ከቴድሮስ ሐይሌ (TADYHA@GMAIL.COM) ‘
’መለስ ወደዚህ ዓለም ጭንቅላቱን ይዞ ለዝህች አገር ለዚህች ምድር የሚጠቅም ሃሰብ አመነጨ ለግሌ ለቤተሰቦቼ ሳይል አንድ ቀን ለራሱ ሳይሆን መንግስት በሚሰጠው ደመወዝ በፔሮል የሚከፈል መሪ በዓለም ላይ መለስ ብቻ ነው።’’ አዜብ መስፍን የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ዝናው ገኖ የነበረው የቀድሞው መንግስት ተራ ወታደር የነበረው ታምራት ገለታ የተባለ አባይ ጠንቋይ ሴት ወንዱን መሃይም ምሁሩን ብቻ ከተራው ዜጋ እስከዘመኑ ባለስልጣናት ሲያሰግድ ለቃልቻ ጣዖቱ ግብር ሲያስገባ የበረታ መንፈሳዊ ሃይል የተቀዳጀ እንደሆነ በአንድ ግዜ በተለያየ ቦታ እንደሚገለጽ ለተማጠነው ሃብት ጤና ትዳር እንደሚሰጥ በመስበክ ብዙ የዋሃንን አሳምኖ እስከ መመለክ ደርሶ የእግሩን እጣቢ እነደ ጠበል ሲያስጠጣ የነሆለሉለትን ሃብታሞች መድሃኒት በማጠጣት ገድሎ ሃብታቸውን የወረሰበትን የዩንቨርስቲ ምሩቃንን ሳየቀር ሳር እያስጎዘጎዘ ቡና እያስወቀጠ ይካደም የነበረበትን ሞራል አልባ የእውነት ድራማ በፍርድ መቋጫ እስካገኘበት ድረስ ያለውን የግለሰቡን የአጭበርባሪ ጥንቆላ ተውኔት ያንድ ወቅት መነጋገሪ ሆኖ የድርጊቱ ሰለባዎችና ራሱ ወንጀል ፈጻሚው ጭምር ለፖሊስ ይሰጡ የነበረውን መረጃ በየፌስቡኩና በዩትዩብ ተለቆ ጉድ ሲባል ነበር። ይህ አባይ ጠንቋይ ታዲያ በማጭበርበር ባካበተው ሃብቱ የገነባቸውን የቢዝነስ ተቋማት የላቡ ውጤት መሆኑንና ህብረተሰቡን በመርዳት ያበረከተው በጎ አስተዋጾ የማይገባ ስም እንደተሰጠው ለመከራከር ያቀረበው እፍረት አልባ ሙግት ተገቢ በሆነ ቅጣት መደምደሙን አስተውለናል።
ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ