ጭራቅ አሕመድ ቆርጦ የተነሳው አማራን በልቶ ለመጨረስ ነው፡፡ አማራን በልቶ ቢጨርስ ደግሞ ምዕራባውያን ጌቶቹ ዝንቡን እሽ እንደማይሉት በግልጽ አሳውቀውታል፡፡ ለነጻነቱ ቀናዒ የሆነው፣ በማንነቱ የሚኮራው፣ ነጭን ከመጤፍ የማይቆጥረው የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ቢጠፋ፣ ያፍሪካ አንድነት ምልክት የሆነችው አዲሳባ ደግሞ አማራና አማራዊነት ሙሉ በሙሉ የተወገደባት፣ አፍርቃዊ አፓርታይድ የነገስባት፣ የአፍሪቃውያን በጎጥ የመከፋፈል ዋና ምልክት የሆነች፣ አፍሪቃውያንን አንገት የምታስደፋ፣ አሳፋሪ ኦነጋዊ ከተማ ብትሆን ምዕራባውያን ደስታውን አይችሉትም፡፡
ስለዚህም የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ያለውን፣ በጭራቅ አሕመድ የሚመራውን፣ የኦነግንና የወያኔን ፀራማራ ጣምራ ጦር ፊት ለፊት መግጠም፣ የእሳት ራት ከመሆን ውጭ ፋይዳ የሌለው አጉል ጀብደኝነት ነው፡፡ የጭራቅ አሕመድ ዓላማ ደግሞ ዘመናዊ መሣርያ እስካፍንጫው የታጠቀውን የኦንግንና የወያኔን ጣምራ ጦር ይዞ፣ የነፍስ ወከፍ መሣርያ ካነገበው ከፋኖ ጋር ፊት ለፊት ለመግጠምና፣ ፋኖን በዚያውም መላውን የአማራን ሕዝብ በመድፍ እየመደፈ፣ በንቦቴ (drone) እየነቦተ የዶግ ዐመድ ለማድረግ ነው፡፡
በሰው ኃይል በመሣርያና ባቅርቦት (logistics) ብዙ እጥፍ የሚበልጥህን ጠላት አንተ በመረጥከው መቸት (መቸ እና የት) እንጅ እሱ በመረጠው መቸት አትገጥመውም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ሌላ ምንም ማለት ሳይሆን የደፈጣ ውጊያ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ያማራ ሕዝባዊ ግንባር (አሕግ) በጭራቅ አሕመድ ከሚመራው የኦነግና የወያኔ ጣምራ ጦር ጋር መፋለም ያለበት በደፈጣና በደፈጣ ብቻ ነው፡፡ ለዚህ የደፈጣ ውጊያ ግብአት ይሆነው ደግሞ አያቶቹ ባርበኝነት ዘመን ይጠቀሙባቸው የነበሩትን ዘዴወች ከማስታወስ በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አሥሩን የሰንሹን (Sun Tzu) የማጥቃትና የመከላከል መርሖች ልብ ሊል ይገባል።
- ድልማድረግ በራስ ሁኔታ፣ ድል መደረግ ደግሞ በጠላት ሁኔታ ይወሰናል፡፡ ስለዚህም ጠቢብ የጦር አዛዥ በራሱ በኩል ሊያከናውናቸው የሚገባውን ሁሉ በጥንቃቄ አከናውኖ አመችውን ጊዜ ነቅቶና ተግቶ በትእግስት ይጠባበቃል፡፡ ታላቆቹ ጦረኞች ትዕግስትና ጊዜ ናቸው፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ዲንጋ ይሰብራል፡፡
- ኢተረችነትበመከላከል ችሎታ፣ ረችነት ደግሞ በማጥቃት ችሎታ ይወሰናል፡፡ ጠላት ሲበረታ ተከላከል፣ ሲደክም አጥቃ፡፡
- ጠቢብየጦር አዛዥ የሚያጠቃው መጠቃት ያለበትን እንጅ ለማጥቃት ሲል ብቻ አያጠቃም፡፡
- ጠቢብየጦር አዛዥ የሚከላከለው መካላከል ያለበትን እንጅ ለመከላከል ሲል ብቻ አይከላከልም፡፡
- ጠቢብየጦር አዛዥ ሲያጠቃ የሚከላከል፣ ሲከላከል የሚያጠቃ ያስመስላል፡፡
- ጠቢብየጦር አዛዥ ሲያስፈልግ እንደ እሳተ ገሞራ ከምድር ይፈነዳል፣ ሲያስፈልግ ደግሞ እንደ መብረቅ ከሰማይ ይበርቃል፡፡
- ጠቢብየጦር አዛዥ ሲያስፈልግ እንደ ንፋስ ይፈጥናል፣ ሲያስፈልግ ደግሞ እንደ ተራራ ይቆማል፡፡
- ጠላትህ ሲጠናከር ሽሸው፣ ሲዳከም አጥቃው፡፡ በግንባርህ ሲመጣብህ በጀርባው፣ በቀኝህ ሲመጣብህ በግራው እየተዟዟርክ አዋክበው፡፡ አወይ አተኳኮስ ወይ ደፋር መሆን፣ ሲሄድ መቀለቻ ሲዞር ግንባሩን፡፡ጠላትህ ሲረጋጋ ባሉባልታ አሸብረው፣ ሲያርፍ በትንኮሳ አዋክበው፡፡ ካጋም እንተጠጋ ቁልቋል ረፍት እየነሳህ፣ እዚህም እዚያም እየበሳሳህ፣ ዘላለም አስለቅሰው፡፡
- ጠላትህትይዝብኛለህ ብሎ የማያስበውን፣ ከያዝክበት ደግሞ ባስቸኳይ ሊያስለቅቅህ የግድ የሚያስፈልገውን ቦታ ሳይስበው በድንገት ያዝበትና ሥራህን ቶሎ ሠራርተህ ሳያስበው በድንገት በመውጣት ትሄድበታለህ ብሎ በማያስበው መንገድ ትሄድበታለህ ብሎ ወደማይገምተው ቦታ በፍጥነት ሂድ፡፡
- እንደመብረቅ በድንገት በርቀህ እንደ አውሎ ንፋስ በድንገት ንፈስ ፡፡ መብረቅ ድንገት ይበርቃል እንጅ ከየት በኩል እንደሚበርቅ አይታወቅም፡፡ አውሎ ንፋስ በድንገት ነፍሶ የሚጠራርገውን ይጠራርጋል እንጅ ከወዴት እንደሚነፍስ አስቀድሞ አይታወቅም፡፡ ሲበርቅ ቢጨፍኑ ከመወጋት አይድኑ፡፡
- ጠንካራ ስትሆን ደካማ፣ ደካማ ስትሆን ጠንካራ፣ ሩቅ ስትሆን ቅርብ፣ ቅርብ ስትሆን ሩቅ፣ ዝግጁ ስትሆን አልዝግጁ፣ አልዝግጁ ስትሆን ዝግጁ መስለህ ለጠላትህ ታይ፡፡ ጠላትህን እንቁ አሳይተህ እነቀው፡፡
- ማጥቃትህስኬታማ እንደሚሆን እርግጠኛ ልትሆን የምትችለው ጠላትህ የማይከላከለውን ስታጠቃ ብቻ ነው፡፡ መከላከልህ ስኬታማ እንደሚሆን እርግጠኛ መሆን የምትችለው ጠላትህ የማያጠቃውን ስትከላከል ብቻ ነው፡፡ በማጥቃት የተካነውን መከላከል፣ በመከላከል የተካነውን ማጥቃት ትርፉ ትልቅ ሽንፈት ነው፡፡
ያማራ ሕዝብ ሕልውናውን ማስጠበቅ የሚችለው የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግሥት ገርስሶ፣ የሚገባውን ሥልጣን ይዞ፣ ዘላለማዊ ጠላቶቹን ወያኔና ኦነግን ለዘላለም ሲያስወግድ ብቻና ብቻ ነው። ከሕልውና ጠላት ጋር ያልሞት ባይ ተጋዳይ የሞት ሽረት ትግል አድርጎ ወይ መግደል ወይ መሞት እንጅ መደራደር፣ መሽማገል የሚባል ነገር የለም።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com