ሊዮን ዘአሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
ዋር ኢዝ ኤ ራኬት በሲሚድሌይ ዲ. በትለር ሜጀር ጀነራል የዩናይትድ ስቴትስ ማሪንስ፣ ኦዲዬ ቡክ / በዩቲዩብ መነባነበ መፅሐፉን ያዳምጡ፤ ሰምተውም ስለ ጦርነት ጋንግስተሮች፣ ጦርነት ሲኦል መሆኑንና ስለ ጦርነት ሚሊየነሮች ትርፍ ሰበኩ፡፡ ጦርነትን መቼም የትም አይደገም!!! (Never and Ever Again) ይበሉ፡፡
ለዶክተር ዳኛቸው አሰፋ፣ ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ለአንዳርጋቸው ፅጌ፣ ወዘተ ለኢትዮጵያ ምሁራን የፍቅር፣ የሠላም እና አንድነት ተሃድሶ ዘመን ያምጣ!!! ‹‹WAR IS A RACKET by Maj. Gen. Smedley D. Butler – FULL AudioBook ������ | Greatest���AudioBooks – YouTube ……………………….(1)
‹‹የኢትዮጵያ ምድር፣ አንቺ የደም ጎዳና፣
መስክሪ አፍ አውጪና፣
የሐገሬ መሬት፣ አንቺ የደም ጎዳና፣
መስክሪ አፍ አውጪና፣
ስንት ወጣት አለቀ፣ስንቱ ደም ፈሰሰ፣
ከቤት ጥዋት ወጥቶ፣መቼ ተመለሰ፣
ወጣት ሽማግሌ፣ደም ያጎረፈብህ፣
ተናገሪ ምድር፣መስክሪ አፍ አውጥተሸ፣
ተናገሪ ምድር፣ በይ መስክሪላቸው
ምሳቸው አለንጋ፣ ጥይት እራታቸው፣
ኖረው ለረገፉት ለእነዚያ ልጆችሽ፡፡›› …………………….(ምኒልክ ወስናቸው ለቀይ ሽብር ሠማዕታት የዘመረላቸው)
ዋር ኢዝ ኤ ራኬት በሜጀር ጀነራል ሲሚድሌይ ዲ. በትለር የዩናይትድ ስቴትስ ማሪንስ፣ በ1935እኤአ የተፃፈች ትንሽ መፅሃፍ ናት፡፡ War Is a Racket (kether.com) PDF ማንበብ ይችላሉ፡፡
ሰንደቅ-ዓላማው ዶላሩን ይከተላል፣ እናም ወታደሮቹ ሰንድቅ ዓላማውን ይከተላሉ!!! ጦርነት በዓለማችን የጥቂት ሰዎች ሚስጢራዊ የንግድ (ቢዝነስ) ሥራ ነው፡፡ ብዙሃኑ ህዝብ ስለ ጦርነቱ ሚስጢር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ጦርነት ጥቂት ሰዎችን ብቻ ሚሊየነሮች ያደርጋቸዋል፡፡ የጦርነት ሚሊየነሮች ዶላር ያሳድዳሉ፣ ወታደሮቹ ሰንደቅ-ዓላማቸውን ይከተላሉ፡፡ ወታደሮቹ ጠላት የተባለውን ያሳድዳሉ፣ (Then the flag follows the dollar and the soldiers follow the flag.) እነዚህ ጥቂት ጦርነት ጠማቂ ፖለቲከኞች የትላንት ያገር ጠላት የሆነውን ዛሬ ወዳጂ ያደርጉታል፡፡ በተቃራኒው የዛሬ ወዳጅ የነበረውን የነገ ጠላት አድርገው ይፈርጁታል፡፡
‹‹ጦርነት ራኬት ነው፡፡ ሁሌም እንደተለመደው ጦርነት እንደ ራኬት ነው፡፡ ጦርነት ጥንታዊና በቀላሉ በጣም ትርፋማ የሚያደርግ የፖለቲከኞች ንግድ ነው፡፡ በእርግጥ በጣም በጨካኔና አረመኔ ድርጊት በመፈጸም በዝርፍያና በነጠቃ፣ የሚገኝ ትርፍ ነው፡፡ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ብቸኛ ክስተት ነው፡፡ ጦርነት ውስጥ ብቸኛው ትርፍ ዶላር የሚዛቅበትና የሰው ህይወት እንደ ቅጠል የሚረግፍበት ትዕይንት ነው፡፡››
‹‹ምን ዓይነት የንግድ ሥርዓት ነው የእኛ የራሽያ ወይም የጀርመን፣ የእንግሊዝ ወይም የፈረንሳይ፣ የጣልያን ወይም ኦስትሪያ፣ የሰው ህይወት በዴሞክራሲ ወይም በንጉሳዊያን አገዛዝ ስር ይሆኑ? ፋሽስቶች ወይም ኮምኒስቶች እንደሆኑ? ዋነኛው ችግራችን የራሳችንን ዴሞክራሲ መጠበቅ ነው፡ በትንሹ፣ ምንም ነገር ቢሆን የሚከናወነው በእርግጠኝነት የአለም አቀፍ ጦርነት የሚከናወነው ጦርነት ሁሉንም ጦርነቶች ለማስቆም ነው፡፡ ››
‹‹የሠላሳ ሦስት ዓመት ከአራት ወራት ወታደራዊ አገልግሎት አበርክቻለሁ፡፡ በሥራ ዘመኔ ቡዙዉን ጊዜዬን ከፍተኛ ጡንቻ ያላቸውን የቢዝነስ ተቆማት ጠብቄለሁ፡ ለዎል ስትሬትና ለባንከሮች የቢዝነስ ተቆማት፡፡ በአጭሩ እኔ ራኬተር ነበርኩኝ፡፡ የካፒታሊዝም ጋንግስተር ነበርኩኝ፡፡››
‹‹በዩናይትድ ስቴትስ የተለመደው የሠላም ጊዜ የቢዝነሶች የትርፍ ህዳግ በመቶኛ ስድስት፣ ስምንት፣ አስር፣ አንዳንዴ አስራሁለት ፐርሰንት ነው፡፡ ነገር ግን በጦርነት ጊዜ ያለ የትርፍ ህዳግ፣ ግን ያ የተለየ ጉዳይ ነው፣ ሃያ ፐርሰንት ፣ ስልሣ ፐርሰንት፣ መቶ ፐርሰንት፣ ሦስት መቶ ፐርሰንት፣ እንዲያውም አንድ ሽህ ስምንት መቶ ፐርስንት ነው፣ ሰማይ ነው ወሰኑ ፡፡››
‹‹ነገር ግን የሞቱት ሰዎች ምንድነው ያተረፉት? የሞቾች እናቶች፣ እህቶች፣ ሚስቶችና ፍቀረኞች ምንድነው ያተረፉት? ልጆቻቸው ምንድነው ያተረፉት? ማንኛውም ሰው ምንድነው ያተረፉት፣ ከጥቂት ሰዎች በስተቀር ለእነሱ ጦርነት ማለት ከፍተኛ ትርፍ ነው? አዎ እና ሐገሪቷ ምንድነው ያተረፈችው? ››
‹‹ ለብዙ አመታት ወታደር እንደመሆኔ፣ጦርነት ራኬት እንደነበረ ጥርጣሬ ነበረኝ፡፡ ጡረታ ወጥቼ የሲቪሊ ህይወት መኖር ከጀመርኩ በኃላ ዋር ኢዝ ራክት መሆኑን በእርግጠኝነት አረጋገጥኩኝ፡፡ አሁን እያየሁ ያለሁት የዓለም አቀፍ የጦርነት ቁልል ዳመናዎች ስብስብን ዛሬ እንደሆነ አድርጌ ፊት ለፊት እጋፈጠዋለሁ እናም ጦርነትን በማውገዝ እናገራለሁ ›› 1935 እኤአ
‹‹ምንያህል ነው የሂሳብ ደረሰኝ? ይሄ ሂሳብ እንዲያ እንዲሆን ማድረግ አስከፊና የሚያሰቅቅ የሂሳብ አያያዝ ሙያ ገጽታን መለወጥ ያሻል፡ አዲስ የመቃብር ድንጋይ ቦታዎች፣ የአካል መጭመቂያ መሳሪያ፣ የተዘጋና የዛጉ ህሊናዎች፣ የተሰባበሩ ልቦች፣ እና ‹ቤት ለእንቦሳ፣ እንቦሳ ሰሮ› የማይሉበት የተዘጉ ቤቶች፡፡ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፡፡ ጣረ- ሞት የሚያንዣብብበት የክፉ ቀን ፅልመት የሰዎች ስቃይ፣ ሰቆቃና ዋይታ የተሰማበት፡፡ ከጦርነቱ በኃላ በሠራተኛው ህዝብ ላይ የተጫነ ወገብ የሚሰብር ግብርና ታክስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል ብሎም ያልፋል፡፡››
‹‹በጦርነት ውስጥ አገሮች ተጨማሪ ግዛቶች ይቆጣጠራሉ፡፡ ድሉን የተቃጁ ከሆነ፣ ግዛቱን ይወስዱታል፡፡ ይሄ በምርኮ የተያዘ ግዛት በጥቂት ሰዎች ይበዘበዛል፡፡ እነዚህ ጥቂት ሰዎች በጦርነቱ ውስጥ ከቆሰሉና ከሞቱ ሰዎች ደም ውስጥ ዶላር ይጨምቃሉ፣ይዘርፋሉ፡፡ በጦርነቱ የምልዕተ ህዝቡ ትከሻ በግብርና ታክስ ይጎብጣል፡፡››
‹‹ስንቶቹ እነዚህ የጦርነት ሚሊዮነሮች ጠመንጃ በትከሻቸው ተሸክመዋል? ምን ያህሉ የጦርነት ሚሊዮነሮች ምሽግ ቆፍረዋል? ምን ያህሎቹ ከዓይጥ መፈልፈያ ጉድጎድ ውስጥ መሽገው ርሃብ ምን ማለት እንደሆነ ተርበው ያውቃሉ? ስንቶቹ የጦርነት ሚሊዮነሮች በእንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን አሳልፈዋል፣ በድቅድቁ ጨለማ በፍርሃት ርደዋል፣ እንደ ዳክያ ጥይትና ቦንብ ታቅፈዋል፣ በቦንብና ሼል ተስፈንጣሪ ቆስለዋል፣ስንቶቹ የጦርነት ሚሊዮነሮች በጦርነቱ ውስጥ ቆሰሉ፣ ወይም ሞቱ?›› …………………………………….(2)
War is just a racket(1935). A racket is best described, I believe, as something that is not what it seems to the majority of people.Only a small inside group knows what it is about. It is conducted for the benefit of the very few at the expense of the masses.
Smedley Butler on Interventionism
— Excerpt from a speech delivered in 1933, by Major General Smedley Butler, USMC.
War is just a racket. A racket is best described, I believe, as something that is not what it seems to the majority of people. Only a small inside group knows what it is about. It is conducted for the benefit of the very few at the expense of the masses.
I believe in adequate defense at the coastline and nothing else. If a nation comes over here to fight, then we’ll fight. The trouble with America is that when the dollar only earns 6 percent over here, then it gets restless and goes overseas to get 100 percent. Then the flag follows the dollar and the soldiers follow the flag.
I wouldn’t go to war again as I have done to protect some lousy investment of the bankers. There are only two things we should fight for. One is the defense of our homes and the other is the Bill of Rights. War for any other reason is simply a racket.
There isn’t a trick in the racketeering bag that the military gang is blind to. It has its “finger men” to point out enemies, its “muscle men” to destroy enemies, its “brain men” to plan war preparations, and a “Big Boss” Super-Nationalistic-Capitalism.
It may seem odd for me, a military man to adopt such a comparison. Truthfulness compels me to. I spent thirty- three years and four months in active military service as a member of this country’s most agile military force, the Marine Corps. I served in all commissioned ranks from Second Lieutenant to Major-General. And during that period, I spent most of my time being a high class muscle- man for Big Business, for Wall Street and for the Bankers. In short, I was a racketeer, a gangster for capitalism.
I suspected I was just part of a racket at the time. Now I am sure of it. Like all the members of the military profession, I never had a thought of my own until I left the service. My mental faculties remained in suspended animation while I obeyed the orders of higher-ups. This is typical with everyone in the military service.
I helped make Mexico, especially Tampico, safe for American oil interests in 1914. I helped make Haiti and Cuba a decent place for the National City Bank boys to collect revenues in. I helped in the raping of half a dozen Central American republics for the benefits of Wall Street. The record of racketeering is long. I helped purify Nicaragua for the international banking house of Brown Brothers in 1909-1912 (where have I heard that name before?). I brought light to the Dominican Republic for American sugar interests in 1916. In China I helped to see to it that Standard Oil went its way unmolested.
During those years, I had, as the boys in the back room would say, a swell racket. Looking back on it, I feel that I could have given Al Capone a few hints. The best he could do was to operate his racket in three districts. I operated on three continents……………….(3)
ምንጭ (tsefa)
- WAR IS A RACKET by Maj. Gen. Smedley D. Butler – FULL AudioBook ������ | Greatest���AudioBooks – YouTube
- Https://Quotepark.Com/Works/War-Is-A-Racket-5894/
- Smedley Butler on Interventionism (fas.org)