ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የዘንድሮው 127ኛ የአድዋ ድል በአል “አንድ ወጥ ” በሆነ መልኩ እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አሳውቋል::
“አንድ ወጥ ” የሚለው የባህልናስፖርት ሚኒስቴር ዝግጅት በትግባር ሲተረጎም-
- ለበአሉድምቀት በሚዘጋጀው ፖስተር ላይ የዳግማዊ አፄ ምንሊክን ፎቶ አስቀርቶ በምትኩ በትግራይ ክልል የወታደርነት ዘመኑ የሚያውቁት ጌቶቹ እንደነገሩን በኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት ወቅት ጏዶቹ የተጣለባቸውን ወታደራዊ ግዳጅ ሲወጡ እርሱ ግን ከበሻሻ እስከ መቀሌ ድረስ የዘለቀ የ ከሰል እሳት ማርገብገቢያ ሽያጭ ንግድ ሲያጧጡፍ የከረመ በዚህም የተነሳ የመቀሌ ጌቶቹ”መሽረፈት” እያሉ የሚያላግጡበትን ምኩን በምትኩ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፖስተር ላይ ፎቶው እንዲታተም ማድረግ
- የዳግማዊአፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ምስሎች የታተሙባቸው አልባሳትን የሚሸጡ ሱቆችንና ማሸግ እና መዝረፍ
- የዳግማዊአፄ ምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱን ምስል የሚያትሙ ማተሚያ ቤቶችን ማስፈራሪያ እና ማስጠንቀቂያ መስጠት እና ማሸግ
- የዳግማዊአፄ ምኒልክ እቴጌ ጣይቱ እናየኢትዮጵያ ባንዲራ የታተመባቸውን አልባሳትም ሆነ አርማዎች ይዘው የተገኙ ዜጎችን ማሰር…( እስካሁን ወደ 50 የሚጠጉ ታስረዋል..)
- የቴዲ አፍሮ ” ጥቁር ሰው” ሙዚቃ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንዳይጫወት ክልከላ መጣል
- ወደ400 የሚጠጉ ሆድ አደር መድረክ እና ወረት( ብር) የተጠሙ አርቲስቶችን ሰብስቦ ምኒሊክ እና የጣይቱ ስም እንዳይነሳ አስምለው ቃለ ተውኔት መቼት ገፀ ባህሪያት አልቦ ቲያትር ማሰራት ወ.ዘ.ተ….
ጥያቄ ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር–
ጋሽ መርዳሳ እነዚህን መፈፀም ይችሉ ይሆን
- የአድዋንጦርነት እና የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ/ እቴጌ ጣይቱን ሚና የዘገቡ በአለም ዙሪያ የተበተኑ የታሪክ መዛግብትን ሰብስቦ ማቃጠል ይቻል ይሆን
- የታሪክምሁራን እና ተመራማሪዎችን አፍ መለጎም ደብዛቸውን ማጥፋትስ
- የዳግማዊ አፄ ምንሊክን እና እቴጌ ጣይቱን ታሪክ ከህዝቡ ልብ መፋቅ እና ማጥፋት ይሞከር ይሆን
ጋሽ መርዳሳ እና አጋሮቻቸው ለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ካላቸው “ልዩ ፍቅር” የተነሳ ይህን ከመሞከር እንደማይታክቱ አምናለሁ::
ይልቅስ ጋሽ መርዳሳን ላመስግን ! እድሜ ለርስዎ እና ለጥረትዎ የታሪክ መፃህፍቶቻችንን ከየወሸቅንበት እና ከጣልንበት እያወጣን በወጉ አራግፈን እና ጠርዘን ለልጆቻችን ውርስ እንድናስቀምጥ ስላነቁን እጅግ እናመሰግናለን! እንዴ ያኛው ሎሌዎ እኮ “ስንሞት ኢትዮጵያ…” እያለን ሸማችንን ተከናንበን ተኝተን ነበር:: አሁን እርሶ ባይኖሩ ማን ይቀሰቅሰን ነበር?!