March 24, 2023
16 mins read

ጆከሩን መዘው ፖለቲካዊ የፖከር ካርታ ጫዎታውን ጠቅላዩ አሥጀምረዋል – ሲና ዘ ሙሴ

6000 1 2 1
#image_title

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ፣ ከረመዳን ፆም ቀድመው ፣ አዲስ ካርታ መዘዋል ። ጆከርን ። በአዲስ የፖለቲካ ቁማር ጫዎታ ብቅ ብለዋል ። ፆሙ በመግባቱ ዛሬ አላህ ልብ እንዲሰጣቸው እንለምንላቸዋለሁ ። መካሪ የሌለው ንጉሥ ሆነዋልና !

” የካርታ ፖለቲካ ወይም ፖለቲካዊ ፖከር ”  በሚባል የማዘናጋት ፣ የማሳሳት ፣ ግልፅ ሐሳብን ያለማሳወቅ ፣ ዕድልና ብልጠትን አዋህዶ ቁማሩን የመጠቅለል ወይም የመብላት   ጫዎታ ጠቅላያችን  ብቅ እንዳሉ ፣ በትግራይ እና በአማራ ክልል ለመተግበር የፈለጉት ፖለቲካ በግልፅ የሚያሳብቅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ   ። የዛሬው ፖለቲካዊ ቁማር ጫዎታ በየጊዜው ከተሰጡን አጀንዳዎች ሁሉ ረቀቅ ያላለ እንደሆነም ከህዝቡ የተሰወረ አይደለም ። ካርታ ጫዎታ ገንዘብን አንድ ሰው ጠቅልሎ የሚወስድበት ፣ የአቋማሪና የቆማሪ ጫዎታ እንደሆነም ከህዝብ የተሰወረ አይደለም ። በዚህ የወገነ የፖለቲካ ቁማር ፣ ቆማሪዎቹና አቋማሪው የሚከብሩበት እንደሆነ ህዝቡ ያውቃል ። ( አሁን በዚች ሰዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ሥንት ፐርሰንቱ እንደሚወዳቸው የመረጃ ሹማቸውን እሥቲ ይጠይቁ ። እውነቱን ከነገራቸው ካልደነገጡ ራሳቸው ሌሎችን የተሳደቡበት ሥድብ  ለራሳቸው እንደሚሆን ከወዲሁ ይገነዘቡት ። )

የእኛው ፣ የዛሬው ፖለቲካዊው ፖከር “ ስፔድስ “  ከተሰኘ የካርታ ጫውታም ፍፁም የተለየ  ነው ። ይኽ ጫዎታ  በ1930ዎቹ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተፈለሰፈ የካርታ ጫውታ ነው ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በወታደሮች የሚዘወተር ጫወታ እንደነበር ይታወቃል  ።

ዛሬ እና አሁን ዓለም እየተጫወተ ያለው ጫዎታ ግን ፖከር ነው ። ይኽ ጫዎታ በመጀመሪያ የተፈለሰፈው በቻይና ነው ። በ9ኛው ክ/ዘ ።

ዘመናዊ የፖከር ጫዎታ ፣ የመጀመሪያው ዙር ቁማር የሚጀምረው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ተጫዋቾች ካርታ ታድለው ነው ። ጫወታው የሚጀምረው  ። ከዛም ካርታ በመሳብ ና ከአቋማሪው በመቀበል  የቁማር ውርርዱ   ይጧጧፋል ። በመደበኛ ፖከር እያንዳንዱ ተጫዋች እጁ ከሌሎቹ ተጫዋቾች ጋር ሲወዳደር ዋጋ አለው ባለው ባመነበት ካርታ   ጫዎታውን ይጀምራል ። እያንዳንዱ ተጫዋች በተራው ከፍተኛውን የቀደመውን የቁማር ውርርድ በጫዎታው ሰዓት ተወራርዶ እንደ ጫዎታው ፍሰት   ውርርዱን  ከፍ በማጦዝ ፣  ደጎስ ያለ ገንዘብ ሊያገኝ ይችላል ። ሁሉም ተጫዋቾች ወደ መጨረሻው  እየተንጠባጠቡ ይደርሳሉ ። ዙሩን አንድ ሰው ጠቅልሎት ቁማሩ  ያበቃል። ከአንድ ተጫዋች በስተቀር ሁሉም በየትኛውም ዙር ላይ ሊታጠፉ ወይም ከጫወታው ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ ። ከመጨረሻው የውርርድ ዙር በኋላ ከአንድ በላይ ተጫዋቾች በፉክክር ውስጥ ካሉ የካርታ ውድድር  ተካሂዶ ከፍተኛ ነጥብ ያመጣ ገንዘቡን ጠራርጎ ይወስዳል ።

ከዚህ ጋራ በተመሳሰለ በህብረት እስከ አምሥት ሰው  የሚጫወተው   የካርታ ጫዎታ አይነት አለ ። ያው ፖከር ነው ። 13  ካርታ ሰጪው ያድላል ። ካርታ አዳዩ ከአምስቱ ከፍተኛ ካርድ የደረሰው ሰው ነው ። 13 ካርድ ለአራቱ ተጫዎቾች ከማደሉ በፊት በደንብ ያሰባጥረዋል ( Paw ያደርገዋል )

ከዛም ለእርሱ አ14 ካርድ ይወስድና በየመልካቸው አሥተካክሎ አነሥተኛ ዋጋ ያለውን እና የማይጠቅመውን ካርታ ይጥላል ። በሥተቀኙ ያለው ተጫዎችም ካርታው ከጠቀመው አንስቶ ይወርዳል ። ወይም ሊዘጋ ይችላል ። በአጋጣሚ የተሰራ ካርታ ሊደርሰው ይችላልና ! ….

በዚህ ጫዎታ ብዙ ሴራዎች ፣ አሻጥሮች ፣ ከቁማሩ ጠረጴዛ ጀርባ ድርድሮች ሊኖሩ ይችላሉ ። ያላወቀ የገንዘብ እንጂ የህሊና ቱጃር ያልሆነ በወጥመዱ ይገባል ። አንድ ሁለቴ ያስበሉታል ። ( ይዘጋል ) ከዛ በኋላ ያልቡታል ። የነቃ ሲመስላቸው አንድ ሁለቴ እየሰጡ ያዘጉታል ። ኮድ አላቸው ። በአይን ይጠቃቀሳሉ ። አውቀው ይጣላሉ ። ደጋግሞ የሚዘጋውን ይሳደባሉ ። ያሽሟጥጣሉ ። ታላቢው በዚህም ይሸወዳል ። ይኽ ጫዎታ ከእኛ ፖለቲካዊ ሴራ ጋር ይመሳሰላል ። ካርታ ተጫዎቾቹን እንደ ፖለቲካ ፖርቲ ዓባላት ተጠሪዎች ውሰዷቸው ። የማዕከላዊ ኮሚቴ ዓባላት አድርጓቸው ። ወዘተ ። ሊሆኑም ይችላሉ ።

ፖከር የካርታ ጫዎታ ከ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ተወዳጅነት ያገኘ እልህ የሚያሲዝ   ቁማር ነው ።  ዛሬ በትንሽ የአድናቂዎች ቡድን ብቻ ​​ተወስኖ ከመቅረት ወደ መላው ዓለም ተሰራፍቶ ከመዝናኛነትም ከፍ ብሎ ለተሳታፊዎች በኢንተርኔት አማካኝነት በቀጥታ አሳታፊ ህኖ ተመልካቾችንም  ጭምር የሚያዝናና የካርታ ጫዎታ ሆኗል ። አቋማሪው  ብዙ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች በማሳተፍም  በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያንቀሳቀስበታል ።

በእኛ አገር  እየተካሄደ ያለውን በመንግሥት ደረጃ እየተከናወነ ያለውን ቁማር የጋሃዱ ዓለም “ፖለቲካዊ ፖከር ” ብዬዋለሁ ። ይኽ ፖለቲካዊ ቁማር ጫዎታ አጫዎቹና መጨረሻ ጠቅላዩም አንድ ሰው ነው ። የፈለገውን ካርታ በተገቢው ጊዜ በሁነኛ ሰዓት ፣ በተመቸ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ይመዛል ። ጆከር ፣  ጦር ፤ ልብ፣ ዳይመንድ ፣ ፍላዎር ፣ …ኬሻ፣ሸሌ፣ወለድ …23456789… ። እንደ አሥፈላጊነታቸው በወቅቱ መዘዝ አርጎ ያሰልፋቸዋል ። ለምሳሌ ዛሬ  ከሁለት እስከ አሥር  የቲዲኤፍ ጀነራሎችን ከአብይ ጎን ናቸው ። አንድ ጦር ፣   ጀነራል ታደሰ ወረደ ነው ።  ወለድ  ልብ ፣ (   ጄ ) ፃድቃን ገብረተንሣይ ነው ። ሞጆሪኖ ኪው ጦር ናት ። ኬሻ ዳይመንድ  ወይም ኬ ፣ ደብረፅዮን ገ/መድህን ነው ። ጆከር ደግሞ ጌታቸው ረዳ ነው ። የትም ብታሥገባው የመሆን ችሎታ አለውና !

እናም በዚህ የፖለቲካ ፖከር መሠረት አቋማሪው   የኢትዮጵያ  ጠ/ሚ አብይ ጌታቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ማድረጋቸው ተገቢ ይመሥለኛል ። በፖለቲካዊ ፖከር ሊበሉት ያሰቡት ቁማር አለና !

ይህንን ” ራያ  የተወለደ  ጆከር ሰውዬ  ፕሬዝዳንት በማድረግ የቁማሩን ካርታ መዘው ጠረጴዛው ላይ ሲያሥቀምጡ ግባቸው የታወቀ ነው ።  የካርታ ጫዎታ እንደ ቼዝ ማሰብን ቢጠይቅም ብልጠትና ዘዴ ፣ የሌሎች ቁማርተኞችንም ቀልብ መሥረቅ ይጠይቃል ። እንግዲህ የእኛም ፕለቲካዊ ፖከር ተመሳስሎቱ እዚህ ላይ ነው ።

መና ከሰማይ የሚወርድልን ይመሥል ” አይዞን ይህንን ዘመን ከተሻገርን ቅቤ በአፍንጫችሁ ይንቆረቆራል ። ” ያሉን እነ ዳይቆን ዳንኤል ክብረትም ይህንኑ የሸፍጥ ፖለቲካ አይተው ነው ። ሰውያችን ጥሩ እያጎ ከጎኑ አሥቀምጧል ። በበኩሌ ጌታቸውና ዲያቆኑ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው ። ሁለቱም መተርተር ሆቢያቸው ነው  ። እንዴ ምን ማለት ነው ፣ አጠቃላይ ኑሯችን ሲዖል ሆኖ ሣለ “ ወደፊት  ዓለም በጎናችሂ ታልፋለች ። ላይፋችሁን ትቀጫላችሁ ። “ ማለት ። …

እርግጥ ዲያቆን ዳንኤልና መሠሎቻቸው ፣ ኑሯቸው ቤተመንግሥት በመሆኑ የተርታውን ህዝብ ሥቃይ እና መከራ ላይገነዘቡ ይችላሉ ። ዛሬ ወላጅ ልጆቹን ለማኖር ፆሙን እያደረ እንደሆነ ማን በነገራቸው ! … በሁሉም ዜጋ ላይ ፣ የምግብና የትራንሥፖርት ዋጋ  በ2014 እና 2015 ዓ/ም  ውስጥ ብቻ በእጥፍ መጨመሩን እና ኖሮን ለመቋቋም እንዳልቻለ  እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ ። ጊዜያቸውን ያሳለፉት የጠቅላዩን መፅሐፍ እያረቱ በመሆኑ አጠቃላይ ኑሮቸው ቤተመንግሥት በመሆኑ  ። ሃቁ ግን ፣ በዓሉ ግርማ እንዳለው መኖርም መሞትም ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል ።

ሥቃያችን በዝቷል ። እውነታውን ላይቀይሩ፣በታሪክ ጥቁር መዝገብ መፃፋቸው ላይቀር ፣ ከህዝብ ልብ ውሥጥ መውጣታቸውን እያወቁ ፣ ዛሬም በኃይል መግዛት እንችላለን በማለት በቀቢፀ ተሥፋ ፣ ሃቀኛ ምሁራንን ማሰቃየታቸውን እና ማሰራቸውን ግን “ ጊዜው የእኛ ነው !” የሚሉ ደናቁርታት ቀጥለዋል ።

የመቀነሥ ትውልድ አፍርተው የመደመር ትውልድ ይሉናል ። ጥላቻን እየዘሩ ፍቅርን አጨድን ብለው ለማታለል ይቃጣቸዋል ። እያሠቃዩ፣ እያሰሩ ፣ እያሥራቡ ና እየገደሉ “ እንደ ኢየሱስ የፅድቅ ሥራ እየሰራን ነው ። “ ማለት የለየለት የፖከር ፖለቲካ ሤራ ነው ።

ነገ አፈር የሚሆነው ደንቆሮ አሽከራቸው ከጥበብ በመራቁ የተነሰ ፣ እንደ ድሮ የፊውዳል  እና የአምባገነኖች ገራፊ ፣  በትዕዛዛቸው መሠረት  ያለርህራሄ ዜጎችን እያሰቃየ ነው ። እነሱም ከቁማሩ ዛሬ የሚያገኙትን የገንዘብ ትርፍ እንጂ ነገ ለልጅቻቸው የሚያተርፉትን ሥድብ፣ ውርደትና መሸማቀቅ ዛሬ ላይ ሆነው አይረዱትም ።

በፖለቲካዊ ቁማራቸው ሳቢያ ሃቀኛ የኢትዮጵያ ልጆች በራሳቸው ቅኝ ገዢዎች ፣ በራሳቸው መንግሥት አሣር መከራ ቢያዩም ( ጎምቱ ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱን ጨምሮ አያሌ የፖለቲካ እሥረኞች በቅኝ ገዢዎቻችን በየእሥር ቤቱ  እየተሰቃዩ ነው ።  )

በራሳቸው አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው እየተሸማቀቁ የሚኖሩ በ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች  ናቸው ። አለአግባብ እየታሰሩ በጉቦ የሚፈቱም በኦሮሚያ ክልል እንደበዙመ የአገሪቱ ደህንነት አያውቀውም ማለት አይቻልም ።   በተቀናጀ መንግሥታዊ በሚመሥል አፈና እየታፈኑ በሚሊዮን እና በመቶሺ እየከፈሉ ከእገታ የሚፈቱ ጥቂቶች አይደሉም ።

በየተቋማቱ ጉቦ እየሰጡ መብታቸውን የሚያስከብሩም ጥቂት ዜጎች እንዳልሆኑ ይታወቃል ። እንግዲህ ይኽን የመሣሠለ ግፍና የዳቦ ችግር በሰፈነበት ህዝብ ላይ ነው ጠቅላዩ ጆከር መዘው “ ጌቾ ምላሡን “ የትግራይ ጊዚያዊ መንግሥት ፕሬዘዳንት አድርጌዋለሁ ያሉት ። ከታላቅ ህቡ ድርድር በኋላ የተመዘዘች የፖለቲካዊ ፖከር ካርታ ናት ። ጆከሯ ። …

ግና ፣ “ ይኽም ያልፋልና “  ጊዜ አልፎ  ነፍሰ ገዳዮች፣ ዘራፊውች ፣ ጨካኞች ፣ አይጠረቄ ሥግብግብች ። ወዘተ ። ሁሉ በሰፈሩት ቁና እንደሚሰፈርላቸው ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም ። እሥከዛው ግን ግፉ ና ፖለቲካዊ ቁማሩ ይቀጥላል ። የኢትዮጵያ ህዝብም አሥቀድሞ ባወቀው ቁማር እንደማይበላ ቢያውቅም በብሥለት እና በብልሃት ከህዝብ ባነሰው መንግሥት እያዘነ የመንግሥትን ፖለቲካዊ የካራታ ቁማር በአንክሮ ይከታተላል ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

336656836 2697093393765720 898162267517684751 n
Previous Story

የአብይ የጤና ሁኔታ ይመርመር

LUUTDZ4TQBMHPEBY3PTGFYXTFI 1 1 1 1 1 1 1
Next Story

ዛሬም ጦር አምጣ መሬት የሚመታ ማን ነዉ ?

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop