ሕዝባችን ንቁ ነው

እንዴት ጀመራችሁ ከየትስ መጣችሁ
ያረጀ መሣሪያ እንደታጠቃችሁ
ክፋት ምቀኝነት ተንኮሉን አዝላችሁ
እሹሩሩ ልጄ እያባበላችሁ
ህዝብን በማሣሣት ሰይጣን ተጣብቷችሁ
ወይ ለህዝብ ሳይሆን ፍትህ ለተራበው
ችግር ለደቆሰው እርሃብ ለጎዳው ለተጎሳቆለው
አሁን ተረዳነው እራስን መውደድ ነው
በሰይጣን ፈረስ እየጋለባችሁ
በሱዳን ምህታት እያታለላችሁ
ወንድምን በመግደል ወንድምን በማሰር እየፎከራችሁ
አገር ለመገንጠል እየዶለታችሁ
ለአንድነት ለህብረት የቆመውን ሁሉ እየገደላችሁ
የመናገር መብቱን ከህዝቡ ነፍጋችሁ
ውሸት ዲሞክራሱ እያራመዳችሁ
በዘር በሃይማኖት ህዝብን ከፋፍላችሁ
በቋንቋ መሰረት ሃገር በጣጥሳችሁ
ለመንገስ ለመክበር ነበር እቅዳችሁ
የእናንተ ውሸት ባቡር የማይችለው
በከንቱ አትድከሙ ህዝባችን ንቁ ነው
ትዝብት ይታወስ
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጡሩነህ፤ የኢትዮጵያ ተደራዳሪወች ወይስ የወያኔና የኦነግ አስታራቂወች? - መስፍን አረጋ
Share