ከታሪክ ማህደር: ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ (ጠ/ሚኒስቴር)

March 16, 2023
4 mins read
180727

ለሀገራቸው ከሰሩት ዓበይት ሥራዎች መካከል በጥቂቱ….

▻ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ተገቢውን ውክልናና ጥቅም እንድታገኝ ያደረጉት ተጋድሎና ጀብድ ቀን በባቡር ፣ ሌሊት በመርከብ እንዲሁም በአውሮፕላን ያለእረፍት ለበርካታ ቀናት እየተጓዙ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ ደክመዋል፡፡

▻ ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረራ ወቅት ባደረሰችው ጉዳት ካሳ ልትከፍል ይገባል ብለው በመከራከር በጊዜው ጥቁሮች እንደሰው በማይታዩበት ጊዜ በአውሮፓ የአለም መሪዎች ስብሰባ ላይ እሳቸው ብቻ ጥቁር በስብሰባው ላይ ተገኝተው ለኢትዮጵያ የሚከፈላት የካሳው ብር 5 ሚሊዮን ዶላር ነው ፤ ተብሎ ቢወሰንም ክቡር አክሊሉ ግን እንደዛ እንደማይሆን በውሳኔው እንደማይስማሙና በመሟገታቸው የክፍያው የብሩ መጠን ወደ 25 ሚሊየን ዶላር ከፍ እንዲል አድርገዋል።

▻ ገና በወጣትነታቸው በዓለም መንግሥታት ማኅበር (League of Nations) የኢትዮጵያ ዋና ጸሐፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ፤ በአፋምቦ ፣ ኦጋዴን፣ ጋምቤላና ኤርትራን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ግዛቶች በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከነበሩ ቅኝ ገዢ አገራት ግዛትነት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ አድርገዋል።

▻ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የእንግሊዝ መንግስት ያቀረበው ድርድር ወድቅ አድርገው የራሳችን ብሔራዊ ባንክ ባለቤት እንድንሆን አድርገዋል።

የእንግሊዞች ሀሳብ የነበረው ባንኩ መቀመጫውን በለንደን ይሆናል የባንኩ አስተዳደሮች በእንግሊዝዋ ንግስት ይመረጣል ኢትዮጵያ ወርቁን ትልካለች ከዛ ተመርቶ ይላክላቸዋል ሲሉ ጀግናው አክሊሉ ሀ/ወለድ ግን “እኛ የራሳችን ባንክ እዚሁ አ/አ እንዲሆን ነው ምንፈልገው ንግስቲቷ በኛ ባንክ ሰራተኞች መራጭ ማን አደረጋቸው እኛ የናንተ ቀኝ ተገዢዎች አይደለንም” በማለት ተከራክረው በማሸነፍ ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ አምራች አድርገዋታል።

▻ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በተሰሩ ታላላቅ ስራዎችና ተቋማት ምስረታ በብዙው መስኮች የተሳተፉ ሲሆን በግንባር ቀደምትነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምስረታ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ።

▻ እኚህ ታላቅ ዲፕሎማት ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ የአገራቸውን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ባሻገር ከነ ዶ/ር ምናሴና ክቡር ከተማ ይፍሩ ጋር በነበራቸው ጥምረት የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትንም በመመስረት በሀገራችን ውጪ ጉዳይ ታሪክ የምንጊዜም ወርቃማው ዘመን ሆኖ በታሪክ እንዲታወስ ታላቁን ሚና ተወጥተዋል።

ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ (ጠ/ሚ)

መጋቢት 5 ቀን 1904 — ህዳር 13 ቀን 1967 ዓ.ም

ክብርና ዘላለማዊ እረፍት ለፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀ/ወልድ

#ታሪክን_ወደኋላ

 

https://youtu.be/E7nnEf2SFzM

ክብርና ዘላለማዊ እረፍት ለፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀ/ወልድ በፎቶ

336031284 1413641412746406 6671468806304169983 n 1 1

Leave a Reply

Your email address will not be published.

336669780 737091404492193 1375882874806800233 n 1 1
Previous Story

ከታሪክ ማህደር – ጋዜጠኛ ብዙ ወንድማገኘሁ (ከማጀት እስከ አደባባይ)

abiy killer 1 1 1 1
Next Story

ልዩ መረጃዎች! “እነ ዶ/ር ይልቃል አኩራፊነትና ግለኝነት አለባችሁ” – ዐቢይ | ስለ ፋኖ የተያዘው ዕቅድ ተጋለጠ!

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop