“ወደው አይስቁ” ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። … የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን አያውቁትም። የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ። እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣ የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም። “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል። ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል። እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም። እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ። የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው። ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው። “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።
አጼ ምኒሊክ አምስት ሚሊዮን ጡት ቆርጠዋል ሲሉን ግን፤ ስሌቱ ላይ የቤት ስራቸውን በደንብ የሰሩት አይመስልም። በአጼ ምኒሊክ ዘመን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ቁጥሩ ስምንት ሚሊዮን ነበር። የአምስቱ ሚሊየን ህዝብ ጡት ከተቆረጠ፣ በዘመኑ ወንዶቹም ጡት እንደነበራቸው ያመላክታል። ግን ያንን ሁሉ ጡት እንዴት ሊቆርጡት እንደቻሉ ተናጋሪው አላብራሩም። ስልጣኔን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት አጼ ምኒሊክ በመጀመሪያ ያደረጉት የጡት መቁረጫ ማሽን ማስገባት መሆኑን ከጉግል ላይ በቅርቡ ሊገኝ ይችላል።
ጉግል፣ ጉግል፣ጉግል፣ጉግል፣…… እያለ መነጋገርያውን ለቆ ወረደ – የምኒሊክን አዲስ ታሪክ የሚያስተምረው።
“ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል።… ይህንንም በቅርቡ ይፋ በሚሆነው ጥናት ታገኙታላችሁ… ።” የሚል ሌላ ተናጋሪ መድረኩን ይዞ ሲናገር ከማርስ የመጣ ፍጡር ነበር የመሰለን።
ጨርቁን ጥሎ እርቃኑን መንገድ ለመንገድ የሚሄድ፤ ወይንም ደግሞ እጅና እግሩ በሰንሰለት የታሰሩ ሰው ስናይ፤ በተለምዶ ይህ ሰው አብዷል እንላለን – ውጭውን ብቻ አይተን። ጥሩ ልብስ ለብሰው በስነልቦና እና በአእምሮ መታወክ የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ እብዶች እንዳሉ ብዙውን ግዜ እንዘነጋለን። እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች በቀን ቅዠት የሚሰቃዩ፣ የስነምግባርና የሞራል እስረኞች በመሆናቸው አእምሯቸው ይታወካል። በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የአጼ ምኒሊክ ጣእረ ሞት እየመጣ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነው።
ፓልቶክን ከሰባት አመታት በኋላ መስማቴ ነው። ይህን ትልቅ መድረክ፣ አንዳንዶች ታሪክ ሰርተውበታል። ሌሎች ታሪክ ሲያወሩበት ሰንብተዋል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ታሪክ የሚያጎድፉ ጉዶች ይዘውታል። ከሰባት አመታት በኋላ የኛ ፓልቶክ ሽቅብ ሳይሆን ቁልቁል አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ቢገርመኝም፤ በአንጻሩ ግን እንደ አዝናኝም እየሆነ መምጣቱን አልጠላሁትም።
እንደሰማነው የፓልቶክ ርእሱ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አልተቀየረም። የዛሬውም መነጋገርያ ርእስ ዳግማዊ ምኒሊክ ናቸው። እኚህ መሪ ካለፉ እነሆ መቶ አመት ሆናቸው። “የሞኝ ለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ!” እንዲሉ አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ስለ አጼ ምኒሊክ አውርተው ሌሊቱንም ይመለሱበታል። ዛሬ ግን ወሬውም፣ ስድቡም ያለቀባቸው ይመስላል። ዛሬ ስለጀኖሳይድ እያወሩ አይደለም። ይልቁንም ጀኖሳይድ እያወሩ ነበር። ወንጀሉን ራሳቸው በቃል እየፈጸሙት…።
ሌላኛው ተናጋሪ ተራውን ጠብቆ መነጋገርያውን ያዘ። የተለመደውን የአጼ ምኒሊክን አጽም ከመቃብር እየጠራ ካወገዘ በኋላ፤ እንዲህ ሲል ተናገረ። “…አበበ ቢቂላን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ አድርገው ታላቅ በደል ፈጽመውበታል።”
መቼም ወደው አይስቁ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች እንኳ አይፈረድባቸውም። ገና ሃገር ሲለቅቁ የለቀቁ ስለሆኑ ለክርክርም አይመቹም። “አበበ ቢቂላ በሮም እና በቶክዮ ላይ የሮጠው በአጼ ምኒሊክ ዘመን ነው።” ብሎ ከሚከራከር ሰው ጋር ሙግት መግጠም እብደት ይሆናል።
“የቁቤ ትውልድ ነን።” የሚል ሌላ ታናጋሪ ደግሞ መጣ። ይሄኛው ደግሞ የቆሪጥ መንፈስ የሰፈረበት ሳይሆን አይቀርም። የሚያወራው ሁሉ ስለ መቁረጥ ብቻ ነው። ሚኒሊክ ጡት፣ እጅ፣ ቆለጥ፣ እግር፣ ጥፍር… ቆርጠዋል አለን። እንደታናጋሪው ከሆነ እኚህ መሪ ያልቆረጡት ብልት የለም። ሃገር ማስተዳደሩን ትተው አስራ ሁለቱንም የሰውነት አካል ሲበልቱ ኖሯል!
አርፍደው የሚገቡት ተሳዳቢዎች ከአፋቸው የሚወጣውን ጸያፍ ስድብ ለመድገም ይዘገንናል። በ”ምሁሮቻቸው” ገለጻ መሃል እንደ አዝማች ጣልቃ እየገቡ በአማራው ህዝብ ላይ ይወርዱበታል። በዚህ ሁሉ መሃል ትንሽ የገረመኝ አንድ ክስተት ነበር። የክፍሉ መሪ በስድድቡ መሃል ገብቶ በኦሮምኛ እንዲህ ሲል ተናገረ።
“ጀሪን ወል አኛተኑ። ማይኪ ኢቲ ኬኒ። ኑ ሂንደጌኛ”።
ወደ አማርኛው በግርድፉ ሲመለስ፣ “ማይኩን ስጣቸው። እነሱ እርስበርስ ይባሉ። እኛ እንሰማለን።” እንደማለት ነው። ዋናው ጨዋታ እዚህ ላይ ኖሯል። ምክንያቱም ይህንን ውግዘት እና ውርጅብኝ ሜንጫዎቹ ያለምክንያት በዚህ ሰዓት አላነሱትም። ነብሳቸውን ይማርና አፄ ምኒሊክ ካረፉ 100 አመት አለፈ። የሙት አመታቸው መከበር ከጀመረ ደግሞ 70 አመት ሆነው። ይህንን ወቅት ጠብቆ በአማራ እና በክርስትና እምነት ላይ ለመዝመት የሚደረገው ሙከራ፣ ግብታዊ ሳይሆን በጥናት የተደረገ ስለመሆኑ ያመላክተናል። ግርግር በመፍጠር እና ዜጎችን እርስበርስ በማባላት፣ ትንሽ የፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚፈጸም የፖለቲካ ዝሙት መሆኑ ነው።
ልብ በሉ! የዚህ የሜንጫ ዘመቻ መሪዎች ኦሮሞዎች አይደሉም። አብዛኞቹ በግማሽ ከሌላ ዘር የሚወለዱ ናቸው። በእምነታቸውም ሆነ በዘራቸው የተቀላቀሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ።
ስድስት ሚሊየን አይሁዶችን የፈጀው አዶልፍ ሂትለር ግማሽ አይሁድ እንደነበር አንዘንጋ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ላይ የጣለችው እገዳ እና አንድምታው . . .

9 Comments

  1. Kinfu Asefa you and your friend Abebe /wered Belew is pushing hard the weyane agenda of dividing Ethiopians by radio and web page and now you bring back the weyane control paltak garrbaeg to spead your poisonous article to create division between Ethiopians.there is no single Oromo on today’s Ethiopia who would have the autorityy to build any statue of anola.it is the weyane/Tigre mafiya group who work hard to make instability by divide and concour Ethiopians.

  2. Let’s preach unity and if so not only Gondar the whole Ethiopia belongs to oromo’s and vice versa. Regarding fosil investigation please examine Emperor Menelik fosil. He might be from oromo origin as Lucy {your findings}.

  3. Emm… I forget one basic thing. The science that reveals Lucy is an Oromo is important for the current ethinic federalism of Ethiopia. Please scale up and every Ethiopians should be tasted to know exactly from which race he/she belongs. Lol

  4. አቶ ክንፉ ፣
    በፓልቶክ ስለምንሊክ ተቃውመው የሚያወሩት ወያኔዎች ናቸው።ድሮ ተመሳሳይ ፓልቶክ “oromia versus ethiopia” እና “አጋሜንና ኤርትራውያን ” የሚያሰዳድብ ከፍተው ነበር።አንዳንድ የዋህ አብሮ የሚያጫፍር አይጠፋም። ይሄን ዘመቻ ለምን ጀመሩት ለሚለው።

    1ኛ፣ ምርጫ ደርሶአል ስለዚህ መከፋፈል ለነሱ ልማዳቸው ነው። እውነተኛ ምርጫ ስለሌለ ይሄ እንኩዋን ብዙም አይደል።
    2ኛ፣ ሁሉም ጎሳዎችና ሀይማኖቶች ነቅተውባቸዋል፣ አንድ እየሆኑባቸው ነው። ስለዚህ ይህን ቲዎሪ ፈጠሩ።
    3ኛ፣ እነሱ የሚሰሩትን ወንጀል ላይ እኛ እንዳናተኩር ፣ የአፄ ምንሊክን ታሪክ እንደመደራደሪያ ሊያቀርቡት ነው። ባለፈው ጊዜ የአፍሪካ መሪዎች ለፍርድ እንዳይቀርቡ ለማድረግ ሲሰበስቡ ነበር። ይህም የሚያሳየው በዚህ ጉዳይ ላይ እነዳሳሰባቸው ነው።
    4ኛ፣የሜንጫ ፖለቲከኞቹ ማጠፊያ ስላጡ፣ጊዜውም ጥሎአቸው ስለሄደ፣ ሌላውን በመጎርበጥ ራሳቸውን ሊያፅናኑ ይሞክራሉ። ወይም ሀገር ቤት ለመግባት ይህን ስራ መስራት ግዴታ የአለባቸው ይመስለኛል።
    5ኛ፣ሌላው ቴዲ አፍሮ አንድ ለአምሰት አልጠነፍርላቸው ብሎ ይሆናል።
    6ኛ፣ ሌላው ደግሞ ይልቃል ጌትነትን ለማዳከም ይመስለኛል።

    ስለዚህ ከኦሮሞዎች ወይም ከቅልቅሎች ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም።
    የጡት ሀውልት አርሲ ውስጥ ሰሩ ፣እኔ አሁን የፈራሁት ደግሞ በትግራይ ከአከሱም ሀውልት ጎንና ጎን በቀግራና በቀኝ የወንድ ልጅን ፍሬ በሀውልት መልክ እንዳያሰሩ ነው። ወይ ጉድ የነ አፄ ዮሀንስና የነ ራስ አሉላ ሀገር እንዲህ መቀለጃ ይሁን።
    አሁን የወያኔ ፖለቲካ ከፓልቶኩ ethio love ጋር እየተመሳሰልብኝ ሊመጣ ነው።

  5. Aye kenfu,

    It is a jock. you and your freinds been talking the same mencha talk on Tigrians on paltalk and that was ok for you and today some says some thing about menelik and you are mad about it.
    it is funny for you guys to blame others racisist while all the diaspora media have been crying laud when it comes to menelik why becouse he is Amhara.
    why don’t you see every ethiopian equal. is isn’t you guys started the boycout game by saying don’t eat enjera, don’t use ethiopian airliance bla bla game and it fires back to you.

  6. They invited me to a secret meeting where they were organizing an underground Amhara organization. On the meeting was one old journalist who escaped to the west. The agenda was set and the others asked the journalist to head an important committee. He refused, but gave me the wake up call that I always believed was true. He said ” journalists” work from behind and not from the front. These days the so-called journalists do not even hide where they come from. Seifu is intoxicated with his Amhara chauvinism. We are used to these kinds of “Dingay rases”. They never open their dead brain to the truth surrounding them. They call as Menchas and we call them Dingay rases. Dingay rases are archaic, dead in their thoughts that they do not see what is right and wrong.

    Human torture cannot be condoned unless you are a “Dingay Ras”. You cannot build a country on torture and assume that every thing was dandy. You have to be a “Dingay Ras” to assume that the victim forgets your ancestors crime. I am not sure where this Dingay Ras got the 70 year celebration of Menelik’s death. Perhaps I have worked in all capacities in Ethiopia and there was no single time his death was celebrated. “Dingay Rases” thought that the incarnation of their dead kings would usher the reappearance of the grit of their kings. We are in 21st century. This time we have different means than our forefathers to teach lesson to the “Dingay Rases”.

  7. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

    Dear Kinfu;

    Good job as always. The intensity of language trash and ignorant seen by these group is beyond any human imagination. When cult leaders of hate organize their followers, the first thing they manipulate the brain of their followers is pumping so much ignorance to their brain so to breed ignorance in them. once cults are pumped with such doctrinarian- they can’t think rational. They have no ability to distinguish what is rational and what is irrational.

    For them, the intensity of talking ignorance is what satisfied them to their soul as they are made to be mannequin to display ignorance in human society. We have seen so many OLF mannequin display OLF’s ignorance in media stores. It is so low and sad to see such human mannequin vastly display in this modern century on media. One will find it hard to measure the intensity of ignorance how much deep that these cults are suffering from the wrong teachings in this century. Such ignorant breeds can’t even be found in any century one think of. These are worst than the Nazi cults. I have never read Nazis display porno status in no where on their ugly politics. OLF is the first porno cult that failed to see what is proper to display to public what is not. Savagery is ignorance and that needs sharp eye to watch it. Hearing such unrestricted madness and ignorance, one never know they can repeat the savagery of the 16 century savagery act against any human being by the “Machete Interhamuwe Revolutionary OLF” which of course happened in 1991 in Ethiopia by the same group. Watch the development of “MIRO” criminals closely, they are blood thirsty group one need to put an eye on.
    Thanks
    Getachew Reda

  8. Kinfe the fool. 8 million doesn’t include Kush Ethiopia. That was Abysinian population. Now go back to your dip sleep with Leaurate Tsegaye in kinjit room

  9. >>> አሁን ባለንበት የቁቤ (የዕቁብ)ትውልድ እያሉ እራሳቸውን የሚያጃጅሉ የሞቀ ውሻ(ሆት ዶግ)ተጠቃሚ አካላት “ሜንጫ የሙስሊም ኦሮሞ አብዮት አራማጆች ሀገርና ትውልድ አምካኝ የፖለቲካ ተንታኝ ህብረተሰብ በታኝ ሆነው፡ አንዳንዶች ባንዳ (ሹምባሽ) በክቡር ገብረመድክን አርዓያ መዝገበ ቃል (የባእድ ወራሪ ዶሮና እንቁላል አቅራቢ) …በፋፋና በዱቄት ወተት የተሸጡ…ከሻቢያ በጉዲፈቻ ኦሮሞ ቤት ጮጮ ልሰው ያደጉ (ጆሌ ቢሸፍቱ)”የኦሮሞ ዝምታ!” የሰላቢው ማስታወሻ” “የሰላዩ ጉዞ” በተሰኘ በኦሮሞ ሊሂቃን ተረቆ በትግሪኛ ተሻሽሎ በአማርኛ በነፃ ብሔርና የትውልድ ማጥፊያ የተረጨ መርዝ…ዙሪያውን እንዳበደች ውሻ ያቅበዘብዛቸዋል። የኦሮሞ ሕዝብ በራሱ ቋንቋ ነግሯቸው አልገባቸውም…ከአልቅት የፀዳ ንፁህ ውሃ፣ለወገቡ አልጋ፣ ለልጆቹ ሕክምናና ትምህርት፣ለሆዳቸው ዳቦ…እናቶቻቻው በኩበት ጭስ ዓይናቸው እንዳይጠፋ …በጉልበት ተንበርኮ ወፍጮ እንዲያበቃ…ከጠላና አረቄ ጠመቃ አልፈው.. የፀዳ ለብሰው የአማራቸውን ጎርሰው በሃይማኖታቸው ፀልየው በሰላም መኖርን ይለምናሉ። ያደመጣቸው የለም!
    ***ሎሎች በቀን አሥር ግዜ እየጋጡ…ደረቅ ጫት እየመጠጡ…የሻቢያህወአት የሙስና ሻንጣ ተሸካሚ ሆነው…ከአህያና ፈረስ ወርደው በሹፌር እየሄዱ የህዝብ ማስለቀሻ…የትውልድ ማናካሻ..የሀገር ሰላም ማደፍረሻን ሴራ በህወአት ጥላ ተከልለው ፳፪ዓመት ያልተገባቸውን መሬትና ሀብት ዘርፈው ባንዲራ ቀርጸው የክልል ካርታ ሠርተው ያናፋሉ። ጭራሽም የብሔር ጥያቄያችን “ከመገንጠል” በቀር ተመልሷል ብለው ጧፍ ዕጣን አጭሰው ቄጠማ ጎዝጉዘው ይዘምራሉ። ለመሆኑ ይህ ሥራ ዕድል መክፈት ከአፍ መክፈት ነፃነት ጋር እንዴት አንድ መሰላቸው። አላግባብ አፍ ሲከፈትም…ምን ይታያል እነጂ የፖለቲካ ትርፋማነት አያስገኝም።ባለፈው ሰሞን ከተስፋዬ ግብረእባብ የነፃ መፅሀፍት እደላ በኋላ ከደቡብ አፍሪካ፣አስካንዲኒቪያን ሀገራት፣ አሜሪካ፣ ካናዳ…አውሮፓና አውስትራሊያ…ያሉ ፅንፈኛ፣ፀረሕዝቦች፣ አሸባሪዎች…በግብጽ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ሲቃወሙ…በደቡብ አፍሪካ ማንዴላ ኦሮሞ ነው ሲሉ…ተስፋዬ በኢሬቻ በዓል በፈረንጅ ውሃ ዳር ሲመረቅና የጀግናው ደራሲ ቅቤ ሲቀባ፣ በቅርብ ቀን የኢትዮጵያን ፖለቲካን ኢኮኖሚ፣ መከላከያን ጨምሮ ለመቆጣጠር ከእያለንበት እንገባለን እኔም የኦሮሞ ዜግነት አለኝ ሲል ደነፋ…እንግዲህ ከአቶ ሌንጮ ለታና ከህወአትሻቢያ ጋር የነበረው የውስጥ ስምምነት አስቀድሞ ደርሶት ታላቁ ትንቢት ፋላስፋ ሆኖ ነበር። **ግን ተመልሰን ገብተን እንታገላላን ሲሉ ትግሉ ምንድነው? ከማነው? ምን ለመጨመር ነው? አንድ ባንዲራ አንገበው ‘ኢትዮጵያ ከኦሮሞሚያ ትውጣ ሲሉ…ይህን ሁሉ መብት ያጎናፀፏቸው ትግራይና ሻቢያን የትኛው ባሕር ሊጨምሯቸው ነው? እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አደለንም ሲሉ ከርመው ኢህአዴግ ጥላ ሥር የተሸጎጠው ቀኝ ክንፋቸው አማራዎችን በመንደራቸው እየገደሉ፣ እየዘረፉ፣በመርዝ እየጨረሱና እያፈናቀሉ ሁሉን ነገር አመቻቹላቸው…። የኦሮሞ ፅንፈኞች ያልተረዱት ይህ ከአማራ ተነጥቆ የተሰጣቸውን መሬት(ኤርትራውያንም ተመልሰው መጥተው አባቶቻችን እናቶቻችንና ልጆቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን የከሰከሱበት መሮት ነው ብለው የመጠየቅ ሙሉ መብት እንዳላቸው አያውቅምን? በማን ልጅ ደምና አጥንት የሙስሊም ኦሮሞ ዲያስፖራ ያናፋል!?)አንዳንድ አልኩ ባይ የህወአት ጡረተኞችም እምዬ ምንይልክን ሲያንቋሽሹ ብሔር ብሔረሰብ ራስን አድል በራስ መወሰን ነፃነት ተረጋግጦ የአማራ የበላይነት ወድቆ ኢትዮጵያን መበተን በሕገመንግስታችን(በማኒፌስቶአችን)ተረጋግጧል ኦሮሞ ‘የጡት ሀውልት’ ደቡብና ትግሬም ‘የቆለጥ’ ተረስተውና ማንንታቸውን የማያውቁ ‘የቂጥ ሀውልት’ አቁመው(የዝሙት) ሴክስ ቱሪዝምን ለሚሽነሪስት አለቆቸቀቸው ወጣት ሴቶችን ለአረብ ሀገር የሸጧቸው ስላከሰራቸው አሁን በሀገር ውስጥ ለመነገጃ ማስተዋወቂያ ማድረጋቸው እጅግ በጣም የወረደና የዘቀጠ የከብት የአዕምሮ የትውልድ ክስረት ማፈሪያዎች ናቸው።
    **ነጮች አለቆቻችው የሚያፍሩበትን ሎሌዎቻቸው ፀጋ ብለው ማቅረባቸው አካባቢያቸውን ማርከሳቸው ባህልና ሀይማኖታቸውን መፃረራቸውን አልገባቸውምን? ወይንም ግብረሰዶምን ተገንጥለው ሊቀውጡት ያሰቡ ዲያስፖራዎች(ፈላሾች) በዚያ አካባቢ ክልል ሊመሰርቱ ኢንቨስት እያደረጉ ነው።የአማራ ሥም ያስጠላት ጫልቱ …ሊሊ፣ ቡኪ፣ ሱኪ፣ቡቺ፣ ፊፊ፣ልትሆን ቋመጠች ጠርጥር ድሮም የነጭ ጉዲፈቻ ማደጎ ምን ተምሮ ይመጣል?ትርፍ የለም ኪሳራ ብቻ ነው በለው! ሌላው የተበላበት ቁማር ብአዴን.. ኦፌዴን.. የሚባለውንና ሌሎችንም የወሮበላ ቡድንን ጨምሮ ለሚያጠፉት ታሪክና ትውልድ ኦነግ ኦብነግን አሰማርተው ኤርትራ የቀጠናው አተራማሽ ህወአት መሪዎች ናቸው የኢትዮጵያ ጠላቶችና አጥፊዎች ማለቱ አያዋጣም እንደ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ መልስ ሁሉም በእየፊናው ሀገር ለማጥፋት ህወአት(ትግሬዎች) እያለ ጣቱን ይቀስራል። ዞረውም በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈው ይበትናሉ>>>ኦፌዴን የአፄ ምኒልክን ሀውልት ለማፍረስ ተሰልፎ አቅም በማጣቱ ብቻ አልተሳካልንም የሚሉት ነጋሶ ጊዳዳ አንቀፅ ፴፱ ከማያከብሩ ጋር አብሮ ለመሥራት አስቸጋሪ ሆኖ በገዳ ደሞክራሲ መሠረት በ፵፰ ዓመት ሥልጣን መልቀቅ ሲገባኝ ሕገመንግስቱ በ፸ ዓመቴ ድረስ ያሰረና ያስቀመጠኝ አላግባብ ነው ከፖለቲካ እርቄአለሁ ግን አልጠፋም! የኢህአዴግንና፣ የአንድነትና የመድረክን ፓርቲ አባላትንና ብዙ ውስጠ ሚስጠር አወጣሉ፣ እተቻለሁ፣ መፅሐፍ እሸጣለሁ፣ብዙ ቃለምልልስና ለ፴፭ኣመት እድሜ ባለፀጋው ሌንጮ ለታ ከቡልቻ ደመቅሳ ጋር በመሆን ከአባልነት ውጭ ሆነን ያለንን ሚስጥር እንመክራለን ብለዋል።” ታዲያ ማን? ከማን? እንዴት? የት? ልዩና የተሻለ ነበር? ተልዕኮአቸውን የፈፀሙ ወደ ሀገር ሲገቡ ሀገር ውስጥ የነበሩ ይሸሻሉ…አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀን ግለሰብ ወይም ቡድን(ድርጅት) ጋር የተነጋጋረ አብሮ የተሰበሰበ ሻይ ቡና ያለ…(በሕግ ተጠያቂ ይሆናል)። በትክክል በተረጋገጠዉ በበደኖ እና አርባ ጉጉ፣ በተፈጸመ ግፍና ጭካኔ ዙሪያ ማስታወሻ ሃዉልቶች ሳይሰሩ፣ በጀዋሪያን ተስፋ በተፈበረከው የውሸት ታሪክ በሕዝብ መካከል ጥላቻና አመፅ ሊያሰፍን የሚችል፣ፀረ ሰላም ዓላማ የሴት ልጅን ጡት የሚያሳይ ሃዉልት በአርሲ መሰራቱ ። በበደኖ በኦነግ ታጣቂቶች ነፍሰ ጡር ሴቶች ሁሉ ሳይቀሩ፣ በሕይወት አይኖቻቸውን ተሸፍነዉ ተጠቅልለው ገድል ዉስጥ እንዲወረወሩ መደረጉ የሚታወቅ ነዉ። በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ.ኢሕአዴግ ታጣቂዎች አቀነባባሪነት፣ በአርባ ጉጉ አርሲ በርካታ ዜጎች በተኙበት ቤታቸው እንዲቃጠል ተደርጎ አልቀዋል።የክርስቲያን ኦሮሞ ቤተክርስቲያንም ፖሊስ ባለበት አቃጥለዋል። ከአሸባሪነት ነፃ ለመሆን ሳያመለክቱ ጥፋተኛን ሳያጋልጡ ምሕረት ሳይደረግላቸው የጡት ሀውልትና የቆለጥ ሐውልት በማቆም የአማራን መሬት ለሥልጣን ማስጠበቂያ ለባዕድ አከራይቶና ሰጥቶ በመቀበል ሽብርተኝነትን ማወራረድ አለን!?
    **ለምርጫ መወዳዳር ምሕዳሩ አሁን እንዴት ሰፋ!? ምን አልባት ማንዴላ ስለሞተ ይሆን!? ወደው አይስቁ አለ…የ፻ዓመት ትዝታ…የ፶ ዓመት ትግል…የ፳፪ዓመት ውዥንብር ለአንድ የጡት ሀውልት ያረጁትም ደነቆሩ ወጣቱም ደነቆረ መልሶ መላልሶ ማልቀስ ሆነ በለው!>>>>ሠላምና ልብ ለሁሉም።

Comments are closed.

Share