July 15, 2023
13 mins read

የአማራ ምሁር ነኝ ያልክ ሁሉ የውስጡም የውጩም ቁማር ይግባህ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

4556tttt 1 1 1

ከጥቂት ዓመታት በፊት አማራን  በማስጨፍጨፍ ታሪክ ከዘገባቸው ጅላንፎ ጭራቆች አንዱ “ፖለቲካ ቁማር ነው፤ ቁማሩን ታሸነፍን ጨዋታው አለቀ” ዓይነት ንግግር ሲያደ ግና “ኢትዮጵያ ሱሴ፣ ስንንኖርም ስንሞትም ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉት የጆከር ካርታዎች አማራን ቁማር ለመብላት የተሰሩ መሆናቸውን በግልጥ ሲናገር ብዙዎች የመጠቅን ነን የሚሉ የአማራ ምሁራን “የአፍ ወለምታ” ወይም እነሱ ምሁር ለመባል በሚመርጡት የእንግሊዝ ቋንቋ “He misspoke” እያሉ ቁማሩን መበላት ብቻ ሳይሆን የባህር ላይ ኩበት ሆነው ተንከረፈፉ፤ ተጃጃሉ::

አንዳንዶቹ ዘግይተውም ቢሆን የቁማሩን ስሌት ተገንዝበው ቁማር መበላታቸው ገብቷቸው ሲንጨረጨሩና ዳግም ቁማር ላለመበላት ሲጥሩ ብዙዎቹ ምሁራን አሁንም በ ገር ውስጡም ሆነ በዉጩ ቁማር ደጋግመው እየተላፉ የበግ አይሉት የአሳማ ኑሮን በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአማራ ምሁር ሆይ! እንደ ቅደመ  አያቶችህ የቁማርተኛ አጥማጅን አመጣጥ ተሩቅ እንደምታጠና ቆቅ እንጅ ጨዉ ሲያልሱት ብኣኣኣ እያለ ተጎትቶ እንደሚሄድ በግ ወይም ሆዱ ተሞላ  ተጎኑ ተጎትቶ ስለሚታረደው ወገኑ ደንታ እንደማይኖረው አሳማ አትሁን፡፡

 

በዚህ ዘመን አገርም ሆነ ዓለም እየተመራች ያለቸው በመለኮት ፈቃድ ሳይሆን በሳጥናኤል የቁማር የካርታ ጨዋታ መሆኑን በደንብ የተረዳህ ሁን፡፡ የአገር  ቤቱ ቁማር የአማራና  ቋንጃ  ቀልጥሞ አገር አልባ ማድረግና ማጥፋት መሆኑ ለሰላሳ ዓመታት ደጋግመው ነግረውህ አልገባህ ሲልም ሕዝብህን በመላ አገሪቱ እየጨፈጨፉ የተቆረጠ አንገት፣ ሆዷ የተሰነጠቀች እርጉዝ፣ የታርደ ህጻን፣ ብልቱ የተቆረጠ ወጣት አሳይተውህም ታልገባህ እግዚአብሄር ምህረቱን ያውርድልህ፡፡

 

ወደ ውጩ የቁማር ጨዋታ ስንመጣም ምዕራባውያን ዲሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት፣ እርዳታ፣ ልማትና ብልጥግና እያሉ እሚለፈልፉት የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ብቻ እንጅ ለሌላ ሕዝብ ጭራሽ አስበው አለመሆኑ ታልገባህ ሶስት ሰባት ፀበል እናስጠምቅህ፡  ስማቸው ራሱ የቁማር መጫዋቻ ካርታዎች መሆናቸውን የሚነግረው ኢንተርናሽናል መኒታሪ ፈንድ፣ የዓለም ባንክ፣ የተባበሩት መንግስታት፣ የዓለም ጤና ድርጅት፣ አምነስቲ ኢንተናሽናልና ሌሎችም አሸብራቂ ስም የለበሱት ድርጅቶች የቁማር መጫወቻ ካርታዎች መሆናቸው ታልገባህ አርባ ቀናት ይፀለይልህ፡፡

የምስራቆቹ መንግስታትም “የራስህን ሕዝብ ብትጨፈጭፈውም ሆነ ቀቅለህ ብትበላው ጉዳያችን አይደለም” እያሉ ለወሮብላ ነፍሰ ገዳይ ገዥዎች የሚሰጡት ብድር፣ የመንገድና    ሌላም ሌላም ሥራ ቁማር መሆኑ ታልገባህ አንዋር መስጊድ አርብ አርብ ይፀለይልህ፡፡

 

የአማራ ምሁር ሆይ! እባክህ የውስጡም የውጩም ቁማር ይግባህ! እስከ ዘላለም ትኖር ይመስል ይህ ነገ ተፈረካክሶ የምስጥ ቀለብ የሚሆነው ሆድህም ሁልጊዜ ቀፍድዶ አያዝህ! እኔ ደልቶች ተኖርኩ ለሌሎች አማሮች ምን አገባኝ የሚለው የአሳማ ባህሪም መስቀል እንደታየው ዛር አጉርቶ ይልቀቅህ፡፡ እንኳን ሰው ጉንዳን እንኳ ዘሩ እንዳይጠፋ የተቻለውን ሁሉ እንደሚደርግ ይታይህ፡፡ በዚህ የቁማር ዓለም የአንተን መልክ የያዘው፣ የአንተን ባህል የለበሰው፣ የአንተን ቋንቋ የሚናገረው ዘርህ ተምድር በቁማርተኞች እንዳይጠፋ በትንሹ ሁለት ነገሮች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸው ይግባህ፡፡

 

. ጉልበትና ኃይል፡ በዚች ከንቱ ምድር ጉልበትና ሀይል ተሌለህ እንኳን ተባባሪ እሪ ብለህ ብትጮህም የሚሰማ የለህ  ጉልበትና ሀይል ተሌለህ ተራ በተራ ባለቤት እንደሌለው ጫካ ተመንጥረህ ትጠፋለህ፡፡ ተምንጠራ የተረፍከውም ሲፈልጉ ቀንበር ጭነውም የሚያርሱብህ ባርያ ሆነህ ትኖራለህ፡፡ ጉልበትና ሀይል ለማግኘት ደሞ መንደርና ሰፈርን አፍርሰህ በዓለት ላይ የተመሰረተ ድርጅትና እንድነት መፍጠር አለብህ፡፡ ይኸንን የተረዱት ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ተደራጅ ሲሉህ “በአማራነት መደራጀት እንደ ሌሎች ማነስ ነው” የሚል የጅላጅል ድስኩር እየደሰኮርክ እርሳቸውን ከማስበላትም አልፈህ ሳትደራጅ በመቅረትህ በአማራ ላይ ዘር ፍጅት ተደጋግሞ እንዲፈጠም አደረክ፡፡ ክቡር ፕሮፌር አስራት ያሉትን ብትሰማ ኖሮ ቁማር የተጫወቱብህ ጭራቅ ጅላንፎዎች እንኳን ቁማሩን ሊበሉህ ቁማሩን ጭራሽም ሊያስቡት አይችሉ ነበር፡፡ የዓለም ሀያላን መንግስታት የሚባሉትም ለምነህ ሳይሆን ለምነው ያነጋግሩህና ወዳጃቸው ያረጉህ ነበር፡፡

 

. ጥበብና ሐብት፡ በዚህ ቁማርተኛ ዓለም ጉልበት እንደሌለው ሁሉ ጥበብና ሐብት የሌለውንም ማንም አይፈልገውም፡  ጥበብና ሀብት የሌለው የትኛውንም ቁማር ተጫውቶ አያሸንፍም፡፡ ስለዚህ እንደ ቅደመ አያቶችህ ጥበበኛ ሁን፡፡ ቅድመ አያቶችህ እንኳን የአገር ቤቱን ጅላንፎ የውጩን መሰሪም በዓይኑ ተሻግረው ስግብግብ አንጎሉ የሚያስበውን አንጠርጥረው ያነቡና ያውቁ ነበር፡፡ ጥበብን በሚገባ ለመጠቀም ሐብት አስፈላጊ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሐብት የጥበብ መጠቀሚያ መሳርያ ነው፡፡ ምዕራባውያንም ሆነ ምስራቆች ሐብትን የሚያውሉት የራሳቸውን ጥቅም የሚያስጠብቁበትን ጥበብ ሸፋፍነው ለመጠቀም ነው፡፡ የዛሬ ዘመኑ የአማራ ምሁርን ጊዜውንና ሐብቱን የሚጠቀመው ግን የራሱን ሕዝብ ከዘር ፍጅት ለማዳን ሳይሆን የዘር ፍጅት የሚፈጥሙትን ጭራቆች ለማባበል ወይም “ዓለም አቀፋዊ ሰው ነው” ተብሎ እንዲጠራ ወይም ለጉራ ነው፡፡ ብዙው የአማራ ምሁር ግዜህና ገንዘብህን የአማራን ዘር ፍጅት ለሚከላከሉ ጀግኖች አውል ከሚሉት የአማራ ዘር አጥፊዎቹና ተባባሪዎቻቸው በኢትዮጵያ፣ በዓባይና በሌላም ሌላም ስም ለሚያቋቁማቸው የአማራ ማለቢያ ድርጅቶች ለማዋል የሚመርጥ ጉድ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ከንቱና ዘልዛላ ምሁር ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ሜዳ ስለወደቁት ጊዜ የጣላቸው አማራዎች ምንም ሳይልና በአማራ የዘር ፍጅት እየተኪያሄደ መሆኑን እየካደ ዳርፉር ስለደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል ወይም ሌላ ቦታ ስለተፈናቀሉት ጣቱን እያፍተለተለ ሲደደኩር የሚታይ ነው፡፡

 

በዚች ቁማርተኛ ምድር ጉልበትን፣ ሀይልን፣ ጥበብና ሐብትን በሚገባ የሚጠቀሙት አይሁዳውያን ወይም እስራኤላውያን ናቸው፡  እስራኤላውያን በልመናና በመለማመጥ አገር እንደማይመሰረት፣ ዋሽንግቶን ዲሲ፣ ለንደን፣ ፓሪስ፣ ፍራንክፈርት ወይም ሌላ ቦታ ሰልፍ በመውጣትና ብቻ ድጋፍ እንደማያገኙ በሚገባ ይገነዘባሉ፡፡፡ በዚህ ከንቱ ምድር የሚሰሩት ጉልበት፣ ሀይል፣ ጥበብና ሐብት መሆናቸውን ከታሪካቸው ተምረው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ሌተ ተቀን ወጥረው ይሰራሉ፣ ጥበብን ያዳብራሉ፣ ሐብት ያካብታሉ፣ ጉልበትና ሀይላቸውን ያጠናክራሉ፡፡ ጥበብ የተሞላበት የዲፕሎማሲ ስራ ይሰራሉ፡፡ ጊዜአቸውን፣ ሐብታቸውንና ጥበባቸውን ለህልውናቸው ማረጋገጫ ያውላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ማርስ ላይ ያሉት ጭምር ተቆጥረው ከአስራምስት ሚሊዮን የማይበልጡ እስራኤላውያን የምዕራቡንም የምስራቁንም ሀያል ሀይል ለምነው ሳይሆን እየተለመኑ ተጎናቸው አሰልፈው ይኖራሉ፡፡

 

ወደ ሰባ ሚሊዮን የሚጠጋ አማራ የጉልበትን፣ የሀይልን፣ የጥበብንና የሐብትን ወሳኝነት በመረዳት በሚገባ ቢደራጅና ወጥሮ ሌተ ተቀን ቢሰራ የእስራኤላውያን አምስት እጥፍ  ሀይል ይኖረዋል፡፡  እንኳን እራሱንና አገሩን ኢትዮጵያን ከመፈጥፋት ለማዳን ለሌሎችም ይተርፋል፡፡ ይኸንን ማድረግ የሚችል ሀይል እንደ ሆነ ደሞ የሶስት ሺው ዘመን ታሪክ አሳይቷል፡፡ ለዚህ እንዲበቃ ግን የአማራ ምሁር ነኝ ያለ ሁሉ መንዘላዘሉን ትቶ የውስጡም የዉጩም ቁማር ሊገባውና ሲሆን ሲሆን ቁማሩን እንደ አያቶቹ ላፍ አርጎ ለመብላት ሳይሆን ሳይሆን ደሞ ላለመበላት መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ዋቢ፡የውስጥም ሆነ የውጭ ቁማርተኞች በራዲዮ፣ ቴለቪዥንና በሌሎችም መገናኛዎች የሚወሸክቱትን ትተው ምድር ላይ የሚጫወቱትን ቁማር ይመልከቱ፡፡

ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

https://twitter.com/TMA1961/status/1680470278436954113?s=20

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop