አዋጅ አዋጅ የደበሎ ቅዳጅ የሰማህ ላልሰማ አሰማ !!!
በጥቁሮቹ ቤኒቶ ሙሶሎኒ እና በግራዚያኒ የእልቂት አዋጅ ታውጆብኃልና ራስህን ለመከላክል በአንድነተ ተነሳ !!
የተከበርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይንም በነሱ አጠራር ብሔር ፣ ብሔረሰብ እና ሕዝብ ሆይ በጥቁሩ ቤኒቶ ሙሶሎኒ (በጠቅላይ ሚንስቲር ዶክተር አብይ አህመድ አሊ) አዝማችነት እና በግራዚያኒ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ፍታውራሪነት ፋሽስታዊ የሆነ የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኃል ።
በእቅድና በፕላናቸው መሰረት የኦሮሚያን ክልል ከሌሎች ብሔር ፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች በማጽዳት ልሙጥ ማንነት እንዲኖረው ለማድረግ በከፈቱት ዘመቻ በሚሊዬን የሚቆጠር ወገንህ አምስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተገሏል ከሞት የተረፈው ተሰዷል ። የዘመቻው ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ አዲስ ኦሮሙማ የምትባል አገር መመስረት ሲሆን ነዋሪዎቿም ያልተከለሱና ያልተበረዙ (ያልተዳቀሉ) የጠራ የኦሮሞ ደም ያላቸው ብቻ ይሆናሉ ። ኦሮሙማ ተብላ በምትታወጅ አገር ሌላው ቀርቶ የጠራ የኦሮሞ ደም ኖሮት እንኳን ቋንቋውን ያልቻለና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነ ኦሮሞም የሆነ ግለሰብ መኖር አይፈቀድለትም ።
የተከበርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዶክተር አብይና በአቶ ሽመሊስ አብዲሳ የታወጀብህ ጦርነት ኦሮሚያን ከሌሎች በማጽዳት ቢቻ የሚያበቃ አይደለም በመሆኑም የአገሪቱን መዲና አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው ሸገርና አዲስ አበባ ካሉ በኋላ ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ እንደ ቆሻሻ ቆጥሮ ቤቱን እላዩ ላይ እያፈረሱ ለምን ተብለው ሲጠየቁ ከንቀታቸው ልቀት የተነሳ ከበላይ አካል አጽዱ ተብለን ነው የሚል መልስ ይሰጣሉ።
አዲስቷ የሚሏት ኦሮሞን የምትመስል ኢትዮጵያ (ኦሮሙማ) የምትባል አገርን ፈጥሮ ያለተገዳዳሪ እና ስጋት ለመኖር ሊሎችን ብሔር ፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች የሚሏቸውን በጉልበት በመጨፍለቅ በስሩ ለማድረግ የግዛት ማስፋፋት ዘመቻው ያልነካው ክልል ከትግራይ በስተእር የለም። ስለሆነም ተራ በተራ አጽመ እርስትህን እየተቀማህ ፣ ልጅ ሚስትህን እየተነጠቅህ እስከ መቼ ትኖራለህ?
እነዚህ የኦሮሞ ጽንፈኞች በሌሎች ብሔር ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መቃብር ላይ አዲስ አገር ለመመስረት ከሃምሳ ዓመት በላይ የታገሉት ዓላማቸው በመሆኑ ለመተግበር ጥድፊያ ላይ ናቸው ። ጥድፊያው ከትህነግ ስህተት የተማሩት ትምህርት ስላለ ነው ይሄውም የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት መንበረ ሥልጣኑን ተቆጣጥሮ ባንኩንም ታንኩንም በእጁ አድርጎ ሃያ ሰባት ዓመት የኢትዮጵያን ሕዝብ መግቢያና መውጫ አሳጥቶ በቁጥጥሩ ስር ባደረግበት ወቅት ከሌሎች ክልሎች የቀማውን መሬት ይዞ ያለ ከልካይ አገር ማወጅ ይችል ነበር ያንን ሳያደርግ እንደ አሮጌ ጅብ ያገኘውን ሁሉ ሲያግበሰብስ ነጋበትና ለቅሌት ተዳረገ ። ይህንን ታሳቢ ያድረገ የሮኬት ፈጥነት እየሮጡ ስለሆነ የቸኮለች አፍሳ ለቀመች እንደሚባለ ብህል ለማድረግ ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል ።
ሁሉንም ኬኛ በሚሉት ስግብግብነታቸው መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገነቡት ሰራዊት ብዛትና በሚያስታጥቋቸው የመሳሪያ ጥራት አንበርክከው ባሪያ ማድረግ አይችሉም ። በሰራዊትና በመሳሪያ ብዛት ሕዝብን ያሸነፈ ኃይል በዓለም ላይ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም እና ነው ።
በኦሮሚያ ክልል በአማራው ላይ በአብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ መሪነት ሲካሄድ የቆየው የኦሮሙማ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አድማሱን አስፍቶ ዛሬ ወደ ሌሎች ብሔር ፣ ብሔረስብ እና ሕዝቦች ጋር በመድረሱ የጉራጌን ፣ የሲዳማን ፣ የወላይታን ፣ የጉማይዴን ፣ የጋሞን ፣ የሱማሌን ፣ የጋምቤላን ፣ የቤንሻጉል እና ሌሎችንም ተጠቂ አድርጓቸዋል ።
የተከበርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ትልቁ ዓላማቸው ኦሮሞን የምትመስል አዲስቷን ኢትዮጵያ (ኦሮሙማን) መመስረት ነው ። ኦሮሞን የምትመስል የሚሏት አገር ዜጋ የሚሆነው ደግሞ ከየትኛውም ብሔር ፣ ብሔረስብ እና ሕዝብ ጋር የደም ቅልቅል የለሌብት ልሙጥ ኦሮሞ ነው ። በዚህ ስሌት እና በጀመሩት ከሰሜን አስከ ደቡብ ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የመሬት ወረራ ጥድፊያ የሚያመላክተን ነገር ቢኖር የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከዘር ማጥፋት ዘመቻው የሚተርፍ ብሔር
፣ብሔረሰብም ሆነ ሕዝብ እንደማይኖር ንው ። ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ላይ ሆኖ የአብይን አገዛዝ ማስወገድ ይዋል ይደር የሚባል ጉዳይ አለመሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል ።
አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ጊዜ ሰጠን ብለው በ21 ኛው ክፍለ ዘመን ሊፈጸም ቀርቶ ሊታስብ የማይችል አረመኔያዊ ተግባር ፈጽመዋል በመፈጸምም ላይ ናቸው ፦
➢የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር ሴት ጽንሷን ከሆዷ ቀዶ በማውጣት ሟችን እናት አስታቅፈው አሳይተውናል ፤
➢ቤትን ሰው ላይ በቡልዶዘር አፍርሰው ለሞት እና ለጅብ ዳርገዋል ፤
➢ከትዳር አፋተው የቤተሰብ ኑሮ እና ፍቅርን ነስተዋል ፤
➢በመንፈሳዊ ህይወት ጣልቃ ገብተው ቅድስት ቤተክርስቲያንን ተዳፍረዋል ፤
➢ታሪካዊ ቅርሶችን አውድመዋል ፤
➢ብሔራዊ በዓላትን እንዳታከብር ክልክለዋል ለሞትም ዳርገዋል ፣
➢በዘር ለይተው ጨፍጭፈዋል ፣ አፈናቅለዋል ፤
➢የንቀቱ ንቀት አቶ ሽመልስ አብዲስ ለአገር መከላከያ ብቻ የሚፈቀደውን የአዬር ወለድ ስልጠና የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን በማሰልጠን ላይ ይገኛል ።
ከዚህ የላቀ ንቀትና ውርድት ሊኖር ስለማይችል በቃ ሊባሉ ይገባል ። እፍኝ የማይሞሉ ስልጣንና ነዋይ ያሰከራቸው የኦሮሞ እና የትግራይ ጽንፈኞች ከመቶ ሚልዮን በላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ እየፈጁና እያሰቃዩ ሊኖሩ ስለማይገባቸው ሆ ብለን ተነስተን ማስወገድ አለብን ። የሚኩራሩበት የመከላከያ ኃይል እና የፖሊስ ሰራዊት ከአብራክህ የወጡ ልጆችህ በመሆናቸው ቆርጠህ ስትነሳ ብዙኃኑ ከጎንህ እንደሚቆም አትጠራጠር። ስለሆነም አዋጅ አሰነግረህ ከዘላለም ባርነት ለአንድ ቀን ነጻነት ተነሳ ።
ከሁሉም በላይ በእነዚህ አክራሪ ጽንፈኞች ያልተጠለፈ እና ኢትዮጵያዊነቱን ለድርድር የማያቀርብ የኦሮሞ ተወላጅ መልካም ታሪኩን እና ከሌላው ወገኑ ጋር ያለውን የዜግነት አንድነቱን ለመበጣጠስ በስሙ የሚነግዱትን ወሮበላዎች ለማስወገድ በሚካሄደው ሁለ አቀፍ ትግል የአንበሣውን ድርሻ መውሰድ ይኖርበታል ።
ለተከበርከው የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ሉአላዊነቷን ላለማስደፈር እና ልትሰዋላት ቃል ኪዳን የገባህላት እናት ሀገርህ በመፍረስ ላይ ትገኛለች ፤ ራሱ ሳይማር አስተምሮህ ለዚህ ያበቃህ ወገንህም በዘር ተለይቶ ከቤት ንብረቱ እየተፈናቀለ እና እየተጨፈጨፈ ነው ። እናት አገርህን ከመፍረስ፣ ወገንህን ከዘር ፍጅት ለማትረፍ የሚችል የተደራጀ እና የታጠቀ ሌላ ኃይል ባለመኖሩ ከወገንህ ጎን ቆመህ ታሪክ የምትሰራበት አጋጣሚ በመሆኑ ልትጠቀምበት ይገባል።
ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል እና የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሥራዊታችን ውለታው ተዘንግቶ ከደረሰበት ክህደት እና ሰቆቃ የምትማረው ትምህርትም እንዳለ መዘንጋት ያለብህ አይመስለኝም ። እነኚህ ጽንፈኞች ከኬኛነት ውጭ ታማኝነትም ሆነ የሞያ ብቃትህ ምናቸውም ስላይደለ እንደ ቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሜዳ ላይ ከመጣልህ በፊት በጊዜ ከኢትዮአጵያ ሕዝብ ጎን ቆመህ ትግሉን መምራት ይኖርብሃል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይጠብቅ
ንጉሤ አሊ