ከምዕራባዉያን ሆነ ከአሜሪካ ቀደም ኢትዮያ ነበረች ፤ ለዘላለምም ትኖራለች

አበዉ መሬት ያለዉ ጦርነት አለበት ይላሉ ፡፡ ይህ በተለይ እን ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በልዩ ሁኔታ የሚሰራ እና ምንአልባትም ለሁለት አገራት በእጂጉ የታለመ ህልም ይመስላል ፡፡

ራሽያ እ.ኤ.አ. በ1941 በጀርመን እና ተበባሪወቿ  ወረራ ተፈፅሞባታል ፡፡ ይህም በዘመናችን በሰሜን ጦር ቃል ኪዳን አባላት አገራት እና በአስተባባሪዋ አሜሪካ ዩክሬንን በመከላከል ሰበብ ጦርነት ተከፍቶ ራሽያን ለማጥቃት እና ግዛቶቿን ለማናጋት  ቀጥተኛ እና የተልዕኮ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን  ድፍን አንድ ዓመት ተቆጥሯል፡፡

ለዚህ መነሻየ አሜሪካ እና ግብረ አበሮች ከጥዋት አስከ አለንበት በአገራት እና በህዝቦች የማይገሰስ ተፈጥሯዊ  የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ፣ ሠባዊነት እና ነጻነት ለምን ያገባኛል እንደሚሉ ነዉ ፡፡

አሜሪካ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ወራሪ ኃይል  በ18በኛዉ እና በ19ኛዉ ክፍለ ዘመን በ40ዓመት ልዩነት ወረራ እና ግፍ ሲፈፀም ምንም ዓይነት የሉዓላዊነት እና የሰባዊነት ርሕራሄ አላሳየችም ፡፡

ይህም ቀርቶ ኢትዮጵያ በወራሪዉ ና ሰተፍሳፊዉ ኢጣሊ መንግስት የደረሰዉን ዕልቂት ፣ ዉድመት ፣ ሞት እና ቀዉስ አላወገዘችም ፤ካሳ ጥያቄ ለማቅረብ ሆነ ለኢትዮጵያ እና ጀግኖች አርበኞች  ተጋድሎ እና መከራ ዕዉቅና መስጠት አልፈለገችም ፡፡

ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጦርነት ወራሪ የዚያድባሪ መንግስት ዕብሪት ያስከተለዉ ኢትዮጵያን የመዉረር እና ግዛቷን የመንጠቅ መሆኑን አሜሪካ ስታዉቅ አሜሪካ ሶማሊያን የማበረታታት እና የማስታጠቅ ተግባር በማድረግ ዳግም ለኢዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ ያላቸዉን ጥላቻ እና ንቀት በማን አለብኝነት አሳይታለች ፡፡

በመቀጠል የኢትዮጵያን አንድነት እና ታሪካዊ የግዛት አስተዳደር ከባህር በር ከማሳጣት ጋር በተሰራ ሴራ ህጋዊ የኢትዮጵያ መንግስት በኃይል በማስወገድ በ1983 ዓ..ም. ህወኃት /ኢህአዴግ  ስልጣን ወንበር ላይ ጎትቶ በማስቀመጥ ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ የራሷን የተፈጥሮ የባህር በር እንድታጣ ተደርጓል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬም የሰሚ ያለህ! ዲያብሎስን ማመን የቀጠልነው መቼ በማተቡ ይጠናል ብለን ነው?

ከዚህ ቀን ጀምሮ አስካሁን እጂግ አሰቃቂ እና በዓለም ህዝቦች ታሪክ ታይቶ እና ተስምቶ በማይታወቅ ሁኑታ በኢትዮጵያ በማንነት ፣ በዕምነት ፣በባህል እና በአመለካከት ከፍተኛ ሠባዊ መብት ጥሰት ፣ ፍጂት ፣ መፈናቀል እና ሁሉን አቀፍ  ግፍ ተፈጽሟል ፤ እየተፈፀመ ና ፡፡ በተለይም ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት ጀምሮ አስከ ዛሬ የሚካሄደዉ ማንነት ተኮር ዘር ፍጂት ፣ስደት ፣ዉርደት ፣ሠባዊ መብት ጥሰት በራስ አገር ባርነት እና ዉርደት ማስተናገድ የሠባዊ ጉዳይ ያገባኛል የምትል አሜሪካ ሆነ በሰባዊ ድጋፍ ስም የሚኖሩ ተቋማት ከማስተጋባት ዉጭ ያደረጉት አለመኖሩን ስናይ ሠባዊነት ልክ እና መልክ በቀለም እና በቦታ ይወሰናል ወይ የሚለዉን ጥያቄ ማንሳት ግድ የሚል ይመስላል ፡፡

የኢትዮጵያ እና የዓማራ ጉዳይ የሚለያይ ሳይሆን አንድ መሆኑ ጠለትነት መሆኑ በሚታይባት አገር በኢትዮጵያ ግዛት ፣ ሠባዊ መብት ፣ ዘር ፍጂት እና ጥቃት …የሚደርሱ ሁሉ ትርጉማቸዉ ከሌላዉ ዓለም የሚለያይ ይመስላል ፡፡

ህወኃት /ኢህአዴግ ለሠላሳ ዓመታት የኢትዮጵያን እና ህዝቧን ጥቅም በፖለቲካ ስልጣን አሳልፎ ሲሰጥ አሜሪካ በዝምታ ስታበረታታ እንጂ ስትገታ አልታየችም ፣

ትህነግ /ህወኃት የኢትዮጵያን ግዛት ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን  እና ወደ ራሷ ትግራይ  ግዛት የኢትዮጵያን በተለይም የጎንደርን እና ወሎን ግዛቶች ወደ ትግራይ ክልል  በማን አለብኝነት ነዕብሪት እና ራስ ወዳድነት በመጠቅለል ለሶሰት አስርተ ዓመታት በዚሁ በወረራ በተያዘዉ እና በመላ አገሪቷ የዘር ፍጂት ፣ ኢሰባዊ ድርጊት፣ ማፈናቀል፣ መግደል …ሲፈፀም ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን  ስቃይ እና መከራ ከዚያ እስካሁን የጠየቀ የለም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  " የጥለዛ ፓለቲካ " ፣ሥለ ፍትህ ፣ ሥለ ሠላም ሥለ ዴሞክራሲ ወዘተ ደንታ የለውም  - መኮንን ሻውል  ወልደጊዮርጊስ 

ይባሰ  ብሎ በዓመታት የህዝብ የለዉጥ እና ከባርነት ቀንበር የመላቀቅ ጥያቄ  በዕምቢተኝነት የህዝብ ማዕበል የተገፋዉ ትህነግ/ኢህአዴግ ለስልጣን ቅርምት ከዉስጥ እና ከዉጭ ፣ከተማ እና ገጠር በመሆን  ወረራ በዓማራ ህዝብ ላይ መፈፀሙን ጠላት የሚመሰክረዉ ዕዉነት ነዉ ፡፡

የትህነግ ወረራ ዓማራን በኃይል በመዉረር ኢትዮጵያዊነትን እና  ኢትዮጵያን ከመስረቱ ማናጋት የቀደመ የዘመናት ህልም በመሆኑ ቀድሞ በጉልበት ከያዛቸዉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ጎንደር እና ወሎ በተጨማሪ አስከ መኃል ሸዋ ዘልቆ የግዛት ማስፋፋት ምኞቱን ዕዉን ለማድረግ ያለማንም ከልካይ ሰተት ብሎ ገብቷል፡፡ በዚህም ፡-

ከፍተኛ ማንነት ተኮር ዕልቂት እና ሞት ተፈፅሟል

የሀብት ዘረፋ እና ዉድመት አድርሷል

የሰባዊ ክብር የማሳጣት እና አዝርዕት እና እንስሳት ላይ ሳይቀር ግፍ ተከናዉኗል ፡፡

ከ1960ዎቹ ጀምሮ በጠላትነት የሚፈርጃቸዉን ኢትዮጵያዊነት፣ ዓማራ ፣ እና ክርስትናን የፖለቲካ መሰሪያ ለማድረግ ሰርቷል  ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል እያለ ላለፉት ሠላሳ እና ለሁለት ዓመቱ የጦርነት ዕልቂት ብቸኛዉ እና ወነኛዉ ተጠያቂ ትህነግ/ ኢህአዴግ ሆኖ ሳለ ራሱን እና አገሩን ከህልዉና ጥፋት ፣ አገሩን ከዉድመት እና ፍረሰት ፣ተፈጥሯዊ  መብቱ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በተለይም የዓማራ እና የአፋር ህዝብ ከመሞት መሰንበት ብሎ ሞቶ መኖርን በመምረጥ የመከላከል ስራ አድርጓል፡፡

ህወኃወሃት ኢህአዴግ ከመንግስት መሳ ለመሳ ከነበረዉ የጦር ዝግጂት አኳያ የኢትዮጵያ  እና ዓማራ ህዝብ  ሽማግሌ ምርኩዙን ፣ ጎልመሳ በትሩን ፣ ወጣት(ፋኖ)  ወኔዉን፣ የኃይማኖት  አባት ዳዊቱን ፣ደካማ ስንቁን….በመያዝ በህልዉና ትግሉ የሚገባዉን እና ታሪክም ሆነ ትዉልድ የማይሽረዉን ተጋድሎ አድርጓል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያን ከዳግም ፍረሰት ታድጓል፤በራሱ አገር በግዞት እና በባርነት የበይ ተመልካች ላለመሆን ቁርጠኝነቱን በፍፁም አገር ወዳድነት እና ብሄራዊ ስሜት ታሪኩን አድሷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማይቀጡት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል - ይሄይስ አእምሮ

የኢትዮጵያዉን የህልዉና እና የነፃነት ተጋድሎ ኢህዴግንም ከሞት ታድጓል ፡፡ ”ራሱን ነፃ ያወጣ ጌታዉንም ነፃ ያወጣል ”እንዲሉ፡፡

ዛሬ ላይ እንደትናንቱ የአሜሪካ በአንድ ሉዓላዊት አገር እና ህዝብ ላይ ጣልቃ የመግባት አባዜ የዓማራ ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ ኃይሎች፣ የኤርትራ ኃይሎች…..በማለት ስለ ኢትዮጵያ ዳር ድንበር ፣ወሰን ፣ታሪክ እና ማንነት ልትናገር መከጀሏ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለታሪክ ያላትን ጥላቻ እና ንቀት በግልጽ የሚያሳይ ነዉ ፡፡

አሜሪካ ምዕራብ ትግራይ የምትለዉ  የኢትዮጵያ ግዛት እና የጎንደር ክ/ሀገር አካል የሆነዉ ሰሜን ጎንደር የሚል በኢትዮጵያ በኩል ሲጠፋ ከረጂም ዓመታት በፊት የባህር በር  በመሳጣት ስትሰራ ስለ ኢትዮጵያ የሚናገር መጥፋቱን ዛሬም ከሞኝ ደጂ …ብላ ተያይዘዋለች ፡፡

ለመሆኑ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ላይ ሲደርሱ ምዕራባዉያን የራሳቸዉ ፍርኃት እና ትምክህት ሊጭኑ የሚፈልጉበት ምክነያት ትልቅነት ወይስ ትንሽነት ይሆን ፡፡ ትልቅ እንድንል እኛንም ሆነ ሩሲያን ያወቁናል ጥልቅ እና ምጡቅ  የራሳችን ከራሳችን አልፎ ለሌላዉ የሚሆን አኩሪ እና ተፈሪ ማንነት አለን ፡፡

ትንሽነት የሚያሳያቃያቸዉ ከሆነ  ሌላዉን በመኮነን ሆነ በማጥላት ፤በጣልቃ ገብበት  ፅድቅ ስራ የለም ፡፡ ጣልቃገብነት እና ማን አለብኝነት ሠባዊነትም ስልጣኔም አይደለም ፡፡

Unity is Power, Power is Every Thing!

Long Live Ethiopia, Ethiopian!

No half, No loaf, Justice is Justice, peace is peace!

Allen Amber

 

1 Comment

  1. Well, the point you tried to make makes sense ! But the very ugly if not stupid way of our political thinking heavily rests or focuses on just blaming external powers as if we are exceptions of the rule and game of world politics and international relations which is of course determined by the very essence of winning or at least not losing the game !
    Why we endlessly complain and blame others where as it is we ourselves are killing one another or ourselves and leave our door very open and let any one mess our home? Is this not politically stupid and morally bankrupt ? Absolutely it is! Sad!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share