አቶ ዮሐንስን የምትወቅሱ፤  የየሱስና የጳውሎስን ታሪክ አትርሱ 

ንስሐ ካማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንሰሐ በሚገባ ባንድ ኃጢያተኛ ሰማያት ይደሰታሉ።” (ሉቃስ 15፡7)

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በቅርቡ ባደረገው ንግግር ሳቢያ አያሌ አወዳሽና አሞጋሾችን ሲያፈራ፣ በዚያው ልክ (እንደውም ከዚያው በበለጠ) ደግሞ አያሌ ወቃሾችና ከሳሾች ተነስተውበታል።  ያቶ ዮሐንስን ያለፈ ታሪክ እያነሱ ባሁኑ ንግግሩ የሚወቅሱትና የሚከሱት ወያኔወችና ኦነጎች በተለይም ደግሞ ጭራቅ አሕመዳውያን ባይሆኑ እንጂ ቢሆኑ አያስገርምም።  የሚያስገርመው ግን የወያኔና የኦነግ ሰለባ የሆኑት አማሮች፣ ያለፈውን ያቶ ዮሐንስን ታሪክ እያጣቀሱ አቶ ዮሐንስን ባሁኑ ንግግሩ ሲወቅሱትና ሲከሱት ማየት ነው።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው (ከልቡ ሆነም አልሆነም) “በሴራ ፖለቲካ ተበልጠናል፣ ነገ ሊገሉኝ ይችላሉ፣ አፋኝና ጨቋኝ መንግሥት እንዳለን ማወቅ አለብን፣ መከላከያ ወዳማራ ክልል የገባው በማን ፈቃድ ነው፣ መከላከያን የፈጠርነው ሊከላከለን እንጅ ሊያሳድደን አይደለም፣ ወዘተ …) በማለት ሲናገር፣ ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል፣ በተለይም ደግሞ የፕሮፓጋንዳውን ዘርፍ እጅግ በጣም እንደጠቀመ ለመረዳት የፖለቲካ ተንታኝ መሆንን አይጠይቅም።  ስለዚህም በብልጽግና አባልነቱ ውስጥ አዋቂ የሆነው አቶ ዮሐንስ ቧያለው ብልጽግናን በተለይም ደግሞ ጭራቅ አሕመድን በዚህ ደረጃ ሲያጋልጥልን ከኛ የሚጠበቅብን እንዲቀጥልበት ማበረታታት ብቻ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ አንዴ ወንጀለኛ ሁሌ ወንጀለኛ አይደለም።  ከወንጀላቸው ተጸጸተው በመመለስ፣ የተወነጀሉበትን በብዙ እጥፍ የሚክሱ ታላላቅ ሰወች ነበሩ፣ አሉ፣ ወደፊትም ይኖራሉ።  ለምሳሌ ያህል የክርስትና መሠረት እየሱስ ቢሆንም፣ ክርስትናን የዓለም ሐይማኖት ያደረገው ግን እየሱስን በጽኑ ያሳድድ የነበረውና በማሳደዱ በጽኑ የተጸጸተው ሐዋርያው ጳውሎስ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።  የወያኔና የኦነግ ጃንደረባ ወይም ደንገጡር በመሆን ባማራ ሕዝብ ላይ የፈጸምኩት ወንጀል ጸጽቶኛል የሚል የብአዴን አባልንም መመልከት ያለብን በዚህ እይታ ነው (በውነት መጸጸት አለመጸጸቱን ለማወቅ ድርጊቱን ባይነቁራኛ እየታዘብን)።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪ (ተመስገን ደሳለኝ )

ከጸጸት የሚበልጥ አነሳሳሽ ስሜት የለም።  በወንጀላቸው በጽኑ የተጸጸቱ ወንጀለኞች፣ ወንጀልን እና ወንጀለኛን ከአልወንጀለኞች በላይ በጽኑ እንደሚጠሉና እንደሚታገሉ የታወቀ ነው።  ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ለማድረግ፣ የጭራቅ አሕመድ ግብራበር በመሆን ባማራ ሕዝብ ላይ በሠራው ወንጀል በጽኑ ከተጸጸተ የብአዴን አባል የሚበልጥ ጠቃሚ ሰው የለም።  ለምሳሌ ያህል ባንድ ወቅት የጭራቅ አሕመድ ቀንደኛ ደጋፊ የነበሩና በደጋፊነታቸው የተጸጸቱ የሚመስሉ የሚዲያ ሰወች፣ ባሁኑ ወቅት ለፀረጭራቅ አሕመድ ተጋድሎ እያደረጉ ያሉትን ጉልህ አስተዋጽኦ በጉልህ እያሳዩን ነው።

ድል የሚገኘው የጠላትን ሰፈር በማዳከምና የራስን ሰፈር በማጠናከር ነው።  የጠላትን ወንጀል በማጋለጥ ከጠላት ሰፈር ወጥተናል ብለው በይፋ የሚያውጁ ሰወች (በውነት ወጡም አልወጡም)፣ በጠላት ተራ ካድሬና ተራ ወታደር ላይ ሽብር ስለሚለቁበት የጠላትን ሰፈር ያፍረከርኩታል፣ ወገንን ደግሞ ጠላትን በጽኑ እንዲታገል ይበልጥ ያነሳሱታል።  ያቶ ዮሐንስ ቧያለው ንግግር ደግሞ ያማራን ሕዝብ ለሕልውናው ትግል ይበልጥ እንዳነሳሳና፣ በጭራቅ አሕመድ ካድሬወችና ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እንደፈጠረ አሌ ማለት አይቻልም።  ስለዚህም አቶ ዮሐንስን ባሁኑ ንግግሩ አይዞህ ልነለው ይገባናል።  አቶ ዮሐንስን አይዞህ ስንል ሲያዩ ደግሞ ሌሎች ብአዴኖች ያቶ ዮሐንስን ፈለግ ለመከተል ይነሳሳሉ

አማራን ያሳደድ የነበረ የብአዴን አባል፣ በወንጀሉ ተጸጽቶ ያማራ ሕዝብ መድሕን የማይሆንበት ምንም ምክኒያት የለም፣ ምንም እንኳን የብአዴን አባል ያማራ መድሕን ከሚሆን፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ ቢቀልም።  ቀንደኛው ፀራማራ አቶ በረከት ስምዖን በአማራ ሕዝብ ላይ የሠራው ትልቁ ወንጀል፣ ብአዴንን የፈጠረው አማራ ጠል ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ሲሉ ማናቸውንም ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ለመፈጸም ቅንጣት የማያቅማሙ ታዛዥ ውሾች የሆኑትን፣ የጃግሬኔት (follower) ሰብዕና አለመጥን የተጠናወታቸውን የደመቀ መኮንንን ዓይነት መፃጉወች በማሾ እየፈለገ በማሰባሰብ መሆኑ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የካቲት ሄደ የካቲት መጣ - አንዱ ዓለም ተፈራ

በወንጀሉ ተጸጽቶ ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል ልቀላቀል የሚል ከሺ አንድ የብአዴን አባል ሲገኝ ግን፣ ካማራ ሕዝብ የሚጠበቀው፣ በወንጀሉ የተጸጸተውን አባል እጁን ዘርግቶ በመቀበል ወንጀሉን በሺ እጥፍ እንዲክስና የወያኔንና የኦነግን ግብአተ መሬት እንዲያፋጥን ማመቻቸት ነው።  ያማራ ሕዝብ ይህን ሲያደርግ ሲያዩ ደግሞ፣ ሌሎች የብአዴን አባሎች በወንጀላቸው ተጸጽተው ትግሉን ለመቀላቀል ይበልጥ ይበረታታሉ።  ትግሉም ይበልጥ እየተቀጣጠለ፣ ወያኔንና ኦነግን ይበልጥ እያቃጠለ፣ ተንጨርጭረው /ድብን/ የሚሉበትን ቀን ይበልጥ እያቃረበ ይሄዳል።

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

4 Comments

  1. እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች “overtaken by events” ይላሉ። ይልቅሰ አቶ ዮሃንስ “ተጠለፈ” ስለተባለው የሰልክ ድምጽ ምን አሉ? ይቅርታ ስላልሰማሁ ነው። ካላስተባበሉ ደግሞ “የሳቸው አይደለም” ብለን ልንጠራጠር አንችልም ማለት ነው። ያም ማለት የፋኖ አስተሳሰብ እና ፍላጎት (ግብ፣ ፕሮግራም፣ ልካዊ አደረጃጀት ስለሌለው!) በእሳቸው በኩል በአማራ ምክር ቤት ተንጸባርቋል ማለት ነው። መንግስትም “እማናውቅ አይምሰልህ” ብሏቸው “ጨሉማ ጀዲ” ብሏል ማለት ነው። መልክቱ ለሌሎች እንደ አቶ ቧያለው በውስጥ ለሚሰሩትን “እንዴ ይነቃብኝ ይሆን እንዴ?” ወደሚል ፍርሃት እንዲገቡ ያደርጋል ማለት ነው። አቶ ቧያለው ከዚህ በኋላ በማናቸውም የፖለቲካ መድረከ (እንደ እስክንድር ነጋ በግልጽ ሸፍተው ጫካ ገብተው ካልታወቀ ቦታ ካልሆነ በስተቀር) እንኳን ሊናገሩ በቦታው አይገኙም። በሌላ አነጋገር ያቺ የተጠለፈች ሰልክ ድምጽ የሳቸው መሆኗን “ዱታ” ነኝ ብለው ካላስተባበሉ እና ትንሽም ብትሆን ጥርጣሬ መጫር ካልቻሉ፣ ብልጽግናዎች “Thank you, Comrade Johnny, for committing political suicide!” እንዲሉ አስችለዋቸዋል ማለት ነው።
    ሰላማችን ይብዛ!

  2. ግሩም አስተያየትነው:: ማንም የሰው ልጅ ሊሳሳት ይችላል ዋናው ጉዳይ ከስህተቱ መመለሱ ነው:: ብዙዎቻችን በዚህ አማራጠል ጠሚ ተታለን ነበር:: ልዩ የምናገኘው ጥቅም ኖሮ ሳይሆን ለህገር በጎ ያስባል በሚል ግምት ነው:: እኔ በግሌ ያንተን ያለፉት አመታት ጠንካራ ፅሁፎች ስቃወም ነበር:: ይህ ሰው ወያኔ መሆን አለበት ያልኩበትንም አስታውሳለሁ ይቅርታ! ጥቂቶች አስቀድማችሁ ነቃችሁ ጥሩ ግምት:: ብዙዎቻችን በዚህ ቀውስ ሰውዬ ተሞኘን:: ያ ጊዜ አልፏል:: አቶ ዮሀንስ ቧያለውን ቀጥተኛነትና ሀቀኛነት አደንቃለሁ::

  3. What ever , Ato yohanis is a right perso. he speaks to the point, call a spad a spad. if u are an Ethiopian

  4. What ever , Ato yohanis is a right person . he speaks to the point, call a spad a spad. if u are an Ethiopian

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share