April 1, 2013
11 mins read

አዜብ እርግጫሽ አልበዛም?

ይነጋል በላቸው

ከሰሞነኛ አስቂኝ ዜናዎችና ሀተታዎች አንዱ የወይዘሮ አዜብ ድህነት ነው፡፡ ‹ባለቤቴ መለስ የባንክ ደብተር ያልነበረው፣ ቤተሰቡን በአራት ሺህ ብር ገቢ ብቻ በችጋር የሚቆላ፣ መላ ሕይወቱን ለእናት ድርጅቱ ለሕወሓትና ለኢትዮጵያ ሲል መስዋዕት ያደረገ …› እያለች ታወራለች አሉ፤ ‹ወጣ ብሎ በትርፍ ሰዓት እያስተማረ እንዳይደግፈን የፀጥታው ሁኔታ አላመቸውም› ብላ አለመጨመሯም እርሷው ሆና ነው – ‹የመለስ አንጎል በበማርኬት ጨረታ በሚሊዮን የሚገመት ሸያጭ ያወጣል› ስትል ቅንጣት ያላፈረች ወራዳ ሴት እኮ ናት፡፡ እኔም ሰው አገኘሁ ብዬ ስለርሷ ጊዜየን ማጥፋቴ እየከነከነኝ ነውአ- አሁን፤ ልፋ ያለው እንዲሉ ነው፡፡ ቀደም ሲልም ‹መለስ ጥሎብኝ የሄደውን የጋራ ልጆቻችንን በማሳደግ እፈተናለሁ› ብላ ነበር አሉ፡፡ የማትለው ነገር የለም ይባላል ይቺ የጉድ ተራራ – ሦስተኛይቱ ዮዲት ጉዲት፡፡
የውሸታም ልጅ ውሸታም ነው መቼም፤ የቀዳዳው መለስ አባትም – አጥንቱን መሬት አትመቸውና – ያ ዜናዊ የሚሉት የሀገር ነቀርሣ – ‹ ልጄ መለስ የገንዘብን ትርጉም አያውቅም፡፡ የዐሥር ብርን ኖት ከአምስት ብር ለይቶ አያውቅም፡፡…› ብሎ ነበር በ97 አካባቢ ለአንድ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ፡፡
የተረገመ ቤተሰብ እርግማኑ ሁለንተናዊ ነው፡፡ እነዚህ የባንዳ ልጆች – መለስም አዜብም ውሸታሞችና ልቅ አፎች ናቸው – ለከት ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውም፤ ግን ግን እስኪ አስቡት – ኃጢያታችን እንዴት ቢከፋ ይሆን ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል ሀገር የሚመራ ደህና ሰው ጠፍቶ ለነዚህ አጋንንት አሳልፎ የሰጠን አያቷ ደጃች ጎላ የዳጃማችነት ሹመቱን ከጣሊያን በባንዳነት እንዳገኙት ሰምቻለሁ፡፡ የመለስ አባትም ሚስት እንኳ እንዳያገኝ አገር በሤራ የረገመው ከሃዲ ባንዳ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ ከእነዚህ እርጉማን ምንም ዓይነት መልካም ነገር እንደማይጠበቅ ግልጽ ነው፡፡
የአሁኑ የአዜብ እርግጫ ግን በዛ፤ ሆዴን ቀበተተኝ፡፡ ይቺ ደደብ! አላውቃትምና ነው?
እዚያ ድንጋይ ማምረቻ የሚባል የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በምትማርበት ጊዜ የሆነቸውን የማላውቅ መሰላት ይሆን? እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ኮርስ ኤፍ ታመጣለች አሉ፡፡ መምህሩንም ትምህርቱንም ጊዜውንም አውቀዋለሁ፡፡ የምናገረው ግን በደፈናው ነው ፤ ስለብዙ ምክንያት፡፡ እናላችሁ – መምህሩ በክፍል ኃላፊው ይጠየቅና ውጤቷን አስተካክላት ይባላል፡፡ እሱ ግን ‹እምቢዬው! በህጉ መሠረት ያገኘችውን አስቀምጫለሁ› ይላል፡፡ ያኔ ጉዳዩ ወደበላይ ካድሬ ይሄድና ፕሬዚደንቱ ቢሮ ተጠርቶ በማስፈራሪያ መልክ እንዲያስተካክል ይነገረዋል – የዚህችን ደደብ ሴትዮ ውጤት፡፡ ያ ጀግና መምህር ግን ወይ ፍንክች!
‹አንተን ፈርተንህ ሳይሆን አክብረንህ ነው እንድታስተካክልላት የምንጠይቅህ፤ እንጂ እኛ ራሳችን…› እያሉ ሊያግባቡት ቢሞክሩ ‹እናንተ የፈለጋችሁትን ማድረግ ከቻላችሁ ለምን ታስቸግሩኛላችሁ › በማለት የቢሯቸውን በር አጋጭቶላቸው ይወጣና ወደሥራው ይሄዳል፡፡ እምቢ ማለቱን ሲረዱ ኤ ይሁን ቢ ሰጥተው ይገላገላሉ – የጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ኤፍ ከምታመጣ እንጠጦጦ በዶሮ ይታረስ ብለው አሻሯትና በግሩም ውጤት ተመረቀች – ማን አትሉም ይቺው ሦስተኛዋ ዮዲት ጉዲት አዜብ ጎላ!
ይቺ እንደኛው ለጉድ የፈጠራት አዜብ የጊዮርጊስን መገበሪያ እንደበላ ሰው አሁንም ልፍለፋዋን አልተወችም፡፡ ምን ይደረግልኝ እያለች እንደሆነ አልገባኝም፡፡ ሰይጣን የሰጣትን ሲሳይ አርፋ አትጎሰጉስም?
በአራት ሺ ስድስት መቶ ብር እንኳን እርሷ እኔም አልኖርኩ፡፡ ልብ አድርጉ – መኪና የለኝም ፤ የረባ ቤት የለኝም – ያማረኝን ቀርቶ መለስተኛ የምግብ ፍጆታ እንኳ ላሟላ አልተቻለኝም – ልብስም ለሳልቫጅ እንኳ አልበቃሁም አይደለም ላስቀድድ፣ ልጆቼን የማስተምረው በመንግሥት ትምህርት ቤት ነው – ቁጠባ የለኝም – ለመታከሚያም ሆነ ለአደጋ ጊዜ መጠባቂያ የሚሆን የለኝም፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ በማገኘው አራት ሺህ ብር አካባቢ ማድረግ የምችለው የቤተሰቤን ሕይወት እንደምንም ከወር እወር ማቆየት ነው፡፡ ጤፍ በኩንታል 1800 ብር፣ ጋዝ በሊትር 15 ብር፣ ክክ ምሥር በኪሎ 30 ብር፣ … ስንቱን ተናግሬ እዘልቀዋለሁ፡፡ ዛሬ አንድ ሺ ብር ማለት የዱሮው ዘመን አምስት ብር ማለት ነው ፤ አዜብ በሃያ ብር እየኖርን ነበር ካለች ከቀዳዳም የመጨረሻዋ መለኪያ የማይገኝላት ቀዳዳ ናት ማለት ነው፡፡ እባካችሁ ጥቂት አእምሮ ያላችሁ ወያኔዎች ምከሯትና ከሀፍረት ዳኑ፡፡ ሀፍረቱ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ይበልጡን የእናንተ የወያኔዎቹ ነው፡፡ ቦሌ ፋንቱ ሱፐርማርኬት በወር ከ400ሺ ብር በላይ ወጪ እያደረገች(ስለማውቅ ነው) ለቤተ መንግሥት አስቤዛ ታደርግ የነበረችው አዜብ በብር አራት ሺ ደመወዛቸው ነበርን? ልቅ አፍ!
እንዴ? ምነው? በዚች በቀላል ነገርማ አትሸወዱ፡፡ በመቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ብርና ልዩ ልዩ የማይመረመር የሀብት ምንጭ ባለቤት የሆነው ኤፈርት ኃላፊ እንዲህ ድሃ ከሆነች እኔ ምን ልበል? ለምን የሰይጣንን ዐይን ትጠነቁላለች? ይህን ያህል ገና ያልተወለደን ልጅ ሳይቀር በሣቅ የሚገድል ውሸት መናገሩ ለምን አስፈለገ? ገንዘቤ ተበላ፣ ባከነ፣ ተመዘበረብኝ ብሎ የጠየቀስ አለ ወይ? ቀልድ ሲበዛ ይመራል፡፡ ወያኔዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋገሩበትና የእርምት እርምጃ ውሰዱ – ቢያንስ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ደደቢቱ ሴትዮ ዝም ትበል፡፡ ሥልጣኑን እኛ ግዴለንም – ግድ ቢኖረንም ለጊዜው ምንም ማድረግ አንችልም – ዕድሉ ካለ የፖሊት ቢሮ አባልም አይደለም እንደሚወራላት የአዲስ አበባ ከንቲባነቱን(የወልቃይትንም መርቁላት ከፈለጋችሁ) ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩነቱን፣ ፕሬዝደንትነቱን፣ ምክትል የሥልጣን ቦታዎቹንና የፓትርያርክነቱን ቦታ ጭምር ሁሉ ጠቅልላ ብትይዘው ሃሳቡ የሚበላው ሰው የለም፤ አዎ – ስጧትና ይለፍላት፡፡ የሥልጣን በሽታ ለያዘው ሰው የሚፈልገውን ሰጥቶ መገላገልና ውሸትን በየደቂቃው መቃም ነው፡፡ አንዴውኑ በሰይጣን ግዛት ሥር መግባታችንን ስለምናውቀውና ድምጻችን ብቻ ሳይሆን ሰው የመሆናችን ጨምሮ መላው መብታችን በዓሣሞችና በቀን ጅቦች እየተረመረመ ስለሆነ ለጊዜው ግዴለም፡፡ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ መስበሩ ዛሬ አልተጀመረም፡፡ ይህን ነጭ ውሸቷን ግን ግዴላችሁም በረድ ታድርገው፡፡ ከሚያመጣላት ክብርና ሕዝባዊ አመኔታ ይልቅ የሚያመጣባት ውርደትና ሳቅ ስላቅ ይበልጣል፡፡ ጤንነቷን የሚጠራጠር ወገንም ይበዛል፡፡ ይህ ደግሞ እዚያው ወያኔ ጉያ ውስጥ ይጀምራል፡፡ እርግጠኛ ነኝ በዚህ ወሬ ብዙ ወያኔዎች አንገታቸውን መድፋታቸውና ማፈራቸው አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ብታንስም ትንሽዬ ኅሊና ቢጤ ትኖራቸዋለች – ቢያንስ የአዜብን ገደብ ያለፈ ውሸት ልትታዘብ የምትችል፡፡ ውሸት እኮ ልክ አለው፡፡ ልኩን ሲያልፍ — እኔ እንጃ ብቻ …

Latest from Blog

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

Go toTop