የሚነዙት ወሬ ፍፁም ሀሰት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህን መርዝ የሚረጩት በአብይ አህመድ አፓርታይዳዊ አገዛዝ የተማረሩት አብዛኞቹ ብሄረሰቦች የአማራውን የህልውና ትግል በመደገፍ እና በመቀናጀት የስርዓት ለውጥ በአጭር ጊዜ ማምጣት እንዳይችሉ አገር አቀፉን ትግል ለማምከን ነው።

አማራው የሃይማኖትን ልዩነት የሚያስተናግድ ማህበረሰብ እንጅ የሃይማኖት ፀር ሆኖ አያውቅም፣ ደግሞስ ራሱ አማራው የኦርቶዶክስ እስልምና ፕሮቴስታንት ካቶሊክ እምነቶች ተከታይ ያለበት ህዝብ መሆኑ ሳይታወቅ ቀርቶ ነው? እንዲሁም አማራው ለሌሎች ነገዶች ቋንቋና ባህል መስፋፋት ፀር ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 83 በላይ ነገዶችና ቋንቋዎች ይኖሩ ነበርን? ከ28 ነገዶች በላይ ከምድረ ኢትዮጵያ

እንዲጠፉ ያደረገው የአማራ ነገድ ነውን? አብይና ግብረ አበሮቹ በ16ኛው ክፍለ ዘመን መሰሎቻቸው እንደፈፀሙት ወረራ የሰው ልጅ ሁሉ ተባብሮና ተከባብሮ በሚኖርበት፣ በኢኮኖሚያዊ ግብይት በተሳሰረበት፣ ከቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር ራሱን እያራመደ ባለበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሁሉም የበላይ ለመሆን የኢትዮጵያ ታሪክ ታሪካችን አይደለም፣ ኦርቶዶክስና እስልምና የእኛ እምነቶች አይደሉም፣ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያን አፍርሰን እኛን የመሰለች ኢትዮጵያ እንመሰርታለን በሚል አገር የማፈራረስ/የማዋለድ ስራ ተጠምደው ይገኛሉ። ታዲያ በህግና በፍትህ ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን በዕኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተነሳውን አማራ የብሄረሰቦች ጠላት አድርጎ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው ለምን ይሆን? አማራው በወሬ ሳይሆን ከሁሉም የኢትዮጵያ ነገዶች ጋር ተጋብቶ፣ ተዋልዶ፣ ባህላቸውን አክብሮ፣ ቁንቋቸውን በመናገር፣ እምነት በመጋራት በጥሩ ጉርብትና እና ወዳጅነት እንደሚኖር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። እውነቱ ይኸ ሆኖ ሳለ በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እውነቱን መለወጥ የሚችሉ የሚመስላቸው ሀቁን ተረድተው ህዝብን ከህዝብ ከሚያቃቅር ድርጊታቸው እንዲታቀቡ እንጠይቃለን።

እማራው እንደ ህዝብ ጠላቴ የሚለው ህዝብ የለውም። ህወሓትና ኦህዴድ በአማራው ላይ በፈፀሙበትና አሁንም እየፈፀሙበት ባለ ግፍ ጠላት ቢያደርጋቸው የትግራይና የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነው ሊባል ፈፅሞ አይችልም። መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ በኢትዮጵያ ላይ የተከሉትን እጅግ አስከፊ ዘረኛ ስርዓት ከስሩ ነቅሎ በመገርሰስ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላማቸው የፀና መብታቸው የተከበረባት፣ ፍትህና የህግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እኩልነት የተረጋገጠባት፣ የሃይማኖት ነፃነት የተከበረባት፣ የሁሉም ነገዶች ባህልና ቁንቋዎች የተከበረባት፣ ከሰሜን ደቡብ ክምስራቅ ምዕራብ ተዘዋዉሮ የመስራት መብት የተከበረባት ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ምኞትና ተስፋ ነው ብለን በፅኑ እናምናለን።

ይህችን የመሰለች ሰላማዊትና ፍትህ የሰፈነባት አገር ለማምጣት ሁሉም የኢትዮጵያ ነገዶች ከአማራው የህልውና ትግል ጋር በመቆም መታገል ይኖርባቸዋል። በዚህ ረገድ የሲዳማ እጄቶወች፣ የጉራጌ ዘርማወች በመግለጫ ለፋኖ ድጋፋቸውን መግለፃቸው የሚወደስ ሲሆን ሌሎችም ነገዶች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲገልጹ እናበረታታለን። በእርግጥ ከደቡብ ኢትዮጵያ የመጡ ብዙ የመከላከያ አባላት ወንድም በሆነው የአማራ ህዝብ ላይ አንተኩስም፣ አብሮን ከተዋደቀው ፋኖ ጋር አንዋጋም ብለው መሳሪያቸውን እያስረከቡ ወደየመጡበት አካባቢ እየተመለሱ መሆናቸው፣ አንዳንዶችም ፋኖን እየተቀላቀሉ መሆናቸው የሚያስመሰግን ተግባር ሲሆን ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

ይህን ዘረኛ አስከፊ አፓርታይዳዊ ስርዓት ከስሩ ነቅሎ በመጣል ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለማምጣት የሚደረገውን ዕልህ አስጨራሽ ትግል ከግቡ ለማድረስ ለአማራው ብሎም ለሁሉም የኢትዮጵያ ነገዶች የሚከተሉትን የትግል ጥሪዎች እናቀርባለን

መሰሪውና ዘረኛው አብይ አህመድ አማራውን በጎጥ ለመከፋፈል ያደረገው ጥረት ሙሉ በሙሉ በህዝቡ ትግል ስለከሸፈበት አሁን ደግሞ ፋኖን የኦርቶዶክስ እምነት ብቻ አራማጅ በማድረግ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ አማራ መካከል ልዩነት ለመፍጠር እየተፍጨረጨረ ስለሚገኝ የጎጡን ክፍፍል አጀንዳ እንዳከሸፋችሁበት ይህንንም መርዘኛ የሃይማኖት አጀንዳ እንድታመክኑበት ጥሪ እናደርጋለን። ማንኛውም አማራውን ለመከፋፈል የሚወረወረወር አጀንዳ ሁሉ የሚጠቅመው አማራውን ሳይሆን ጠላቱን ነው።

በመከላከያ በፓሊስ አድማ ብተና ሺምቅ ተዋጊ በደህንነት ውስጥ ያላችሁ አማራወች ህዝባችሁ በድሮንና በመድፍ እየተጨፈጨፈ ይህንን ግፈኛ ስርዓት ለማውረድ ከፋኖና ከህዝባችሁ ጎን የምትቆሙበት ጊዜ ነገ ሳይሆን ዛሬ በመሆኑ ህሊናችሁን ፀፀት ውስጥ የማይከት ቁርጠኛ ውሳኔ ወስናችሁ ፋኖን እንድትቀላቅሉ ወይም ባላችሁበት ሆናችሁ እንድትተባበሩ እንጠይቃለን።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ድንበር መጠበቅ እንጅ ህዝብን መጨፍጨፍ ስራችሁ ባለመሆኑና ከተጠያቂነትም ለማምለጥ ህዝብ ጨርሱ የሚለውን ትዕዛዝ ባልመተግበር እንድትተባበሩ ጥሪ እናቀርባለን። እምቢ ካለ መሳሪያችሁን ህገወጥ ትዕዛዝ ወደሚያስተላልፈው እንድታዞሩ እናሳስባለን።

የእምነት ተቋማት ባአጠቃላይ የአማራ ንፁሐን በከተሞች ውስጥ በድሮን በጀትና በተለያዩ ከባድ መሳሪያወች እንዲያልቁ ሲደረግ ግልፅ የሆነ ተቃውሞ አለማሰማታችሁ በጣም የሚያስተዛዝብ ነገር ነው። ይህ ትግል በአሸናፊነት ካልተጠናቀቀ በእምነት ነፃነት ላይ በሰው ልጆች የመኖር መብት ላይ ሊደርስ የሚችለውን መከራ ትስቱላችሁ ተብሎ አይገመትም። ስለዚህ በአስቸኳይ የተቃውሞ ድምፃችሁን፣ ግሳፄችሁን እንድታሰሙ ጥሪ እናቀርባለን።

የአማራ ህልውና ትግል መልስ የሚያገኘው በስርዓት ለውጥ እንጅ በሽምግልና ወይም አካባቢያዊ ድርድር ባለመሆኑ በስርዓቱ የምትላኩ ሽማግሌወችና የሃይማኖት አባቶች የአብይ አህመድ ስልጣን ማራዘሚያ፣ የአማራው ሰቆቀቃ ማስቀጠያ፣ ከመሳሰሉ ድርጊቶች እንድትቆጠቡ ጥሪ እንደርጋለን።

የአማራ ወይም የሌላ ነገድ ባለሀብቶች አብይ አህመድ በአማራው ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ለሚያግዝ ተግባር ገንዝባችሁ እንዳይውል ጥንቃቄ እንድታድርጉ እንጠይቃለን።

የለውጥ ፋና ወጊ በመሆን የሚታወቁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪወችና መምህራን ይህን በአማራ ፋኖ የተጀመረውን የስርዓት ለውጥ ትግል በየከተሞች እንድታቀጣጥሉ ጥሪ እናደርጋለን።

የሶማሌ፣ አፋር፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጉራጌ፣ ጋምቤላና፣ ሌሎች ነገዶች ይህን የስርአት ለውጥ ትግል በመደገፍ እንድትነሱ እንጠይቃለን።

የኦሮሞና ትግራይ ህዝብ ህወሓትና ኦህዴድን አንቅረህ በመትፋት ወንድምህ ከሆነው የአማራ ህዝብ ጋር በመቆም ይህን ኢትዮጵያን ምድራዊ ሲኦል ያደረጋትን ስርዓት ተባብሮ በመገርሰስ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የተመቸች አገር እውን ለማድረግ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

የብልፅግና አባላት በሙሉ ለጥቂት አምባገነኖች ስልጣን ማስቀጠል መሳሪያ ከመሆን ራሳችሁን በስልት በማግለል ቢያንስ ትግሉን ባለማደናቀፍ እንድትተባበሩ ጥሪ እናቀርባለን። ሞቶ ሊቀበር አንድ ሀሙስ ለቀረው ስርዓት መዋደቅ ትርፉ ከህዝብ ጋር የዘላለም ጠላት መሆን ነው።

11.በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የአማራውን የህልውና ብሎም የስርዓት ለውጥ ትግል ለመደገፍ በሙሉ አቅማችሁ እንድተባበሩ እንዲሁም እብሪተኛው አብይ እህመድ በፍኖተሰላም፣ ቡሬ፣ የጁቤ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረብርሃን፣ ሸዋ ሮቢት፣ ቆቦና ሌሎች የአማራ ከተሞች ውስጥ በድሮን በጀትና በተለያዩ ከባድ መሳሪያወች በሽወች የሚቆጠሩ አማራወችን እየጨፈጨፈ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረስብ እንድታጋልጡ ጥሪ እናቀርባለን።

አማራው ከመሰል ወንድም ነገዶች ጋር በመተባበር ይህንን ከፋፋይ፣ ዘረኛ ስርዓት

አስወግዶ ፍትሐዊት ኢትዮጵያን ዕውን ያደርጋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የጂብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል ፤ የሟች ችኩል ገዳይን ይከተላል !

185255
Next Story

ኦነግ ያልቻለውን፤ የዐቢይ ጦር አደራ ተቀበለ | በዕውቀቱ ስዩም አብይን አስጠነቀቀ | የሃዋሳ ከንቲባ ተሰወረ

Go toTop