የአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በወያኔ በግፍ መፈናቀልን አስመልክቶ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ በሚመለከት የተሰጠ የግል አስተያየት

  በአሌክስ ታየ

የአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በወያኔ በግፍ መፈናቀልን አስመልክቶ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትዬው ነበር፡፡እጅግ በጣም በሳል አስተያየት ነው፡፡እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ የማውቀውንና የሚሰማኝን እንደሚከተለው የተወሰነ ለማለት እፈልጋለሁኝ፡፡በመሰረቱ ድርጊቱ እጅግ አሳፋሪም አሳዛኝም ነው፡፡ይህ የወያኔን እውነተኛ ድብቅ የጥፋት ተልእኮ ገሀድ እያወጣ ያለ ነገር ነው፡፡ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ድርጊቱን ከወያኔ የዘረኝነት ፖለቲካ እና ከዝርፊያ የኢኮኖሚ ኢምፓየር መሰረታዊ ተፈጥሮ ጋር በማያያዝ ወያኔን ዘረኛ ዘራፊ በማለት በሁለት ነገሮች መጥቀሳቸው መሰረታዊ ገሀድ የወጣ ሀቅ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን አንድ የሚቀር እጅግ ወሳኝ ገላጭ ቃል ግን ይቀራል፡፡

ይኸውም ወያኔ የባእዳን ሃይሎች ታማኝ ቅጥረኛ በመሆኑ ቅጥረኛ የሚለው ወሳኝ ሃይለ ቃል የወያኔን እውነተኛ ድብቅ ማንነት (አሁን በእርግጥ ገሀድ እየወጣ ነው) ለመግለፅ እጅግ ትልቅ ትርጉምና ፋይዳ ያለው ነገር ነው፡፡አዎ ወያኔ በአጭሩ ዘረኛ ዘራፊ ቅጥረኛ በሚሉት በሶስት መሰረታዊ ነገሮች ነው ሊገለፅ የሚገባው፡፡አምባገነን የሚለው ቃል ብዙም የወያኔ የተለየ ባህሪ አይደለም ምክንያቱም በአፍሪካም ሆነ በመላው ታዳጊው አለምና የሰለጠነውም አለም አምባገነንነት እንዳለ ይታወቃልና ማለት ነው፡፡ለምሳሌ ደርግ የለየለት አምባገነን ነበር ነገር ግን ደርግ እንደ ወያኔ ዘረኛ ዘራፊ ቅጥረኛ አልነበረም፡፡አምባገነንነት በራሱ የመጥፎ ነገር መገለጫ ብቻ ሆኖ ለመጥፎ ስራ ብቻም ሳይሆን ለጥሩም ስራ ቢሆን መጠቀም ግድ የሚልበት ብዙ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ስለዚህም ወያኔ  አምባገነን ካልሆነ በአስተማማኝ ሁኔታ ዘረኛ ዘራፊ ቅጥረኛ መሆን ስለማይችል ሃይል እየተጠቀመ አምባ-ገነን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው ማለት ነው፡፡መልካም ስራ የሰሩት የጥንት ነገስታቶቻችን ሁሉ አምባገነን ነበሩ፡፡የዓለም ልእለ ሃያል ሀገር አሜሪካም አምባገነን ነች፡፡አባወራ እና እማወራ በሚያስተዳድሩት ቤተሰብ ውስጥም በተወሰነ መንገድ አምባገነን ይሆናሉ ፡፡ዋናው ቁምነገሩ ግን አምባገነንነትን ለጥሩ ወይንስ ለመጥፎ እየተጠቀምንበት ነው የሚለው ነው፡፡ዋናው ቁምነገሩ ግን አምባገነንነትን ሃላፊነት ከመውሰድ ጋር አስተባብረን መያዛችን ነው፡፡እንደዚሁም የአምባገነንነት ተቃራኒ ስለሆነው ዲሞክራሲ ስናስብና ስናወራም ዲሞክራሲ ማለት እንዲያው ዝም ብሎ ሃላፊነትና ግዴታ የሌለበት ዋልጌነት ልቅነትና መረንነት እንደሆነ መረዳትም የለብንም፡፡

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሞራል ዝቅጠት ካሉት ወይንም እኔ አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠት ከምለው ጋር በተያያዘ ወያኔ እየፈጠረልን ያለው የተኮላሸ ትውልድና ማህበረሰብ እጅግ የሚያሳሰብ ነው፡፡አዎ ወያኔ በጫት በአደንዛዥ እፅ በአልኮል በሞኖፖል በተቆጣጠረው ኤፍ-ኤም ሬድዮ ጣቢያ በአውሮፓ እግር ኳስ በመጤ ባህልና በከንቱ የማይረባ ብልጭልጭ ሸቀጥ ነገር ሁሉ ትውልዱን እያኮላሸው እያደነዘዘውና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተው ነው፡፡እንግዲህ ይህ ሁሉ ወያኔ ለሀገራችን ያመጣልን ጠቃሚውን ስርዓት የያዘውን የሰከነ ዲሞክራሲ ሳይሆን ጎጂውንና ሃላፊነትና ግዴታ የሌለበትን የዋልጌነት የልቅነትና የመረንነት ዲሞክራሲን ነው፡፡ወያኔ ይህንን አይነት ትውልድ ገዳይ ጎጂ ዲሞክራሲ ለሀገራችን ያመጣልን ደግሞ እውነተኛውን የሰከነ ስልጡን ዲሞክራሲ ሊሰጠን ስለማይችልና በእውነተኛው የሰከነ ስልጡን ዲሞክራሲ አማካኝነትም ህዝብ የስልጣን ምንጭ ባለቤት ሆኖ ስልጣኑን እንዳይነቀንቀውና እንዳይፈታተነው በሩቆ ለመከላከል አቅዶ ያደረገው ነገር ነው፡፡እንግዲህ ይህ አይነት የሞራል ዝቅጠት ወይንም አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠት እየተፈጠረ ያለው ደግሞ ወያኔ ዝም ብሎ እንደ ደርግ አይነት ባለው ተራ አምባገነን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በከፋ ወያኔ በተፈጥሮው ዘረኛ ዘራፊና ቅጥረኛ ስለሆነ ጭምር ነው፡፡ወያኔ ይህንን የዘረኝነት የቅጥረኝነትና የዘራፊነት ፕሮጀክቱን በዘላቂነትና በአስተማማኝነት ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ የግድ አብዛኛውን ማህበረሰቡንና ትውልዱን የተዝረከረከ የተኮላሸና የማይረባ ምናልባትም ተመስገን ደሳለኝ እንዳለው ምንም አይነት ተገቢው ንቃተ-ህሊና የሌለውና በደመ-ነፍስ የሚንቀሳቀስ ዞምቢ ማድረግ አለበት፡፡ይህ አይነት ትውልድና ማህበረሰብ ሲፈጠር ደግሞ ወያኔ በዚህች ሀገር ላይ የፈለገውን አይነት ነውር ነገር ቢያደርግ በተቃውሞ ሃይ የሚለው ምንም አይነት ተቃዋሚ ሃይል አይኖርም ማለት ነው፡፡

ወያኔ ዘረኛ ዘራፊ ብቻ ሳይሆን ቅጥረኛም ጭምር ነው ስል ወያኔ ይህንን ሁሉ አሳፋሪና አሳዛኝ ነውር በዚህች ሀገር ላይ እያደረገ ያለውና ይህንንም አይነት የሞራል ዝቅጠት ወይንም አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠት እየፈጠረ ያለው ለአንድ መሰረታዊ ምክንያትና ግብ ነው፡፡ይኸውም ወያኔ ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነት የጥፋት ተልእኮ ያነገበ ዘመናዊ የውክልና የእጅ አዙር ቅኝ-ግዛት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ላይ በቅጥረኝነት እየተገበረ ስለሆነ ነው፡፡ዛሬ እነ ስብሀት ነጋ በአደባባይ አማራንና ኦርቶዶክስን ከስልጣን አለያየናቸው የሚለው ነውረኛና ተንኮለኛ አባባል የዚህ ድብቅ ሰይጣናዊ ተልእኮ ማለትም በወያኔ ቅጥረኝነት እየተተገበረ ያለው ዘመናዊ የውክልና የእጅ አዙር ቅኝ-ግዛት መገለጫ ነው፡፡በአማራውና የአማራ እምነት እንደሆነ ተደርጎ በተሳሳተ መንገድ እየተተረጎመና እየቀረበ ባለው ኦርቶዶክስ እምነት ላይ የተከፈተው የረቀቀና የተቀነባበረ የቅጥረኝነት ጥቃትም ዋና መንስኤው የአድዋው ጦርነት ነው፡፡እንደነ ስብሃት ነጋ መለስና ሌሎችም ተመሳሳይ ባንዳ ልሂቃን ወያኔዎች አስተሳሰብ ከሆነ የአማራው ገዥ መደብ ናቸው የተባሉት አፄ ምኒልክም ሆኑ አፄ ሃይለስላሴ በተለይም አፄ ሃይለስላሴ የፋሽስት ኢጣልያን ወረራ መቃወም መመከትና መቀልበስ ሳይሆን የነበረባቸው ለኢጣልያ ወራሪ ቤት ለእንግዳ ብለው ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ውስጥ እንድትወድቅ ማድረግ ነበረባቸው፡፡አፄ ምኒልክ አድዋ ሲዘምቱ እሳቸውና ህዝባቸው የሚያምኑበትን ታቦት አስቀድመው መሆኑና ከዘመቻው ወስልተህ የተገኘህ ማርያምን ምሬም አልምርህ የሚለው ድንቅ የዘመቻ ጥሪና ቅስቀሳ ንግግራቸውና የተገኘውም አኩሪና ፋና ወጊ የአድዋ ድል ለቅኝ-ግዛት የባእዳን ተስፋፊዎች ዋና እንቅፋትና ጠላት አማራና ኦርቶዶክስ እንደሆነ ተደርጎ እንዲሳል ሆነ፡፡ነገር ግን የፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎውና ድሉ የአማራው ገዥ-መደብና የአማራው ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊ የሆነው የትግሬው የኦሮሞው የጉራጌው የደቡቡ ወዘተ ነበር ወደፊትም ይሆናል፡፡ነገር ግን አማራው በባእዳን ተስፋፊ የቅኝ-ግዛት አራማጅ ሃይሎች ዘንድ ቁጥር አንድ የጥቃት ኢላማ የሆነበት ምክንያት የፀረ-ኮሎኒያል ትግሉ ዋና መሪና አስተባባሪ ነው ከሚል የመነጨ ነው፡፡ፋሽስት ጣሊያን ከአድዋው ጦርነት በኋላ ዳግም አርባ አመት ሙሉ ተዘጋጅታ በተቀሩት ቅኝ-ግዛት አስፋፊ አውሮፓውያን ጭምር እየተደገፈችና እየተበረታታች ያደረገቸው ዳግም ወረራም እንደ አድዋው ጦርነት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ባይጠናቀቅም ቅሉ ግን ኢትዮጵያን ዳግም በቅኝ ግዛት ውስጥ የማስተዳደርን አለማና ፍላጎት በፈጣሪ እርዳታ ጭምር የተጨናገፈበትና ኢትዮጵያም ሉአላዊ አንድነቷንና ህልውናዋን እንደገና ለማስከበር የቻለችበት የታሪክ አጋጣሚ ነበር፡፡ይህንን ሁሉ ፈተና አልፋ ኢትዮጵያ ወዲያውኑ ብዙም ሳትቆይ ህልውናዋና ሉአላዊ አንድነቷን ማስቀጠል መቻሏም ብቻ ሳይሆን ለተቀሩት በቅኝ ግዛት ውስጥ ለሚማቅቁት የአፍሪካ ሀገራት የነፃነት አርአያ ሆና የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ጭምር ለመመስረት አንጋፋ ባለድርሻ መሆኗ ፋሽስት ጣሊያንን ብቻም ሳይሆን የተቀሩትን ተስፋፊ አውሮፓውያን በተለይም ከጣሊያን ወረራ መገታት በኋላ ቀጣይ የኢትዮጵያ የሞግዚት አስተዳደር ሆና ለመቀጠል ፍላጎት የነበራትን እንግሊዝን ያስከፋ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡የኤርትራ መገንጠል በዘመነ ደርግ የነበረው የሶማሊያ ጦርነትና ዛሬ በዘመነ ወያኔ እየተተገበረ ያለው በዘር ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምና በኦጋዴን እየተፈጠረ ያለው ቀውስ ሁሉ ከዚህ እነ ጣሊያንና እንግሊዝ አዳፍነውት ከሄዱት መጥፎ እሳት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ስለዚህም እሳቱ ተዳፍኖ ብቻም አልቀረም የሚቀሰቁሰው ሃይል ስላስፈለገ ባእዳን ተስፋፊ የቅኝ-ግዛት አራማጅ ሃይሎች ወይንም ቄሳራውያን ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ አይነት አማራን ብሎም የተቀረውን መላውን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በቂም በቀል ለማጥቃት ለማዳከምና ከተቻለም ለማጥፋት በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ እንደነ ስብሃት ነጋ መለስና ሌሎችንም ባንዳ ወያኔዎችና ሻእብያዎችን በቅጥረኝነት መጠቀምን እንደ ዋና አዋጪ ስልት ተጠቀሙበት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን? - አንዱዓለም ተፈራ - የእስከመቼ አዘጋጅ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሁለት ነገሮችን ማለትም ዘረኛ እና ዘራፊ ብለው ሌላው ሰስተኛው የዘነጉትና ምናልባትም የሁለቱም ዋና መንስኤ ሊሆን የሚችለውን እጅግ ወሳኝ ነገር ቅጥረኛነት የሚለው ነገር ነው፡፡የወያኔንም ሆነ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያዊነትን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ታሪካዊ አደጋ ላይ የጣለው ይህ የባእዳን ሃይሎች ቅጥረኝነት ነው፡፡ወያኔ በዘር በሃይማኖት በፆታ ወዘተ እየከፋፈለ በከፋፍለህ ግዛው ስልት ሀገሪቱን እርስ በርስ እያናከሰና እያተራመሰ ያለው ስልጣን ላይ ለመቆየት ብቻም ሳይሆን ከዚህም በዘለለና በከፋ ከተቻለው ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከምና ከተቻለም በስተመጨረሻ ለመበታተንና በራሱና በቄሳራውያን የቅዠት አለም ውስጥ የፈጠራትን የትግራይ ትግሪኛ ሊፐብሊክን እውን አድርጎ ለመመስረት ካለው የባእዳን ቅጥረኝነት ሰይጣናዊ ተልእኮ የመነጨ ነው፡፡ይህ አይነት በአማራው ላይ እየወሰደ ያለው አይን ያወጣ አስነዋሪ አሳዛኝና አሳፋሪ ስራ ደግሞ ዝም ብሎ ባለማወቅ በግብታዊነት የተደረገ ሳይሆን ሆን ተብሎ ታስቦበት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ብቻም ሳይሆን ከዚያም በላይ ኢላማ ያደረገ ተንኮል ነው፡፡አንደኛው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት አማራውን በዚህ ሰበብ በተለየ ሁኔታ በዘረኝነት እንደተጠቃ አድርጎ ተሰምቶት ወደ አንድ ጎጥና ዋሻ ውስጥ እንዲሰበሰብና እንዲደበቅ አድርጎ ብዙ መስዋእትነት የከፈለለትንና ዋና መለያው የሆነውን ኢትዮጵያዊነቱን ለጠበበው ለአማራነቱ ማንነት አሳልፎ እንዲሸጥ ለማድረግ የቀረበ እጅግ ከባድ ፈተና ነው፡፡ሁለተኛው ምክንያት በእርግጥም ከላይ እንዳልኩት ለዘመናት ጥርስ ከነከሱ ከባእዳን ተስፋፊ ቅኝ-ግዛት ሃይሎች ቂም በቀል ጋር በተያያዘ አማራውንና ኦርቶዶክስን ቁጥር አንድ የበቀልና የጥቃት ኢላማ ማድረጉ ሊድበሰበስ አይገባውም፡፡ስለዚህም ለ3ኛው ታዳጊው አለም የፀረ-ኮሎኒያሊዝም ትግል ዋና ፋና ወጊ አርአያ የሆነችውንና የዘመናት የነፃነት ታሪክ ያላትን ታላቋን ኢትዮጵያን ለመበቀል ለማጥቃትና አዳክሞ ለመበታተን ቅድሚያ አማራንና ኦርቶዶክስን ማጥቃት በባእዳን ሃይሎች እንደ አንድ ትልቅ ፕሮጀከት የተያዘ ነገር ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያልተገታ ምላስ አማራውን ይጎዳዋል አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ሶስተኛው ምክንያት ይህ አይነት በዘር በሃይማኖት በፆታ ወዘተ በከፋፍለህ ግዛው ስልት ከውስጥ የሚፈጠር የእርስ በርስ መናከስ መጋጨትና መለያየት ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ወደ ሀገራዊ መበታተን ፍፃሜ ነው የሚያደርሰው፡፡የቀዝቃዛውን ጦርነት ማክተም ተከትሎ በዩጎዝላቭያ በሶማሊያ በሩዋንዳ በኢራቅ በሱዳን በሊቢያ በናይጄርያ በሶርያ ወዘተ ተፈጥረው የነበሩና በቀጣይም እየተፈጠሩም ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች ተገቢው አስተዋይ ሀገር በቀል ጥንቃቄና መፍትሄ ካልተሰጣቸው በስተቀር ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ወደ ሀገራዊ የመበታተን ፍፃሜ ነው የሚያደርሱት፡፡ወያኔ ላለፉት 22 ዓመታትና አሁንም ሆነኝ ብሎ አስቦበት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እያደረገ ያለው ይህ አይነት እርስ በርስ ማናከስ ማጋጨትና ሲከፋም አማራውንና ሌላውንም ዘር እየለየ የማፈናቀል አሳፋሪና አሳዛኝ ተግባር ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ሁኔታዎች ወደዚህ አይነት ሀገራዊ የመበታተን ፍፃሜ  እንዲያመሩ ለማድረግ የታለመ ስልት ነው፡፡ወያኔ አማራውን ክልልህ አይደለም ውጣ ሲል ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ በወያኔ ስርዓት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለየ የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ የሆነውና ከክልሉ ውጪ ከፍተኛ ሀብትና ንብረት ያፈራው የትግሪኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ የወደፊት እጣ ፈንታው ምን ሊሆን ነው እረ?ወያኔ ይህ እንደሚመጣ ጠፍቶት ነው?ፈፅሞ አይጠፋውም ነገር ግን የወያኔ ዋና 3ኛ መገለጫ የሆነው የባእዳን ቅጥረኝነት መዘዙና ፍፃሜው የግድ ይህንን አይነት አደገኛና ቆሻሻ ስራ እንዲሰራ ግድ የሚለው ስለሆነና በዚህም በአማራውና በሌላውም ላይ በሚፈፅመው ግፍና ወንጀል ተባባሪ ነው ተብሎ ከሚታሰበው ከትግራይ ማህበረሰብ ጋር በሚያስከትለው ትውልድ ተሻጋሪ የማይታረቅ ቅራኔ መናከስ ቂም በቀልና ግጨት የተነሳ ይህንን እንደ ዋነኛ ምክንያትና ሰበብ በመጠቀም ነገ ከነገ ወዲያ ወያኔ የራሱን እና የቄሳራውያንን የዘወትር ህልም የሆነውን የትግራይ ትግሪኛ ሊፐብሊክን ለመመስረትና እውን ለማድረግ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው፡፡ማለትም የዚህ የወያኔ ተንኮል መጨረሻው የትግራይን ማህበረሰብ ይህ ሁሉ ወንጀል ተፈፅሞ ከዚህ በኋላ ከአማራውና ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዴት አብረን በጋራ መኖር እንችላለን ነገ ከነገ ወዲያ ውሎ አድሮ አማራውም ሆነ ሌላው የተጠቃው ኢትዮጵያዊ ዝም ብሎ አይቀመጥም ይህንን ሁሉ ወንጀልና ግፍ ይበቀላል ስለዚህም ትግራይ እንደ ኤርትራ መገንጠል አለባት ወደሚል ድምዳሜ ለማምጣት ማለት ነው፡፡ለዚህም ነው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት የወያኔ አደገኛና ሰይጣናዊ ስርዓት ችላ እየተባለ ይበልጥ ስልጣን ላይ በቆየ ቁጥር በቀላሉ ሊስተካከልና ሊመለስ የማይችል ብዙ ትውልድ ተሻጋሪ ጥፋትና ቀውስ እየፈፀመ ወደፊት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል የሚሉት ነገር ምንም የማያከራክር የሚሆነው፡፡አሁን በአማራው ላይ እያነጣጠረ ያለው ጥቃት ፈተናውና መዘዙ ለአማራውም ብቻ ሳይሆን ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ለራሱ ለትግሬውም ጭምር ነው የሚሆነው፡፡

ወያኔ ደግሞ ይህንን ሁሉ ፀረ-አማራ ብቻም ሳይሆን ከዚህም በከፋ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ሰይጣናዊ ተልእኮ ስራ የሚሰራው ዘረኛና ዘራፊ ብቻ ስለሆነ ሳይሆን ከዚህም በከፋ ቅጥረኛ ጭምር ስለሆነ ነው፡፡አማራውንና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ቁጥር አንድ ኢላማ አድርጎ የማጥቃት የማዳከምና ከተቻለም በሂደት የማጥፋት የወያኔ እና የቄሳራውያን አለቆቹ ሰይጣናዊ የጥፋት ተልእኮ ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ በሂደት ዋናውንና ታሪካዊውን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማጥቃት የማዳከምና ከተቻለም በሂደት የማጥፋት ሰይጣናዊ የጥፋት ተልእኮ ዋና አካል ነው፡፡ስለዚህም ዛሬ በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው የጥቃት ኢላማ ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ማነሽ ባለ ሳምንት እያለ የተቀረውን የኦሮሞውን የጉራጌውን የጋምቤላውን ወዘተ ቤት በየተራ የሚያንኳኳ ነው የሚሆነው፡፡ስለዚህም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት ኢትዮጵያዊነትን እንደ ዋነኛ ቁጥር አንድ ተቀዳሚ አይዲኦሎጂ አድርጎ መቀበልና ይህንንም ኢትዮጵያዊነት በቀናኢነትና በቆራጥነት ማራመድ ከገባንበት የዘመኑ ጥልቅና ሰፊ ዘርፈ ብዙ ችግር እንደ ዋነኛ የመጀመሪያ መውጫ ቀዳዳ መፍትሄ ነው የሚሆነውና ኢትዮጵያዊነትን አጥብቆ መያዝ ዋነኛ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡ስለዚህም የደፈረሰው እስኪጠራ እውነቱም እስኪገለጥ ድረስ ለጊዜው ያሉንን ልዩነቶች አክብርንና አቻችለን ለጊዜው ወደጎን አስቀምጠን ነገር ግን ፖለቲካችን ዲሞክራሲያችን ኢኮኖሚያችን ሃይማኖታችን ባህላችን ብሄራችን ወዘተ ቅድሚያ የተገለጠ እውነት ለሆነውና ለዘመናት ለቆየው ነገር ግን ታሪካዊ ፈተናና አደጋ ላይ የወደቀው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ይሁን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሚናወቻቸውን የተለዋወጡት አቡነ ኤርምያስና አቶ ታየ ደንድአ

አምባገነንነት ለጊዜው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከጥፋት የሚታደግ ጊዚያዊ የመፍትሄ አማራጭም ከሆነ ለጥፋት ከሚሆን ከውሸት የምርጫ ዲሞክራሲ ይልቅ አምባገነንት የተሻለ ነውና ማንኛውንም ሞራላዊና ተገቢ አካሄድና አማራጭ ተጠቅሞ ይህችን ሀገር ከወያኔ ሰይጣናዊ መንጋጋ አላቆ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን እያንዣበበ ካለው የጥፋት አደጋ የሚታደግ ማንኛውም ቆራጥና ቀናኢ ሃይል  ስልጣን ላይ ቢወጣ እኔ በግሌ ደጋፊ ነኝ፡፡ ሌላው ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ወያኔን ከገለፁበት ዝርፊያ የሚለው ቃል መረዳት ያለብን ይህ አይን ያወጣ የዝርፊያ ተግባር ወያኔ ከሚከተለውና ከሚያራምደው የኢኮኖሚ ስርዓትና በቅጥረኝነት ከሚያስፋፅመው ፕሮጀክት የመነጨ ጭምር ነው፡፡ስለዚህም ወያኔ ዝም ብሎ የተለመደው አይነት አምባገነን ወይንም ዘረኛ እና ቅጥረኛ ብቻ ሆኖ አይደለም የቀረው በተጨማሪም የኢትዮጵያን ህዝብ አንጡራ ሀብት እንደዚሁም የሚያስፈፅመውን የቅጥረኝነት ፕሮጀከት ማስፋፀሚያ እንዲረዳው ከውጪ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም በገፍ የሚቀበለውን እርዳታና ብድርን ጭምር እየመዘበረና እየዘረፈ እራሱ በፈጠረው የዘረኝነት ሰንሰለት ውስጥ ኢፈርት የተባለውን ትልቅ የኢኮኖሚ ኢምፓየር ለመመስረት የቻለ ስርዓት ጭምር ነው፡፡ለዚህም ነው በተደጋጋሚ እንደምናገረው ወያኔ ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት የጥፋት ተልእኮ ያነገበ የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀከት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እያስፋፀመ ያለ ዘረኛና ዘራፊ የሆነ የባእዳን ቅጥረኛ ነው የምለው፡፡ኢፈርት ወያኔ ወይንም ሌሎች እያወሩት ያለው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መገለጫ ሳይሆን በተቃራኒው ያለው የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀከት መገለጫ ነው፡፡ኒዎ-ሊበራሊዝም ማለት በአጭሩ በቀለለ አባባል ኪራይ ሰብሳቢነት ወይንም ሙስና እየተባለ የሚድበሰበሰው ነገር ግን በግልፅ አባባል የረቀቀና የተቀነባበረ ዘመናዊ ዝርፊያ ማለት ወይንም ድህነትን ለማጥፋት ድሆችን ማጥፋት የሚል ፖሊሲ የሚከተል የዘመናችን የኢኮኖሚ ስርዓት መገለጫ ነው፡፡ኒዎ-ሊበራሊዝም ማለት በአጭሩ በቀለለ አባባል  ከእለት ወደ እለት ብዙሃኑን ህዝብ እያቆረቆዘና እያደኸየ የምድር ገሀነም ውስጥ እየከተተ በተቃራኒው ደግሞ ጥቂቶችን እያደለበና እያበለፅገ የምድር ገነት ውስጥ እየከተተ ያለ የዘመናችን አለም አቀፍ ስርዓት መገለጫ ነው፡፡

ወያኔም አንድ ጊዜ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሌላ ጊዜ ደግሞ ልማታዊ መንግስት እያለ ያምታታ እንጂ ላለፉት 22 ዓመታትና አሁንም በቀጣይነት በተግባር በሀገራችን እየተከተለና እያራመደ ያለው ይህንን ኒዎ-ሊበራሊዝም ስርዓት ነው፡፡መቼም የኢኮኖሚክስ ዋና ባለሙያ ለሆኑት ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ማስረዳት ለቀባሪው አረዱት አይነት ነው የሚሆነው፡፡ነገር ግን ስለ አምባገነንነትና ስለዲሞክራሲ ብዙ የሚያወሩት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአለም አቀፉንም ሆነ የወያኔን የኢኮኖሚ ስርዓት በድፍረትና በግልፅነት እውነታውን ተከትለው ሙያዊ ማብራሪያ ሲሰጡ ማየት አልተለመደም፡፡እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት የሌለው ህዝብ እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት ሊጎናፀፍ አይችልም፡፡እንደዚሁም እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት የሌለው ህዝብ እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት ሊጎናፀፍ አይችልም፡፡ስለዚህም ውስጣዊው እምነትና ውጪያዊው ምግባር እንደማይነጣጠሉና ውስጣዊው እምነት ውጪያዊው ምግባር እንደሚገለፀው ሁሉ እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት እና እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ነገር ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞችና ምሁራን ልሂቃን ከምርጫ ዲሞክራሲና ይህንንም ተከትሎ ከሚመጣው ከፈጣን ሎተሪ ስልጣን ጋር በተያያዘ ፖለቲካውን ብቻ በማየት ዲሞክራሲ አምባገነን ነፃ-ፕሬስ ሰብዓዊ መብት ወዘተ እያሉ ከመጮህ ውጪ የኢኮኖሚ ስርዓቱን በጥልቀትና በስፋት በጥሞና ለማየት አልቻሉም፡፡በዚህ የተነሳም በአንድ በኩል ወያኔን ስልጣን በምርጫ የማይለቀው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚከተል ስርዓት ስለሆነ ነው ይሉና በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ በዘረኝነት ላይ ተምርኩዞ በዝርፊያ ኢ-ፍትሃዊና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የመሰረተውን ኢፈርት የተባለ ትልቅ የኢኮኖሚ አምፓየር ከዚህ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከሚባል ጋር ለማስማማት ሲቸገሩ ይታያል፡፡

ይህ ሁሉ በጥራዝ-ነጠቅ አስተሳሰብ ስለምንመራና በወያኔ ላይ ብቻ ስላተኮርንና ወያኔ በቅጥረኛነት ከበስተጀርባ እያራመደው ያለውን  የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀከት በጥልቀትና በስፋት ስላልተረዳነው ነው፡፡

ኢፈርትን እያሰብንም ወያኔ ዝም ብሎ ተራ አምባገነን ወይንም ዘረኛ ብቻም ሳይሆን ዘራፊ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ከሁሉም የከፋው ግን ወያኔ ቅጥረኛ መሆኑ ነው፡፡በአማራውም ላይ እየደረሰ ያለውም ጥቃት ዋነኛው ምንጩ የወያኔ ቅጥረኝነቱ ነው፡፡ስለዚህም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወያኔ ዘረኛና ዘራፊ ነው ብለው የወያኔን ተፈጥሯዊ ባህሪና ማንነት ለመግለፅ ሁለቱን ብቻ መናገርዎ ጥሩ ቢሆንም ቅሉ ግን በራሱ በቂ አይደለምና ስለዚህም ወያኔ ከዚህም በከፋ የባእዳን ቅጥረኛ ነው የሚለው ይጨመርበት፡፡

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

2 Comments

  1. Dear Alex, I agree with most of your comments regarding woyane and the ongoing slaughter against the Amharic speaking Ethiopians. However as most opinions we read on various articles by the Diaspora educated elite, yours also missed one important issue that Dr Berhanu and some prominent members in his group waged a relentless campaign against Adwa/Maichew and Emperor menilik inorder to show their support of OLF. It is on public record. Therefore when you or everyone for that matter oppose any thing anti Ethiopian it should be in a consistent manner. Selective outrage won’t take us anywhere.

  2. Berhanu is the last person to talk about the atrocities of Amharas. In his relentless press release he was attacking Amharas, it is hard to forget some of his comments like “yAmara chequagni abarerea y Tegrean chequagni langese alfelegm” this was his low graded comment on Amhara on most meetings prepared as a guest speaker. He is the very few who has benfited from the system and would have given up all his benfits if he was serious. The guy was a close associate of Melse, Berket, Seye and his words should not be taken seriously.

Comments are closed.

Share