ዛሬም ጦር አምጣ መሬት የሚመታ ማን ነዉ ?

ከኢንግዲህ  ኢትዮጵያዊ የሆነ ሠዉ ሁሉ በራሱ አገር እና አያት ቅድመ አያቱ የህይወት ዋጋ  ገበረዉ በደም እና በአጥንት በመሰረቷት አገር በየዋህነት ለዳግም ባርነት እና መናጆ ዜጋ ሆኖ ሲጎተት የሚጎተት አይኖርም፡፡

ላለአለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ኢትዮጵያዉያን በማንታቸዉ እና ኢትዮጵያዊዉ በመሆናቸዉ ብቻ ከፍተኛ ሠባዊ እና ቁሳዊ በደል እና አድሎአዊ ከፋፋይ እና ጥላቻ የሞላበት የአንድ ወገን ጭቆና ያስከተለዉ ምሬት ለነፃነት እና ለህልዉና ትግል ላይ ነበሩ ፡፡

ይሁን እና ከዓመታት ትግል እና ህዝባዊ ተጋድሎ በኋላም ከዉስጥም ከዉጭም በእብሪት  ከሁለት ዓመታ አስቀድሞ በትግራይ ነፃ አዉጭ ኃይሎች /ትህነግ / ኢህአዴግ በከፊል ከስልጣን ወንበር ሲላቀቅ ከታልኩ አልወርድም ባዩ ዳግም የኢትዮጵያን አንድነት እና የዓማራን ህዝብ በጠላትነት በመፈረጂ ወረራ በማድረግ የደረሰዉ ሠባዊ ዕልቂት እና ዉድመት ከምንም ሳይቆጠር የሠላሳ ዓመት የሠባዊ ፣ የጦር ፣ የዘር ፍጂት  እና አገር ክህደት ድርጊት ተዳፍኖ ዳግም የተከፈለዉ ኢህዴግ ገጠመ ፡፡

ይህ ኢህአዴግን የመጠገን ሂደት በህህ ሽፋን ለመሸምለል ጥረት እየተደረገ ባለበት የህወኃት ሊቀ መንበር ህወኃት ለሁለተኛ ጊዜ ነጻ እንደሚወጣ ከነበራቸዉ ግምት በመነሳ መግለጫ ሰጥተዉ ተመለከትን ፡፡

ያሉት የሚጠበቅ እና አንድ ነበር የትግራይን ግዛት ለማስጠበቅ የሚሆነዉን ሁሉ እናደርጋለን አሉን ፡፡

ግን ምን እና አስከየት እንደሆነ እንደከዚህ በፊት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ፤ዓማራን በባርነት አካባቢዉን በግዞት ያላሉት ላለመድገም ካልሆነ መልዕክቱ ጦር ጠማኝ ነዉ፡፡

ዕርሳቸዉ የትግራይን ግዛት ሲሉን ትግራይ በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሆነች የኢትዮጵያን ግዛት ለማስፋፋት እና ለማፋፋት ቢሉ ቢያንስ ለዋና ኃሳቸዉ …ትግራይን ለማስፋፈት እና ለማደራጀት ይጠቅማቸዉ ነበር ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቁም ኑዛዜ - የጎንቻው (ወቅታዊ ግጥም)

የኢትዮጵያ ግዛት በሱዳን መንግስት ከ70 ኪ.ሜ. በላይ ዘልቆ ለሁለት ዓመት በላይ ዕግሩን ዘርግቶ በሚኖርባት የተደፈረች አገር ይዞ ፤ ኢትዮጵያዉያን በአገራቸዉ ስደተኛ እና ምንደኛ ሆነዉ ባሉበት የሆድን በሆድ ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ ማለትን ማሰብ እንዴት ይረሳል ፡፡

የጎንደርን እና የወሎን ግዛት ክፍሎች በታሪክም በመልካምድር አቀማመጥ ሆነ በማንኛዉም መመዘኛ የኢትዮጵያ አካል እንጂ የአዲስ ግዛት አካል ለማድረግ ዛሬም ጦር አምጣ እያሉ መሬት መደብደብ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን አይበጂም ፡፡

ለፖለቲካ ትርፍ እና ስልጣን ሲባል የሚደረግ ጥረት ለማንም ምንም አይደለም ፡፡ ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን እንደ ጥንቱ ኢትዮጵያዊነት እንጂ ለፖለቲካ ስልጣን ክፍፍል ሲባል አገር እና ህዝብ መበደል ፤አንድን ህዝብ ሆድ እና ጀርባ አድርጎ ደም ማቃባት እና ማቆየት ቢቆም ኢትዮጵያን እና ዜጎችን ሲጠቅም ፖለቲከኞችን ጥቅም ሊያሳጣ ይችላል ፡፡ በአበባልም እኮ “ተቃራኒዎች ይገናኛሉ” ይባል የለ ፡፡ አዎ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን  ለሽ ዘመናት ኖረዋል ፤ ይኖራሉ እና አገር እና ትዉልድ ይቀጥል ዘንድ ከዚህ በላይ ምንም የለም ፡፡

ኢትዮጵያዊነትንም ሆነ ዓማራ ለኢትዮያዊነት የተገኘ ተፈጥሯዊ ስያሜ እንጂ  ማንም የሚሰጠዉ ፤የሚነሳዉ ሊሆን አይደለም ፡፡

የኢትዮጵያም ሆነ የዓማራ ህዝብ ለሁሉም ለአገርም ሆነ ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን ወገን እና አለኝታ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡን የአሁን ላይ ሁነት ሲሆን ከዚህ በኋላ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ አስተሳሰብም ሆነ ድርጊት ለማንም አይጠብቅም ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆነ ብዙኃኑ ዓማራ ኅዝብ በኅልዉናዉ እና በአገሩ ላይ ለራሱ ከራሱ በላይ ለማንም የማይሰጠዉ የታሪክ አደራ ያለበት በመሆኑ እንደከዚህ በፊቱ ባዶ እጁን ሞቱን የሚጠበቅ አለመሆኑን ከዓመታት መከራዉ ካልመከረዉ ለኢትዮጵያም ሆነ የራሱ መከራ ተጠያቀዉ ራሱ ኢትዮጵያዊዉ ዓማራ እና መሪ ድርጂቶች ብቻ ይሆናሉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቤ ጆቤና ሥጋቱ - ይሄይስ አእምሮ

ዛሬም በኃይል እና በማን አለብኝነት አንድን ህዝብ እና ታሪካዊ ግዛት እና ዳር ድንበር ለመዉረር እና ለማስገበር ጦር አምጣ ብሎ መሬት የሚመታ የማይድን አባዜ መድኃኒት አልባ በመሆኑ አስተናጋጂ ለዕግሩ ቄጠማ ፤ ለዕጁ  ችቦ አበባ በመያዝ እጁን ሸርቦ እንዲጠብቅ የሚጠይቅ የመጣንባችሁ መልዕክት ነዉ ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ

 

Allen Amber !

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share