አባ መላ ሳይበላ ተበላ! – ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!

ከአዜብ ጌታቸው

አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው። ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3ኛ 4ኛ….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።

ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል ።

ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ወያኔን ጉማሬ ብለው የገለጹበትም ምክንያት ይህው ነበር፡፤ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ “አባ መላ” የሚለውን ቅጽል ያወጡለት ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን መሆናቸውn (he was my best friend) አይነት ድምጸት) ሲናገር ሰምቸዋለሁ፡፤ የሞተ አይጠይቅ ሆነና ዝም ብለን ሰማነው።

ይሁን እንጂ በበኩሌ እንደሚታየኝ ብርሃኑ ዳምጤ የተሰ|ኘ የተሰፋ ሙዝ የሚሸጥ የምናለሽ ተራ ቁጭ ይበሉ (ምንጭ አብሮ አደጉ)ና የብርቅየውን ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬን ጓደኝነት እንኳን በዕውን በልቦለድ ድርሰትም ቢካተት ለአንባቢ የሚጥም አይመስለኝም፡፤ ልቦለድም ቢሆን እኮ የገሃዱ ዓለም እንጂ የከሃዲው አለም ነጸብራቅ ነው አልተባለም።….

ወደ ቀምነገሩ ልመለስ፦ አዎ ብርሃኑ ዳምጤ እነ ሎሬት ጸጋዬን እየጠቃቀሰ ፕሮፊይሉን ከፍ ከፍ እያደረገ ቢቆይም ሰሞኑን በሰራው ታሪካዊ ክህደት ያበገነው አብሮ አደጉ ያለ ከፈን ምናለሽ ተራ ቀብሮታል።

ለዚህም ነው ብርሃኑ በሰሞኑ ተግባሩ ከማንም በላይ የጎዳው ራሱን ነው ያልኩት፡፤

ከልብ አጢናችሁት ከሆነ የብርሃኑ ዳምጤ ችግር “ሞራል አልባ” መሆኑ ነው። ሞራል አልባ ሰዎች የሌላውንም ሞራል ለመጨፍለቅ ሁለቴ ማሰብ አያስፈልጋቸውም። ሞራል አልባ ሰዎች ፤ ምን ይሉኝ? አይሉም።ምን ይሉኝ የሚለውን ጥያቄ በአግባቡና በቦታው ማንሳት፤ የሞራል ድቀት ከሚያስከትል አደጋ ያድናል። ብርሃኑ ዳምጤን መሰል ሰዎች ይህን ጥያቄ አያውቁትም።

ለዚህም ነው ትናትና እንኳን ለተሰዳቢው ለሰሚው በሚዘገንን ጸያፍ ስድብ ያበሻቀጣቸውን የወያኔ ባለስልጣናት ዛሬ “ማሪኝ ብዬሻለሁ” እያዜመ የሚለማመጠው።

ግን ለምን?

ጥሩ ጥያቄ ነው…ሞራል አልባ ሰው የማንነቱ ነገር ብዙም አያስጨንቀውም። ተደፈረብኝ። ተገሰሰብኝ የሚለው እሱነት የለውም። ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም። ለሱ ማንነት? ከሚለው “የስብዕና” ጥያቄ ይልቅ ምቾት፤ ድሎት፤ ቅንጦት፤…..የተመቸ ህይወት ቅድሚያ አላቸው። በአጭሩ ሞራል አልባ ሰዎች ከምንም ከምንም ይልቅ ለሆዳቸው ቅድሚያ ይሰጣሉ።ብርሃኑ ዳምጤም ያደረገው ይህንኑ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹ኮነሬል አብይ ዋግ ኽምራን ከአማራ ክልላዊ መንግሥት የማስገንጠል የፖለቲካ ሴራ!!! በዋግ ኽምራ 200 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የብረት መዕድን ሃብት መገኘቱን አክሰስ ካፒታል ኩባንያ በጥናቱ አረጋግጦል!

ከወያኔ ኩብለላ

የወያኔ ባለ ስልጣናት የአውራቸውን ሞት ተከትሎ በራሳቸው የውስጥ ችግር ተንጠው፤ ውጭ ለታሰሩት ውሾች ይሰ|ጡ የነበሩትን መደበኛ መሽሩፍ አቋረጡ። በዚህ ምክንያት አለን ከሚሏቸው ተናካሽ ውሾቻቸው አንዱ (አባ መላ) ሰንሰለቱን በጥሶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ተቀላቀለ።

በተቃዋሚው ጎራ ቆይታ፦

ሰንሰለቱን በጥሶ የመጣው አባ መላ አክቲቪስት ተባለና(ይታያችሁ ሞራል አልባ ሰው የሰባዊ መብት ተሟጋች ሲሆን) የድሮ ጌቶቹን አብጠለጠለልን። ሙታንታ ማድረግ የማያውቁ ፍልጦች የሚል ኢ.ሞራላዊ ስድብ አወረደባቸው። እግረ መንገዱንም ሙታንታን ያህል የግል ገበና ሁሉ አውቃለሁ አይነት ራሱን አካበደ።

የጦር ሃይሎች ኤታ ማዦር ሹሙን በዓለማችን የመጨረሻው ደደብ ጀነራል ሲል ተሳለቀበት። የጀኔራሉ ህጻን ልጅ የኦሮሚያውን ፕሬዘዳንት በልምጭ ሲገርፈው “ አባዱላ እንደ ፈርስ ያስካካ እንደነበር ገለጸልን፡፤ ሞራል አልባው አባ ዱላ ለሆዱ ብሎ በህጻን ተገረፈ ብሎ እራት ግብዣ ላይ ያየውን ተረከልን። እረ ማን ቀርቶ… የአዜብን አካላዊ ገጽታ አብጠለጠለ … የበረከትን ሴረኝነት አማሰለ…ስብሃትን በዝሙት በስካርና በገዳይነት ወነጀለ … ብቻ አብዛኞቹ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት እጅግ በሚዘገንነው በምናለሽ-ተራ ጩቤ ምላስ ተተለተሉ።ባለ ስልጣናቱ ተዘናግተው ምሱን ባለመስጠታቸው … በሞራል አልባ አንደበቱ ዘመተባቸው። የአዜብ አፍንጫ ጠማማነት ምን የፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ባይገባንም ፈገግ ማለታችን አልቀረም።

ብርሃኑ ዳምጤ እንዲህ እንዲህ እያለ በተቃዋሚው ጎራ ቆየ፡፤ ወደ ኢሳት ቢያንዣብብም …. በወያኔ የጎደለበትን ምሱን የሚተካበት ምናምኒት ሊያገኝ የቻለ አልመሰለኝም። ቀጠለና በሳውዲ መንግስት ግፍ የተፈጸመባቸውን ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት በተቋቋመው አለም አቀፍ ግብር ኃይል ገብቶ እድሉን ሞከረ፡፤ እንደ ልኳንዳ ቤት ውሻ አይኑ እየተንከራተተ ምራቁን ገርገጭ አድርጎ ከመዋጥ በስተቀር አሁንም ጠብ የሚል ነገር አልተገኝም። በዚህን ግዜ ብርሃኑ ዳምጤ፤ ከወያኔ ጉያ መውጣቴ ታሪካዊ ስህተት ነው ሲል፡ ታሪካዊ ስህተት ያለውን በታሪካዊ ሞት ሊያርመው ወሰነ።አመቺ ግዜም ጠበቀ።ረዳት ፓይለት ኃይለ መድህንን በቴሬሪስትነት በመፈረጅ ለወያኔ የመጀመሪያውን የምህረት ጥየቃ ደውል ደወለ! ኦሮማይ…….!

ዳግም ወደ ወያኔ…

ብርሃኑ በደርሶ መልሱ ጉዞ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው ያልኩት ያለ ምክንያት አይደለም። በክብር የያዙትን ጌቶቹን አስቀይሞ ሲያበቃ ዛሬ ተመልሶ ለምህረት ደጅ መጥናቱ፤ ዋጋውን ዝቅ አድርጎ ራሱን ለዳግም ሽያጭ ማቅረቡ፤ እንደ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም ስብዕናውን ማዝቀጡ እየታየኝ እንጂ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህወሓት የፈጠረችው ዘረኛ ስርአት እና የአሀዳዊነት እውነተኛ ግጽታ - መንግስቱ ሞሴ

ከበድን መሃል ምኑን ይመርጧል አትበሉኝ እንጂ፦ በኔ እይታ ዛሬ ከሰሎሞን ተካልኝና ከቤን የዘቀጠ ሞራል ላይ የሚገኘው ብርሃኑ ነው። ይህን ለመረዳት ደግሞ ከቤን ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ማድመጥ ብቻ በቂ ነው፡፡ በ

ቃለ መጠይቁ ቤን ሌጌቶቹ ባለው ታማኝነት በመኩራራት የሚሰነዝራቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች “ደግ አላደረክም ቢሆንም እንምርሃለን” አይነት ድምጽ ነበራቸው፡፤ አባ መላም በአንጻሩ ጭራውን እየነሰነሰ ጌታው እግር ሥር እንደሚንከባለል ውሻ አይነት በልምምጥ ስሜት ነበር የሚመልሰው፡፤ ከባሪያም ተራ…..!

ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል!

ከብርሃኑ ዳምጤ ድፍረት ሁሉ ያስገረመኝ ፡ ታማኝ በየነንና ማንጓጠጥ መሞከሩ ነው። በርግጥ ወያኔ ከማንምና ከምንም በላይ ታማኝ ቢዋረድላት እንደምትደሰት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፤ በዚህ ስሌት ይመስላል ብርሃኑ ዳምጤ ታማኝን ለማብጠልጠል የሞከረው። ነገር ግን አልተሳካም፡፤ ወያኔም ቢሆን ጀግና ታከብራለች ሲሉ ሰምቻለሁና ከብርሃኑ የገለማ ቃል ይልቅ የታማኝን ግልጽ ጠላትነትን የምታከብር ይመስለኛል፡፤ ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል ይባል የለ። ብርሃኑ ለኛም ለወያኔም ሞቷል።

ይህን የምለው በታማኝ በየነና በአባ መላ መካከል ያለው ፍጹም የሆነ ልዩነት እየታየኝ ነው፡፤ ቃላቶች ካልተመሙብኝ እስኪ በንጽጽር ልግለጻቸው።

ታማኝ ከአላሙዲን የዶላር ማማ ላይ “እረ ወግድልኝ!” ብሎ ወርዶ ከተገፋው ወገኑ ጎን በመቆም ከፍተኛ የሞራል እርከን ላይ የሚገኝ የህዝብ ልጅ ነው።

ብርሃኑ ደግሞ በአንጻሩ በደም ከጨቀየው ከወያኔ ደጅ የወዳደቀ ምንምን አይቶ፤ ይሁን እስቲ ካወጣነው የሞራል ማማ ላይ ቁልቁል ተምዘግዝጎ የወረደ የግፈኞች ወዶ ገብ ባሪያ ነው።አለቀ።

በነገራችን ላይ ብርሃኑ የወያኔን የምህረት ደወል በቤን አማካኝነት ሲያስደውል፤ አብሮም የኢሳትንና የግንቦት ሰባትን ብዙ ሚስጥር ገጸ በረከት እንደሚያቀርብ ነግሮናል። እውነት እውነት እላችኋለሁ ብርሃኑ እስካሁን ከቀበጣጠራቸው ነገሮች ውጭ አንድም የሚያውቀው ነገር የለም። ለምን በሉኝ? ምክንያቱም ዋናው ቁጭቱ ወደ ሚስጥሩም ወደ …ካዝና ሊያቀርቡት አለመፍቀዳቸው በመሆኑ ነው።ጨዋታ በጋራ ሂሳብ በግል ተባለ….አልወደደውም።

አክቲቪስት ስለመባሉ….

በኢሳት ጋዜጠኞች አክቲቪስት መባሉ ለኔ ብዙም እንደ ጥፋት አልታየኝም። አክቲቪስት የሚለው ስያሜ እንደ ወታደር ቤት በአገልግሎት ዘመን ተመዝኖ የሚሰጥ ሹመት ሳይሆን አመለካከትን ብቻ መሰረት አድርጎ የሚስጥ በመሆኑ ብርሃኑም ወያኔ ማብጠልጠል በጀመረበት ቅጽበት አክቲቪስት መባሉ አልተገቢነቱ አይታየኝም፡፤ በኔ አመለካከት
በእጅጉ የሚያስቆጨኝና ስህተት የምለው “አክቲቪስት” የሚለውን መጠሪያ መስጠቱ ሳይሆን አንድ የ11ኛቢ ተማሪ (ከአብሮ አደጉ የሰማሁት ነው) የምናልሽ ተራ ቁጭ በሉ እነ ሙሉጌታ ሉሌን ከመሰሉ በሳል ሰዎች ጎን ፖለቲካ ሊተነትን መቀመጡ ነው። የሚያናድደኝ ከነታማኝ በየነና አበበ ገላው ሌሎችም ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያን እኩል አለም አቀፍ ግብር ኃይል ውስጥ መግባቱ ነው። “እኩያ ቢስ ..!” ይሉ ነበር ቀኛዝማች እንቶኔ እንዲህ አይነቱ ያለአቻ… ….ሲገጥማቸው። ይህ አይነቱ ስህተት እንዳይደገም ሊታሰብበት ይገባል ይመስለኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት የተሰጠ መግለጫ

አሁንም በኔ እይታ ብርሃኑ ዳምጤ (ከሟቹ አለቃው ከጠ/ሚ አጸያፊ አባባል ልዋስና) ከመበስበስ… ወደ.. መታደስ…. እንደገና ወደ መበስበስ ያደረገው የደርሶ መልስ እንቅስቃሴ በአጭሩ ሲቀመጥ፡

እንሆ ብርሃኑ ዳምጤ ጥቅም(ሆዱ) ስለጎደለበት ወያኔን ከድቶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገባ። የወያኔ ባለስልጣናትን በአጸያፊ ስድብ ማዋረድን ለተቃዋሚው ጎራ እንደ ገጸበረከት አቀረበ።አሁንም በተቃዋሚ ጎራ ለህሊና እንጂ ለሆድ የሚሆን ነገር በማጣቱ የአሞሌ ተመኑን ቀንሶ ራሱን ለቀድሞ ጌታው ዳግም ለሽያጭ አቀረበ። ይህው ነው። መጣ እነሱን ሰደበ …ሄደ..ራሱን ሰደበ!

ብርሃኑ ዳምጤ ከዚህ በኋላስ?

ብርሃኑ ከዚህ በኋላ አይደለም ፖለቲካዊ ህይወት ሰዋዊም ህይወት የሚዋጣለት አይመስለኝም።በቅርቡ አንድ አብሮ አደጉ ብዙ ብዙ አሉታዊ ባህሪያቱን እንዳጋለጠው ሰምተናል። ብርሃኑ የሰሞኑ ተግባሩ ከራሱ ሌላ ማንንም ላለመጉዳቱ ሌላው መገለጫ በይደር ተይዞ የነበረ፤ በቀይ ሽብር ዘመን ከኢህአፓ ውልቅ ደርግ ጥልቅ ብሎ ያስቀጠፋቸውን ሁለት ወጣቶች ጉዳይ ከሟች ቤተሰቦች አንደበት ለማሰማት እንቅስቃሴ መጀመሩ ነው።ይህ ማስፈራሪያ ሳይሆን በቅርብ የማውቀው ወዳጄ እየሰራበት ያለ ጉዳይ ነው።

በኔ እይታ ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናትን ከሰደባቸው አጸያፊ ስድብ አኳያ እጃቸውን በምህረት የሚዘረጉለት አይመስለኝም። እንደ ሰሎሞን ተካልኝ “የቅንድቡ ውበት” አይነት ሙገሳም የሚያዋጣ አይሆንም። እናም አባ መላ በፓልቶክ ውስጥ ተፈጥሮ በፓልቶክ ውስጥ ኖሮ በፓልቶክ ውስጥ ሞተ ! የሚለውን ዜና የምንሰማበት ግዜ እሩቅ አይሆንም።አባ መላ ሳይበላ ተበላ! ይሏል ይህ ነው…..

ለድህረ ገጾች

ኢሳቶችና ድህረ ገጾች ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናት በአጸያፊ ስድብ ሲያዋርዳቸው የተቀዳውን ኦዲዮ እየመረጣችሁ በማስደመጥ የምህረት ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይገኝ ብታደርጉ እኔን ያየህ ተቀጣ! ነውና አስቡበት….. እያልኩ ከአጼ ቲዎድሮስ ታሪክ ላይ በተዋስኳትና ስሟን ወደ ራሴ በቀየርኳት ስንኝ ልሰናበታችሁ….

ይህንን ሲሰማ ያጓራል ላመሉ
ማናትም ቢላችሁ አዜቧ ናት በሉ!

አዜብ ጌታቸው

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር

6 Comments

  1. You nailed it !!…kkkkk…aba bela is busted. I always wander how he’s going to blend with the regime leutents and cadres that he used to bash and trash with a harsh street language…..on his own words, the ” moron prostitute Azeb”, the “fake” Meles, the “egg seller” Samora, “shanta teshekami” embassy staffs….the list will continue…hahaha…….
    We should continue utilizing his own words and recordings to trash and expose the regime including himself….
    Debur made a political suicide!!…kkkkkk

  2. መጣ እነሱን ሰደበ …ሄደ..ራሱን ሰደበ!
    “መታገል አድርባዩን ነው አድርባይ ለመወደና ለጥቅሙ ሲል ይጎዳል!” ታጋይ አዜብ መስፍን ጎላ…ይህ ፓልቶክ ከተባለ ክበብ የአየር በአየር የፖለቲካ ተንታኝና በታኝ እንጂ አንድም ደህና ሰው ሳይመረቅ ሁሉ እነደተረገመ!

    ግን ለምን?..
    **በአንድ ወቅት ሻላቃ ኅይሌ ገብረስላሴ ፕሬዘዳንት ሊሆን አስቧል ተብሎ ያነበበ አስተያየት ሰጪ “እባክህ አርፈህ እሩጫህን ለዝና ቀጥል ፖለቲካ እንኳን ለኅይሌ ገ/ስላሴ በምላሱ ትኩስ ቂጣ ለሚገለብጠውም ለልደቱ አያሌው አልሆነም “ያለው ሁሌም ያስቀኛል። የብርሃኑ ዳምጤ የፓልቶክና የኢሳት ቴሌቪዥን ላይ የሰጠው ትንታኔና ያለው አስተዋጽዎ ምን እነደነበር አልገባኝም። በእርግጥ “የኢህአዴግ ጎራ በዲያስፖራው ተተኪ ሳያዘጋጅ ብርሃኑ ዳምጤን በማጣታቸው ከፍተኛ ድንጋጤና መረበሽ እንደተፈጠረ እራሱ ለእራሱ ምስክርነት ሲሰጥ ሰምቻለሁ።” መለስ ዜናዊን በሕገመንግስቱ አንድ ገፅ ተኩል ሙሉ ሥልጣን አስጠቅልለው ብራሰልስ ካስጠቀለሉ በኋላ “ተተኪ መኖሩን ባወቀ ሞት እንዲህ ባልተጨነቀ!አሉ። በብሀሔር ብሄረሰብ ቋንቋ ሲተረጎም እንደሚፈነገል አውቀን ተዘጋጅተንበታል ማለት ነው። ጎፈር ባለው የተባለው አብሮ አደጉ ብርሃኑ ስለ ግንቦት ፯ ፣ ኢሳትና፤ ኢሳያስ አፈወርቂ ብዙ መረጃ አለው ቢሉት..ብርሃኑ ደቡር “እንኳን መረጃ ሊሰበስብ የሰጡትንም መረጃ ይበትናል”ተንታኝ ይሆናል በታኝ በለው!

    ከወያኔ ኩብለላ፡-
    **ብርሃኑ ዳምጤ እንደሚለው”በፊትም አልወጣሁም! አሁንም አልገባም!ወደፊትም አልመለስም!የት ይገባል? ይላል..”ባለፈው ሁለት ሳምንት በፊት ኢትዮጵያ ነበርኩ ከኢህአዴግም ጋር አብሬ ብሰራ ችግር የለብኝም!” ወጣቱ ፓለቲካ ተንታኝና በታኝ ጃዋር መሐመድ “በውጭው ዓለም ብዙ ነን በቅርብ ቀን ሁላችንም ተያይዘን ሀገራችን እንገባለን ኢትዮጵያዊነቴን የሚሰጠኝም የሚነሳኝም የለም!ተስፋዬ ግብረእባብ….አቤት የፖለቲካ ዓላማ መመሳሰል!ዘይገርምዩ ነገር..

    በተቃዋሚው ጎራ ቆይታ-
    ***ብርሃኑ ዳምጤ በተቃዋሚው ጎራ፤ ወደ ኢሳት ቢያንዣብብም ….በወያኔ የጎደለበትን ምሱን የሚተካበት ምናምኒት ሊያገኝ የቻለ አልመሰለኝም። ለመሆኑ ይህ ኢሳት የተባለ ቴሌቪዥን ከምን ብረትና ሲሚንቶ ቢሰራ ነው!? አንዱ መዶሻ፣ ሌላው ቡልዶዘር፣ ይዞ ሌላው ሠራዊቱን አሰልፎ ዙሪያውን ይጮሃል ወይ ፍንክች እሳት ጭረሽ የውሃ ጓደኛ ሆኖ…አረፈው!ምንም እንኳ ብዙ የሚስተካከልና የሚሻሻል ነገር ቢኖርበትም አንድን የሙስና መር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ ብሔርተኛ መንግስት መቋቋም መቻሉ ብቻ መሥራቾቹ፣ባለቤቶቹ፣ሠራተኞቹ፣ ኢትዮጵያውዊያን ናቸውና ያስመሰግናቸዋል የማይሳሳት ምቀኛ ወሬኛ የማይሰራ ብቻ ነው ።አራት ነጥብ።

    ዳግም ወደ ወያኔ… “ኢህአዴግ ፲ ቦታ ጥዳ ፱ አረራባት “አለ-
    ***ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ ለመሆን መስፈርቱ ምንድነው? *በንግርህና በፅሁፍህ ሁሉ..ትምክተኛ! የቀድሞ ሥልጣን ናፋቂ! ሀገራችን ወደፊት እንጂ ወደቀድሞው ሥርዓት አትመለስም! ብሀየር በሔረሰቦችና ህዝቦች ሁኑ ሕዝቦች! እድገታችን አይደናቀፍም! መካካለኝው ገቢ ካላቸው እንሰላፋለን! ራዕዩን አናስቀጥላለን! ታጋይ አይሞትም የጀግና እረፍቱ ሞቱ ነው!ነፍጠኞች ይውደሙ!..የጋራ መብት እንጂ የግለሰብ መብት እራስን ለማሳበድና ለማጥፋት ነው!አንገት ልብስ ካኒቴራና ባርኔጣ በሰፊው ህዝብ ማደል!ብሔራዊ ለቅሶና ደረት መድቃትን በክልሎች ማወዳደር!ኢሳትን ማብጠልጠል!ግንቦት ፯ መወንጀል በግንቦት ፳መማል አንጋፋውን የህወአት/ኦነግና/ኦብነግን አባት ሻቢያ ኢሳያስ አፈወቂን መሳደብ ማጥላላት ሀገርና ሕዝባቸውን ማሳነስ!ከኢትዮጵያ ይልቅ ለኤርትራ መጨነቅ!ያለፉ ነገስታትን ማጥላላት…ይፍርስ፣ይቃጠልን መደገፍ…በኢህአዴግ ጥላ ትግሬን እያጥላሉ..የራስን የጥፋት አጀንዳ ለማስፈጸም የህወአት ታጋይ ፊት ወድቆ እራስን የቦንብ መፈተሻ አድርጎ መሰዋት መሆን!በባዶ ሆድ፣ በባዶ እግርና ቂጥ፣ በባዶ ሜዳ መጨፈር!የቀድሞ አጥፊዎች የአሁን ልማታዊ እንቨስተር ባለሀብት፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን መቆጣጠርን ማድነቅና መደናነቅ…ስብእናን በቁስ ለውጦ እንደበቀቀን ነገር መድግም…የተተፋውን እየላሱ መልሶ በድሃ ሕዝብ ላይ መትፋት…የሥርዓቱ ደጋፊና ተደጋፊዎቹ መገለጫና ባህሪያት ናቸው።ለመሆኑ ይህን ለማድረግ የደረጃ ትምህርት ያስፈልጋልን? አባ መላስ እንጂ !?

    ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል!
    **ብርሃኑ ዳምጤና ዳዊት ከበደ እኩል አልሰለጠኑም!? ዳዊት አውራአምባ ግንቦት ፯ ሊ/መንበርን ቃል ጠለፈ..ይቅርታ ሳይጠይቅ ተጋብዞ ገባ። ግን ብዙም አልተዛበተም!!ብርሃኑ ደቡር “ማስረጃና መረጃ አለኝ” አለ። ከድርጅትም አልፎ ግለሰቦችን ወርዶ ዘለፈ..ይች እንግዲህ በፓልቶክ ምጣድ የተቆላችውንና ተደጋፊዎች የሚያንገበግባቸውን ነጥብ በጨረፍታ ሲያሸትት ነበር። እሱም የቀዳት ወሬ ትኖራለች “weak link” “የሞተስ አረፈ አንዱን ወጉን ያዘው…በቁሙ የሞተስ የሀገር ሸክም ነው።

    አክቲቪስት ስለመባሉ….
    **ቀፈታቸው የበረከተ..እራሳቸውን የሚያደንቁና የሚደነቁ፣ መድረክ የፈጠሩ፣መድረኩ የሚመቻችላቸው፣ምሕዳሩ ሁሉ የሰፋላቸው..በእረጃጅም እጅ የሚደገፉና እረጃጅም ምላስ ያላቸው ሁሉ፣ ሰለሀገራቸውና ሕዝባቸው ሠላምና አንድነት እኩልነት ነፃነት ከሚሰማቸው እኩል ማዳበሉ አደጋ አለው።”ምንም ይሁን ምን ለቆመበት ዓላማ የሚፀና ደስ ይለኛል”አቶ ለገሠ መለሰ…አማራን’በአስተሳሳብ ወክለው’ከእሳቸው በፊት ቦንብ መሞከሪያ ለመሆን ለቆረጡ ብአዴን አማራር አካላት የሰጡት የሙገሳ ቃል ነበር። አክትቪስት ማታ ማታ ተሳድበህና አምተህ ቀን ቀን ከበታኝ ጋር ሲዶሉቱ መክረም ያስተዛዝባል። ለመሆኑ በረዳት አውሮፕላን አብራሪው ገብረመድክን አበራ አውሮፕላን ማገት፣ በግንቦት ፯ አማራር፣ በኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ የቀጠናው አተራማሽነት፣ አስተሳሳባቸው የተናወጠው በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትነት አንድነትና ጥቅም በጭረሽ አልደራደርም ያሉት ብርሃኑ ደቡር ኢህአዴግ ለሱዳን በሰጠው መሬትና የኦሮሞ ሙስሊም ሜንጫ አብዮተኞችን ውስጣዊ መረጃ አውጥቶ ሀገር ወዳድነቱን ያሳይ ይሆን? ወይንስ የኢሳትና የግንቦት ሰባትን ጋብቻ ሙዜው ነኝ ብሎ ያወጋን ይሆን ?ለመሆኑ በነፃ ሚዲያ በነፃነት ተንፈላሶ የተናገረበትንና ተሳደበበትን ምሕዳር ለምን በሀሚታ እጅ መንሻ አደረገው? ኑ..አውሩበት ተናገሩበት በልተው ያስበላችሁን እሙበት ስደቡበት ያለን ተቋም ጭራሽም “የኢቲቪን ዜና ፊትና ኋላ አድረጎ ነው የሚዘግበው”ከተባለ ኢህአዴግ ኢሳትን በረዳት ሚዲያ ተቋማትነቱ የኢሳትን ሠራተኞችና አየር ክፍያ በመክፈል የመርዳት ሀገራዊ ግዴታ አለበት።የዜና ጨዋታ በጋራ የሂሳብ ክፍያም በጋራ ሀሚታ በግል ….መሆን አለበት።
    **ብርሃኑ ዳምጤ ከዚህ በኋላስ? ታጋይ ጥራኝ !ጓዶች ጥሩኝ መረጃ አለኝ ወይ እኔ አለ!ባቄላ ጠፋ ቢለው ፈስ ቀለለ አለው…መለስ ቢኖር ባይኖር….ፋጡማ(አዜብ)ብትኖር ባትኖር” ታላቂቷ ሀገራችን አንድ እናት ናት ለዘለዓለም ትኑር..ሹንባሽ ነበር ሄደ በለው!
    ይህንን ሲሰማ ያጓራል ላመሉ
    ማናትም ቢላችሁ አዜቧ ናት በሉ!
    ጠይቆ አስጠይቆ እንዳይደናገረው
    አዜብ ጌታቸው! ሁኝበት በአለሽበት ከአክብሮት ሰላምታና ምስጋና ጋር!

  3. ከዚህ አይነቱ ውርደት ይሰውረን ነው የሚባለው! ምነው ያለዝና መኖር ምንገዶ? እንዲህ እንክትክት የሚያደርግ ቅሌት በስተእርጅና ነውርም አይደል!!!! አቶ ብርሃኑ ለንስሀ እድል እንዲሰጥህ ምጝቴ ነው! !!!!!

  4. ሰው የምንፈልገውን ሲናገር አክቲቪስት እያልን ማሞገስ ከኛ የተለየ ሃሳብ ሲይዝ ደግሞ ሆዳም ከርሳም እያሉ ማዋረድ የሚጠቅመን አይሆንም በአካዳሚያዊ ትምህርት ጎበዝ የሆነ ብቻ ነው ፖለቲከኛ የሚሆነው ለሚባለው ደግሞ ታሪክን አለማንበባችን ብቻ ነው የሚያሳብቀው እንደዛማ ቢሆን ኖሮ እነ አነስታይን እስከሁን ስማቸውን እያስጠራ ያለውን የዕውቀት ብርሃን መፍጠር ትተው ፖለቲከኞች ይሆኑ ነበር እነ አብርሃም ሊንከንም የታላቅ ሀገር መሪ አይሆኑም ነበር እግዚአብሄር አገራችን ይባርክ

  5. I didn’t know that this man is immoral to this extent!
    What many of us do not realize is that EPRDF has been and still is “incubating” hundreds of thausands of such immoral people in the country. Read Dr Birhanu’s and Gibot 7s past and recent books, you would be able to see the abyss we are heading in to.
    Thank you Azeb

  6. አዜብ – በዘመናችን አፋቸውንና ሥጋቸውን ሽጠው የሚኖሩ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን። አባ መላ መላ ካጣ ዘመን አልፎታል። ከሁሉ የሚያሳዝነው የቀድሞ የኢህአፓ አባል ነበር መባሉ ነው። በዘመናት መካከል ህብር ሆነው በብልጭታም ሆነ በጉልህ ከታዪን የፓለቲካ ድርጅቶች እንደ ኢህአፓ የሃገርን አንድነትና የወገንን ጥምረት የሚሻ ድርጅት አልተነሳም። እንደ አባ መላ ያሉት መሃል ሰፋሪዎችና ከሞቀው ዘፋኞች ለሃገርም ሆነ ለራሳቸው አይጠቅሙም። አንቺም እንዳልሽው አባ መላ ሳይበላ እንደሚበላ ግልጽ ነው። ወያኔ ቂም አይረሳም። ቆይቶም ዘግይቶም መርዝ ያበሉታል። መኖር ይሉሻል እንዲህ ነው ለወስላቶች። እንደ ውሻ መልከስከስና የልብ ሳይደርስ ይህችን ዓለም መሰናበት።

Comments are closed.

Share