አርቆ ለማየት ግመል ጀርባ ላይ መቀመጥ ያስፈልገናል ወይ? – ከመኳንት ታዬ (ደራሲና ገጣሚ)

ከመኳንት ታዬ(ደራሲና ገጣሚ)

መሬት ከሠው ልጅ ጋር ቁርኝት ካደረገችበት የዘመን አመታት ከዚህ ግዜ ጀምሮ ሀጥዑ ነበር። ከዚህ ግዜ ጀምሮ ፃዲቅ አልነበረም ብላ ለፈጠራት ያማረረችበት ርዕስ አልተፃፈም።መሬት ከአፈር አፈር ከሰው ልጅ አለና እንዲህ ባለ የእድገት ርዝማኔ ውስጥ የትዬእለሌ የሆኑ በክንዋኔዎች ተካሂደው ዘመነ ፍዳ አልፎ ዘመነ ድህንነት ተተክቶ እንደየ ግዜው ብልጠትና ጥበት ብሎም እድገት እየተራዘመ መጥቶ ዛሬ ላይ ደርሰን። ዛሬ የሰጠንን ጨምረን ሸክፈናል።

እንደ መግቢያ ከላይ ያለውን ካልኩኝ በሗላ አርቆ ለማየት ግመል ጀርባ ላይ መቀመጥ ያስፈልገናል ወይስ በአይነ ህሊናችን ቅርቡንና እሩቁን ጅምሩንና ጭርሱን፤ እየሆነ ያለውንና መፂውን መተለም በእውኑ ከእኛ ያለ ገንዘባችን አልነበረም ወይ?የዚህ ሁሉ ጥያቄ ባለቤቱ እራሱ የእኛ ሠው ይሆናል።ፅሁፋችን አማርኛ ፀሃፊው ኢትዮጲያዊ እንደመሆኑ መጠን ጉዳዮቹ እኛን ይመለከታል። ሥለእኛም ያሳውቃል። ስለዚህ በዝርዝር አጠር በላ ዝርዝር ከተከመረው ጉዳያችን ለመቀነት የሚበቃውን ጥጥ እንፍተል።

ፖለቲካችን

ፖለቲካችን ልክነቱ በቋንቋችን በባህላችን በአጠቃላይ በኢትዬጲያዊ ስልጣኔአችን ብሎም በትውልድ መሃከል ባለ የእድሜና የአስተሳሰብ ደረጃ መሆኑ ይገመታል። የጠነከሩት ክሮች ለጋቢ ሲበቁ የነተቡት ተበጥሰው ከመንገድ እየቀሩ የሸማኔው ቆሻሻ ሆነው ተጠርገው ይወጣሉ። ይሁን እንጂ ለፈታዩ ክሮች ሆነው ቀሰሙን ሞልተው ሸማኔው ጋር ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።ይሁንና እንዲህ ባለ ጥሎ ማለፍ ጫወታ ሸማኔው በየፈርጁ ለብሶ ውበቱን ትውልድ እንዲጠቀምበት እንዴት እና በምን ምክንያት ከትከሻ ትከሻ እንዴት መተላለፍ እንዳለበት ፖለቲካ እራሱ ገዢ መሬት አለው። ሆኖም ግን የፖለቲካው ሸማኔ ድርና ማጉን እየመረጠ ፋሽኑን እየቀየረ ለገበያ ማቅረብ ያለበትና ከባለፈው ስራውና አሁን እየሰራ ካለው ገበያተኛ የወደደውን ወይም በርከት ያለ ሸማች ያለውን ማቅረብ ግድ ሳይለው እንደማይቀር ፖለቲከኛ ሆኜ ባላየውም የማነበው አልጠፋምና ሳይበዛ የተገነዘብኩ ይመስለኛል።

ታዲያ የተከበረው የፖለቲካ ጥበብ ከምን ተነስቶ ምን መድረስ አለበት የሚለውን በሚሊዬዎን ለሚቆጠሩ አዋቂዎች ለመንገር አይዳዳኝም። ግን ለቀባሪው ማርዳት የሚለውን እንኳን ትተን፤ ሊያረዳ የሚመጣ ካለ ያልቀበረም ማስታወስ ይችል ስለመሰለኝ ነው። እንደማለዘቢያነት የእኛ ሃገር ፖለቲካ ጫወታ መንቹ ሲወረወር ብዙ ግዜ የሚያርፈው የትውልድ መስመር ላይ እየሆነ መፎረሹ አልቀነስ አለንሳ። እንደ አብነት የትላንቱ ደርግ. በኢሃፓ ሰበብ ኢትዮጲያ መቼም ቢሆን ልትተካቸው የማትችለውን ትውልድ እንዳጣች ታሪክ ይዘግብልናል። የአሁኑ ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ አስከ ነገ የምታጣውን እየሰራ ነው ።የነገው ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚቺል መገመት ያስቸገራል። “ያልዘሩት አይበቅልም “ብዬ ለመናገር ፈራለሁ። ምንአልባት ድንጋይና ድንጋይ ሲፋጭ እሳት ይፈጥራልና እርሱም ከነደደ ከበርሃንነቱ በዘለቀ ትውልድ አብስሎ የሚበላበት ይሆን ይሆናል።የሗለኛውና የፊተኛው ድንጋዮች ታገጭተው የፈጠሩት እሳት።ወደፊት ተራምዶ የታሻለ ገመድ የማይስብበት ነገር አለ አልልም ።ይታየኛል እና።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወድቃ አትቀርም የኛ እናት!

ግን የእኛ ሓገር ፖለቲካ ፤እንደምጣዳችን ፤እንደ እንስራችን አፍ እንደ ሌማታችን ፤ክብ ክብ የመሆኑ ሚስጥር ይሆንን? ኳስ አንድ አንግል መያዝ አቅቶአት ዘመኑ እና ትላንቶቹ ተቀይረው የዛሬዎቹ ቢመጡም ትውልድ ለነገ እንደ ግብ የሚቆጥረው ያጣ ይመስላል። ዘመኑ ሲሻገር፤ ትልቅ ጉዳይና መልካም ቢሒል ይዞ መሻገር ይፈልጋል። ሂሳቡ ሲሰላ በአስተሳሰብ + የህዝብ ስልጣኔ + የህዝብ ብዛት ውጤቱ አንድ በጣም የተሻለ ነገር መሆን ነበረበት ። ግን ያ የለም። ታዲያ ምን አለ፤ “አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ “? ቦታ ቀይሮም የበቀለበት ቦታም ቢሆን “ስምና ምን አልባት ብሔር ቀይሮ ያው ያለውን መተወን። “ሺ ቢታለብ ያው በገሌ”።

ግን አስከመቼ? ሌላ ጥያቄ። ያኔ በሗለኛው ዘመን ከሚኒልክ ወደ ሐይለስላሴ ስንሸጋገር በዘመኑ ያልነበረውን ነገር በመጨመር የተሻለ እየሆነ ዛሬ የምናነሳው ነገር አገኘን። ውሕደቶቹም ከደርግ ወደ ኢሕዴግ እያለ መጣና ትውልድን እንደ ግራዋ ማጣንት በሩቅ የሚያስሉት እሴቶች የሚታዩ ይመስለናል። አበስኩ ገበርኩ አለ የሐገሬ ሰው። በዚህና በዚህ ምክንያት 1+1 በስምምነት በሚመጣ እውነት መሃከልና 1+1 ከእውነት በተገኘ አንድነት በሚነሳው ጥግ የማይስቡት ርዝመት ተከስቶ እውነት የሆነውን እምነት ትላንት የነበረው አለንጋ እጅና ደጅ ቀይሮ ስለመታው ወይም እየመታው ግርፍ ያረፈበት ሰንበሩ እየባሰ መጣ። በዚህ ሁነት የእኛ ሐገር ፖለቲካ ከየት ተነስቶ የት ሊደርስ ነው? ብሎ ዘመኑ ሲጠይቅ መላሹ ማነው?

እምነታችን

በዚህ ርዕስ ሐላፊነቱን ለመውሰድ እኔው አለሁበትን እምነት ብቻ ላንሳ። የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ክርስቲያንን።

መጀመሪያ ቃል ነበር ። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር። ቃልም በእግዚያሐብሔር ዘንድ ነበር(ዮሃ1፤1) እንዲህ እያለ ሲጀመር ሲፈፅምም መያዣ ያደረገው ፈጣሪውን እንደሆነ ለምስክርነት ከገነት የተባበረረው አዳም አሁን እራሱን እያባረረ እስከሚኖርባት ዘመን ድረስ ከአምላኩ ጋር ቁርኝት ያደረገባትንና የጌታችን የመድሀኒታችን ደሙ የነጠበባትን ደጀ ሠላምን እንደ መሰላል ተጠቅሞ በቅዱስ ስራውና በንስሃው ዘውትር እየወጣና እየወረደ እየተገለገለባት ይኸው አለ። ስለዚህ በአሁኑ ሁነት የሐጢያት ደረባ ፈርሶ አከባቢውን ሲያቆሸሸ ማየት የአማኞች ፍቃድ አደለም።እርግጥ ነው አማኞቹ እኛው ከሃዲዎቹ እኛው ሥለሆንን እኛን ብቻ ማየቱ ፅሁፌን እድሜ ሥለሚያራዝምልኝ ከእኛው ጋር እየታገልኩ ላብቃ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞሳድ የበላው ነጭ ድመት - ሱሌማን አብደላ

እንዲህ ሆነ። አለቃ ገብርሃና የታባሉ የሗለኛው ዘመን አስቂኝ (ኮመዲ) በአንድ ወቅት የሆነ ቦታ ላይ እክል እንዲገጥማቸው ተደርጎ ነበርና ያንን ለማምለጥ እንዳውራ ደሮ ጮኹ ተባለ። (ዛሬ ቢኖሩ ደሞ ግራ ሲገባቸው እንደ ሲካካ ዶሮረ ይጮኹ ነበር) በዚህ ግዜ ነገር ያዘጋጀው ሰው ከምሃከል ተነስቶ “አለቃ ምነው?”ቢላቸው “አለቃም ለዚህ ሁሉ ዶሮ አውራው እኔ አደለሁም ወይ? አሉ ይባላል ።ቕድስት ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ናት።ለእኛ ከጥበብ ጋር የመኖር ሚስጥር፤ካባሕላችን ጋር የመኖራችን ሚስጥር አረ ስንቱ፤ ብቻ ከእኛነታችን ጋር የመኖራችን ሚስጠር ፤የኢትዮጲያውያን ከብዙ ማሸነፍ ጋር የመኖራቸው ዘዴ ቅ/ቤተክርስቲያን ናት ።በዚህ ሁሉ ሁነት ውስጥ ግን ገረገራውን ተሻግሮ መቅደሱ የገባውን ፈተናዋን ሳናነሳ አናልፍም።በጣም ጥቂት እንደው ለአሉታ ለተወሰኑ ማይክሮ ሰከንዶች የሚበቃውን እናውጋ።

የጎደላት ሳይኖር ያልጎደለባቸው ልጆቿ ያጎደሉባት እና ጎደለ ብለው አደለ አጎደልን ብለው አደል ብቻ እንዲሁ በዋል ፈስስ ሆንን። ይሄም ያልፋል አይባል ነገር ፈተናው እመቅደስ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ግራ ማጋባት ከጀመረ ቢቆይም ባሳለፍናቸው 20 አመታት ደግሞ በአይነቱ የተለየ ሆነ። መንገድ ላይ ስንመጣ ከሚገጥመን ነገር ጀምሮ ቤተ መቅደስ አስክንደርስ ድረስ ያለውን ጨምረን ልናስቀድስ ስንቆም በየልቦናችን ኪስ ገብቶ ሰው የዳቢሎስን ስም ተክቶ እከሌ እንዲህ አደረገ እንጂ ሰይጣን አሳሰተው፤ በስህተት ካልሆነ የማይባልበት ደረጃ ደረስን።ይኸም ይመስላል ዘመን አመጣሽ ወረረሸን ከሊቅ አስከ ደቂቅ ተናፍሶት አዲሱ ፕሮቴስታናዊ አካሄድ ፖለቲካን ካባ አድርጎ ቤ/ክ ይዛ የመጣቸውን መንገድ ለማቋረጥ የትውልድን አመለካከት ሲቆፍር ይስተዋላል። ይህ አካሄድ ደግሞ ወዴት ያመራናል? በእውኑ ልዩነታችን በማመንና ባለማመን ውስጥ ነው ወይስ መፍታት በሚቻልና በማይቻል ጉዳይ?። ይህ ከሆነ እሩቅ ሳንሄድ ትላንት እግዚያብሔር የለም ያሉትን አስታውሶ ዛሬ ኦርቶዶክስን ማጥፋት ግባቸው ከሆኑት ጋር ኩታ ገጠም እንሆናለን ያሰኛል። ስለ እምነታችን የሚለውን ስናነሳ ስንዱ እመቤት እንደሆነች አውግቼአችሁ ነበር። አዎ አሁንም ናት። ግንሳ ቀሚስ ለብሶ የገባውን የመንግስት መዳፍ ድምጿን ሊሰሙ የመጡትን በጎቿ በእረኛዎቿ ድክመትና ቀንዳቸው ከውበታቸው በተላለፈባቸው በጎቿ አማካይነት ከበረት የሚወጡትን ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ።በዚህ ሁኔታ ሩጫው ወዴት ነው ?።መጨረሻውስ ምንድ ነው ? ከገረገራው አልፎ እስከ ቤተ መቅደስ በሚሠራው ስህተት አዲሱ ፕሮቴስታናዊ ፖለቲክስ እጅህ ከምን? በእውኑ እምነት ወይስ በእምነት ስም የማህበረሰብ ስብስብ። አዋጭነቱስ አስከምን ድረስ ነው? እምነት ከሆነ በመላው አለም የምንገኝ ኦርቶዶክሳዊያን (በተለይ በውጭ ሃገር)የሚወክለን የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ጠፋ ወይስ ዳግም ክርስቶስ እስኪመጣ እንጠብቅ?።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትጥቅ የማስፈታት ድርድር!! - ቴዎድሮስ ጌታቸው

እርግጥ ነው በዚህ ዙሪያ የሚደረግ ንግድ ቢሆን ቢሆን “ቁርበት ነጋዴ ምን ትነግዳለህ ትርፍህ ምንድነው ዘጭ ዘጭ”ይሆናል :፡ግን ደሞ ጠላት ዳቢሎስ ሰዎችን ለመፈተን ምክንያት የሆነው ወንድም/እህት(ወገኖች) መዳን አይገባቸውም ወይ ? እነዚህን እና ሌሎቹን ጥያቄዎኦችን የሚመልስ እራሱ የተባረከ ነው። ብዬ ጥያቄው ብዙ ምላሹ ብዙ የሆነውን ጉዳይ ልቋጭ።ስጀምር መጀመሪያ ቃል ነበረ (ዮሃ1፤-1) አሁን ደግሞ ቁ14 ላይ ሄደን ቃልም ስጋ ሆነ ፀጋና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ”የሁላችንም የፀጋው ባለቤት መሆን ከሚመጣው ጥፋት ለመዳንና ከአሮጌ ደፈተራችን ላይ እያነሳን አዲስ የቤት ስራ ለትውልድ በመስጠት የዳቢሎስ ስም በእኛ እንዳይተካ መጠንቀቅ የግድ ሳይለን እንዳልቀረ መንፈሴ ያሳሰበኝን ለማለት ወድጄአለሁ።

ባህላችን

ባሕላችን እና ቋንቋችን ከሌላው አለም ትንሽ ለየት እንደሚያደርገን ሁሌም የምናወሳው ነው። በዚህም አንዳች የተለየ ነገር ሲገጥመን ምነው ኢትዮጲያዊ አደለህም/አደለሽም ወይ እንባባላለን። ታዲያ” ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ አልጠፋምና” በዚህ ምክንያት “ይሉኝታ” የሚባል ግርማ መጎስ የሆነን ቆባችን አለን። ይህን ስናወልቅ ጦሩ የተሰበረበት አዳኝ እነሆናለን። በዚህ ሁኔታ እኛንም በስህተታችንና በይሉንታ ማጣታችን ሊከሰንና ሊበላን ከሚችል የህሊና አውሬ ለመዳን መፍተሔውን ገንዘብ ብናደርግ። አውሬዎቹን ለመጥቀስ ያህል ፤እርስ በእርስ መናናቅ ዘረኘነት፤ ጎጠኝነት መከፋፈል በአሁኑ ግዜ ጥርሳቸው ከሾሉት አውሬዎች ውስጥ ናቸውና። ታዲያ እንዳይንዘላዘል አድርጎ አዝሎ መዞሩ ወዴት ያደርሰናል? ውርስስ እናድርገው ብንል ይጠቅማል ወይ? ሁሉም እራሱን ይጠይቅ። በካይነቱን እና በቶሎ መራባቱን አውቆ ተፈጥሮ እና ሐይማኖት ብሎም እናት ኢትዮጲያ ካደለችው ጥቂቱን በመጠቀም የባህላችንን ክብሩነቱን ጠቀሜታውን ከወሬ ባለፈ ብናሳይ እንዴታ የተዋበ ነው።

እውነት ነው የርዕሱ ስፋት እንዲህ በጥቂት ብለውት ወይም ተፅፎ የሚያበቃ አደለም። ለመወያየት ታህል “ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም ” ነውና ልብ እንበል።

ቸር እንሰንብት።

2 Comments

  1. ይሔን ዝባዝንኬህን ለሰው ስታቀርብ እንዲያው ምን ይሰማሃል? እንደ እንስሣ በወያኔ ከርስቲያን መሰል ካድሬዎች እየተመራችሁ ሰላማዊውን ቤተክርስቲያን በጠበጣችሁ። ለመምሰል ደግሞ ፖለቲካ መናምን እያልክ ታነሳሳለህ። ምንም የተለየ ነገር በደብረሰላም አልተደረገም። ወያኔ የሾማቸውን ‘ፓትርያርኮች አንቀበልም ማለት የእምነት ሥርአት ማጉደል ነው ትላላችሁ። ወያኔ ከመንበራቸው ያባረረውንስ ምንድን ነው የምትሉት? ለችግሩ መፍትሔ ለማምጥት ከላይ እታች ሲባል ለአመታት የተለፋበትን ጥረትስ ማን አኮላሸው? የቤተክርስቲያንን ገዳማት ማን ፈታ/ አያሌ ቤተክርስቲያናትስ በአላዊያንና በካድሬዎች እንዲቃተሉ እና እንዲፈርሱ ማን አደረግ? ቅድስት የሆንች አገርስ ክብሯና ሉዐላዊነቷ በማን ተዋረደ? ሌላም ሌላም… ታዲያ ምነው ይህ ሁሉ ግፍና በደል ሲፈጽም ተለጎማችሁ? እውን ወያኔ የሾመውን ጳጳስ ስም አለመጥራት ነው በደሉ ወይንስ ይህን ሁሉ ጥፋት አይቶ እንዳላየ ሆኖ ለዛሬ ብቻ ለሆድ ማደርና ሰላምንንና አንድነትን፣ ስብሐተ እግዚአብሔርን ማስታጎል የበደል በደል? እ
    ንዲያው በደፈናው ቤተክርስቲያን አንድ ናት የአባቶች ሥርአት …እያሉ መቀባጠር ሳየሆን የአባቶችን ታሪክ በሚገባ ማወቅ ያሻል። ከአላዊ ‘መንግሥት ጋር ወግነው አገርንና ቤተክርስቲያንን እየበደሉና እያጠፉ ያሉ ሁሉ ፍርድ ከእግዚአብሔር አለባቸው። ወያኔ ዘላለማዊ አድርጋችሁ እስከመቼ? እያላችሁ በጎዶሎ እምነታችሁ ከአጥፊ ጋር እንሰለፍ ለማለት ማን ጃስ አላችሁ? እናንተ ብቻ ለቤተክርስቲያን አንድነት ጠበቃ ማን ሾማችሁ? በእውቀት፣ በእድሜ፣ በልምድ፣ ወዘተ ብዙ የሚበልጧችሁን እየናቃችሁ፣እየሰደባችሁ ብሎም ቤተክርስቲያን ውስጥ እየረበሻችሁና ለፈጣሪ ብቻ የሚቀርብን ዝማሬ ለአመጽ የሰውን ድምጽ ለማፈን እየተጠቀማችሁ የእናንተ ክርስትና የቱ ጋር ነው? ሕሊናህ ከወስጥ እየገረፈ ከሚያሰቃይህ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመለስ። ይህ እምቢ ያለ ህዝብ ሳይፈቀድ አንዳች የሚሆን ነገር የለም! የሚደረግ ነገር ሁሉም ለውዳሴ ከንቱ ሳየሆን በትክክል ለዘላቂው ለቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት የሚያመጣ ነገር እንጂ አቦ አቦ ለመባልና ለግል ጥቅም መሆን የለበትም። ያለውን እውነታ ሁሉ በመረጃ ማቀረብ እንጂ አብዬ ሌላ መታወቂያው ሌላ መሆን የለበትም። ስለዚህ ለቤተክርስቲያን፣ ለራሳችሁና ለሰውም እባካችሁ ሰላም ስጡ።

  2. Really sorry to say this.
    Are you Sure you are poet or writer? who gave you these title? Do you think is it as such is to get the title?
    Do you Undestand what you write on this puplic journal? Look the title, then the body, then the subject. Is it about thinking,Poletics or religion?

    I know you are brave to write anything since you got the space.But please think before you write. Everyting in the body you raise is unrelated. Please ask your friends and take there geniun comment. I belive that will improve your writing.otherwise please ….

Comments are closed.

Share