April 2, 2023
4 mins read

ተዓይን ጆሮን የማመን ደዌ! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ ([email protected])

336656836 2697093393765720 898162267517684751 n

መደመር ወይም ማቀላቀል የተባለው የይሁዳ ማእበል እንደ ገለባ የጠረጋቸው ብዙ ምሁራንና ጋዜጠኛ ተብዮዎች ሰሞኑን ደማሪዎቻቸው በቁማር ምዕራፍ-አንድ ተደላድለናል በሚል እንደ ፊኛ በሚተነፍስ ጥጋብ እነሱ የፈለጉትን የካድሬ መፈክር አልተናገሩም ብለው ቅሬታቸውን እንደ ጎርፍ እያዥጎደጎዱት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው እነዚህ አንደ ለማኝ እህል እየታፈሱ የሚደመሩ ወይም የሚቀላቀሉ ጥሬዎች ዛሬም ተዓይናቸው ጆሮሯቸውን የሚያምኑ በሽተኞች መሆናቸውን ነው፡፡

ይህ የማያባራ አዙሪት የሚያመለክተው ደማሪዎቻቸው ዛሬም እንደ በፊቱ “ኢትዮጵያ እኮ ሱስ ናት፤ ስንኖርም ስምሞትም ኢትዮጵያ፤ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አገር ናት” እያሉ ቢወሸክቱ  ተፈርኦን ቤት ያደጉት ባህር አሻጋሪዎች ሙሴና ኢያሱ መጡ እያሉ እንደገና መቀመጫቸውን እንደ ጋሊሊዮ ፔንዱለም  እያወዛወዙና ላባቸውን እንደ ዝናብ እያወረዱ ዳንኪራ የሚመቱ አድሮ ቃሪያዎች መሆናቸው ነው፡፡

እነዚህ አድሮ ቃሪያዎች የሰይጣን ተከታዮች የሚናገሩትን ለመስማት የሚጠባበቁትና የሚቀባጥሩትን ማዳማጥ የሚያቆሙት መቼ ይሆን? ተጀርባው ጦር የያዙ ፈሪሳዊ አረመኔዎችን አስከትሎ ጉንጭ የሚስመውን ይሁዳ በሥራው እንጅ ሥሞ በጦር በሚያስወጋ ምላሱ መመዘኑን የሚያቆሙት መቼ ይሆን? እነዚህ ድንፈፎች ተሰይጣን ተከታይ ይሁዳዎች ዘንድ መልካም ነገር ይመጣል ብለው የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል እንደኖረችው ቀበሮ ሲንዘላዘሉ ኖረውና ሕዝብ አስፈጅተው ማለፍን የሚያቆሙት መቼ ይሆን?

ተደማሪ ምሁራንና ጋዜጠኛ ተብዮዎች ዛሬም እንደ ጋማ ከብት ነድተው ተደመሯቸው ሙሴዎች መልካም ነገር ጠብ ይላል በሚል የጅላንፎ ልብ የሚናገሩትን ለመስማት ጆሯቸውን የጅብ ጠረን እንደ ሸተታት አህያ ከፍተው እየተጠባበቁ ነው፡፡ እነዚህ ተደማሪ ምሁራንና ጋዜጠኞች “ሙሴ መጣ” የሚል የካድሬ ድስኩር ለፍልፈውና አዘናግተው ያስጨረሱት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ ጭራሽ ሳይፀፅታቸው ዛሬም አማራ ተዳራጅቶ ራሱን ተጭራቆች እንዳይከላከል ቀበቶ የማስፈታትን የደማሪዎቻቸው ቁማር ምዕራፍ-ሁለት እያራመዱ ነው፡፡

ጅላንፎ ምሁራን፣ ጋዜጦችና ሌሎችም በስብከት እስተንፋስ እንደ ብናኝ ተጠርገው የሚሄዱ ገለባዎች ተዓይን ጆሮን የማመን ደዌ የሚድኑት መቼ ነው? እነዚህ እያዘናጉ ንፁኻንን ያሳጨዱ ከንቱዎች ተዚህ  ሕዝብን ታስፈጀ ቆሌና አቴቴ የሚላቀቁት የትኛው ፃድቅ በመላእክት ክንፍ መጥቶ “ተዓይንህ ጆሮህን የማመን እርኩስ ባህሪም ሆነ የሰይጣን ተከታይ ይሁዳዎችን መስማትን አቁም!” እያለ ፀበል ቢያርከፈክፍባቸው ነው? እግዚኦ!

መጋቢት  ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop