May 20, 2023
3 mins read

በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተለቀቀ

Temesgen
#image_title

“ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ”

ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ የተወሰደው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ምሽት አምስት ሰዓት ገደማ መለቀቁን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገረ። ተመስገን ለ“ጥያቄ ትፈለጋለህ” በሚል፤ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተወስዶ ለሁለት ሰዓት ገደማ መቆየቱን ገልጿል።
ተመስገን ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ነጻ በተባለበት ክስ ጋር በተያያዘ፤ ይግባኝ እንደተጠየቀበት ዛሬ ምሽት በፖሊስ እንደተገለጸለት አስረድቷል። በዚህ ክስ ይግባኝ የቀረበለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገቡን በሚያዝያ 12፤ 2015 ዘግቶት እንደነበር ተመስገን አስታውሷል። ይህም ሆኖ ጉዳዩ እንደገና በጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚታይ በፖሊስ እንደተነገረው ተመስገን አክሏል።
ለዚህም ሲባል ሰኞ በአካል የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲቀርብ መጠየቁን እና ይህንኑ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ላይ መፈረሙንም ጋዜጠኛው አስታውቋል። ከዚህ ሂደት በኋላ የመታወቂያ ዋስ በማስያዝ ከሁለት ሰዓት እስር በኋላ መለቀቁን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አብራርቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በኩል የሚገኘውን መረጃ አካትተን፤ ዝርዝር ዘገባ ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን።
ጋዜጠኛ ተመስገን ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 12፤ 2015 ምሽት በአዲስ አበባ ጃንሜዳ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ የተወሰደው በሁለት ፒክ አፕ ተጭነው በነበሩ እና የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ ኃይሎች መሆኑን የዓይን እማኞች ቀደም ብለው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቀው ነበር። እስከ ምሽት ድረስ ከቅርብ ጓደኞቹ ጋር የነበረው ተመስገን፤ ወደ መኖሪያ ቤቱ በሚገባበት ወቅት የግቢ ዙሪያው በጸጥታ ኃይሎች ተከብቦ ማግኘቱንን የዓይን እማኞቹ ተናግረው ነበር።
© ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Telemt heAD 1 1
Previous Story

ከዓለም አቀፍ የጠለምት ዓማራ ማንነት ድጋፍ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

Ethiopia will be the next china 1
Next Story

ወደርየለሹ ያሜሪቃ መንግሥት ተመጻዳቂነት፤ ካማራ (Amhara) እና ዊገር (Uyghur) አንፃር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop