በአንድ ወቅት ጊዜዉ 2008 ዓ.ም ክረምት አከባቢ ነዉ በጊዜዉ የነበሩት ኢህአዴግ ጠ/ሚኒስቴር በጊዜዉ የነበረዉን የሕዝብ ጥያቄ እና የፖለቲካ ትኩሳት ለማስታመም ጥልቅ ተሀድሶ በሚል ርዕስ እንዳለ ተቀበል በሚል ዉይይት በማን እንደተጻፈ ባልታወቀ የተሀድሶ ዉይይት ላይ በመጨረሻ መግለጫ ሰጥተዉበት እንደነበር እናስታዉሳለን ፡፡
በዚህም በጥልቅ ተኃድሶ ስም የማንነት እና የግዛት ወሰን ጥያቄ የሚያነሳ ቀጥታ በፀረ……ምን እየተባለ ይፈረጂ ነበር ፡፡ ይህ አልበቃ ብሎ ያለፉትን ስርዓት በመዉቀስ እና በመከስሰስ የተጠመደ ዉል ያጣ ስብሰባ ነበር ፡፡
በተለይ አምባሳደር ሆቴል በነበረ ስብሰባ የስብሰባዉ መሪዎች ለህዝብ እና በወቅቱ ለነበረዉ ህዝባዊ ጥያቄ የነበራቸዉ ንቀት እና ጥላቻ ሳስብ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በተሸከሟቸዉ መዥገር ፖለቲከኞች በጉለትነት እና በባርነት እንደያዟቸዉ ያሳያል ፡፡
ይባስ ብሎ ከሁለት ሳምንት አሰልች ስብሰባ በኋላ በወቅቱ የነበሩት ጠ/ሚኒስቴር በትዕይነተ ወሬ ብቅ ብለዉ ጥልቅ እና አስተማማኝ ተሀድሶ የተደረገ እና ይህም የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥቄ ለአንዴ እና ለዘለቄታ የፈታ ነበር አሉን ፡፡
ሰንበት ብለዉ ሁሉም ስራ ፈላጊ ሠፌዱን ይዞ ወርቅ ለማፈስ ወደ ወደ ትግራይ ተከዜ አሉን ፡፡
የተናገሩት ሳይረሳ ኢህዴግ……ሞቷል…..ነቅዟል ….. ማሸበር ስራዉ ሆኗል …..ሲሉን ባጁ ፡፡እንግዲህ ጥቁር ሲደመር ጥቁር ነጭ አይሆንም እና ከጥልቅ ተሀድሶ ወደ ወደ መግደል መሸነፍ ነዉ ፣ ጁንታ፣ ህግ ማስከበር፣ ድልን ማስቀጠል፣ ….ዛሬ ደግሞ “ዕዉነትን በመዘንጋት በዉሸት መስማማት እና መተካት ” መድረሳችን የጥልቅ ተሀድሶ ቀጣይ ምዕራፍ ነዉ፡፡ የእኛ ችግር በተለይም በፖለቲካ ስርዓት እና ፖለቲከኞች በህዝብ ጥገኛ መሆንን እና በፖለቲካ ስልጣን ኮርቻ ታዝሎ የዕድሜ ልክ ጥገኛ እና ጡረተኞች ከራሳቸዉ አፍንጫ የማይርቁ ሠዎች ስብስብ ከራሳቸዉ ድምፅ ዉጭ የማይሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ የሚሉ ናቸዉ ፡፡
ይህም ዉሸት ሲዉል ሲያድር ይለመዳል እና አስመሳዮች ሲሰባሰቡ ሰይጣን ራቱን ሊበላ ይጋበዛል እንዲሉ ኢህዴግን ረስተን ኢህአዴግን ራዕይ እና ፍላጎት ለማስቀጠል ዉሸት ዕዉነት ይሆናል ማለት
ምን ያህል ፖለቲከኞች በህዝብ ጫንቃ ተንጠልጥለዉ ለህዝብ እና ለአገር ያላቸዉን ንቀት እና ጥላቻ የሚያሳይ ነዉ ፡፡
ኢህአዴግ ጥቁሩን ነጭ ብሎ ማሳተጋባት ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በላይ የሄደበት መንገድ እና አሁን የደረሰበት መሆኑ ልክ ቢሆንም ጥፋቱ ጨለማዉን ብርኃን ሲባል አዎን የሚል ተባባሪ መኖሩ ዞትር በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ደቀመዝሙሮች የቀንድ አዉጣ ፖለቲካ አራማጆች እና አቀንቃኞች እንዲሆኑ ይህም ልማድ ሆኖ ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ከሁሉም በላይ ሲሆኑ በአድር ባይነት መታየቱ ነዉ ፡፡
በኢትዮጵያ ለፖለቲከኞች አገር እና ህዝብ ክዶ ፣ አዋርዶ እና ሁሉን ጥፋት አድርጎ መኖር ትክክለኛ በሆነበት እና ከልካይ በጠፋበት የጋራ የሀሰት ስምምነት ዕዉነትን መተካት ያስችላል ብሎ ማለት ሊገርም አይገባም ፡፡
በዕዉነት የሚሆነዉን ከድኖ በዉሸት የሚነገረዉን ተቀብሎ የሰማይ መና ለሚናፍቅ ህዝብ ጨለማዉን ብርኃን ሲባል አሜን ለሚል ወደ ኋላ የማይቀየሩትን ዕዉነት እና ታሪክ በሀሰት የመተካት ጉዞ በአገር እና በህዝብ ተቋማት ላይ እንደተሰራዉ እየናዱ መካብ የኢህአዴግ ሩጫ የዕድሜ ልክ ጥገኛነት ፍላጎት በላይ በህዝብ እና በአገር ክህደት እና ጥፋት ለደረሰዉ ብሄራዊ ግፍ እና መከራ ክፉ ስራ በሳለቤትነት እና ተጠያቂነት እንደከዚህ በፊት ዛሬም ዕንቅልፍ ቢነሳዉ የማይቻለዉን ” ዕዉነት እና ታሪክ ” በሀሰት እና ሀሰተኛ ትረትክት ለማጀል መሞከር ከህወኃት / ኢህአዴግ ለምድ እና አመጣጥ የሚጠበቅ ነዉ ፡፡
በሌለ እና ባልነበር መስማማት ዉሸት ይሆናል ይህ ግን ዕዉነትም ፤ታሪክም አይሆንም ፡፡ ታሪክ ዉሸት ሲጨመርበት ልብ ወለድ ከመሆን ዉጭ ታሪክ ሊሆን ከቶ አይቻል ፡፡
“ዓለም የተስማማበት ሁሉ ዕዉነት አይደለም ፡፡”
አንድነት ኃይል ነዉ !
Allen, Z amber!