August 16, 2023
3 mins read

የፖለቲካ ሥልጣን ቢኖረኝ (በቀለ ገሠሠ)

በህይወቴ የፖለቲካ ሥልጣን ተመኝቼ አላውቅም። ፍላጎቴ እግዚአብሔር ይመስገን ባገኘሁት ከፍተኛ ትምህርትና ዓለማቀፍ የሥራ ልምዴ ወገኔን ማገልገል ብቻ ነበር።
ዛሬ ግን በተለይ በአማራው ወገኖቻችን ላይ ያነጣጠረው የጅምላ ጭፍጨፋና መፈናቀል ስመለከት አንጀቴ ያራል፣ ልቤ ይቆስላል፣ በህይወት መሰንበቴን ያስጠላኛል። አማራ የትግሬ፣ የኦሮሞ፣ ወዘተ ህዝብ ጠላት ሆኖ አያውቅም። ያገኘውን ልክ ጥቅም አልነበረም። እንደ ሁሉም ዜጋ ጥሮ ግሮ ህይወትን አቸንፎ የኖረ ደግ ህዝብ ነው። ስለዚህ በምናብም ሆነ በተግባር ጭቁን ህዝባችንን ለመታደግና ውድ አገራችንን ከጥፋት ለማዳን ሥልጣን ቢኖረን የምንፈጽማቸው ተግባራት የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፣
ሀ) ሁሉ አቀፍ የሽግግር መንግሥት አናቋቁማለን፣ ዘረኝነትን፣  የወገን ጭፍጨፋ፣ መፈናቀልና ሰቆቃ እናቆማለን፣  በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚሳተፉት በነፃ ፍርድ ቤት  እንዲጠየቁ እናመቻቻለን።  በመቀጠል የተለያዩ ፓርቲዎች ነፃና ፍትሐዊ በሆነ መልክ ተወዳድረው መንግሥት እንዲመሠርቱ እናመቻቻለን፣
ለ) ሕገመንግሥቱ እንዲለወጥ አናደርጋለን፣
ሐ) የተረጩት የውሸት ትርክቶች እንዲታረሙ አናደርጋለን፣
መ) ዕርቀ ሰላም እናወርዳለን፣ የማንም ዜጋ ህይወት በግፍ እንዳይጥፋ እንከላከላለን፣
ሠ) የተፈናቀሉትን ወገኖች መልሰን አነናቋቁማለን፣
ረ) ግፍ ለደረሰባቸው ወገኖች ካሣ እንከፍላለን፣
ሰ) ለገበሬው ሰላምና  ድጋፍ አናመቻቻለን፣
ሸ) ነጋዴው በነፃ ተዟዙሮ መነገድ መቻሉን አናረጋግጣለን፣
ቀ) ወጣቶች ጥሩ ትምህርት እንዲያገኙ እናመቻቻለን፣ እንደግፋለን፣
በ) የሀገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ የሚገባውን ሁሉ ድጋፍ  እንሰጣለን፣ ለምሣሌ ጠፍ መሬቶች ማልማት፣ ወንዞቻችንን መገደብ፣ የመስኖ እርሻዎች ማስፋፋት ፣ የአካባቢ አየር ብክለት መከላከል፣ ወዘተ ።
ውድ ወገኖች፣
እላይ እንደጠቀስኩት ጥረቴ የመንግሥት ስልጣን ፍላጎት አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም። ዋናው ምኞቴን ለመግለጽ ስለሆነ ተረድታችሁ ለዘላቂ ሰላምና ዕድገት  የሚቻላችሁን ጥረት እንድታደርጉ በትህትና እጠይቃለሁ፣
ቸሩ አምላካችን ይጨመርበት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop