አንድ አጭር ጥያቄ ለፍትህ ምኒስትሩ ለዶከተር ጌድዮን ጢሞትዮስ

Gedion Timotheos

የፍትህ ምኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የመንግስት ባለስልጣን ከመሆኑ ጥቂት ቀደም ብሎ  በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን አስፍሮ  ነበር።

በፖለቲካ ውሳኔ፣ ለፖለቲካ  አላማ ክስ ይመሰረታል።  በፖለቲካ ውሳኔ፣ለፖለቲካ አላማ ክስ ይቋረጣል።  ስልጣንን ለመጠበቅ ሰዎች ይታሰራሉ፣ ስልጣንን ለማቆየት ደግሞ ይፈታሉ። ሕግ  ሙሉ  በሙሉ በፖለቲካ ሞግዚትነት ስር በሚያድርበት ሀገር፣  ሕግ  ለሃቅና ለፍትህ ባዳ ሆኖ  በፍርድ አደባባይ  ሸፍጥ ይገናል።  ለማንኛውም፣  ፓርላማ ልናያቸው  ሲገባ ዘብጥያ የከረሙት  ሊፈቱ  መሆኑ  ደስ ይላል።   ሆኖም “የፍትህ”  ስርዓቱ ፈርሶ  ካልተሰራ  ይሄው በፖለቲከኞች ፈቃድ የ ማሰርና የመፍታት ዑደት ይቀጥላል 

ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ዛሬ ላይ ቆሞ፣ ላለፉት ሶስት አመታት፣ እሱ ከጠቅላይ ዓቃቤ እስከ አሁን ካለበት የፍትህ ምኒስቴር፣ መአዛ አሸናፊ ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ሆና በመምራት ላይ ያሉት ተቋማት የሚያስተዳድሩት ስርዓት፣ ‘ፈርሶ የተሰራ’ የፍትህ ስርዓት ነው ብሎ ያምናል? ወይንስ ፈረንሳዮች እንደሚሉት “plus ça change, plus c’est la même chose  በግርድፉ ‘ነገሮች የተለወጡ በመሰሉ ቁጥር እንዳሉ ይቆያሉ”  ነው?

አበጋዝ ወንድሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

mekonen 2
Previous Story

እንበል…( መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ )

280806060 587901019567824 2869604625930085400 n
Next Story

በዘመነ ካሤ ላይ ተኩስ ተከፍቷል!!

Go toTop