ከአስረስ
የአማራ ህዝብ በታሪክ ለብዙ ዘመናት ሌላውን ኢትዮጵያዊ ወንድሙን በማስተባበር ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ እና ሃብቷን ሊዘርፉ ከመጡ ዘራፊዎች ጠብቆ አቆይቷታል። ነገር ግን አለም ሰላም በሆነችበት ባሁኑ ወቅት ሁሉም የአፍሪካ እና በተለያዩ የአለም ክፍል ያሉ ሃገራት ሃብታቸውን ሊዘርፉ ከመጡ ዎራሪዎች ነጻ ወጥተው የነጻነት አየርን እየተነፈሱ እድገታቸውን በሚያፋጥኑበት ግዜ ምስኪኑ አማራ በጠባቦቹና በዘረኞቹ ህውሃቶች ላለፉት የ22 አመታት በጭቆና እና በአፓርታይድ አገዛዝ ስር ሲርገጥ ቆይቷል። አማራው ለሃገር ነጻነት ክልሌ ምኔ ሳይል ታግሎ ታግሎ ባሁኑ ዎቅት አለም በትብብር በምትሰራበት ዎቅት አማራ ተነጥሎ መገለሉ ፣ በበደሉ እና መገደሉ : ያስቆጫል ፣ ያንገበግባል!!
ጠባቦቹና በዘረኞቹ ህውሃቶች ላለፉት የ22 አመታት አገዛዛቸው የአማራን ህዝብ ነጥለው በጥይት በማሳደድ ፣ በመግደል ፣ በማፈናቀል ፣ አማራ የተባለን በሙሉ አስነዋሪ ስድቦችን በመሳደብ ፣ እንዲሁም በትምህርት ወደ ኋላ እንዲቀር በማድረግ እንደፈለጉ ሲጫወቱበት ኖረዋል። አሁን በቅርቡ እንኳ ከቤኒሻንጉል እና ከደቡብ ከ ዘጠና ሺ በላይ አማራዎችን በማፈናቀል እና በመግደል እነሱ የተፈናቀሉበትን የደቡብ እና የቤኒሻንጉል መሬት ለአረቦችና ለራሳቸው ማለትም ለህውሃት ባለሃብቶች እየሰጡት ይገኛሉ።
በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን የእርሻ መሬትም ለሱዳን በመስጠት የተረፈውንም የህውሃት ባለሃብቶች እየተቀራመቱት ይገኛሉ። ባጭሩ የአማራው ህዝብ በሃገር አንድነት ስም እየተጃጃለ ላለፉት 22 አመታት በዝምታ መኖሩ የትግራዩን ህውሃት ጠቀመ እንጂ አማራውን ከመሰደድ እና ከመሞት በስተቀር ምንም ሲጠቅመው አላየንም:: ከዚህ በኋላ ግን እኛ የአማራ ዎጣቶች ተሰባስበን ለህዝባችን ልንደርስለት እንዲሁም ህውሃትን በቃህ ልንለው ተዘጋጅተናል:: አማራ አህያ ነው ፣ ሸንታም ነው ፣ አማራን ቀብረነሃል ፣ ወደፊትም እንዳትነሳ አድርገን እንቀብርሃለን ያሉንን ህውሃቶች እንደማንረሳቸው ለማሳየት እኛ የአማራ ዎጣቶች በተግባር ማሳየት አለብን። በተለይ ተማርን የተባልን የአማራ ተዎላጆች ወገናችን እዚህ ድረስ ለውርደት ሲጋለጥ ሊቆጨን ሊያንገበግበን ይገባል!!
እኛ ከትግራይ ህዝብ ጋር ወንድማዊ ፍቅር እንጂ ጥቅም እንዳላስተሳሰረን ህውሃቶች በደንብ ሊያውቁት ይገባል:: ቡናው ፣ ማሩ ፣ ጤፉ ፣ የኢንዱስትሪ ምርቱ ዎይስ ምኑ እንዳይቀርብን ነው የምንለማመጣቸው? በቃን! በቃን! በቃን! እንዴ በህዝብ ቁጥር ባራት እና ባምስት እጥፍ ከኛ የሚያንሱ ለቁጥር የሚያታክት ድርጂቶችን ያቀፈውን የEFORT ባለቤት ሲሆኑ የአማራው ህዝብ ግን እስካሁን ባዶ እግሩን እየኳተነ ይገኛል። አሁን ግን በቃን ልንታገል ይገባናል:: ትግላች የፈጀውን ግዜ ይፍጅ እንጂ ከህውሃት የአፓርታይድ አገዛዝ ነጻ ልንዎጣ ይገባናል:: ለነጻነታችን እና ለህዝባችን ስንታገል ልንረሳው የማይገባ ነገር ደንቆሮው ህውሃት በአማራው ላይ እንዳደረገው እና እያደረገ እንዳለው ማለትም አንድን ህዝብ እንደ ህዝብ በጨቋኝነት እና በጠላትነት በመፈረጅ ሳይሆን ጠላታችን ህውሃት ብቻ እንጂ የትግራይን ህዝብ እንደህዝብ እንዳልሆነ የማያወላውል አቋም በመያዝ ሊሆን ይገባል::
ህውሃት ጠባብነቱን እና ስግብግብነቱን ትቶ ፍትሃዊ የሃብት የስልጣን ክፍፍል ሊያደርግ እንደማይፈልግ በግልጽ ነግሮናል ስለዚህ አላማችን ምን መሆን አለበት? ዝም ብሎ መሞት : መፈናቀል : የበይ ተመልካች መሆን : መሰደድ ዎይስ ህዝባችን ነጻ እንዲዎጣ እና የሃብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ተደራጂቶ መታገል? የኔ ሃሳብ ይሄ ነው 1 መደራጀት መደራጀት መደራጀት መተባበር መተባበር ልክ እንደ ሙስሊም ዎንድሞቻችን 2 ጣላታችን በግለሰብ ደረጃ ለይቶ ማዎቅ እና ያንን ግለሰብ በሁለገብ ትግል መታገል ላምሳሌ ከብዙዎቹ አንዱ እና ዋናው መሰሪ በቁም ያለው የአማራው ህዝብ ጠላት ሽማግሌው ስብሃት ነጋ እንደሆን በማያሻማ ሁኔታ አምኖ ግለሰቡን መታገል::
በመጨረሻ በአውሮፓ የምንገኝ የአማራ ተዎላጆች የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ (Amhara Youth Movement) የተሰኘ ህብረት በመመስረት “Save Amhara” “አማራን ከሞት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል ከሙስሊም ወንድሞቻችን የቀሰምነውን የትግል ስልት ለመጀመር እየተንቀሳቀስን ሰለሆነ ሃሳባችን የምትደግፉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ድምጻችሁን በያላችሁበት ሃገር እና በየትኛውም መድረክ (በተቃዋሚዎችም ሆነ በዎያኔ ስብሰባ) “አማራን ከሞት እንታደግ” የሚል ጥሪ እንድናሰማ እጠይቃለሁ::
አማን ያሰንብተን
ድል ለጭቁኑ ለአማራ ህዝብ!!
አማራን እንታደግ (Save Amhara)!!
Latest from Blog
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !
ዘመነ ካሴ በድሮን በቤተሰቡ ላይ ስለደረሰው ጥቃት/ የጎንደር ፋኖ አንድነት እና የቀጠለው ከባዱ ውጊያ / ፓርላማው በትግራይ ግምገው ያረጋገጠው
ዘመነ ካሴ በድሮን በቤተሰቡ ላይ ስለደረሰው ጥቃት/ የጎንደር ፋኖ አንድነት እና የቀጠለው ከባዱ ውጊያ / ፓርላማው በትግራይ ግምገው ያረጋገጠው
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና
ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!
[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ
ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)
January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ
ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ ታየማ ታየ ነው
አማራ ፋኖ አነጋጋሪው የኤርትራ ሙዚቃ Nahom Yohannes New Eritrean Music ክመረብ ማዶ አድማስ የመጣው ዝማሬ የሚለው ገብቶኛል መድህን ነው ላገሬ አንከፋፈልም በተገንጣይ ወሬ ሑለቱ አንድ ናቸው ጥንትም ሆነ ዛሬ —
አማራ ፋኖ አነጋጋሪው የኤርትራ ሙዚቃ Nahom Yohannes New Eritrean Music
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ” — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ ራሳችንን እንፈትሽ ። እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ
ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል። ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ
አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!
ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት
80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?
በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና