April 2, 2014
13 mins read

ፋሲል የኔዓለምን የምተችበት ምክንያት አገኘሁ! • ‹‹መሬት ተሸጠ አልተሸጠ›› ኢህአዴግ መደገፍን ምን አመጣው?

ከጌታቸው ሽፈራው

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ሰሞኑን ‹‹ኢህአዴግን የምደግፍበት አንድ ምክንያት አገኘሁ፡፡ መሬት አይሸጥም፤ አይለወጥም›› የሚል ጽሁፍ አስነብቦናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስርዓቱን የሚተቹ ወይንም የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን ‹‹ኢህአዴግን የምደግፍበት ምክንያት አገኘሁ›› ማለት ይቅርና ትችታቸው የሰላ ሆኖ ካልተገኘ ‹‹ወያኔ›› መባላቸው የተለመደ ሆኗል፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ፋሲል ይህንን የፖለቲካ ባህላችን እያወቀና ደፍሮ ‹‹ኢህአዴግን የምደግፍበት አንድ ምክንያት አገኘሁ!›› ማለቱ በራሱ ይበል የሚያሰኝ አዲስ ባህል ነው፡፡
በእርግጥ ፋሲል ኢህአዴግን እደግፈዋለሁ ሲል በጭፍን አይደለም፡፡ ከግራ ፖለቲካው የተቀነጨበ ‹‹ካፒታሊስቶች መሬቱን ተቆጣጥረው አርሶ አደሩን መሬት አልባ ያደርጉታል፡፡›› የሚል መከራከሪያ አንስቷል፡፡ ይህ መከራከሪያ በዚህ ዘመን ደግሞም ፋሲል እደግፈዋለሁ ያለው ኢህአደግ ራሱም ሆነ በቅርቡ የሚገኙት ባለሃብቶች መሬትን በተቆጣጠሩበት በአሁኑ ወቅት ባይሆን ኖሮ ‹‹ለአቅመ መከራከሪያነት›› ብቁ በሆነ ነበር፡፡

‹‹መደገፍን ምን አመጣው?››

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)
ፋሲል የኔዓለምን የምተችበት ምክንያት አገኘሁ! • ‹‹መሬት ተሸጠ አልተሸጠ›› ኢህአዴግ መደገፍን ምን አመጣው? 1

ፋሲል በአሁኑ ወቅት መሬት ቢሸጥ ቢለወጥ በተወሰኑ የስርዓቱ ደጋፊ ካፒታሊስቶች እንደሚያዝ ሲፈራ ስርዓቱ በመሬት ጉዳይም ብልሹ መሆኑን እየገለጸልን ነው፡፡ ታዲያ የዚህ ብልሹ ስርዓት ተግባራዊ የማትሆን አንዲት ዘለላ ‹‹መርሁ›› እንዴት ትደገፋለች? ኢህአዴግ መሬትን አይሸጥም አይለወጥም የሚለው አርሶ አደሩን ጨምድዶ ለመያዝ እንደሆነ ፋሲልን መምከር የሚቻል አይደለም፡፡ በዚህ መንገድ ኢህአዴግ ዘመናዊ ጭሰኛ መፍጠሩ መቼም ቢሆን ድጋፍ ሊያስገኝለት አይችልም፡፡
በሌላ መልኩ የፋሲል መደገፊያ ምክንያትም ቢሆን በአሁኑ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው፡፡ ፋሲል መሬት ቢሸጥ ቢለወጥ ካፒታሊስቶች መሬት ስለሚያካብቱ የአርሶ አደሩ መሬት በጥቂት ግለሰቦች እጅ ይወድቃል ይለናል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የጥቂቶች መንግስት መሆኑን ይነግረናል፡፡ መሬት የ‹‹መንግስት ነው!›› ሲባል ህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናትን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅምን ከማስጠበቅ ውጭ ‹‹መንግስት›› በሚባለው መዋቅር እያገለገለ ነው ሊለን አይችልም፡፡ ስለሆነም ወረቀት ላይ ‹‹መሬት አይሸጥም አይለወጥም›› ተብሎም ቢሆን መላው የአገሪቱ መሬት ጥቂቶቹ ገዥዎች እንደፈገሉ የሚጠቀሙበት ከመሆን አልዳነም፡፡
ለኢህአዴግ ምቹ እስከሆነ ድረስ የትኛውም ካፒታሊስት የቻለውን ያህል መሬት የማካበት መብት ተሰጥቶታል፡፡ እነ አላሙዲን መሬት እስከፈለጉ ድረስ የተፈናቀለው አርሶ አደር ተፈናቅሎ አርሰው የማይጨርሱት መሬት ለ99 አመት በነጻ በሚባል ዋጋ እየተሰጣቸው ነው፡፡ በእርግጥ በየ ክፍለ ሀገሩ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ውስጥ ድሃዎች ተፈናቅለው ሰፋፊ መሬቶች ምንም ሳይሰራባቸው ፋሲል ‹‹መሬቱን ይቆጣጠሩታል!›› ብሎ በሚፈራቸው ካፒታሊስቶች ያለምንም ተግባር ታጥሮ ይገኛል፡፡ ምን አልባት ይህ ነገር የተባባሰው ፋሲል ከአገር ከወጣ ከሆነ አላውቅም፡፡
በአንድ ወቅት ጋምቤላ ውስጥ የተሰራ ጥናት የክልሉን ሰፋፊ መሬት የተቆጣጠሩት 75 በመቶ የሚሆኑት የህወሓት ሰዎች መሆናቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህን ጉዳይ ኢሳትም ሰፊ ዘገባ ሰጥቶት እንደነበር ይታወቃልና ለእነ ፋሲል አዲስ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለ ሰብዓዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ሌሎች ጉዳዮች የማያነሱ ካፒታሊስቶች መሬት ከጠየቁ የፈለጉት ቦታ ላይ ይሰጣቸዋል፡፡ አላሙዲን ሳውዲዎችን ይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቷል፡፡ የቱርክ፣ የህንድ፣ የኳታር…… ካፒታሊስቶች ኢትዮጵያውያንን እምብዛም ለማይጠቅም አበባ፣ ሩዝና ሌሎቹንም ምርቶች ለማምረት አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ቀጥለዋል፡፡ አርሶ አደሩ እየተፈናቀለ ለ99 አመት በሲጋራ ዋጋ እየተሸጠላቸው ነው፡፡ ታዲያ መሬት በይፋ ‹‹ይሸጥ›› ቢባልስ ከዚህ በላይ ምን ያህል አርሶ አደር እንዳልተፈናቀለ ነው? ከዚህ የባሰ ምን ያህል ወረራስ እንዳልተደረገብን ነበር?

ከምንም በላይ ፋሲል ‹‹መሬት አይሸጥም አይለወጥም!›› የሚለውን የኢህአዴግን አቋም ለኢትዮጵያ አስቦ ያስቀመጠው ያህል አስቦት ‹‹እደግፈዋለሁ!›› ማለቱ ነው የሚገርመው፡፡ ኢህአዴግ ወረቀት ላይ ‹‹መሬት አይሸጥም አይለወጥም!›› ማለቱን እንደ እውነት ቆጥሮም አንድ መደገፊያ ነጥብ ማስቀመጡ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አርሶ አደሩን የስልጣን ምንጭ አድርጎ ስለሚመለከት መሬትን በመያዢያነት መጠቀሙ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ መሬትን በይፋ መሸጡ ኢህአዴግን ተጨማሪ አንድ ቀን የሚያቆየው መስሎ ከታየው ዛሬውኑ እንደሚሸጠው ጥርጥር የለውም፡፡ ኢህአዴግ ፋሲል ከሚፈራው ‹‹ካፒታሊስቶች››ና ከአርሶ አደሩ የትኛው እንደሚጠቅመው ያውቃል፡፡ በእርግጥ ሁለቱንም አብሮ ማስኬድ ችሏል፡፡ ፋሲል መሬት ‹‹ካልተሸጠ›› መሬት አያክብቱም ያላቸው ካፒታሊስቶች ‹‹እድሜ ለኢህአዴን!›› እንጅ አርሰው የማይጨርሱት መሬት ከአርሶ አደሩ ነጥቀው አጥረዋል፡፡ ቀሪውን የአርሶ አደሩን መሬት ደግሞ ‹‹አይሸጥም አይለወጥም!›› ብሎ የሚገዛና ምቹ ካፒታሊስት እስኪመጣ ድረስ ጨምድዶ ይዞታል፡፡ በሁለቱ መካከል ግን ፋሲል የሚለው ኢህአዴግና ‹‹መርሁ›› የለም፡፡ አንደኛ ነገር እሱ ለእራሱ እስጠቀመ ድረስ እንጅ ለአገር ብሎ አይደለም‹‹አልሸጥም!›› የሚለው፡፡ ደግሞም ፋሲል ለፈራቸው ካፒታሊስቶች እንደፈለጉ እየቸበቸበላቸው ነው፡፡
እንዲያው ለካፒታሊስቱ ባይሸጥ ኖሮስ ከነ ሌሎቹ ድክመቶቹ መሬትን አልሸጠም ተብሎ እንዴት ይደገፋል? በኢትዮጵያ ፖለቲካ መሬት ብቸኛው የልዩነት መስመር አይደለም፡፡ መሬት ከሚዲያ ነጻነት፣ ከዴሞክራሲያዊና ነጻ ምርጫ፣ ከፍትህ…..ብቻ ከበርካታ ጥያቄዎች መካከል አንዱ እንጅ ብቸኛው ሆኖ አያውቅም፡፡

አንድ ምሳሌ ላንሳ!

ኢህአዴግ ኢትዮጵያውያንን ያስራል፣ ያፈናቅላል፣ ከመብቶቻቸው ይገድባል፡፡ ለአብነት ያህል እነ እስክንድር ጠያቂ ከልክሏቸዋል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ የታሳሪዎች ቤተሰቦች ይጉላላሉ፡፡ በህገ ወጥ መንገድ ከመታሰራቸውም በላይ እስር ቤት ውስጥ በርካታ ችግሮች ይገጥማቸዋል፡፡ ኢህአዴግ የእነ እስክንድር የፍርድ ጉዳይ ባለው ህገ ወጥነት እንደቀጠለ ከበርካታ ችግሮቻቸውና ጥያቄዎቻቸው መካከል አንዱን ቢፈቅድ ልንደግፍው ነው ማለት ነው፡፡ እኔ የፋሲልን መርህ ከዚህ በተመሳሳይ ነው የማየው፡፡ ምን አልባት የመሬት ጥያቄ ቢመለስ እንኳ በኢህአዴግ ላይ የምናደርገውን መማረር (ተቃውሞ) ወደ ሌሎቹ ጉዳዮች ይቀይረዋል አሊያም ምሬታችን ይቀንሰዋል እንጅ ሊደገፍ አይገባውም፡፡ የሚገባህን የቀማህን አካል ጮኸህም ሆነ እንዲሁ ሲመልስልህ በዛ ቅጽበት ‹‹አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣….›› እያልክ ‹‹በምክንያት›› ልትደግፈው አትችልም፡፡ ምክንያቱም ያችን አንዲት ነገር መልሶም (ፋሲል ላልተመለሰው ነው የደገፈው) ጥፋተኛ ስለሆነ ማማረርክን፣ መቃወምክን ልታቆም አትችልም፡፡ ኢህአዴግ በመሬት ጉዳይ ከብልሹነት አልወጣም፡፡
በዚህ ብልሹ ዘመን መሬት በግልጽ ቢከፋፈል ጉዳት ያመጣ ነበር ተብሎ ‹‹በምክንያት›› መደገፍ መንግስት ያለ ህግ መነሻ አስሮ ጠያቂ ለከለከለው እስረኛ ጠያቂ ሲፈቅድ ‹‹አንድ ምክንያት›› ጠቅሶ እንደመደገፍ ነው፡፡ አሊያም ሁለት ሶስት እቃ መስረቅ ይችል ነበር ተብሎ የተገመተን ሌባ አንድ እቃ ሰርቆ ስለወጣ ይህን ሌባ የመመረቅ ያህል ነው፡፡ ሌባ ሌብነቱን፣ ብልሹ መንግስት ብልሹነቱን ጨርሶ እስካላቆመ ድረስ ከብልሹነቶቹ መካከል ሳይመቼው ስለቀረ አሊያም ስላላሰበው ብቻ አንዱን ወይንም ሁለቱን ስለተወ አሊያም ስላልፈጸመ ሊያስደግፈው የሚገባ አይመስለኝም፡፡ በመርህ የምናምን ከሆነ ማለቴ ነው!

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop