July 29, 2023
4 mins read

ጥንብ ባለበት  ጂብ አይጠፋም  

tinbu 1 1ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ማለት ድሮ ነበር ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ሰማይ በጭለማ መሬት በጭቃ በሆነበት ሀምሌ ወር ተደጋጋሚ ጉድ ይሰማል፡፡

ይህ ሀምሌ አስራ ዘጠኝ ቀን በጯሂት በዕለተ ዕረቡዕ በሬ አርዶ የኢትዮጵያን ኃይማኖት  እና ታሪክ ማራከስ አዲስም ድንገተኛም አይደለም ፡፡

ከሁሉ በፊት ወያኔ/ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም. በሰሜን ምዕራብ ህዝብ ተጋድሎ እና ፊታዉራሪነት ከደደቢት በርኃ ቀበሮ ጉድጓድ ስቦ በማዉጣት ለመኃል አገር እና ለማዕከላዊ መንግስት አብቅቷል፡፡

ሆኖም ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ እንዲሉ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ኢትዮጵያን ፣ ኢትዮጵያዊነትን እና መገለከጫዎችን  ዕዉነታ እና ይሁንታ ማሳከር እና ማደናቆር ታሪክን ፣ዕምነትን እና ባህልን  በሀሰተኛ ትርክት በማመሰቃቀል በጥላቻ እና በበታችነት ልክፍት ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ማሳዘን እና መበቀል እንደነበር ከደደቢት የተቀዳ የጥፋት ጎርፍ ነበር ፡፡

ለዚህም ብዙ የሚነገሩ ቢኖሩም  የህወኃት ታጣቂዎች ደብረ ማርቆስ በወርኃ ሁዳዴ የነስኃ እና የትንሳዔ ፆም ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ በንቀት እና በማን አለብኝነት በሬ አሳርደዉ አሻሻ ገዳሜ ሲሉ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ሞት ለዉያኔ ብሏል በዚህም ብዙ ሠዉ በጭካኔ ተገድሏል፡፡

ያኔ ነበር ህጻናት ሳይቀሩ  አ.ህ.አ.ዴ.ግ የልጂ ልጂህ አይደግህ በማለት አምርረዉ አዉግዘዋል፡፡

ይኸዉና  አበዉ ጠላት በመቶ ዓመቱ የወተት ጥርስ ነዉ እንዲሉ ዛሬም በግላጭ በጎንደር ጯሂት ገዳማት የሆነዉ ከብዙዎች አንዱ የጥላቻ ማሳያ እንጂ አዲስም መጨረሻም አይሆንም፡፡

አማኞች ጫማጨዉን አዉልቀዉ በሚከበሯት ቤ/ክርስቲያን የእምነት ተከታይ ያልሆነ ጓዳ ጎድጓዳ  ያለምንም ከልካይ በሚወጣ በሚገባባት እንደ አዲስ አያወሩ መታከት ለምንም ለማንም አይሆንም ፡፡

የኢትዮጵያን ታላቅነት ፣ጥንታዊነት፣ታሪካዊነት ከኢትዮጵያ ቀደምት ሠሪዎች፣መስራቾች እና መሪወች ዕዉነት በማይቀበሉ እና በተከበሩበት መንበር ለመቀመጥ፤ በተጠቀሙበት ዕቃ ለመጠቀም በፍርኃት እና በጥላቻ የሚመለከቱትን ገዳማት ክፍት መሆን ከዚህ በላይ ቢሆን የሚደነቅ ቢኖር ሰባዊነትም ፤ዕምነትም የከዳዉ መሆን አለበት ፡፡

ዕምነት ፤ኃይማኖት ፣ባህል እና አገርን ለያይቶ ማየት ያስከተለዉ መዘዝ እና አድር ባይነት የበዛበት ቸልተኝነት  ኢትዮጵያን ከሚጠሉት ጋር የሚስማሙ  የጂብ ጓደኛ ከጥንብ ያደርሳል እንዲሉ የሆነዉ እና የሚሆነዉ ሁሉ የታወቀ እና የተጠበቀ ነበር ፤ ነዉ፡፡ “ጥንብ ባለበት ሁሉ ጂብ አይጠፋም ” እና ከታሪክ እና ከመከራ አለመማር አለመኖር ነዉ ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

Allen

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop