ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

01/19/2014

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን።

በምእመናን ተመርጠው ቃል የገቡ አንዳንድ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ባለፈው ዲሴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም የቤተከርስቲያናችን ጠቅላላ ጉባዔ ቤተከርስቲያናችን በአባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየትና መወጋገዝ እስኪያበቃና አንድ እስኪሆኑ ድረስ ለ20 ዓመታት ስትመራበት የነበረው የገለልተኝነት አስተዳደር እንዲቀጥል በማለት በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ የወሰነውን ውሳኔ አንቀበለውም አናስፈጽምም በማለት ላይ ይገኛሉ። ይህም የተመረጡበትን አላማ አለማወቅና ኅዝብንም የመናቅ አካሔድ ነው። በምእመናን የተመረጡት የራሳቸውን ፍላጎትና አላማ ለማስፈጸም ሳይሆን የህዝቡን ውሳኔና ድምጽ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ነው።

የቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 ክፍል 3 ‘ሀ’ በግልጽ እንደሚደነግገው ‘‘ የቦርዱ አጠቃላይ ኃላፊነት ጠቅላላ ጉባኤው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በሙሉ በሥራ ላይ ማዋል ይሆናል’’ ይላል። በተጨማሪም በአንቀጽ 4 ‘ሸ’ ላይ ‘‘ በጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተግባራዊ ይሆናሉ’’ ካለ በኋላ የቦርዱን ሊቀመንበር የሥራ ኃላፊነትና ተግባር በዘረዘረበት አንቀጽ 6 ክፍል 3 ‘ሀ’ ላይም ‘ሊቀመንበሩ የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎችን በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።’ በማልት በማያሻማ ሁኔታ በኅዝብ ድምጽ የተመረጡ የቦርድ አባላትን ኃላፊነትና ተልዕኮ ደንግጎ ይገኛል።

ቤተክርስቲያናችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም የምትተዳደረው በሕግና በሥርዐት ነው። በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 1 ክፍል 3 ውስጥ እንደሰፈረው አስተዳደርን በተመለከተ ቤተክርስቲያኗ የምትመራው በሚኔሶታ የቤተክርስቲያናት ማቋቋሚያ ሕግ መሠረት ነው። ግልጋሎትም የምትሰጠው በአሜሪካ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት ከታክስ ነጻ የሚያደርገውን መመሪያ 501c(3)ን ተከትላ ሲሆን ከእነኝህ ሕግጋት መውጣት ወይንም ባልተጻፈና ስቴቱም ሆነ ፌደራል መንግሥቱ በማያውቁት ሕግና አሠራር መመራይ ቅጣቱ ከባድ ነው። ከዚህ አኳያ የቤተክርስቲያናችን የኅዝብ ተመራጭ የቦርድ አባላትም ሆኑ ካህናት እንዲሁም ምእመናን ባጠቃላይ ቤተክርስቲያናችን የምተደዳደርበትን የውስጥ ደንብና ሕግጋት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሕጎችን ማወቅና ከእነርሱም ጋር የማይጋጭ አካሔድን መከተል ይጠበቅባቸዋል። ይህን ባለማወቅ ከሕግና ሥርዓት ውጪ በሆነ አካሔ በሚደረግ እንቅስቃሴ ምክንያት በግል ሕይወትና ታሪክ እንዲሁም የሕብረትሰባችንን መልካም ስም በማጉደፍ የሚደርሰው ጉዳት ቀላል ሊሆን እንደማይችል ከወዲሁ አበክሮ ሊታሰብበት ይገባል። ሕግን አለማወቅ ከቅጣት አያድንምና!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልቃይት ጠገዴ መሬቱን እንጂ...! | ሳምሶን ኃይሌ

በምንኖርበት አገር ሰው ሁሉ በማናቸውም ሁኔታ ድምጹን የመስጠትና ያለምስጠት፣ የመደገፍና ያለመደገፍ መብት ያለው ሲሆን፤ ትክክል አይደለም ብሎ ያመነበትን ጉዳይ ደግሞ ሕግን ብቻ ተከትሎ አቤቱታውን ማቅረብና በፍርድቤትም ሆነ በሚመለከትው አካል ብይን የማግኘት መብት አለው። ከዚህ ተጻራሪ በሆነ ሕገ-ወጥ አካሔድ በመሔድ ግን ማናቸውንም ፍላጎት ወይንም አላማን ማስፈጸም ግን በፍጹም አይቻልም። ምክንያቱም በተለምዶ እንደሚባለውና በርግጥም እንደምናየው THIS IS AMERICA! ስለሆነ ነው።

ምናልባት ከውጪ ሆነው ግፋ በለው እያሉ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማናጋት እየሰሩ ያሉ የወያኔ ፖለቲካ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ሆድ አደር ጋሻ ጃግሬዎች በተለያዩ አካባቢዎች እንዳደረጉት ቤተክርስቲያናችንን የማዘጋትና አገልግሎቷን የማቋረጥ አላማ የሚሳካላቸው መስሏቸው ከሆነ ፈጽሞ ተሳስተዋል።

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም እውነተኛው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት ብቻ የሚፈጸምባት ቦታ እንጂ የዘረኝነት አቀንቃኞች መፈንጫ ከቶውንም አትሆንም!

በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፖለቲካ ጣልቃገብነት(በወያኔ ቀጥተኛ ጣልቃገብነት) በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት በምንም መሸፋፈንና መቀባባት አይቻልም። ይህ መከፋፈል የመጣው በኃይማኖት ላይ የተለያየ አቋም ስላለ አይደልም። የቤተክርስቲያንን መዋቅራዊ አሰራር ባለማወቅ የተከሰተም አይደለም። ወይንም የአባቶች ጳጳሳትን ክብርና ድርሻ ካለማወቅ የመጣ አይደለም። በውጪ አገርም አገር ቤት የሌለው ነፃነት ስለተገኘ አይደለም። የቤተክርስቲያን ቀኖናና ነፃነት በፖለቲከኞች መጣሱን፣ የአገር ሉአላዊነት መገሠሡንና የኅዝብ መብት መገፈፉን ተከትሎ እንጂ! ስለሆነም በማጭበርበርና ሕገወጥ አካሔድ በመከተል የሚመጣ ለውጥ ስለሌለ አርፎ መቀመጥ ይበጃል እንላለን።

እጅጉን ከሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ለዚሁ የጥፋት ተልእኮ ወያኔ ያሰማራቸው የቤተክርስቲያንን እና የህዝብን ገንዘብ ዘርፈው ሳለ በወንጄል የሚፈለጉ ሰው ስለመልካሚቷ ቤተክርስቲያናችን የሐሰትና የጥላቻ ስብከታቸውን ማሰማታቸው ነው። አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ በዘረፉት የኅዝብ ገንዘብ ምክንያት በወንጀል ስለሚፈለጉ ወደ አገር ቤት ለመሔድና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳን ለመገኘት የማይችሉ ሰው በዓለም ላይ የተናኘ ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት እየሰጠች ያለችን ቤተክርስቲያን መሳደባቸው ከማሳዘንም አልፎ ያስገርማል። ይቅርታ አባ ዘካርያስ ሚኔሶታ የሚዘረፍ ቤተክርስቲያንም ሆነ ገንዘቡንና ንብረቱን አሳልፎ የሚሰጥ ምእመንም የለም!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአውሬ-አምባው ካድሬ ዳዊት ከበደ - (ከያሬድ አይቼህ)

እኚህ ሰው ላለፉት 5 ዓመታት በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልተገኙም። እንደቤተክርስቲያ ሕግ ግን ከሁለት ጊዜ በላይ መቅረት አይቻልም። እርሱም በፈቃድና በበቂ ምክንያት ብቻ ነው። የቀድሞው አባ ጳውሎስ ከወንጀል ክስ ለማሸሽ ሲሉ በቅጡ መናገር እንኳን የማይችሉትን ሰው በአሜሪካ መድበው በውጪው ዓለም ብዙ መስራት የሚጠበቅባትን ቤተክርስቲያን እያዘቀጧት ይገኛሉ። ገንዘብና ንብረታቸውንም አናዘርፍም ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይዘልፋሉ። ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ሞተናል ካሉ በኋላ ለአለማዊ ፖለቲከኞች ተገዝተው ቅድስቲቱን አገርና ንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ከሚያጥፋ ኃይል ጋር ሆነው ፍርድን ለራሳቸው ያከማቻሉ። እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው።

በመጨረሻም የሚኔሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ምእመናን ዛሬም እንደትናንቱ ቤተክርስቲያናችንን ከውስጥና ከውጪ አፍራሽ ቡድኖችና ግለሰቦች ነቅተን እንጠብቅ።
ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን።

2 Comments

  1. የት ያሉ መስሏቸው ነው? እንዳባታቸው ወያኔ በጉልበትና በሃይል የሚሰራበት አገር ያሉ መሰላቸው እንዴ? የመረጥናቸው የወሰነው ውሳኔ ምንም ይሁን የነርሱ ስራ ያንን መተግበር ነው እነኝህ የማያፍሩ ደሞ መጀምሪያ ቦርድ መመረጥም አልነበረባቸውም የቦርድ ሀላፊነት ይሄ መሆኑን ያሳወቃችሁን እናመሰግናለን ሲፈልጉ ለምን ለቀው አይወጡም እኛ የወሰነውን እነሱን ደስ ለማሰኘትና እነሱ የሚፈልጉትን ባይሆንም መቀበል ግዴታቸው ነው በንሱ ፍላጎት የምንመራ ከሆንማ ለምን እንሰበሰባለን የፈለጉትን እየወሰኑ ለምን አይነግሩንም ካልተቀበሉት ጥለው መውጣት አለባቸው በምትካቸው የራሳቸውን ሃሳብ ሳየሆን የኛን ውሳኔ የሚቀበሉ እንመርጣልን የዲሞክራሲ አገር ላይ ተቀምጥው እንደውያኔ ያስባሉ እባካችሁ። ቤተክርስቲያኑን እንኳን የማያከብሩ ሰው ሲናገር አላናግር የሚሉ ባለጌዎች ናችው። እንኳን ለቤተክርስቲያን አንድነት ሊያስቡ የቆሙበትን ቤተክርስቲያን እንኳን የማያከብሩ ናቸው እነዚህ ተላላኪዎች በህግ ግን መጠየቅ አለባቸው ለመረብሽ እንደማይቻል ማሳየት ያስፈልጋል የህግ አግር ላይ ነው ያለነው የምናመልክበትን ቦታ መረብሽ ወንጀል መሆኑን የት ያቁታል ውሳኔያችን ተቀይሮ የንሱ ለወያኔ ሊሸጡን ያሰቡት አይሆን ከእንግዲህ በኋል እንደው ባይፍጨረጨሩ ይሻላቸዋል እነዚህ……ዘይገርም ነገሮች።

  2. It is really interesting article. Who they think they are to object the people’s voice? We elected them to serve us,not to impose on us their will. We elected them we can change them if they are not willing to carry out our decision. I appreciate you guys for letting us know the by laws. Those people who are yelling and disturbing our church proved that their mission is not spiritual. Sorry for their soul. They need to learn the hard way that this is a land of law.

Comments are closed.

Share