የህወሓቶች ገመና ሲጋለጥ (ከአብርሃ ደስታ)

የካድሬው ወንጀል በማይጨው ሆስፒታል
====================

ብርሃኑ ሃይለስላሴ ይባላል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ ጥናቱን ትቶ በካድሬነት ተግባር የተሰማራ እንደነበር አውቃለሁ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምንማር የትግራይ ልጆችን እየሰለለ ነበር የሚውለው።

ተመረቀና በህወሓት አባልነቱ መሰረት የትምህርት ዉጤቱ ግምት ዉስጥ ሳይገባ፣ ሳይወዳደር (ሌሎች ብቁ ሰዎች እያሉ) በእምባ አለጀ ወረዳ የጤና ጥበቃ ሐላፊ ተደርጎ በፓርቲ በመሾሙ ዓዲሽሁ ከተማ ገባ። በዓዲሽሁ ከተማ ብዙ ሴቶችን ደፈረ። ህዝብ ጮሆ። ሰሚ የለም። ምክንያቱም ሐላፊ ነው።

ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከመክሰስ ይልቅ ሌሎች ሰራተኞች ያላገኙት የማስተርስ ትምህርት ዕድል ተሰጠው። ሴቶች ስለደፈረ ተሸለመ ማለት ነው። በጦላይ ለስልጠና ተልኮ እዛም ሌላ ሴት ደፈረ። የተደፈረች ሴት የሕግ ከለላ አጥታ ከሱ ጋር እንድትታረቅና ክስ ላትመሰርት ተገደደች።

ከስልጠና በኋላ ህወሓቶች የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል CEO አድርገው ሾሙት። እነሱ ምን ይሳናቸዋል!? በማይጨው ከአንድ ዓመት ባልበለጠ ግዜ ዉስጥ አስራ አራት ሴቶችን ደፈረ፤ ስልጣኑን ተገን በማድረግ። ሴቶች አቤት ይላሉ። ግን ሰሚ የለም። በማይጨው ሰው በመኪና ገጨ። ራሱ ሰው ገጭቶ ሽፌሩ እንደገጨ ለማስመሰልና ከቅጣት ለመዳን ከሽፌሩ ጋር ተዋዋለ። ክስ ተመስርቶበት፣ በፖሊስ ተይዞ በስድስት ሺ ብር ዋስ ተለቀቀ።

ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም የማይጨው ኗሪዎችና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ቅሬታ አሰሙ። ረበሹ። ተሰበሰቡ። የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተሰብሰበው ከፓርቲ አባልነቱ እንዲወገድ ጠየቁ (ምክንያቱም የገዢው ፓርቲ አባል በመሆኑ ስልጣኑ ተገን አድርጎ ነው ግፍ እየፈፀመ ያለው ከሚል እሳቤ)። ከስራ (ከሐላፊነቱ) ታግዶ በፖሊስ እንዲያዝ ወሰኑ። ቢሮው ታሽጎ ሁለቴ ቁልፍ ሰብሮ መግባቱ ተረጋገጠ። ማንም አልጠየቀውም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የታላቁን ወር ረመዳን መግባት አስመልክቶ ከታሳሪ ጀግኖቻችን የተላለፈ አጭር የ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› መልእክት - ከድምጻችን ይሰማ

አቶ ብርሃኑ ሃይለስላሴ በሰራተኞቹ ስብሰባ ቀርቦ ሁሉም የተጠቀሱት ወንጀሎች መፈፀሙ አምኖ ይቅርታ ጠየቀ። በተበዳዮቹና ሰራተኞቹ ግፊት በፖሊስ እንዲታሰር ተደረገ። ህዝቡ ተረጋጋ። እኛም “ኮርማው ታሰረ!” ብለን በፌስቡክ ፃፍን። ህወሓቶች ለምን አስራ ስምንት ሴት እስኪደፍር ድረስ ዝም አሉት? ሕግ ለካድሬዎችስ አይሰራም ወይ? ብለን ጠየቅን። የህወሓቶች አድሎአዊ አሰራር ወቀስን። መታሰሩ ግን ጥሩ መሆኑ ጠቆምን።

አቶ ብርሃኑ በፖሊስ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ መለቀቁ ሰማሁ። መለቀቁን አስመልክቼ በፌስቡክ ፃፍኩ። መለቀቁ ግን በሌላ አካል አልተረጋገጠም ነበር።

አሁን ከአስራ ስምንት ሴቶች በላይ የደፈረ ባለስልጣን ምን ቢቀጣ ጥሩ ነው!? አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት አቶ ብርሃኑ አልታሰረም። ወደ ሌላ የስራ ቦታ ተዛወረ እንጂ። ህወሓቶች አንድ ባለስልጣን ወንጀል ከሰራ ባለስልጣኑ ከመቅጣት ይልቅ ወደ ሌላ የስራ ሐላፊነት ይቀይሩታል። ቅጣት ግን የለም። ሽልማት እንጂ።

አሁን አቶ ብርሃኑ ከዞን (ከማይጨው) ወደ ክልል (መቐለ) የስልጣን እርከን አድጎ በመቐለ የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ የHMIS ዲፓርትመንት expert ሁኖ በሙሉ ደሞዝና የተሻለ የሐላፊነት ደረጃ እየሰራ ይገኛል። ይህን ጉዳይ የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ሐላፊዎች አረጋግጠውታል። ለምን የሚል ጥያቄም አስነስተዋል። አሁን በማይጨው ሆስፒታል ሰራተኞች ጥሩ ስሜት የለም።

አሁን እንደሰማነው ግን ከእሰር የተፈታው በህወሓቶች ነው። በክልል ጤና ቢሮ እንዲሰራ ትእዛዝ ያስተላለፈውም አቶ ሃይሉ አስፈሃ የተባለ የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳድሪና የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ ነው። የሆስፒታሉ ሰራተኞች ይሁኑ የቦርዱ አባላት ሳይሰበሰቡና ምንም መረጃ ሳይኖራቸው አቶ ሃይሉ አስፈሃ (የቦርዱ ሰብሳቢ) ግን የቦርዱ ዉሳኔ እንደሆነ አድርጎ ደብዳቤ በመፃፍ በክልል ጤና ቢሮ እንዲቀጠር ማድረጉ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰው በተፈጥሮው ልዩ ና ግለሰባዊ ነው መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ባሁኑ ሰዓት በማይጨው ከተማ ኗሪዎችና ለምለም ካርል ሆስፒታል ሰራተኞች በከባድ ቀውስ ዉስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ችያለሁ። የማይጨው ህዝብ በዋና አስተዳዳሪው አቶ ሃይሉ አስፈሃ ከፍተኛ ቅሬታ እያነሳ ሲሆን ህወሓቶች ለህዝብ ያላቸው ንቀት እያሳዩን ነው በሚል የተቃውሞ መንፈስ እንዳለ ከማይጨው ኗሪዎች የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

አይ ህወሓቶች መቼ ነው ለህዝብ ደህንነት የምትቆሙ? በትግራይ የሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች ቢጋለጡኮ ስንት ጉድ በሰማን ነበር! ይህን ጉዳይ እስከመቼ እንችለዋለን?!

በህወሓት እምነት የለኝም። ከዚህ በላይ ምን ሊያደርገን ይችላል!? እናንተስ?

It is so!!!

6 Comments

 1. His name is Brhane Haile Selassie? How about calling him Darkness Haile diablos. When you see Andualem, Eskindir, Bekele, Reyot, and Co. in prison and rapist, looters, murderers, torturers out on the street, there is something fundamentally wrong about that country.

 2. Don’t we have one LAWER to organize evidence about the 18 Rape cases, and put him in Jail??
  I mean just one ….Humble and professional Lawer?
  Don’t tell me judges crap!
  Just organize the cases and put him on trial., then report what happens at the court to the public…let the Public know it!!
  Let the voters know it!!

 3. The corrupt ethno-fascist TPLF thugs carry out rape, murder and looting and get away with it. Victims go to the kangaroo courts and instead of receiving judgement they get accused fr challenging the corrupt TPLF mafia and end up in jail.

 4. ሰላም አብርሃ – እኔስ ስትጠፋ ምን ሆኖ ይሆን በማለት አስቤ ነበር። እስቲ ሰላም ያርግህ! ወያኔ ወንጀል መስራትና ሰውን በውሽት ማስር፤ ማፈን ገና በርሃ እያለ የተካነው ብልሃት ነው። አሁን ያካፈልከን ወሬ በተደጋጋሚ በተለያዬ የሃገራችን ክፍሎች የሚፈጽሙት እንጂ በትግራይ ብቻ የተወሰነ አይደለም። አሁን የወታደራዊ ኤታማጅር ሹሙ አቶ ሳሞራ ሁለት ሴቶችን ወያኔ በረሃ እያለ ይደፍራል። ሚስጥሩ እንዳይታወቅበት ሁለቱንም ሴቶች በፓለቲካ ሰበብ እንደረሽናቸው የዓይን ምስክሮች ያወሳሉ። እኔ ደግሞ ካየሁት አንድን ጀባ ለበልህ። አንድ ሰው አዲስ አበባ ውስጥ በነፍስ ግድያ ይፈለጋል። ፎቶው ሁሉ በየስፍራው ተለጥፎአል። ለሥራ ጉዳይ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረ በህዋላ ወደ ሰሜናዊው የሃገራችን ክፍል አምርቼ አንድ ሆቴል ውስጥ ቡና እየጠጣሁ ያ የሚፈለግ ሰው ብቅ ይላል። ዓይኔን ማመን አቅቶኝ ደጋግሜ በሥርቆት ካየሁት በህዋላ አስተናጋጅዋን ስሙ ማን እንደሆነ ስጠይቃት በለሆሳስ አስረግጣ እሱ እንደሆነ ነገረችኝ። እከታትላም የእነርሱ ሰው ስለሆነ ይጠንቀቁ አለች። እኔም በስውር (periscope view) ተጠቅሜ ፎቶ አንሳሁትና ለአ.አበባ ምርመራ ክፍል ኢ-ሜል አደረኩላቸው። መልሳቸው አንድ ነበር። ፎቶውን አጥፋው፤ እኛም የላከውን ሰርዘነዋል። ለአንተም ለእኛም ጥሩ አይደለም። ይህ ወንድማዊ ምክራችን ነው ይላል።
  ወያኔ ማፊያ ነው። የሰው ደም በአንድ ቦታ አፍሰው በሌላ ቦታ ሂደው ይንፈላሰሳሉ። ወይም ምን ይመጣብናል በሚል ትዕቢት ወንጀሉን በሰሩበት ስፍራ ከወንጀል ወንጀል እየጨመሩ ይኖራሉ። ማንን ፈርተው? የአንተም ታሪክ ያኑኑ ነው አጉልቶ የሚያሳየን።

 5. It is an atrocious crime committed by Berhanu Haileselassie..Shame on the TPLF thugs for not taking disciplinary action. This is contempt for the valiant people of Tigray.

 6. ‘ጉድ በል ጎንደር!’ የሚለው ነባር ብሂል ‘ጉድ በይ ትግራዋይ!’ ወደሚለው ተለወጠ ማለት ነው:: የሚገርም አሳዛኝ ታሪክ ነው:: ወያኔ ከዳር እዳር አሸንቶናልና:: እንዴ? እንታይ’ዩ ጉዱ? እንታይ ክሳብ ክገብሩና ኢና ንፅብዮም ዘለና? ካብዚ ዝበለፀን ካብዝን ዝገደደን እንታይሞ ክገብሩ ይህሉ? እንታይ አይነት መኣት እዩ ብላእሊ ኩሎም ህዝብታት ኢትዮዽያ እንዳወረደ ዘሎ? እቶም ወየንቲ አህዋትና እዝንን አይኒን የብሎም’ዶ?
  ወያኔዎች ሆይ! እግዜርን ባታውቁትና ባትፈሩት እባካችሁን አባታችሁን ሰይጣንንም ቢሆን እፈሩት:: ዋይ ለሚ ዘመን! ትሃልፍ’ዶ??

Comments are closed.

Share