ለጀርመን ድምፅ ራዲዮ አዘጋጆች – ከ ሸዋ ሕዝብ ድርጅት (ሸሕድ)

ሸዋ ሕዝብ ድርጅት (ሸሕድ)
SHOA  PEOPLE’S  ORGANIZATION (SPO)

16.07.2023

ይድረስ ለጀርመን ድምፅ ራዲዮ አዘጋጆች
ለእነ  ሥዩም ጌቱ፣ ሂሩት መለሰና ነጋሽ መሐመድ

ቦን/ጀርመን

በተቀዳሚ የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ።

በመቀጠልም በ10.07.2023 ዓ.ም «የአርጎባ ጀበርት ይፋት ሱልጣኔት ሹመትና ተቃዉሞ» በተባለው ርእስ ያናፈሳችሁን የፈጠራ ትርከት ተመልክተን ምላሽ ለመስጠት ግድ ብሎን ተነስተናል። ይታወቅ ሸሕድ ታሪካችን፣ ባሕላችንና መላዉ ሸዋ ከአባይና ግቤ ወንዞች በመለስ እስከ ዘይላ በርበራ ኤደን ባሕረ ሰላጤ ባለዉ ጥንታዊ ምድራችን ላይ የተደረገዉንና የሚደረገዉን ተስፋፊነትና ወራሪነት፣ የፈጠራ ዝባዝንኪ ትርክትን በጥብቅ እንቃወማለን።

የዶይቸ ቬለ አማርኛ ቋንቋ ስርጭት ወይንም «ራዲዮ ኮሎኝ»
የዶይቸ ቬለ አማርኛ ቋንቋ ስርጭት ወይንም «ራዲዮ ኮሎኝ»

እረ! ለመሆኑ በ”አፋር ክልል” አርጎባ ልዩ ወረዳ ተብዬዉ እንዴትና ለምን ተፈጠረ? ጋቼና፡ ጨኖ፣ ዱለቻ ወዘተረፈ ከአዋሽ ወንዝ በመለስ ያንኮበር ወረዳ የቆራሬ/አልዩ አምባ ና የሐር አምባ/ገና መምቻ ምክትል ወረዳ ቀበሌዎች ያማራና አርጎባ እስላሞች መኖሪያ ምድር ከጥንት ጀምሮ ያለ ነዉ። ታዲያ! ከአንኮበር ወረዳ ግዛት አዋሽ ወንዝ በመለስ ያሉ የአርጎባ መኖሪያ ቀበሌዎችን ከዋናዉ ቆራሬ/አልዩ አምባና ሐር አምባ/ገና መምቻ ጋር በቁንቁዋና ባሕል ሆነ በመልካ ምድር አንድ የነበረዉን ማኅበረሰብ ያለ አግባብ ሸንሽነዉ ወደ አፋር ክልል ያደረጉት፤ አብሶም ያርጎባና ዐማራ ጥንታዊ ርስት በሸዋ የሁኑትን ፈንታሌ፣ መተሃራ፤ አዋሽ ያለዉን ለኦሮሚያ ክልል ተብዬዉ አጠቃለዉ ወስደዉ፣ አርጎባዉና ዐማራዉን ባገሩ በምድሩ በኦነጋዉያን ይገደላል፣ ይፈናቀላል። ይህም መሆን የጀመረዉና ዛሬም ቀጥሎ ያላዉ ወታደራዊ ደርግ ወድቆ በምዕራባዉያኑ በተለይም ባሜሪካንና በእንግሊዝ መንግሥታት ዋና አስተባባሪነትና ድጋፍ ወያኔ ትግሬ ትሕነግ ና ኦነግ ሥልጣን ይዘዉ፣ በኢትዮጵያ የባንቱስታ አፓርታይድ የጎሣ ክልልን ልክ እንደ ወራሪዉ ፋሽስት ጣሊያን ሸንሽነዉ፤ ያማራዉን ሰፊ ሕዝብ አግልለዉ፣ በከተሞች ሆነ በገጠርም መብትየለሽ አድረገዉ፣ የሽዋ ዐማራ፣ ዟይ፣ ጉራጌና አርጎባ ምድርን ሰልቅጠዉ በያለበት ይልቁንም “ኦሮሚያ” ብለዉ በፈጠሩት ክልል ዉስጥ በሐረርጌ፣ በአሩሲ፣ በባሌ፣ በጅማ፣ በወለጋ ወዘተረፈ የዘር ፍጅትና ማፅዳትፋት በኦነግ ዘማችነት፣ በትህነግ አዝማችነት ሲፈፅሙ ቆይተዉ ዛሬም ባሰ እንጂ አልተገታም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአሜሪካን ባለሥልጣነት ሆይ በወድማማቿች መካከል ጠብ መዝራታችሁን አቁሙ ፡፡ መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ፀረ ዐማራ፣ በተለይም ፀረ ሸዋ የሆነዉ ወያኔ ትግሬ ከመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 45 ከመቶ በላይ ዐማራ መሆኑና ከትግሬ ክፍለ ሀገር በስተቀር በሌሎች ክፍለ ሀገራት ነዋሪዎች ጋራ ታዛምዶና ተስማምቶ መኖሩን ለማጥፋት አስቦና አቅዶ ባማራዉ ሕዝብ መሐከል በሰላም ከሚኖሩት ኅዳጣን ነገዶች ዉስጥ ጥቂት አሳማ ተለጣፊ ምልምል ቅጥረኞችን ማደራጀቱ ይታወቃል። የአርጎባ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አብዴን) ተብዬዉ ሆነ ሌሎች እንደ የቅማንት፣ የአገዉ ሸንጎ፣ የዋግ ኽምራ፣ ብአዴን ወዘተረፈ በወያኔ ትሕነግ ቅጥረኛ ግልገል ፋሽስት የአናሳ ትግሬ ጎሣ ድርጀት የተዘጋጁበት ዋና ዓላማ ያማራዉን ትልቅ ብሔርነት ለማክሰም ነዉ። እንኩውን በጋቼና አልዩ አምባ ጉዋሮ ይቅርና በመላዉ ዳዋሮ (ምዕራብ ሐረርጌ- ጨርጨር ጋራ ጉራቻ ፣ ሐብሮ፣ ጋራ ሙለታ፣ ወበራ)፣ በአዳል ( ምሥራቅ ሐረርጌ – ጉርሱም፣ ጅጅጋ፣ ኦጋዴን ፣ ዘይላ፣ በርበራ፣ መቃዲሾ) የይፋት- አዳል ዑመር ወላስማ ሱልጣንት ትዉልድ ወራሽ ነኝ የሚል የዚህ ዘመን ትዉልድ ፍጹም ቅጥረኛ ፀረ ዐማራ ሴራ ቅንብር ለመሆነ የተረጋገጠ ነዉ።

እራሳቸዉን ሐረሬ፣ ያ17ኛዉ ክ.ዘመን ወራሪ መጤ ጋሎች አደሬ ብለዉ የሚጠሩዋቸዉ የወያኔ ትግሬ ምርጥ ቅጥረኛ ምልምል፣ በሐረር ከተማ በዙኃን ዐማራ ሕዝበ ክርሲትያንና እንዲሁም በቅርባቸዉ ባለዉ ከጋላ ወረራ ፍጅት በታላቅ ጀግንነት የተረፈዉን የአዳል አርጎባ ማኅበረሰብ ላይ ከፍተኛ ንቀትና ጥላቻ ሲያደርጉ እንደኖሩና እንዳሉም በትክክል ይታወቃል። ስለ እዉነትና ታሪካዊ ሐቅ ቢዘከር የይፋት አዳል ወላስማ ሥርዎ መንግሥት ተወላጅ ዝርያዎችማ በግራኝ አሕመድ ተጨፍጭፈዉ ከወደሙት የእነ ሱልጣን አቡበከር ዝርያ በተአምር ተርፎ ቢኖር እንኩዋ ከሐረር ጀጎል ዉጭ የራሳቸዉን ምሽግ ገንብተዉ ከሚኖሩት አርጎባ በተሰቦች ብቻ ሊሆን ይችላል እንጂ ዛሬ በሸዋ ይሁን በወሎ ከሚኖሩት አርጎባዎች የዘር ሐረግ የሚገኝ የለም። ስለሆነም ነዉ የይፋት ሱልጣኔት ሹመት በአፋር ክልል ልዩ ወረዳ ተብሎ የተከወነዉ ትራኢትና የተናፈሰዉን የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ትርክት የፀረ ዐማራ ቅስቀሳ ዘመቻ ዘርፍ ስለሆነ ተቃዉሟዎችን ለመላዉ ኢትዮጵያ ሕዝብ ይድረስልን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መጻሕፍተ መነኮሳት ፡-የፓትርያሪክ፣ የጳጳሳትና የሌሎችም መነኮሳት የግብር ሚዛን!

የዉሸት ትርክቱና ያለ አግባብ የይፋት ሱልጣኔት ሹመት ዉድቅነት በዝርዝር ቀርቧል።

፩ኛ/ከዋናዉና ጥንታዊው አርጎባ ማኅበረስብ ተለይቶ በአፋር ክልል ልዩ ወረዳ የሆነዉ የጋቼና አርጎቤ ተብዬ መላዉን አርጎባ ማኅበረስብ አይወክልም። እነዚህ የወያኔ ትግሬ ፍጡራን ስብስብ ነበሩ፣ ናቸዉ።

፪ኛ/የይፋት ሱልጣናት ዘመን ከ1285-1415 ዓ.ም ያላዉ ሲሆን በታዋቂ ጦረኛዉ አጤ አምደ ጽዮንና ተተኪዎቹ እነ አጤ ዘርዐ ያዕቆብ ተሸንፈዉ በ1332 ዓ.ም የይፋት ወላስማ ሱልጣኖችና መሳፍንቶች ሽዋ ይፋትን ትተዉ አዋሽ ማዶ በርቁ ከላይ ከዳዋሮ ምሥራቅ (ሐረርጌ) በስተደቡብ ምሥራቅ አካባቢ ላይ አዳል የሚባል አገርን ሰይመዉ እስከ ዘይላና በርበርበራ ሕንድ ዉቅያኖስ ጠረፍ ዳርቻ ያለዉን እስላም ምዕመናን ሁሉ የወላስማ ሥርዎ መንግሥት መሥርተዉ ቀጥሎም ሐረር ከተማን ዋና ማዕከል ያደረጉት። የአዳል ወላስማ ሱልጣኖች ሲመቻቸዉ ማለትም ክቀይ ባሕር ማዶ ከየመን በቂ ርዳታ ሲያገኙ ክርስቲያኑን የኢትዮጵያ አጤ መንግሥት እየተዋጉት፣ ሳይመቻቸዉ ደግሞ እየገበሩ ብዙ ዘመናት ኖረዋል።

፫ኛ/አርጎባ ማለት አረብ ገባ የሚባለዉ ትርክት ግንዛቤ ማቅረብ አግባብ ስለሆነ ይኽዉ። እርግጥ ነዉ እስልምና ሃይማኖት በነቢዩ መሐመድ ከተጀመረ በሁዋላ ተከታዮቹ በፈጠሩት ቁርሾ እስከ መግዳደል ደርሰዉ ስለነበር ገዳዮች ሸሽተዉ በኢትዮጵያ አክሱም ግዛት ደቡባዊዉ ሸዋ ገብተዉ ነዋሪውን አማራ ሕዝብ አስልመዋል። የሸዋን ሱልጣናት (896-1255) መሥርተው ለክርስቲያኑ አጠ መንግሠት እየገበሩ ቆይተዋል። ሌላዉ የሽዋ ሱልጣናት ገባር የነበረዉ በአዲሱ መጤ አረብ ኡመር ወላስማ በይፋት፣ ከመጤነት ወደ መስፍንነት ተቀይሮ የሸዋን ሱልጣናት በጦርነት በ1285 ዓ.ም ደምስሶ የይፋት ወላስማ አዳል ንጉሥ ነኝ ብሎ እስከ ዘይላ በርበራ ጠርፍ ድረስ በሠፈሩት እስላሞች ሁሉ ላይ ነገሠ። የይፋት ሱልጣናት ዘወትር ከኢትዮጵያ አጤ መንግሥት ጋር ሲዋጋ ቆይቶ በ1445 ዓ.ም ይፋት ዉስጥ እጉባ በተባለዉ ሥፍራ በተደረገዉ ታላቅ ጦርነት ሱልጣን አሕመድ በደላይ ከተገደለ በሁዋላ ነዉ የይፋት ሱልጣናት በሸዋ አልቆለት የአዳል ስሉጣናትን ከአዋሽ ወንዝ ማዶ የወላስማ ሥርዎ መንግሥት ማዕከሉን አድረጎ የቀጠለዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልቃይት ጠገዴ መሬቱን እንጂ...! | ሳምሶን ኃይሌ

፬ኛ/ ማንም ሊያውቀው የሚገባዉ ሃቀኛ ግንዛቤ አርጎባ ማለት እስላም ዐማራ ማለት ነዉ ። ያርጎቤዉ ማኅበረስብ ምድር ደግሞ መላዉ ያዋሽ ሸለቆ፣ ከአሩሲ አርባ ጉጉ እስከ ባሌ ደጋማዉ ክፍል፣ እንዲሁም ጨርጨር ጋራ ጉራቻ፤ ሐብሮ፤ ጋራሙለታ፤ ወበራ፣ ጉርሱም፤ ዘይላ፤ በርበራ ወዘተረፈ ናቸዉ።

ሸሕድ

ሃጂ ይስማን አብዱል ሳላ (ሊቀ መንበር) ከአልዩ አምባ

መሃንዲስ ተፈረደኝ ኃይሌ(ዋና ጸሐፊ) ከይፋት/ኤፌሶን (አጣዬ)

ዶክተር ወይዘሮ ፋጡማ ኑሩ (የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ/አዲስ አበባ)

 

2 Comments

  1. ጸሃፊው ትክክል ናቸው። ለጊዜዎና ለእውቀትዎ በጣም እናመሰግናለን!!

  2. የኢትዮጲያችን ጉዳይ በፈጣሪ ብቻ መፍትሄ እንዲያገኝ በያለንበት እንትጋ::
    በጋራ ብዙ መልካም ገድሎች ያሉን የኢትዮጲያ ህዝቦች የሚለያዩንን ያለፉ ጥቂት ታሪኮች በማንሳት መከፋፋቱን ማተናከር የለብንም:: ታዋቂው የታሪክ ጸሃፊ ተክለጻዲቅ መኩሪያ እንደዘገቡት በታሪካችን ባንድ ወቅት ኦሮሞ በሌላ ወቅት አማራ ገናና በመሆን ሌልቾኡን ወደራሳቸው ባህል ቁዋንቁዋ ስያሜ መቀየራቸውን መካድ የለብንም:: ስለዚህ ባለህ እርጋ ብለን በቅን ምሁራን ትብብር ለትውልድ የሚበጄውን መዘገብ ይገባናል:: ራሴ ይህን የምጽፈው ከአርሲ የተማረክ ጀግና ኦሮሞ ዋቆ የመንዜዋን የአቦ ረድኤትን የገግንነቱና በመልከ-መልካምነቱ ያገባ መሆኑን ደጃች ባልቻ ምስለኔ በምድረግ ያሰማሩዋቸው የአባቴ አጎት የተረኩልኝ ሲሆን ሴት አያቴ የወሎ አባትና የከፊቾ እናት ያላት ናት:: በፊዳሉ ዘመን የመናናቅ መሰዳደብ ዛሬ ተማርን በሚሉ መደገሙ በጣም የሚያሳዝን ሲሆን የባሰው ደግሞ የድሮ ቅድም አያቶቻችን ሰሩ ተብሎ ከሚነቀፉበት የባሰውን ግፍ የዛሬ ትውልድ በክፉ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጠማማ ትርክት የከፋ ጭካኔ መፈጸሙ ነው:: ይህ ይብቃን በክፉ ቃል ኦሮሞውን መስደብ ለቀደመው ሁሉም ዘርን ባካተተው የፍውዳል ግፍ አማራውን ብቻ ተጠያቂ ማደርግ ይቁም::አሜሪካኖቹም አውሮፓዊያኑን በዚህ ጥላቻና መተላለቅ ያለፉበትን ተምረን እኛም በምህረት በይቅርታ የጋራ ሃገራችንና ተውልዳችንን እናድን። ኤዲ /አደፍርስ ሃብቴ መካሻ ዋቆ የመንፈሳዊና ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share