የአባ መላ (ብርሃኑ ዳምጤ) መገለባበጥና ኢሳት

ከእንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)

አባ መላ ማን ነው?

በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው (ምንም እንኳ ስራው እንደ እድሜው ባይሆንም)። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል።

ብርሃኑ ዳምጤ ከደርግ መውደቅ በኋላ በስደቱ ዓለም (ዳያስፖራ) ፖለቲካ መድረክ ብቅ ያለው በምርጫ 97 ወቅት የዝነኛውን ቅንጅት ማልያ ለብሶ ነበር። ይሁንና በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ወያኔ መንግስት ምርጫውን አጭበርብሮ፣ የምርጫውን መጭበርበር የተቃወሙትን በገፍ በአደባባይ በጥይት ደብድቦ፣ ህዝቡ የመረጣቸውን የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨመሮ ከ50 ሺህ በላይ ባብዛኛው ወጣቶችን አስሮና በየጦር ካምፖቹ አጉሮ በአምባገነንነቱ ለመቀጠል ሲወስን ብርሃኑ ዳምጤም ባፋጣኝ የቅንጅትን ማልያ አውልቆ የህወሃት/ኢህአዴግን ማልያ ለብሶ ቁጭ አለ።

ሰሞኑን ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ አስደናቂ መገለባበጥን ፈጽሞ የህዝብን አይን አስበልጥጧል። እነዚህ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ሰሞኑን የሚፈጽማቸው መገለባበጦች በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ከነበሩት የመገለባበጥ ትሪኢቶቹ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር አሁን መገለባበጡን የሚፈጽመው በቀጥታ ስርጭት ወቅት (በፓልቶክ) መሆኑና ጉዳዮን በመሪ ዜና መልክ የሚዘግብለት የቴሌቪዥን ጣብያ “ኢሳትን” ማግኘቱ ነው።

ብርሃኑ ዳምጤ ከጥቂት ወራቶች በፊት ነበር የተሰለፈበት የህወሃት/ኢህአዴግ ጎራ በተለይም ከወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ እየተዳከመ መምጣትን አይቶና ገምቶ ወያኔዎችን “አፍንጫችሁን ላሱ፣ እኔ ከአሁን ብኋላ የድሮው አባ መላ አይደለሁም፣ እንዲያውም ጉዳችሁን አዝረጠርጣለሁ…” በማለት ፉከራ ቢጤ አሰምቶ የዲሞክራሲና የነጻነት ታጋዮችን ጎራ መቀላቀሉን ያበሰረው።

ተጨማሪ ያንብቡ:   ከአድዋ ድል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ቀን ድልም እንማር!!  - ከ ይሁኔ አየለ

መንፈቅ እንኳ ሳይሞላ አባ መላ በመጣበት አይነት መንገድ ተመልሶ ህወሃት/ኢህአዴግን ለማገልገል መወሰኑን ይፋ አደርጓል። ለሱ እምብዛም አዲስ ያልሆነውን የክህደት ቁልቁለትም ዳግም ተያይዞታል።

አባ መላ፣ ኢሳትና ዳያስፖራው

የኢሳት ጋዜጠኞች፣ አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞችም ጭምር ይህ አባ መላ የሚባለውን ቦታ እየቀያየረ ይሚጫወት ዝቅተኛ ካድሬ ከሚገባው በላይ ቦታ ሰጥተውት እንደነበር እገምታለሁ፣ በውጤቱም ተከታዮቻቸውን ያሳሳቱና ያዘናጉ ይመስለኛል። ይህንን ጉዳይ ማንሳቴ “ብዬ ነበር” ለማለት ሳይሆን ይልቁኑም ይህ ክስተት እንደ መማሪያ ሆኖ እንዲያልፍ በመፈልጌ መሆኑን አባብያን እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ።

እንደ አባ መላ አይነቱ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ የመገለባበጥ ብቃቱን ያሳየ ወለፈንዴ ተቃዋሚ ጎራ ገብቻለሁ ሲል አያያዛችን ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ሊሆን ይገባል። በቅርቡ ተገልብጦ ሊያሳፍረን ይችላል ብሎ መስጋት፣ ለጉዳዩ መጠነኛ የአየር ሰዓት መስጠትና ውሎ አድሮ ደግሞ መርጋቱን እያዩ ወደሌላው መተላለፍ ተገቢ ነው። እንደው በአንድ ጊዜ ይህን ከምላስ በስተቀር ቁም ነገር የሌለው ተራ ካድሬ ወደላይ ቆልሎ አንድ ጊዜ “አክቲቪስት” ሌላ ጊዜ ደግሞ “የፖለቲካ ተንታኝ” እያሉ በኢትዮጵያውያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅትን እንዲመራ ማጨት ድረስ መጓዙና አሉ ከሚባሉ ፖለቲከኞች ጋር መድረክ እንዲጋራ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ አገባብ አልነበረም።

የኢሳት ባልደረባ ደረጀ ሃብተወልድ የአባ መላን መገልበጥ አስመልክቶ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ ግን ኢሳቶች ከስህተቶቻቸው ሊማሩ የተሰናዱ አይመስልም ይልቁኑም አባ መላን አስመልክቶ ሊቀርቡ የሚችሉ ትችቶችን ቀድሞ ለመከላከል ነው ሙከራ የሚያደርጉ ያሉት። ደረጀ ሃብተወልድ እንዲህ ነበር ያለው፣

“ነገሩ ወዲህ ነው። አባ መላ ኢህአዴጎችን እየሰደበ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ሲቀላቀል “አገኛለሁ” ብሎ ያሰላው ጥቅም ነበር። ሆኖም ሀሳብን በነፃነት ለመግለጽ ከሚያስችል ነፃ መድረክ ውጪ ሌላ ነገር ሊያገኝ አልቻለም። ባገኘው ነፃ መድረክም ማንም ሳይቆነጥጠው ከትንሽ እስከ ትልቅ የቀድሞ አለቆቹን እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ነግሯቸዋል። እኛንም አስቆናል። ስንስቅለት ጨምሮ ጨማምሮ አቅምሷቸዋል። እኛም፦“የአገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ” እያልን ተዝናንተናል። ከዚያ ባለፈ ግን ለቁም ነገር ያሰበው ሰው ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ።”

ተጨማሪ ያንብቡ:    የተስፋ ጣዝማ - የአሻም ብራ! -ሥርጉተ ሥላሴ

የደረጀን አባባል ሁሉም ሰው የተቀበለው አይመስልም ይህን ለማሳየት ከተቃውሞ ሃሳቦች መካከል አንዱን ከዚያው ከደረጀ ሃብተወልድ የፌስቡክ ገጽ ልበደር፣

“የአባ መላን መገልበጥ ተከትሎ ኢሳቶች ከተወቃሽነት ለመዳን የዘየዳችሁት ይሄው ነው? ደረጀ “አባ መላን ለቁም ነገር ያሰበው ያለ አይመስለኝም” ያልከው ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፣ በሳውዲ ወገኖቻችንን ለመታደግ በተቋቋመው አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ከታማኝ እና አበበ ገላው ቀጥሎ ሶስተኛ ሰው ተደርጎ አልነበረም? በጣም ብዙ ማለት ይቻላል… “እጄን በጄ” ሆኖብን እንጂ። ለማንኛውም ከስህተቶቻችሁ ተማሩ፣ በጣምም አንፍጠጥ ያስተዛዝባል።” Ethiopian Unity

ለማጠቃለል ያህል የሚሰራ ጋዜጠኛ፣ ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ ፖለቲከኛና የዲሞክራሲ ታጋይ በሂደት ውስጥ ስህተት ሊሰራ ይችላል፣ ከስህተቶች ትምህርት ወስዶ ለሁለተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ስህተትን ላለመድገም ጥረት ማድረግ ግን ሊለመድ ይገባል። ነገሮቻችን ሁሉ “ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ” እንዳይሆኑ ሃላፊነት ወስደን ከስህተቶቻችን ለመማር ዝግጁ እንሁን።

13 Comments

  1. Esat is always naive and quick to jump in to a conclusion.guys patriotism by itself is nothing.u also should have to be able to smart enough as well….ut was obvious how they were in hurry to inflate this shailock….what about Tariku who said himself a bible preacher and human right activist who got huge amount of coverage from london base Esat….where is he now? not only God, we also knows….who is the next?..of course Dimitsachin yisema, who is weighting his perfect time to bend and start to assassinate the Ethiopian history from the back.

  2. This is a very clear indicator that the Opposition camp and the activists donot have any clear Guideline for recruting members and engage in various activities that are vital to strengthen the Impact of their role towards forcing the government to improve ist repressive rules back home.
    The first day a Person provides an opinion against the government the next day he is a guest on ESAT and also recieves a warm well come from most People without taking time to study the motives behind the Change of mind from supporting the government to become an Opponent. They should be challenged in many ways to compensate the damage they did while they have been promoting the interest of an oppressing Regime. A derg remains to be a derg and the same is true for woyanne. There is no any Logical reason for a human being in this world to propagate for a Regime which is against the interest of its own People starting from the beginning till to date. No record has been shown that the Regime had shown any slight move from ist original Situation in 1984.

    Some People are happy when they eat and drink and that is their ego. We cannot force them to think better since that is how they built up themselves.

    Jawar, Tesfaye gebreab, Dawit Kebede are very good examples that are doing what they like by understanding the Situation in the opposite camp. I am not sure how many mistakes one should make to understand the tricks by some People, which are trying to Play double Standard in their acts.This is how the Regime is doing ist work and the Opposition camp is still not half way to it. the Impact of this reluctance by the Opposition camp and the activists would have dear consequences in that it will discourage potential supporters from joining the Team. Please work on it and try to create a good mechanism for avoiding such crisis in the future, good luck

  3. “ባዶ ቀፎ ከፊት ሲም ካርድ ከኋላ
    ከፊት ያፋሽካል ከኋላ እየበላ
    ተጣርቶ አይመልስ መልሶም አይጠራ
    “Who is in Charge?”አለ ሰሚ አጥቶ ቢጣራ።
    በለው!
    “በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትቅም ላይ ጠንካራ አቋም አለኝ” አባ መላስ…. በኢትዮጵያ አየር መንገድ እረዳት አብራሪ ኀይለመድክን አበራ የጠለፈን አውሮፕላን ሳይ አስተሳሰቤ ተናወጠ…የኢትዮጵያ ጥቅም ሉዓላዊነት ተነካ ዘራፍ አለ። በለው!ግለሰቡ አቋሜን ለወጥኩ ሲል በድረ-ገፁ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራን ሶስቱን ቀለማት ወደ ጎን ስሎ ኮከቡን ውጭ አስቀምጦት ነበር፣ አንዳንዴ ልማታዊ ካድሬ ወደብ፣ አውሮፕን፣ዳርድንበር፣ ፻፶ሺህ ስደተኛ በአረብ ሀገር መደፈር፣ መደብድብ፣ መዋረድና አንገታቸው በሜንጫ ሲቀላ ለቁጥር መሙሊያና ለዝና አለቀሱ እንጂ ሀገርና ፓርቲ ይምታታባቸዋል ልማትና ጥፋት አይገለጥላቸውም…ሳይናገሩ የሚጨበጨብላቸው የራሳቸው አማኝ የዋህ ተከታዮችና ሆዳቸውን አቀብድደው ቱልቱላ የሚነፉበት መድረክ ስላላቸውና ስለሚመቻችላቸው እራሳቸውን በማግዘፍ ነው።

    ***”የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳን ጋር በድንበሩ ጉዳይ እየተዳደረና ተግባራዊ እያደረገ ያለው የቀድሞወች የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት እና የደርግ መንግስት ተፈራርመውት የነበረውን ነው ብሎ ተናግሮት የነበረውን አስመልክቶ የደርግ መንግስት ከሱዳን ጋር ምን የተፈራረመው ነገር አለ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ መንግስቱ ኃይለማርያም መስል ሲሰጡ ምንም የተፈራረምነው ነገር የለም። ኃይለማርያም እና ወያኔ ውሸታሞች ናቸው። ደርግ ከሱዳን ጋር የተፈራረመው ሰንድ ካለ ለምንድን ነው ወያኔወች ሰነዱን ለህዝብ ይፋ የማያደርጉት? …” የቀድሞው የኢ/ፕ/ ኮ/መንግስቱ ኃይለማርያም

    ***”የኢሕአዴግ መንግሥት ለሱዳን መሬት ቆርሶ የሚሰጥበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት ያደረገው ነገር ቢኖር አንድ ነው፡፡ በ1996 ዓ.ም. ከሱዳን ያለፉ አሸባሪዎች በአዲስ አበባ የግብፅ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ላይ የግድያ ሙከራ በመደረጉ ምክንያት በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ግጭቶች ነበሩ፡፡ በዚህ ግጭት ወቅት በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ ያሉ የሱዳን አርሶ አደሮችና ኢንቨስተሮች ተፈናቅለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ድንበሩ አካባቢ በተጨማሪ መሬት ክፍት ሆኗል፡፡ ይህ ተጨማሪ መሬት ክፍት በሚሆንበት ጊዜ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ይህንን መሬት ማረስ ጀምረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ቀደም ሲል ከነበሩ ስምምነቶች ተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው ነገር ቢኖር በዚህ መሬት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ባንነካቸው፣ አጠቃላይ የድንበር ማካለሉ ሥራ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ማንኛውም አርሶ አደር እንዳይፈናቀል የሚል ስምምነት እንዲፈረም አድርገናል፡፡ ይህንን ስምምነት የሱዳን መንግሥት ተቀብሎ ተጨማሪ ነገር ነው ያደረገልን፡፡ ስለዚህ እኛ የምናጣው የሰጠነው ወይም የምንሰጠው መሬት የለም፡፡ ስለዚህ ይህ ጉዳይ የሚነሳበት ትክክለኛ መነሻ የለም፡፡ አሁን የተከለለ መሬት የለም፡፡ የተከለለ መሬት በሌለበት ይህ ለዚህ ተሰጥቷል የሚባል ነገር የለውም፡፡ እንዴት እንደሚካለል ግን ከአፄ ምንሊክ ጀምሮ የተደረጉ ስምምነቶች መሬት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የተቋቋመ ኮሚቴ አለ፡፡ ነገር ግን ኮሚቴው ሥራውን ጨርሶ ያስረከበበት ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ ይህ ስምምነት ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ከሕዝብ ጋር ተወያይተን እንዴት ተግባራዊ እናድርገው የሚል ሥራ ወደፊት ይጠብቀናል፡፡ በቅርቡ በተካሄደው የሁለቱ አገሮች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የማካለልና የሕዝብ ማስፈር ጉዳይን ምን እናድርግ የሚል ተነስቷል፡፡ ይህንን ጉዳይ በሚመለከት የተቋቋመው ኮሚቴ ሥራውን አልጨረሰም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሥራውን አጓትቶታል፡፡ ስለዚህ ሥራውን እንዲሠራ ማድረግ ይገባል ከሚል ስምምነት በስተቀር ወደማካለል የሚያደርሰን ደረጃ ላይ አልደረስንም፡፡”ኃይለማርያም ደስአለኝ ከልማታዊ ጋዜጠኞች ጋር..

    ***”ይገርማል!።አንዳንዱ መሬቱ አሳልፎ ላለመስጠት ይሰዋል። ሌላ ደግሞ የሀገር መሬት በአሮጌ አውሮፕላን ይለውጣል፣ ይሸጣል። ወይ ህወሓቶች! የኢትዮጵያን መሬት እየቆረሱ ለመቸብቸብ ነው እንዴ ስልጣን የያዙ?
    በቃ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱ ተረጋግጧል። ዉሳኔው ሕገወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው። መሬታችንን እናስመልሳለን።” ..አብርሃ ደስታ ከመቀ(ቐ)ሌ(ለ)

    ***”የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው:: በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::” ጄኔራል ሳሞራ የኑስ…

    ***“ኢህሃዴግ አለቅጥ ሰብቷል በስብሷልም፤ በዚሁ ሁኔታው በቀጣዩ ምርጫ እንደ ዘጠና ሰባቱ በዝረራ መሸነፉ አይቀሬ ነው” ይለናል። እኛም ይሄንን ነገር ራሱ ቤን ከበደ (ከኢትኦጳያ ፈረስት!)ነው የሚናገረው ወይስ በላዩ ላይ ያደረው መንፈስ እየለፈለፈ ነው የሚለውን እያጣራን ነው። ቁምነገሩ ግን ቤንም እንደ ሌሎቹ ኢህሃዴግዬን “ላጥ በይ” ብሎ ሌላ ሊወሽምባት ከጅሏል ወይ ደግሞ ተለይቷት ፈት ሆኖ መኖሩን መርጧል። ዘንድሮ እንደሁ ክኢህሃዴግ የማይፋታ ባል እና ባላባት የለም… (እዘች ጋ ሳቅ አለ… )አቤ ቶክቻው እንደዘገበው።
    አባ መላ ኢህአዴጎችን እየሰደበ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ሲቀላቀል “አገኛለሁ” ብሎ ያሰላው ጥቅም ነበር። ሆኖም ሀሳብን በነፃነት ለመግለጽ ከሚያስችል ነፃ መድረክ ውጪ ሌላ ነገር ሊያገኝ አልቻለም። ባገኘው ነፃ መድረክም ማንም ሳይቆነጥጠው ከትንሽ እስከ ትልቅ የቀድሞ አለቆቹን እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ነግሯቸዋል። እኛንም አስቆናል። ስንስቅለት ጨምሮ ጨማምሮ አቅምሷቸዋል። እኛም፦“የአገሩን ሰርዶ ባ’ገሩ በሬ” እያልን ተዝናንተናል። ሆይ መላ ነሽ.. ሆይ መላ… ድንቄም አባ መላ? በለው! በቸር ይግጠመን

  4. Oh humanity!
    When you see that this planet produced people such as Moses, David, Jesus Christ, St. Paul and Peter, Leonardo Da Vinci, Sir Isaac Newton, Albert Einstein, mahatma Gandhi, Dr. Martin Luther King and the likes, that feels your heart with joy and hope. However, to know the same planet produced aba mela makes you depressed. The love of money is the root of all evil. I heard the interview aba mela gave to tplfites radio. The host made him apologize countless time. Aba mela must know that tplf does not play the game that aba mela wants to play. They got him now, and they got him big time.

  5. ለአባ መላ
    አባ መላ እኮ ነው ሌላ መሰላችሁ፣
    ተገለባበጠ ለምን ትላላችሁ ?
    ከኪህ ከእኛ ጋራ እንዲያር ፈለጋችሁ፣
    ቪስኪውን ይጠጣል ቢራውን ይጠጣል፣
    ያንን የሚሽፍን ወጭ የት ይመጣል፣
    ቪስኪ በሌለበት ቢራ በሌለበት እንዴት ይቀመጣል ?
    ምነው ተገርማችሁ ሄደ የምትሉት አልሄደም ይመጣል፣
    ቪስኪ ካመጣችሁ ቢራ ካመጣችሁ አብሯችሁ ይጠጣል፣
    እሱ መች ይዳረቅ እሱ መች ያርና ይገለባበጣል፣
    ኢሕአፓ መኢሶን ወዘተ የሚለው ታሪኩም ይገልጣል።
    ሆዳሞቹ ዉጡ ተገለባበጡ ትግሉን አትበጥብጡ፣
    ብትኖሩም አትጠቅሙ ለውጥ አታመጡ።

  6. enndelebu ,kkkkk i was laughing when i read your comment.do you have the moral to say anything on abba mella or esat while you sell the vibrant discussion forum current affair to weyane.esat was right as a media outlet to gave us the valuable information they get from abba mella,offcourse abba is weyane but he told us how courrupt weyane is and thier fake federal government for minors which works only for tigres and he expose weyane how cruel and fascist on the oromo ,amhara,and all nations and nationalites.eendelbu if you think this is the time to atttack esat and find a hole to make it a big deal because of one cellout weyane is nonsense.you better see your self and ask appology first for the offended ethiopians because of your do nothing current affair room which you gave it to weyane.there is a steel a chance if you are series on your comment to make your ecadf room for the good of the ethiopians.instead of working for weyane and upgrade your website on very current ethiopians issues.and do not forget we are a society of culture belife and moral. the picture you have posted on your website does not refelect our moral value .we ethiopians have so many problems to deal with not the picture u posted .

  7. Once a woyane , always a woyane. So i hear a small time two faced turd by the name of Berhanu Damte aka Aba mela is stinking up the cyber space with his small time talk about toxic diaspora politics and politicians. He came down hard on everyone from individuals to political groups accusing them as lackeys of foreign powers such as Eritrea and Egypt who have ill feelings towards Ethiopia. His excuse for jumping ship according to him was diaspora Ethiopians misguided position about Hailemedhin Abera, the hero who diverted Ethiopian ( now woyane ) airlines to Switzerland to seek asylum.Aba mela insulted diaspora Ethiopians intelligence by making up a stupid excuse to abandon ship. To the credit of diaspora activists, no one fell to his con game and as a result he was unable to accomplish his mission–collecting diaspora best kept secrets. Time and again, woyane outed its covert agents at crucial times when the going got tough or when the earth moved under their feet. It is a counter measure designed to control damage, confuse the diaspora, and to stop opposition’s push on its track. It is also safe to assume Aba mela forced to come out to control the looming disaster due to Hailemedhin’s defection and the consequences of giving away Ethiopian land to the Sudan. When the shit hits the fan, many more woyane sleeping cell members masquerading as the opposition will come out of the closet in great numbers. We shall witness character assassinations and fabricated evidences in the coming days and months. The question then is why would people like Aba mela try to resurrect a seriously ill regime from its death bed? Why woyane took the chance of outing Aba mela now as opposed to waiting for a while? It is because they are running out of options. The end is near and they know it. It is a matter of short time before woyane collapse to smithereens. In the opposition camp fear is giving way to courage and death is not a factor anymore. That point was proven the other day with the women’s 5000 meters run. A tsunami is about to sweep woyane off their feet. All hell is about to get lose within this calendar year effectively ending woyane’s minority rule over Ethiopia. Aba mela’s gymnastics is part of woyane’s desperate moves to divert attention. The opportunist, two faced loser will have his day in court for aiding and abetting the worst criminals who ever walked this earth. Judgement day is around the corner!

    LONG LIVE ETHIOPIA!!!
    FREE ALL POLITICAL PRISONERS IN ETHIOPIA!!!!

  8. ሆ! ምንድን ነው ይህ የምሰማው ወሬ? እውነት አባ መላ እንደገና ወደወያኔ ተገለበጠ ነው እምትሉኝ ያላችሁት? ከመቼው? “መቼ መጣሽ ሙሽራ፣ መቼ ቆረጠምሽ ሽምቡራ” አሉ፡፡ ይህን ጽሑፍ አባመላ ማንበብ አለበት፤ ከዚያም እውነተኛውን ተገቢ መልስ መስጠት ይጠበቅታል፡፡ የሚፈጥረው ውዥንብር ቀላል አይደለም፡፡ እኔ ምሣየን እንደምንም ምንም ነገር ቀምሼ ለእራት የምጨነቅ ከቤተ መንግሥት በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ውስጥ የምገኝ ምስኪን ዜጋ በ23 ዓመታት ውስጥ አንዴ እንኳን ወደ ወያኔ ሳልገለበጥ አሜሪካን ያሉ ምናልባትም ከኔ ይልቅ የደላቸው ሰዎች እንዴት ብዙ ጊዜ ይገለባበጣሉ? ነጎሩ እውት ከሆነ የዲኤንኤ ምርመራ ያካሂዱና ወደአንድ የሚቀርባቸው ሆስፒታል ሄደው የዲኤንኤ ቅያሪ/ለውጥ ያካሂዱ፡፡ ከስቃያችን ጎን ለጎን ሳቃችንም እኮ አላባራ አለ፡፡ ለዚህ ሁሉ ጉድ ለመገልፈጥ ጥርስስ የት ይገኛል – በሚሰማውና በሚታዬው ግርምቢጥ ጉድ ሁሉ በለበጣ ሣቅ ለመንፈቅፈቅ ደግሞ ጥርስ እንለምን? እስ በሞቴ ወደወያኔ እንዴት እንደሚገባ መንገዱንና ዘዴውን ጠቁሙኝ፡፡ አሁንስ መሮኛል፡፡ ይበልጥ ያስመረረኝ ደግሞ በተቃውሞ ጎራ የሚታየው ጠርዝ የለቀቀ ቀልድና ጨዋታ ነው፡፡ ሕዝብ በርሀብና በስደት እያለቀና በምሬት እየተንገፈገፈ እነሱ የሚሠሩትንና የሚለዋወጡትን የነገር ሞርታር ስታዩ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ሰብኣዊ ስሜት ያላቸው ሰዎች ይሆኑ ይሆን? ብላች ለነሱ ለራሳቸው ልትጨነቁላቸው ትችላላችሁ፡፡ እኔስ ሳስበው በየሥርቻው የሚጣለው እንግዴ ልጅ በድብቅ ነፍስ እየዘራ ወደተቃውሞ ጎራ ሳይቀላቀል የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እንደዚያ ካልነ እንዴት ቆም ብሎ የሚያስብ ልብ ያለው አስተባባሪ ሰው ይጠፋል? እንግዴ ልቹ በተቃዋሚና በወያኔነት ተቧድነው ሲቆራቆሱ ጤነኛው ልጅ በአፈ ሙዝ ተኮድኩዶ የእግዚአብሔርን የብርሃን ቀን ይጠብቃል፡፡ ያም ቀን ጅቦችና ዝንጀሮዎች ከሚያደርጉት የጦፈ ጦርነት ማግስት ጀምሮ እውን ይሆናል፡፡ ወዮ ለልክስክስ ዓሣሞችና ጅቦች! ወዮ የገዛ ትውከታቸውን ለሚመገቡ እሪያዎችና ውሾች! ወዮ ከሰውነት ላነሱ ሆዳሞችና አቋም የለሾች! ወዮ! ቀን አይተው ለሚከዱ ግልብ ራሶች! …
    ወይ ኢትዮጵያ ፣ እንዴቱን ያህል የላግጣና የቀልድ ሀገር ሆነሻልና! እግዜር በምሕረቱ ይጎብኝሽ ከማት ውጪ ምን እንላለን? ተናደን ተናደን ከነጭ ፀጉርም አልፈን ቀንድ አበቀልን – ቀንድ! ግን የቀልዱና ፌዙ ዙር እየከረረ እንጂ እየቀነሰ ሲሄድ አይታይም፡፡

  9. Enndelubu, first of all you have no gut to tell esat about wrong doings while you are a vagabond dude who uses insult and characther assisination for anyone who doesnt agree with you in your paltalk room as a result you have make sure that you are either insulting and barking like a mad dog against anyone who opposes your stupid arrogant idea, secondly you are not diffrent from aba mela when it comes to money as your priority is money and you are doing everything to collect money in your room in the name of the struggle, and finally you have to understand that ESAT is a media and as a media esat is always striving not only to give a forum for aba mela but also esat is trying its best to give a forum for the current weyane leaders and its servants, however for a stone head and arrogant nonsense lempon dude who doesnt know anything about the ABC of politics except screaming day in and day out in your paltalk you think esat should only give for a forum for selective individuals, and before you run to write your long garbege attacking esat first of all you should wake up from your nonsense dream and learn how politics can be played, secondly before you point out your stincky fingers on others you should open the doors for other alternative ideas in your room and allow anyone to critisize your stupid idea, in stead of using stupid path in creating an arrogant group to attack individuals who doesnt share your nonsense crippled idea….shit head shame on you

  10. I don’t understand why all these fuss about aba bela. By the way, aba mela refers to the great patriotic Ethiopian HabteGiworgis Denegde not opportunistic parasites like aba bela. I want to congratulate the opposition Diaspora that the tumor is removed. Now it is up to the woayne camp to keep an eye on him. Because everyone realizes that this dude can flip flop better than the Olympic gymnasts and available for sell for the highest bidder. Regarding ESAT, I do not believe that interviewing him is a mistake. ESAT interviewed him as a defector but never offered him a job that he was hoping for. We can use his own words and interviews to bash, trash, name and shame himself and as well as the regime. I am just wondering how he will blend the system he used to call racist and corrupt as well as in his own words, “fogariw” Meles and the “prostitute” Azeb camp…..kkkkk…..woayne camp, enjoy aba bela….hahahaha

  11. በጣም ገረመኝ፡፡ ከገረሙኝ ነገሮች አንዱና ዋናው የጊዜ ርዝማኔው ነው፡፡ መገልበጡን መጠበቅም ከነበረብኝ ልጠብቀው ከምችለው እጅግ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ነው የተገለበጠው – የተዋጣለት አክሮባትና የአእምሮ ህመምተኛ መሆኑን አስመስክሯል፤ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ላይ አስመዝግቡት – እንደዚህ ያለ ፈጣን ተለዋዋጭ መኖሩን ሰምቼ አላውቅም፡፡ የለውጡ ዓይነት ደግሞ ከጨለማ ወደ ብርሃን ዓይነት subliminal ነው፡፡ የሰው ልጅ በባህርይው እንዲህም ነው፡፡ የርሱ ባሰ እንጂ፡፡ ሲናገር እኮ ያፈዛል፡፡ ለነገሩ “ሰይጣንም ለተንኮሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል” ይባላልና ሰውዬው የሚያደርገው ሁሉ ለእኛ ለሞኞች እንጂ ለርሱ መደበኛና ጤናማ ነው፡፡
    አንድ ግብረሶዶማዊ ወይም ሌዝቢያን ወይም ሌባና አጭበርባሪ ድርጊታቸው ለነሱ ለራሳቸው በጣም “ጤናማ” ነው፡፡ ጤናማ የማይሆነው እነዚህ ነገሮች ለማያደርጉ ሰዎች ነው፡፡ በሥነ ልቦና ትምህርት እነዚህ ሰዎች በሽተኞች ናቸው፡፡ በሽተኞች ተደማጭነትና ከበሬታን ካገኙ ግን ችግር ነው፡፡ አንደኛ አድማጩና አክባሪው በቅድሚያ ይጎዳሉ፡፡ አንድ ሰው ነበር – በእግዚአብሔር አያምንም አሉ፡፡ እሱ ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በእግዚአብሔር እንዲያምኑ የሚያደርግ የአነጋገር ለዛና ተሰጥዖ ነበረው፡፡ ዳምጤም መርዝ በተደበቀበት በማር የተለወሰ አንደበቱ አነሆለለንና “ሰው አገኘን” አልን፡፡ ግን ግን ድመት መንኩሳ ዐመሏን እንደማትረሳ ይህ በሽተኛ ሰውዬ የዋሆችን ጉድ ሠርቶ ወደካምፑ ተመልሷል ማለት ነው፡፡ በበኩሌ “ ይህ ክስተት መማሪያ ይሆነናል” ማለቱ ጅልነት ይመስለኛል፡፡ እስከመቼ እየተጃጃልን እንኖራለን፤ እስከመቼስ የአጭበርባሪዎች መናኸሪያ እንደሆን እንቀራለን፡፡ ይህን ሰው ጅባት ብሎ መተውና ወደፊት መቀጠል ነው፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው፡፡ እንዲህ ያሉ እስስቶችና አጋሰስ ጌኛዎች መኖራቸውን ማወቁ በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን ትምህርት ይሆናል ከሚል ሞኝነት ማንንም አፈጮሌ እያስጠጉ ጓዳ ጎድጓዳን ማስቧጠጥ ደግ አይደለምና ለወደፊቱ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ በአንድ መጣጥፌ የአባ መላ ነፍስ መግዛት ጥሩ መሆኑን ጠቅሼ ነገር ግን ለተንኮል አለመሆኑ ይጤንበት ማለቴን አስታውሳለሁ፡፡ ለውጥ አለ፡፡ ነገር ግን የለውጥን እውነተኝነት መመርመር ተገቢ ነው፡፡ አለበለዚያ ሰውን ማመን ቀብሮ ነው እንዳለችው እመት ቀበሮ በውብ ቋንቋ እየከሸነ የሚናገርን አሰለጥ ሁሉ እንዳለ ተቀብለን ከፈዘዝን ኤድስ የያዘው ቆንጆ ሰው አነሁልሎ ቢተኛን የምንሆነውን መሆን ለመሆን መስማማት ነው፡፡ የዚህ ሰው በሽታ ሆድና በየትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ስመጥርነትን ማግኘት ነው፡፡ በሰይጣን ቤትም ይሁን በእግዚአብሔር ቤት ዋናው ሹመቱን ያግኝ እንጂ ስለምክንያታዊነቱ ሃሳብ አይገባውም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው የራሱ የሆነ አእምሮ የለውም – ማሕጸን እንደሚያከራዩት ዓይነት ድሆች የፈረንጅ ሀገር ሴቶች እርሱም ብልጣብልጥ አንደበቱንና ቀፎ ጭንቅላቱን በገንዘብ እያከራዬ መኖር ነው ሥራው፡፡ እንደተባለው ልጁንም ሸጦ ቢሆን ገንዘብ ከማግኘት ወይም በዝና ማማ ላይ ፊጥ ከማለት አይመለስም፡፡ የሰውን ባሕርይ አንዴ ማወቅ ነው፤ ከዚያ መጠንቀቅ፡፡ ከዚህ በኋላ ስለርሱ መነታረክ በፈሰሰ ውሃ መጨቃጨቅ ነው፡፡ ይልቁንስ ገና ያላወቅናቸው ብዙ በሽተኞችና እስስቶች አሉ፡፡

Comments are closed.

Share