ባቡሩ ወደ መዳረሻው በተቃረበ ቁጥር በየፌርማታው የሚንጠባጠቡት ተሳፋሪወች ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ያማራ ሕዝብ የራሱን ሕልውና በማስጠበቅ የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስጠበቅ የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል በከፍተኛ ደረጃ እየተቀጣጠለ ነው፡፡ በዚህ ደረጃ መቀጣጠሉን ከቀጠለ ደግሞ ዋናውን የአማራና የኢትዮጵያ ጠላት (ማለትም ጭራቅ አሕመድን) በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚያንጨረጭረው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
በተጨማሪ ደግሞ ያማራ ትግል ይበልጥ በተቀጣጠለ ቁጥር፣ ወላፈኑ ይበልጥ አስመሳይ የነበሩትን ፀራማሮች ይበልጥ ስለሚፈጃቸው ከትግሉ ይሸሻሉ፡፡ ኤርምያስ ለገሰ ያደርገውም ይሄንኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ ያማራ ትግል ይበልጥ በተቀጣጠለ ቁጥር፣ ራሱንና ጦቢያን የማዳን እድሉ ይበልጥ እየሰፋ ስለሚሄድ አገር ወዳዶች ትግሉን ይቀላቀላሉ፡፡ መሳይ መኮንን እያደረገ ያለውም ይሄንኑ ነው (በዚሁ እስከቀጠለበት ድረስ)፡፡
ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ፣ ፀረኦሮሙማው ትግል ኤርምያስን አጥቶ መሳይን ካገኘ ደግሞ አትርፏል እንጅ ምንም አልተጎዳም፣ ይበልጥ የሚያተርፈው ሁለቱም የትግሉ አካሎች ቢሆኑ ቢሆንም፡፡
አቶ ኤርምያስ ለገሰ ከኢትዮ360 ራሴን በራሴ አሰናብቻለሁ ብሏል፡፡ እንኳን ተሰናበተ፡፡ በኤርምያስ መሰናበት ደግሞ ኢትዮ360ወች ማለት ያለባቸው ፈረንጆቹ እንደሚሉት እንኳን ተገላገልን (good riddance) ነው፣ የተገላገሉት በመኻላቸው ተሰንቅሮ የነበረው እጅግ አደገኛ ነቀርሳዊ ሰንኮፍ ነውና፡፡
አቶ ኤርምያስ ለገሰ ከኢትዮ360 የለቀቅኩት በማስተላልፈው ዝግጅት ምክኒያት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ቤተሰቦቸ ስለተቀየሙኝ ነው የሚል፣ ለኢትዮ360 ታዳሚወች ያለውን ከፍተኛ ንቀት በገልፅ የሚያሳይ ተልካሻ ምክኒያት አቅርቧል፡፡ በሌላ በኩል ግን አቶ ኤርምያስ ለገስ በዚህ ተልካሻ ምክኒያቱ የተሳደበው እሱን ራሱን እንዲሁም የገዛ ራሱን ቤተሰቦች ነው፡፡
እንደ ተልካሻ ምክኒያቱ ከሆነ፣ አቶ ኤርምያስ የጭራቅ አሕመድን ወንጀሎች በመዘርዘር የሚያቀርበው ዝግጅት በጭራቅ አሕመድ ደጋፊወች ላይ የሚያሳድረውን ስሜት ቤተሰቦቹ እስኪሚነግሩት ድረስ አያውቅም ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ኤርምያስ የሚያውቀው መተንተኑን እንጅ፣ ስለ ትንተናውን ውጤት ፍንጭ የለውም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አቶ ኤርምያስ እውቀቱ ከፊል እውቀት፣ እውነቱ ግማሽ እውነት (half truth) ነው ማለት ነው፡፡ ከፊል እውቀት እና ግማሽ እውነት ያለው ሰው ደግሞ ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለሱ ለራሱም እጅግ አደገኛ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ጭራቅ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ጭፍጨፋና ማፈናቀል ሳያሰለስ በሚያጋለጠው በኢትዮ360 ውስጥ በመሥራቱ የኤርምያስ ቤተሰቦች ኤርምያስን ከተቀየሙት፣ ቤተሰቦቹ የጭፍጨፋውና የማፈናቀሉ ተሳታፊወች ወይም ደጋፊወች ወይም አትራፊወች ናቸው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤርምያስ ቤተሰቦች የኦሮሙማ አቀንቃኝ ኦነጋውያን ናቸው ማለት ነው፡፡ የኦነጋውያን ቤተሰቦቹን ወቀሳ ሰምቶ ኢትዮ306ን ከለቀቀ ደግሞ እሱም ራሱ የኦሮሙማ አቀንቃኝ ኦነጋዊ ሁኗል ማለት ነው፡፡
የቆየ ልማድ በዋዛ አይወገድ (old habits die hard) እንዲሉ፣ ኤርምያስ የወያኔ ጉዲፈቻ ስለሆነ፣ ከወያኔ የወረስው አለቅጥ ማጋነን እንዲሁም አለልክ መዋሸት ጨርሶ እንዳልለቀቀው የኢትዮ360 ታዳሚወች በደንብ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን ለመልቀቁ ተልካሻ ምክኒያት ማቅረቡ እንደለመደበት መዋሸቱ ነው፡፡
አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን የለቀቀው ኢትዮ360ን አዳክሞ የማጥፋት ልዩ ተልእኮ አንገቦ ነው፡፡ ተልእኮውን ከከፍተኛ ገንዘብ ጋር የሰጠው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መለስ ቀለስ የሚለው አቶ ታከለ ኡማ ነው፡፡ አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን አዳክሞ ለማጥፋት ያሰበው ደግሞ ጭራቅ አሕመድ አማራን አዳከሞ ለማጥፋት እየተጠቀመበት ባለው ዘዴ ነው፡፡ ዘዴው ደግሞ የሚከተለው ነው፡፡
አቶ ኤርምያስ አቶ ታከለ ኡማ የሰጠውን ገንዝብ በመጠቀም በሁሉም ረገዶች የተሟላ፣ ደረጃውን የጠበቀ፣ ቆንጆ እስቱዲዮ በቅርብ ጊዜ ይከፍታል፡፡ የሚዲያውን ሥራ ማስኬጃ ደግሞ የጭራቅ አሕመድ መንግስት በየጊዜው ፈሰስ ያደርግለታል፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞች ነን የሚሉትን አማራ ጠሎችን (ልደቱ አያሌው፣ ታምራት ላይኔ፣ ያሬድ ጥበቡ፣ ቴድሮስ ፀጋየ ወዘተ. ) በተደጋጋሚ እየጋበዘ በማር የተለወሰ መርዝ ላማራ ሕዝብ በየዕለቱ ይመግባል፡፡ ይሄን የሚያደርገው ግን የኢትዮ360 ታዳሚወችን ወደሱ በመሳብ ኢትዮ360ን ለማዳከም ሲል ብቻ ነው፡፡ እንዳሰበው ኢትዮ360ን ካዳከመ ደግሞ ግቡን ስለመታና ተልእኮውን ስለጨረሰ እውነትኛ ማነነቱን ገሃድ አውጥቶ ፀራማራነቱን በግለፅ ያውጃል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማራን አዳክሚያለሁ ብሎ በማሰቡ አሁን ላይ ፀራማራነቱ በግልፅ እንደተናገረ፣ ኤርምያስም ኢትዮ360ን ማዳከም ወይም ጨርሶ ማፍረስ ከቻለ ጊዜው ሲደርስ ኦነጋዊነቱን በግልፅ ይናገራል፡፡
ስለዚህም ኢትዮ360ን የምትወዱ የኢትዮ360 ታዳሚወች ሆይ፣ ከቀጣዩ የኤርምያስ ለገሰ እሥሥታዊ እርምጃ ተጠንቀቁ፡፡ ያማራና የኢትዮጵያ ሕልውና የሚያስጨንቃችሁ አገር ወዳዶች ደግሞ ታከለ ኡማ ለኤርምያስ የሚከፍትለትን ፀራማራና ፀረጦቢያ ሚዲያ ባንድም በሌላም መንገድ በመደገፍ ያማራንና ያገራችሁን ሞት እንዳታፋጥኑ ትመከራላችሁ፡፡ ባንድ ወቀት አቶ ኤርምያስ በውጭ አገር የባልደራስ ተወካይ ስለነበር፣ በአስክንድር ነጋ ላይ ይህ ሁሉ መከራ የደረሰበት አንዱ ምክኒያት አሁን ላይ ገልፅ ሊሆንላችሁ ይገባል፡፡
ኢትዮ360ወች ደግሞ በበኩላችሁ ሁለት ነገሮችን አድርጉ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ የኢትዮ360 የመረጃ ምንጮችን ኤርምያስ እንዳያጋልጣቸውና ለጭራቅ አሕመድ አሳልፎ እንዳይሰጣቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ በተለይም ደግሞ ኤርምያስ ከኢትዮ360 ኮምፒተሮች ላይ ማህደሮችን (files) እንዳያወርድ (download) ከኮምፒተሮቹ አጠገብ አታስደረሱት፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኤርምያስ ለገሰ ግርፎች አሁንም በመካከላችሁ ስላሉና በደንብ ስለሚታወቁ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርሱ ባስቸኳይ ሸኟቸው፡፡
የኢትዮ360ና የመሰሎቹ ሚዲያወች እልህ አስጨራሽ ኢትዮጵያዊ ትግል፣ በኢትዮጵያዊነቱ በማይደራደረው ባማራ ሕዝብ ላይ ፍሬ አፍርቶ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እያቃረበ ነው፡፡ ባቡሩ ወደ መዳረሻው በተቃረበ ቁጥር ደግሞ በየፌርማታው የሚንጠባጠቡት ተሳፋሪወች ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ትናንት ኤርምያስ፣ ነገ ደግሞ ….
መስፍን አረጋ