August 6, 2023
7 mins read

በ እ ው ነ ት   ተ ጠ ያ ቂ ው   ማ ነ ው ?

ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ላይ (በተለየ በአማራ ላይ) እየደረሰ ላለውና መቆሚያ ላጣው ለዚህ ታሪክ ይቅር ለማይለው መከራና በደል  ተጠያቂው ማነው?
ኑ! በታሪክ መረጃ  በእውነት
            እንዋቀስ!
በአጉል ትርክት ተነፋርቆ ከማልቀስ!
ይሻለናል በምክክር እውነቱ ላይ
             መድረስ!
አንችልምና ሰይፍ መዘን ወደ አፎቱ
              መመለስ!
ማንም ይወቅ ይረዳ የዛሬ ተረኛ
    እንደሚሆን የነገ አልቃሽ!
   ስለዚህ ቆምና ረጋ በለን:
ታሪክ ይመርመር በደንብ ይጠና፣
ለምን እንድሚታረድ አማራ በጎዳና፣
ውጣልኝ እየተባለ ከሰፈር ከቀጠና!
በእውነት አገሩ የትነው የአማራ?
ድንገት በሩቅ ይሆን በኢራቅ ተራራ?
ምነው ሰው ጠፋ የሚራራ ለአማራ?
እንዲህ ሲታረድ በጸሐይ ጠራራ!
*** Please click this link to see something about the history of Amhara***
             ይህን ያህል መከራ:-
ስደት፣ ረሀብ፣ ጮኸት፣ ግፍ በደልና ሞት በአማራ ላይ በእውነት ከምን የተነሳ ነው?
ለዚህ ታሪካዊ በደልና ግፍስ በእውነት ዋና ተጠያቂው ማነው? የታሪክ ጸሐፊዎችስ በእውነት ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡት ነው?
*** በልጅነቴ አንድ ከደቡብ ምእራብ ወደ ተወለድኩበት አንዱ የሰሜን ትንሽ ከተማ አስተማሪ ሆኖ የመጣ መምህር ቆንጆ የሆነችውን የአጎቴን ልጅ ወዶ የተቸገረ መሆኑን፣ ነገር ግን በህሊናው በተቀረጸ የበታችነት ስሜት ታስሮ መጠየቅ አቅቶት ሲጨነቅ አባቴ ከሌሎች አስተማሪዎች ድንገት ይሰማል! ከዚያም ተማራችሁ በምትባሉ ሰዎች መካከል በሰዎች እንዲህ ያለ የተበላሽ የልዩነት ሃሳብ መኖሩ ተገቢ አይደለም ብሎ በመውቀስ ጉዋደኛቸው ልጅትዋን እንዲያገባ በማድረግ የዚህን አስተማሪ የበታችነት ስሜት ሃሳብ ችግር አስወግዶ ባሁኑ ሰዓት በርካታ ልጆችና የልጅ ልጆች እንዲወለዱ መደረጉን አውቃለሁ::
እኔም ካባቴ ካገኘሁት ከዚህ “ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረና እኩል ነው” በሚለው እሳቤ በማደጌ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ወቅት ከቅርብ ዋና ጉዋደኞቼ መካከል:-
1) ያለፈውን 27 የኢሕዴግ አገዛዝን ዘመን አያድርገውና (እርግፍ አድርጎ ስለተወኝ) የአድዋው አብርሃም አበበ የመጀመሪያው የቅርብ ጉዋደኛየ ነበር፣ ( በእውነት ባለፈው የጦርነት ወቅት ልረዳው ፈልጌ ያጣሁት ከዳተኛ የድሮ ጉደኛዬ)
2) ዛሬ የት እንዳለና ምን እንደሚሠራ ባላውቅም የወለጋው ሙሉጌታ ልግዲ አንዱ የማከብረው ጉዋደኛየ ነበር፣
3) ሌላውና እስከ አሁን ድረስ ያልተለወጠ ጉዋደኛዬ የአሩሲው ተውላጅ ኢኮኖሚስቱ ጥላሁን ታደስ (ነፋስ እንደፈለገ ሊያደርገው
የማይችል ታማኝ ጉዋደኛ) ወዘተ ነበሩ::
ታዲያ ትናንትን ዛሬ ላይ ሆኜ ሳየው ለዛሬ የአማራ መገደል ዋና ምክንያቱ ሰው ሁሉ ሰው ነው በሚል እሳቤና አገሪቱን ደግሞ አገሬ ናት ብሎ በሄደበት ሥፍራ ሁሉ በሙሉ ልብ ሰፍሮ፣ ሠርቶ፣ አግብቶና ጎረቢቱን እንደ ቤተ ሰቡ ቆጥሮ በማመን ተዘልሎ አብሮ መኖሩ ነው:: እኔም በዚህ ማንነት ተወልጄ ያደኩ በመሆኔ እና በሰዎች አፈጣጠር  መካከል ልዩነት አለ ብየ ስለማላምን ወለጋ
የምኖር ብሆን ኖሮ እኔም ዛሬ ታርጄ ነበር::
በእውነት በዚህ መልኩ የተበላሸን የኢትዮጵያን አስደናቂ የአንድነት ታሪክን በምንና እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል ሳስበው ግራ ይገባኛል? ምናልባት መልኮት በራሱ ታምራዊ ጥበብ ይህን የልብ ቁስል ካልፈወሰ በስተቀር በሰሜን በተለይ እንደ TPLF ትእቢት እና እንደ ኦነግ ቂመኛነት በሰው ደረጃ የሚቻል አይመስለኝም::
***አማራውን እንዲህ የመስዋእት በግ ያስደረገው ሌላው ክፍተትና ደካማ ጎኑ የጋራ መድረክ ፈጥሮ በሰከነ መንፈስገና ከጅምሩ ቁጭ ብሎ በመደማመጥ ተነጋግሮ ከመደራጀት ይልቅ ቆሞ ለመተኮስ የሚያደርገው ፉከራና ጫጫታ እስከአሁን ድረስ መፍትሄ ያጣለት ደካማ ጎኑ ነው***
አሁንም በሁሉም አቅጣጫ ለተካኑ/ለበሰሉ
ሰዎች አመራሩን በጥንቃቄ ካልሰጠ እና በሕዝቡ አእምሮ ላይ ተገቢው የማንቃት ሥራ ካልተሠራ በደሉና ልቅሶው የሚያቆም አይመስለኝም::
እኔን የበለጠ ያሳዘነኝና የገረመኝ ኢትዮጵያን
እንወዳለን የሚሉት የሌሎች ብሄረ ሰቦች አባላት በተለይ በአማራ ላይ ይህን ያህል የመከራ ዶፍ ሲወርድ አንድ ቀን እንኩዋን ልክ አይደለም! ነገ በእኔ/ኛ በሚል ድጋፍ አብሮ እንደኖረ ሰው አለማድረጋቸው ልቤን አሳዝኖታል::
እንዲህ ያለ መጨካከን ከየት እንደ መጣ በጥናት ተዳስሶ መፍትሄ ቢበጅለት አዲሱን ወይም መጪውን ትውልድ መታደግ ነው::
ከማክበር ሰላምታ ጋር
ሙናች ነኝ
ከአባይ ማዶ
ፊላው ሥር
ገሳውን ለብሶ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop