ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ለአማራ ህዝብ ጥሪ አቀረቡ/የደምበጫ አሁናዊ ሁኔታ/አስደንጋጭ-ኢትዮጵያ በተፈናቃይ ቁጥር1ኛ ሆነች

https://youtu.be/p9Ho-49jCbQ

ተጨማሪ ያንብቡ:  መከላከያው ተቋማዊ ወይስ ኔትዎርክ – ከፍትህ መጽሔት የተወሰደ – በተመስገን ደሳለኝ

3 Comments

  1. ቀይ ለባሽ በርትተህ ለጌታቸው ተዋጋለት ትናንት ነብስህን ያዳኑትንም ጨፍጭፍ ጠላትህ ወገንህ እንጅ በተኛህበት ያረደህ አይደለም። ይኸው ነው እንግዲህ መከላከያው ከሰውነት ወጥቶ ወደ ሮቦትነት ሲቀር አሁን መከላከያው ውስጥ ከአብይ፤ከአብረሃም በላይ፤ከአበባው ታደሰ ከብርሃኑ ጁላ በተሻለ ሁኔታ የሚያስብ ጠፍቶ ነው እንደ ሃብታም ዘበኛ በፈለጉበት ቦታ እየላኩህ ከህዝብ የሚያጣሉህ? ማን እንበላችሁ የኢትዮጵያ መከላከያ እንዳንላችሁ ለኢትዮጵያ አልቆማችሁም።

  2. በመንገድህ ላይ ቆም ብለህ ለማሰብና የራስን ውሳኔ ለመወሰን ከጅምላ አስተሳሰብ ነጻ መሆን ያስፈልጋል። እንደ ጉንዳን አንድን ተከትሎ ከሚተም ሰው በጎ ነገር አይገኝም።ትዕዛዝ ተቀባይና የጫኑትን የሚጫን በመሆኑ።የብልጽግናው መንግስት ወያኔን አቅፎ አማራ ላይ ዘመቻ መክፈቱ እጅግ አስገራሚና አሳዛኝ ነው። ይሁን እንጂ ባንጻሩም ትጥቅ በመያዛቸው ብቻ ከመንገድ የወጣ አስተሳሰብ በመያዝ አማራን የሚያሰቃዪ ስመ ፋኖዎችና ታጣቂዎች እንዳሉ በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎች ያመላክታሉ። በመስጊድና በገዳማት ተጠልሎ ውጊያ የሚባል ነገር ሊኖር አይገባም። ግን የሆነው ይህ ነው። ውጊያ መግጠም ካስፈለገ ህዝባችን የሚያሰቃየውን ወያኔና ኦነግን መፈለግ እንጂ ለነፍሳቸው ባደሩ ሰዎች መካከል ራስን አስጠልሎ ለአማራ ህዝብ እየታገልኩ ነው ማለት ውስልትና ነው። አሁን ላይ የአማራ ጠላቱ ራሱ እንደሆነ የሚያመላክቱ ነገሮች በመከሰት ላይ ናቸው። ይህ ሊታረምና ሊቆም የሚገባው ነገር ነው። ኮ/ሌ ደመቀ ዘውድም የሚናገረው ይህኑ ራስን ክፍት አርጎ ለጠላት ማመቻቸት መቅረት አለበት እያለ ነው።
    በሰከነ መንገድ የዓለምን ፓለቲካ ብሎም የሃበሻውን ፍትጊያ ለተመለከተው የተሸዋረረና ገዳዳ ለመሆኑ ምስክር አያሻም።በትግራይ እልፍ ሰው ያስጨረሱት ወያኔዎች ዛሬም እንመራሃለን ማለታቸው የሚያሳየን በምድሪቱ ላይ ፍትህ እንደሌለ ነው።ስንቶችን የድሃ ልጆች ነው ከፊትና ከህዋላ እየተተኮሰባቸው ገብተው የነደዱት? ስንቶች ናቸው አውድም፤ዝረፍ፤ግደል ሁሉን አጥፋ ተብለው በአማራና በአፋር ደም ያፈሰሱትና የዘረፉት? አሁን ማን ይሙት ከሞት እንኳን ቢተርፉ ጤነኛ ጭንቅላት ይኖራቸዋል ያን ሁሉ ግፍ ፈጽመው? በጭራሽ! ግን የወያኔ ታጣቂዎች መግደል ያለባቸው የወያኔን መሪዎች ነው። 99.99% የትግራይ ህዝብ በችግር ውስጥ ሆኖ የወያኔ መሪዎች ለህክምና ወደ ውጭ ሃገር አሁን ላይ ሲሄድ ማየት ደምን ያፈላል። በትግራይ የሚበላው ጠፍቶ፤ የህክምና እቃዎችና መድሃኒቶች እየተሰረቁ እየተሸጡ እነዚህ የቁም ሙቶች ውጭ ሃገር ሲዝናኑ ማየት ተናንቀህ ሙት ያሰኛል።
    ችግራችን አንድ ነው። ሁሌ ነገሮችን ለመፍታት የምንጠቀምበት መንገድ ያዘው ጥለፈው ግደለው፤ እሰረው በማለት በተኮስ መታገዙ ነው። ይህን ድርቡሻዊ ድርጊት ለማጎልበት በዘር፤ በቋንቋ፤ በሃይማኖትና በሌሎችም ጥቃቅን ነገሮች ሰውን በመከፋፈል በለውና በይው እያልን ይኸው እንሆ ዛሬ ላለንበት እንኩሮ የፓለቲካ አስተሳሰብ ደርሰናል። አሁን በወልቃይት፤ በጸገዴ፤ በራያ ወይም በሌሎች ስፍራዎች ያለው የሃሳብና የነፍጥ ፍትጊያ ለእነዚህ የቁም ሟቾች እድሜ ማስቀጠያ እንጂ ለህዝባችን አንድም ጥቅም የለውም። ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ናት። አማራ ክልል የኢትዪጵያ ምድር ነው። ማንም የሃገሪቱ ዜጋ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ሰርቶ ለመኖር መብቱ ነው። ግን በክልል በተዋቀረችው የአሁኒቱ የሃበሻ ምድር ቋንቋዬን ካልተናገርክ ምግብ አላቀርብም የሚሉ ምግብ ቤቶች ያሉባት ምድር ሆናለች። ወልቃይት የትግራይም የአማራም ምድር ነው።ግን አንድ በጉልበት በሌላው ላይ የራሱን ጫና ለማሳደር መሻቱ ለዚህ ሁሉ ስርግብ አድርሶናል። ሲጀመር እነዚህ አካባቢዎች የትግራይ ክፍል ሆነው አያውቁም።
    አማራ ተሞኝቷል። ኢትዪጵያ ኢትዮጵያ እያለ ራሱን ለጥቃትና ለመከራ ዳርጓል። ይህ ደግሞ ዛሬ ላይ ብቻ ሳይሆን በፊትም ቢሆን ክፋት ሲፈጸምበት የኖረ የዋህ ህዝብ ነው።ይህን ለመረዳት በሰከነ ስነ ልቦና ከመረጃው ጋር መመልከት ያስፈልጋል። ገድለውት ለቅሶ አብረው ተቀምጠው የእዝን ንፍሮ ከሚበሉ ፍጡሮች ጋር ነው ተወዳጅቶ የኖረው። የአማራ ህዝብ ራሱን በማደራጀት አንድ ለአንድ ደራሽ በሚሆንበት ደረጃ ላይ እስካልሆነ ድረስ አሁንም እየተጠቃ ነው፤ ወደፊትም የበለጠ ጥቃት ይደርስበታል። የወልቃይ፤ የጸለምትና የራያ ጉዳይ የፈሰሰ ውሃ ነው።ዳግም ወያኔ እነዚህን ስፍራዎች አያስተዳድርም። የትግራይ አካልም አይሆኑም።በሰላም አብሮ መኖር ግን ይቻላል። ችግሩ የወያኔ ሰዎች ሰላምን አያውቁም። ጦርነት ፈጣሪዎች አይደሉ። አሁን ከሚጋልባቸው ከአሜሪካ ጋር ሆነው ተንኮል እንደሚጠነስሱ ግልጽ ነው።ለእኔ የሚገርመኝ የዶ/ር አብይ መንግስት ከልክ ያለፈ ለወያኔ ማጎብደድ ነው። የሰሜን እዝን በተኛበት ጥቃት ያደረሱት እኮ ወያኔዎች እንጂ የአማራ ህዝብ አይደለም። ለነገሩ ኦነግና ወያኔን አንድ የሚያደርጓቸው ከብዙ ነገሮች መካከል አንድ ኢትዮጵያንና የኢትዪጵያን ኦርቶዶክስ ቤ/ክ መጥላት ነው።ህብረታቸውን የጋራ የሚያደርገው የአማራን ህዝብ በተረት ተረት ታሪክ ተመስርተው እንደ ጠላት መቁጠራቸው ነው። ያው ሁሌ እንደምለው ኦነግና ወያኔ ካለፈ ታሪክ የማይማሩ እድሜ ልካቸውን መከራ እንደዘሩ የሚኖሩ ድርቡሾች ናቸው። አይናቸው ደክሞ፤ ጉልበታቸው ላልቶ፤ እድሜአቸው ገፍቶ እንኳን በቃኝ የማይሉ የሰው አሳማዎች ናቸው። 60 ዓመት ሙሉ ውሃ ወቀጣ። ትርፍ የለሽ ፓለቲካ። በህዝብ ስም መነገድ አይበቃም? ወለጋ ውስጥ በሸኔ ምክንያት በተዘጉ ት/ቤቶች ሳይማሩ የቀሩ ወገኖቻችን ለኦሮሞ ጽንፈኞች ደንታ አይሰጣቸውም። ግን ያኔም ዛሬም ወደፊትም የሚያለቅሱ አይኖችን እንባ ዘርና ቋንቋ፤ ሃይማኖትና ክልል ሳይለይ የሚያብስና አይዞሽ አይዞን የሚሉ ሰዎች ከአዲሱ ትውልድ መካከል እናገኝ ይሆን? ጠብቆ ማየት ነው። በቃኝ!

  3. ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ድቀት በአንድነት ሠላም ድሞክራሲ ፍትህ አስተዳደር አለመኖር ና በጠባቦች ና በዘረኞች አገዛዝ ለውድቀት ና ለመበተን የተቃረበች ባለችበት ወቅት ፓርቲዎች ሙሁራን ዝምታው ከምን ይሆን ? ከፍርሃት ወይስ የሀገር ፍቅር ስሜት አለመኖር ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share