ሳያስቡበት በቅጡ፣ ሰይፍ ካፎቱ አያውጡ
ካውጡ ደግሞ ካቃጡ፣ እንዳይመልሱት ሳይቆርጡ፡፡
ተዋሕዶ በሕልውናዋ ላይ የመጣባትን ኦነጋዊ ሳጥናኤል ለመቆራርጥ ሰይፏን ካፎቱ አውጥታ በሳጥናኤሉ ላይ አቃጣችበት፡፡ ሳጥናኤሉም በተዋሕዶ ሰይፍ ሊቆራርጥ መሆኑን አውቆ እጁን ወደላይ በማንሳት በፍርሀት መቅለብለብና መወራጨት ጀምረ፡፡ ባለመታደል ግን የሳጥናኤሉን ቃላባይነት በመዘንጋት፣ ሳጥናኤሉ የሰጣትን ባዶ ቃል አምና ሰይፏን ወዳፎቱ በመመለስ፣ ምናልባትም ለሞት የሚያበቃትን ትልቅ ስሕተት (fatal mistake) ፈጸመች፡፡ የተዋሕዶ ሰይፍ ወዳፎቱ በተመለሰበት ቅጽበት ደግሞ ሳጥናኤሉ ተዋሕዶን ቆራርጦ ድምጥማጧን ለማጥፋት ስሎ ያስቀመጠው የዳንኤል ክብረት ሰይፍ ካፎቱ ተመዘዘ።
ተዋሕዶ ወደ አፎቱ የመለሰችውን ሰይፍ እንደገና ለመምዘዝ አትችልም ባይባልም እንኳን በጣም ከባድ ይሆንባታል፣ ረዥም ጊዜም ይወስድባታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ የዳንኤል ክብረት ሰይፍ ተዋሕዶን ሙሉ በሙሉ ቆራርጦ ግብአተ መሬቷን ሊፈጽም ይችላል፡፡
ስለዚህም ትልቁ ጥያቄ ተዋሕዶን በጭራቅ አሕመድ ከሚታዘዘው ከዳንኤል ክብረት ሰይፍ ማን ይታደጋት የሚለው ነው፡፡ ይህ ትልቅ ጥያቄ ደግሞ ተዋሕዶ የማን ናት የሚለውን ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ ባብዛኛው የተዋሕዶ ታሪክ ስለሆነ፣ ተዋሕዶ የተዋሕዶወች ብቻ ሳትሆን፣ ባገሩ ታሪክ የሚኮራ የሁሉም አገርወዳድ ጦቢያዊ ናት፡፡ በመሆኗም የተዋሕዶ ጉዳይ የሚመለከተው ተዋሕዶወችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አገርወዳድ ጦቢያውያን ነው፡፡ ተዋሕዶ የተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የሆነችውን ያህል፣ የሙስሊሙም፣ የካቶሊኩም፣ የእግዜርቢሱም (atheist)፣ የፖለቲከኛውም፣ የምሁሩም ናት፡፡
ስለዚህም፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ተዋሕዶን ከኦነጋውያን ለመታደግ አመራር መስጠት እማይችልበት ደረጃ ላይ ከሆነ፣ ይልቁንም ደግሞ ራሱ በኦነጋውያን ተበልቶ ተዋሕዶንም ጦቢያንም በኦነጋውያን የሚያስበላ ከሆነ፣ ተዋሕዶን የማዳኑን አመራር አነግን የሚፋለሙ አምራሮች ሊይዙት የግድ ነው፡፡ የኦነጉን መሪ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ማድረግ፣ በተዋሕዶና በጦቢያ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በማስወግድ ባንድ ዲንጋ ሁለት ወፍ ያስመታል፡፡
መስፍን አረጋ