May 23, 2023
5 mins read

በወቅታዊ ጉዳዮች ከማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት የተላለፈ መልእክት!

mahbere Kidusan 1 1

ማኅበረ ቅዱሳን በኢ/አ/ተ/ቤ/ን ቅዱስ ሲኖዶሶ በ1984 ዓ.ም እውቅና አግኝቶ በ1994 ዓ.ም በጸደቀለት ሕገ ደንብ መሠረት አገልግሎቱን ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም የቅድስት ቤተክርስቲያን ዐቢይ ተልዕኮ የሆነውን የእግዚአብሔርን ወንጌለ መንግሥት በስፋት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ እንዲዳረስ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል። በየጊዜው ያጋጠሙትን ፈተናዎችን እግዚአብሔር ቸርነት በከፍተኛ ትጋትና ጽናት ያለፈ መሆኑን ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ማኅበሩ ካሉት የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ አንዱ የብሮድካስት አገልግሎቱ ሲሆን፤ በ2012 ዓ/ም የተጀመረው ይህ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጨው የወንጌል አገልግሎት በመላው ምእመን ዘንድ አማራጭ ሚዲያ ከመሆን አልፎ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው የየዕለት ስንቅ በመሆን በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ እንደ ዐይን ብሌን የሚጠብቁት ሚዲያ ለመሆን በቅቷል።

የብሮድካስት አገልግሎት ልዩ ጥንቃቄ የሚሻ ሥራ ከመሆኑም በተጨማሪ ማኅበራችን አገልግሎቱን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና መንፈሳዊ ቅኝት የሚያከናውን በመሆኑ ሁሌም ምስጉንና የተከበረ ጣቢያ መሆኑን ምእመናን ሁሉ የሚመሰክሩት እውነታ ነው።

በዚህ መነሻነት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሜቴ ያዘጋጀውን መግለጫ በማስተላለፋችን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ “ጊዜያዊ እገዳ” ማድረጉን ገልጾልናል፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለጊዜያዊ እገዳ የሰጠው ምክንያት ማኅበሩ ከተቋቋመለት ዓለማ ውጭ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

እንኳን ሊያሳግድ ይቅርና ጥያቄ ሊነሳበት የማይገባ ጉዳይ መሆኑን ማኅበሩ ይረዳል። የእግዱ ሂደትም የመገናኛ ብዙኃን አዋጁን ያልተከተለና የሚዲያውን አገልግሎት በጸሎት፣ በገንዘብና በእውቀታችሁ በመደገፍ ሊዚህ ያበቃችሁትን ካህናት፣ ምእመናንና አባላትን ያሳዘነ መሆኑን ተረድተናል፡፡

በመሆኑም እግዱ የምእመናን ድምጽ የሚያፍን ብሎም ትምህርተ ወንጌልን የመማር መብታቸውን የሚገድብ መሆኑን በማሳወቅ ለሚመለከተው አካል አቤቱታውን በደብዳቤ አቅርቧል።

አቤቱታውም በአግባቡና በሕጉ መሠረት ታይቶ በጎ ምላሽ እንደሚሰጠው ተስፋ እናደርጋለን። እንዲሁም ማኅበራችን ጉዳዩ የሕግ አግባብን ተከትሎ ውሳኔ እስከሚያገኝ አስፈላጊውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲገነዘብልንና ይህንኑ በየጊዜው በይፋ የምናሳውቅ ስለሆነ በታላቅ ትዕግሥት አንዲጠብቅ እንጠይቃለን።

በዚህ አጋጣሚ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ስለ ጉዳዩ በተፈጠረባችሁ ቁጭትና ከፍተኛ የቁጣ ስሜት የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር ለምታደርጉት ተነሳሽነት ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ከፍተኛ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።

በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦቱ ርክበ ካህናት ስብሰባ ግንቦት 14/2015 ዓ.ም ባደረገው ምልአተ ጉባኤ ችግር ባለባቸውና አስፈላጊ በሆኑ አኅጉረ ስብከቶች ፱ አዳዲስ ኤጴስ ቆጶሳትን በጥናት ለመሾም አስመራጭ ኮሜቴ መሰየሙ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የምርጫ ሄደቱም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የተከተለ፣ ግልጽነት ያለው፣ ካህናትና ምእመናንን ያሳተፈ እንደሚሆን እንጠብቃለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop