ኢትዮጵያ የጋራችን ኤርትራ የግላችን! “ከ 40 ግድብ አንድ የአሰብ ወደብ” – ከሰመረ አለሙ

ኤርትራዉያኖች ተበልጠዉ በኢትዮጵያ ተንደላቅቀዉ የሚኖሩበትን ሁኔታ ከተነጠቁ በሗላ እንደገና እጃቸዉ ለማስገባት በተለያየ ዘዴ ቢጠቀሙም ህዋአት እና ሻቢያ “እባብ ለባብ ይተያያል ካብ ለካብ” አይነት ሆነና ኤርትራዉያን የፈለጉትን ያህል ሳይሆንላቸዉ ቀርቶ እዚሀ ላይ ተደረሷል። የጸሀየ ግብአተ መሬት ፉከራ ከከሸፈ በሗላ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያን ሊበትንልን ይችላል የሚሉትን ሀይል እና ዘዴ ቢበደሩም መላ ቢመቱም ቢያሰባስቡ እና ቢያሰለጥኑም፤ የኢትዮጵያ አንድነት ፍንክች ሳይል ቀርቶ እዚህ ላይ ይገኛል። የኤርትራ ምሁራን ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸዉ ተራ ወርደዉ የሚያስገምት ጽሁፍ ቢጽፉም፤ በቀይ ባህር ማተሚያ ቤት የእዉሸት ፋብሪካቸዉ ተረት መሰል የኢትዮጵያ ታሪክ ቢያሳትሙም፤ ቅጥፈት የተሞላዉ ወረቀት ቢጽፉም ድካማቸዉ ሁሉ ያለምንም ፍሬ ልፋት ብቻ ሁኖ ቀርቷል
ታድያ ለሁሉም ብልሀት አለዉ እንዲሉ ይህ ዘዴ ያለመስራቱን የተረዱ ኤርትራዉያን አቶ መለስንና ለኤርትራ ስስ ልብ ያላቸዉን የህወአት ባለስልጣኖች በመጠቀም ዛሬም ከዜጋዉ በላይ የኢትዮጵያን በረከት እየተጎናጸፉ ይገኛሉ። በተለይ ከአቦይ ስብሀት አለንላችሁ መግለጫ በሗላ ብዙ ኤርትራዉያን ባላቸዉ ንክኪ አማካኝነት በብዛት ወደ ሀገር ጎርፈዋል ከኢትዮጵያ ሳይባረሩ የቀሩትን ወገኖቻቸዉንና በዉጭ ሀገር በሚኖሩ ኤርትራዉያን አማካይነት የዉስጥ ለዉስጥ ግንኙነታቸዉን በማጠናከር ኢትዮጵያ ዉስጥ የቀድሞ ቦታቸዉን ይዘዋል።
በቅርቡ በወጣዉ ጽሁፍ ወደ 1700 የሚሆኑ የኤርትራ ተወላጆች ከኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በላይ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዉ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ጎርፈዋል ይህ አፊሲያላዊ ቁጥር ነዉ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ቁጥር እንዳላቸዉ እማኝነት ያላቸዉ ዜጎች በቁጭት ይገልጻሉ። እንግዲህ ልብ ይበሉ እንደ አይን ብሌን በምናያቸዉ የትምህርት ተቋማት ኢትዮጵያዊዉ ወጣት በጫት የቀን ህልም ሲያልም ትላንት ኢትዮጵያ ላይ የተኮሱ ዛሬም ለኢትዮጵያ ክብር እና ፍቅር የሌላቸዉ ኤርትራዉያን በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ሲማሩ በእጂጉ ያሳዝናል።እነሱ እንዲማሩ ሌላዉ ኢትዮጵያዊዉ ቦታዉን ለነሱ መልቀቅ አለበት ማለት ነዉ።
ይህ በትምህርት ዘርፍ የተገኘዉ መረጃ ነዉ። በንግድ፤እርሻ፤ፐሮፐርቲን በተመለከተ ከሀገሬዉ ነዋሪ በላይ እዛ ያሉትም ከኤርትራ፤ከአዉሮፓ እና አሚሪካ እየጎረፉም በከፍተኛ ሁኔታ በመጠቀም፤በመጠቃቀም፤ከባንክ በመበደር እና በማምታት ህገ ወጥ ጥቅም በማግኘት ላይ ይገኛሉ። ገንዘብ ማሸጋገር ዋናዉ አገር መጉጃቸዉ ነዉ በዚህም ሂደት ገንዘብ አገሩን እየለቀቀ በባህር ማዶ ባንክ እና በዉጭ ሀገር ኢንቨስትመንት ላይ ይዉላል። እነሱም በዚህ ህገ ወጥ ስራ አንድም ጠላታቸዉ ኢትዮጵያን ይጎዳሉ አንድም ትርፋቸዉን ያደልባሉ። በህጋዊ መንገድ ቀረጥ ከፍለዉ ከመስራት ይልቅ ህገወጥ የሆነዉ መንገድ ባያተርፋቸዉም ይመርጡታል።
የሚያሳዝነዉና አንጀት የሚያበግነዉ እኛዉ መሀል ስንት ቤት ሰርተሀል? ሰሞኑን ምን ልከሀል? ትንሺ ገንዘብ ሰጥተህ በትግራይ በኩል ዘመድህን አስመጣ እያሉ በድፍረት ሲያወሩ በጣም ልብ ይሰብራል። ይህች ሀገር መች ነዉ ለዜጎቿ የምትሆነዉ? መች ነዉ ዜጎቿን የምታከብረዉ? መች ነዉ ዜጋዉ ከእንደዚህ አይነት ጥቃት ድኖ ሀገሩ የእርሱ መሆኑን የሚረዳዉ ብዬ አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለሁ። እንደዉም ደግሞ የድፍረት ድፍረት ከህዋአት ጭቆናም ነጻም የሚያወጡን እነሱ ሁነዉ ተገኝተዋል ጆሮ የማይሰማዉ የለ። የአለሙ ሚዲያ አምነስቲ ኢንትርናሽናልን ጨምሮ በወር 3000 ኤርትራዊ አገሩን ይለቃል ሲባል አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ከህዝቡ ፍቅር የተነሳ ያለ አጃቢ ነዉ የሚሄዱት ብለዉ ተቃዋሚዎቻችንን ሊያሳምኑን ይከጂላቸዋል ታዲያ ይህ ሁሉ ፍልሰት ነጻነት ፍለጋ ካልሆነ ፍለሰቱ አድቬንቸር ነዉ ማለት ነዉ ወይስ አቶ መለስ እንዳሉት ኤርትራዉያን እግር እንጂ አገር የላቸዉም የሚባለዉ አባባል እዉነት ሊሆን ነዉ?
በመሰረቱ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖራቸዉ ቅር የሚለኝ ሰዉ አይደለሁም ባለፈዉ ጽሁፌም እንደገለጽኩት ሀገሪቱ ዛሬ በስልጣን ላይ ቁጭ ብለዉ ከገደሏት በላይ ለሀገራቸዉ ኢትዮጵያም የሞቱ ታላላቅ የኤርትራ ተወላጆችንም ገልጫለሁ ምንም እንኳን ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ለነሱ ያለኝ አድናቆትና ክብር ከጊዜዉ ጋር የሚደበዝዝ አይሆንም። እኔም የምኖረዉ በዉጭ ሀገር ነዉ ልዩነቱ እኔ ዛሬ የምኖርበትን ሀገር በክብር እና በፍቅር የማገለግል ነኝ በሀገሩ ተጠቃሚ ሁኜ ለሀገሩ ጥፋት የምመኝ አይደለሁም። ይህ ነዉ የእኔና የዘመኑ ኤርትራዉያን ልዩነት።
ዛሬ ሰዉ ምን ይለኛልም ቀርቶ ኤርትራዉያን በግላጭ ኢትዮጵያ የጋራችን ኤርትራ የግላችን፤ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚል ፌዝ የሚመስል ፌዝ ያልሆነ ቋንቋ በብዛት ሲጠቀሙ ይሰተዋላሉ። የሚገርመዉ ሀገር ዉስጥ ኑሮዉን ዘርግቶ የሚገኘዉ ኤርትራዊ ወይም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በፍልሰት የሚገባዉ ኤርትራዊ ስለ አሰብ ምን ታስባለህ ስለ ባድሜ ምን ታስባለህ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ለማያዉቃት፤ ላልኖረባት ፤ ላልተጠቀመባት፤ ለተንገላታባት አገሩ ኤርትራ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአፍሪካ ቀንድ፤ ዙሪያው እሳት መሀሉ ብሶት - በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

ኤርትራዉያን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ሰፈር እንዴት ተንሸራተዉ እንደገቡ ግንዛቤ ቢያስፈልግ አንድም የህዋት ንክኪያቸዉን በመጠቀም፤ማንነታቸዉን በመለወጥ ሲሆን ሌላዉ ደግሞ በግንዛቤ የተጎዳዉን ኢትዮጵያዊ እየመረጡ በመጠቀም ነዉ። አንበሳዉ አለማየሁ መሰለንማ ማን ይደፍረዋል ተጠቃሚዉን ይጠቀምበታል እንጂ። እንግዲህ ወደፊት በስፋት ብመለስበትም ጀግና በጠፋበት ዘመን እንደ ቀድሞቹ ጀግኖች አያቶቹ በጠላት ሜዳ ተረማምዶ ግዳይ ጥሎ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ አስመስክሮ ኢትዮጵያዉያን ሰፈር እንደገና የተሀድሶ መንፈስ ለሰጠዉ አለማየሁ መሰለ በያለንበት ዋንጫችንን እንድናነሳ በትህትና እጠይቃለሁ ገድሉም ከጊዜዉ ጋር ሊደበዝዝ አይገባም። በእዉነቱ አለማየሁ ያነን የመሰል ገድል ሲሰራ ዉቅያኖስ ጠልቆ ዉሀ ሳይነካዉ እንደወጣ ዋናተኛ ነዉ የምቆጥረዉ። ከጀብድ ስራዉ በላይ ደግሞ ንግግሩ የቀድሞዎቹ አንበሶች አያቶቹን መንፈስ የሚያንጸባርቅ ነበር። አለማየሁ በአንድ ቃለ መጠይቅ “ተስፋዬ ምንም እንኳን የሻቢያ ሰላይ ቢሆንም እኛም ከእሱ በላይ መስራት እንችላለን በሚል ጽኑ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ስራዬን ተያያዝኩት” ነበር ያለዉ። ቆፍጣናዉ አለማየሁ በእዉነት የዘመናችን በላይ ዘለቀ ቢባል ብዙም ማጋነን አይሆንም ሰዉ የሚለካዉ እንደየዘመኑ ነዉና።

ኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ገናና አገር ነች በዚህ በረጂም ዘመኗ ረጅም ስርን ተክላለች በረጂም ዘመኗም ብዙ ጠቃሚ እዉቀቶችን፤እምነቶችን፤መረጃዎችን ለዜጎቿ እና ለአለም አበርክታለች ከዚህ እና ከሌላም ስንነሳ ኢትዮጵያ እንደሀገር ኢትዮጵያዉያንም እንደተከበረ ዜጋ በቀጣይነት መኖር አለባቸዉ። ኢትዮጵያ ትላንት በግርግር እንደተፈጠረች ሁሉ አንዳንድ ብሄረተኞች አንድም የበታችነት መንፈስ በተጠናወታቸዉ በሌላም በባእድ ሀይሎች እየተገፉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ለመፈታተን የሚያደርጉት ጥረት ያለ ይሉኝታ ሊመከት ይገባል እላለሁ።
እንግዲህ እንዲህ ያለዉን አልፎ ሂያጅ የግርግር መንፈስ ሳይበግረዉ በእዉቀቱ ስዩም እንዳለዉ ወጣቱ ኢትዮጵያ አገሩን ከአባቶቹ በበለጠ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ማድረስ ይገባዋል እላለሁ። ዛሬ እንዲህ አደርግልሀለሁ እንዲህ ብናደርግ የምድር መንግስተ ሰማያት እንኖራለን በሚል ቀቢጸ ተስፋ የሰፈሮቻቸዉን ልጆች እያማለሉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ወገኖችን የሚያስኮርፉ ነገ ሀሳባቸዉ ተሟልቶ እነሱ ኢትዮጵያን ቢከፋፈሉ እንደ ደሀ አጥር ሁሉም እየጣሳቸዉ ይሄዳል እንጂ እነሱም ተጠቃሚ እንደማይሆኑ በልምምጥ ሳይሆን በድፍረት ሊነገራቸዉ ይገባል። ፍቅርን የሚያዉቅ ጀግና ብቻ ነዉ እነሱ ግን ፍቅርን ልምምጥ ያደርጉታል። እነሱን ትልቅ ያደረገ እንዲህ የማኩረፍ ነጻነት ሁሉ የሰጣቸዉ ኢትዮጵያዊነት ነዉ። በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሐይሌ የዘረኞች እብሪት ሲበዛ አይተዉ ለአንዱ ዘረኛ በሰጡት መልስ ምንሊክ ባይሰበስቡህ እራስህን አንዱ የጎረቤት አገር ታገኝዉ ነበር ያሉት ዛሬም በባዶ ሜዳ ለሚያብዱ ነገር ለጠፋባቸዉ ዘረኞች በግልጽ ሊነገር ይገባል እላለሁ። እነዚህ የምንሊክን ታላቅ ስራ የማያዉቁ ደካሞች ምንሊክ ባይሰበስቧቸዉ ስማቸዉ ሌንጮ/ሀጎስ/ጫላ/ለማ… ከመሆን ይልቅ ሪካርዶ/ሮበርት/ዴቢድ ሲሆን ሀይማኖትም በልካቸዉ ይሰፋላቸዉ ነበር። የሚያሳዝነዉ የፕሮፌሰሩ ጽሁፍ ከግማሽ ቀን በላይ በድረ ገጾች ላይ አልዋለም ምክንያቱም የታወቀ ነበር።
እዚህ ላይ ላልፈዉ የማልፈልገዉ ስለ ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ በኢሳይያስ ታግተዉ ጻፉ በሚባሉ ዘረኞች በነ አስመሮም ለገሰና 12ኛ ክፍል ባልጨረሰ መሀይም ተጽፎ ለንባብ ሲበቃ ማየት በእጅጉ ያሳዝናል ዛሬ በኢትዮጵያ ምስረታ በኢትዮጵያ ስነጥበብ በኢትዮጵያ አስተዳደር የኦሮሞ አሻራ ያላረፈበት አንድም ነገር አይገኝም። በሀገር እና ከሀገር ዉጭ ታላላቅ የኦሮሞ ጠቢባን ባሉበት አለም ስለ ኦሮሞ ህዝብ ታላቅነት፤በደል፤ጭቆና ከኤርትራ ኤክስፖርት ሲደረግ ከምንም በላይ የሚያሳፍረዉና የሚያዋርደዉ የኦሮሞን ህዝብ እንጂ ሌላዉን አይሆንም። የኦሮሞ ህዝብ ሞግዚት የሚያስፈልገዉም አይደለም የኦሮሞ ህዘብ በደሉን እና ጥቅሙን በሚገባ ያገናዝባል የኦሮሞ ህዝብ ህመም ከአማራዉ፤ጉራጌዉ፤ወላይታዉ…. በላይ እነ አስመሮም ለገሰንና ተስፋዬ ገ/አብን ለምን እንዳመማቸዉ ነገሩ ግልጽ ነዉ እነሱን ያቃታቸዉን ሀይል እነሱ እንዲሞክሩላቸዉ ታስቦ ነዉ ታዲያ ኦሮሞ ይህን አጣ? የምን ንቀት ነዉ? ከኦሮሞ እና አማራዉ የተወለደ 10 ሚሊዮን ህዝብ ከመኖሩም በላይ የአንዱን ደም አጥርቶ አንተ ከዚህ ነህ አንተ ከዚያ ነህ የሚያሰኝ ሁኔታም አይኖርም። አሁንም የኦሮሞን ህዝብ አታላግጡበት አርፋችሁ ቁጭ በሉ ሊባሉ ይገባል። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምነዉ ተስፋዬ ገ/አብ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ሆነ ያሉት እነ አስመሮም ለገሰን አፍ አዘግቶ እዛዉ እስር ቤታቸዉ ሊያስቀምጣቸዉ በቻለ ነበር ታድያ እነሱ ለክብር ስላልተፈጠሩ በተቻላቸዉ መጠን ቶሎ ትርፍ ያመጣልናል ብለዉ የሚሉትን ብቻ መሞከር ስለሆነ ሊማሩ አይችሉም። እንደ እዉነቱ ከሆነ በዛሬዉ አለማችን ከማንም በላይ በባርነት ቀምበር ስር ያለ ህዝብ ቢኖር ኤርተራዊ በመሆኑ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ካማራቸዉ እዛዉ በእስር ቤት የሚኖረዉ ህዝባቸዉንና እራሳቸዉን ነጻ እንዲያወጡ ይጠየቃሉ ለዛም ካልታደሉ ተራ የኢሳይያስ ካድሬ መሆናቸዉ ቀርቶ በክብር እንዲቀመጡ እናሳስባለን 90 ሚሊዮን ህዝብን መናቅ የጤንነት አይመስልም።
ለማጠቃለል በስልጣን ላይ የተቀመጡት ህዋቶች በአቶ መለስ ምንጠራ አክራሪ ትግሬዎች ተነስተዉ በአብዛኛዉ ኤርትራ እና አፍቃሪ ኤርትራዉያን ቦታዉን በመያዛቸዉ የትግራይ ወንድሞቻችን ነገ ከሚመጣዉ ጥፋት እራሳቸዉን ለመከለከል ከወገናቸዉ ጋር ሰልፍ እንዲቆሙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ትላንት የትግራይ ወንድሞቻችንን ነፃ ለማዉጣት፤ የትግራይ ክልል ባድሜ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ድምበሮች እንዲከበሩ በዛ የፈሰሰዉ ደም ከንቱ ሁኖ ቀርቷል። ባድሜም ለኤርትራ ሊመለስ ዉስጥ ለዉስጥ ዲፕሎማሲዉ ተጧጡፏል ኤርትራዉያንም ያለምንም ችግር በኢትዮጵያ የቀድሞ ቦታቸዉን በመያዝ ላይ ናቸዉ። ትላንት የትግራይ ህጻናትን በቦምብ የፈጀ ሀይል ዛሬ ለትግራይ ህዝብ ወዳጂ የሚያደርገዉ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ህዝቡም አስተዳደሩም ትላንት የነበረ ነዉና። የኢትዮጵያም ህዘብ በችግሩ ጊዜ የችግሩ ተካፋይ ካልሆናችሁ የችግራችሁ ጊዜ ብቻ ድረሱልን ብትሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግነቱና እርዳታዉ ቀጣይነት ሊኖረዉ ስለማይችል ካሁኑ ማሰብ አግባብ ነዉ እላለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዛፎች የህልውና ተጋድሎ - በላይነህ አባተ

እንግዲህ በእነ ገበየሁ ባልቻ፤በላይ ዘለቀ፤በላይ ቃለአብ፤ኡመር ሰመታን፤ታከለ ገ/ሀዋያት፤አብዲሳ አጋ በነ አፈወርቅ ወ/ሰማያት እና ዛሬ ደግሞ እንደ ጎሹ ወልዴን
http://www.youtube.com/watch?v=me5_siVG-ys

አለማየሁ መሰለን የመሰሉ ጀግኖቻችን ባሉበት አገር ወገን ዉርድተን መቀበል በእጂጉ ይከብደዋል። እንግዲህ የተኛዉ ወገን ነቃ ብሎ እንዲጠበቅ መሰሪዎችም እንዲጠነቀቁ ያህል ነዉ እንጂ ምን ያልተጻፈ አለ ሰሚ፤ አንባቢና አገናዛቢ ከተገኘ። ይህችን ጽሁፍ ከከተብኩ በሗላ በህዋትና በሻቢያ መሀከል በራቸዉን ዘግተዉ ኢትዮጵያንን አግልለዉ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ በተዋራጅነት የሚያስቀምጥ አንዳንድ ድርድሮችን በማድረግ ላይ እንደሆኑ ጠቋሚ ጽሁፎች በብዛት ተሰራጭተዋል። ኤርትራ ኢትዮጵያ ኮሚቴም የሚባል የማወናበጃ ስብስብም በየቦታዉ እንደ አሸን ብቅ በቅ እያለ ነዉ። ብዙ ለግላጋ የኢትዮጵያ ህጻናት ያለቁበት የትግራይ ከልል ባድሜም በተዋራጂነት ለኢሳይያስ አፈወርቅ በእጅ መንሻነት ህዋአት ሊያስረክበዉ እንደሆነ ይገመታል። እንግዲህ ይህንና ሌላዉን አጠቃለን ስንመለከተዉ ኳሷ ያለችዉ የትግራይ ወንድሞቻችንን ክልል ስለ ሆነ ወደ ወገናቸዉ ተጠግተዉ የሚጠበቅባቸዉን ግዴታ እንዲወጡ አሳስባለሁ ለራሳቸዉም ጥቅም ሲባል። ከላይ እንደገለጽኩት የህጻናት ትምህርት ቤት በቦምብ ያጋየ ለትግራይ ህዝብ ወደፊት ወዳጂ ይሆናል የሚል እምነት ስለሌለኝ ከህዋአት ዉጭ ማሰብ እንዲችሉ በድጋሚ አሳስባለሁ።
እስከዛዉ በቸር ይግጠመን ሰመረ አለሙ ነኝ ከባህር ማዶ መልካም የፈረንጂ ገና
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

32 Comments

  1. LOOOOOOOOOOOOOL LOSER. Assab ina badimew keritobih Guraferdawin bagegneh. Tarikihin ferenj new yetsafelih. Le Oromo manim litsif yichilal. Gin lemin Oromo rasu alitekawemem, Bekiribu and memihir ke mekelle yetsafutin ye Ethiopia tarik bitaneb yemitaweraw hulu daydreaming indehone yigebahal. Egiziabiher Ethiopian indemiwedat yawekut kahun behuala ye Amhara gezi silemayinor new. Inanite sitimelesu izaw Bahir Darachiw tikeralachiw. Zeregninetin yetekawemachihu mesluachihu yeleyelet zeregnoch nachihu. VIVA FEDERALISM

  2. መልካም ነው አንተንም እንኮዋን ለፈረንጆቹ ባዓል በሰላም አደረሰህ ሃሳብህን ሙሉ በሙሉ እጋራለሁ እኛ ችግራቸውን ከወያኔ ላይ ነው ያለው ኢትዮጵያ ሃሰብን የማግኘት እድሎዋ ከወያኔ ውድቀት ጋር የተያያዘ ነው። ወያኔ ከወደቀ ሃሰብ የኢትዮጵያ እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው። ግን ችግሩ ወያኔ የጊዜ ገደቡ በተራዘ ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ትውልድ እየተቀየረ ይሄዳል በዛው ልክም ክሃዲው እየበዛ ይመጣል ሃገራዊ እና ወገናዊ ጥቅሞች ቀርተው ስለ ግል ጥቅም ብቻ ይሆናል ሃሳባቸው። አሁን እንደምናየው ማለቴ ነው ከዚህ በፊት መለስ እንዳለው 20 ዓመት መምራት ከቻልን አንድ ጭራሽ ስለ ሃገሩ የማይቆረቆር ዚጋ ማፍራት እንችላላን እንዳለው እና አሁን 20 አልፈው ወደ 30 ተሸጋግረዋል ይሄ ማለት ደግሞ ካባቶቻችን የወረስናቸውን የአልገዛም ባይነት እና የግል ጥቅምን አሳልፎ ለብሄራዊ ጥቅም የመስጠት ባሃላችን ጠፋ ማለት ነው። ብሄራዊ ስሚት የለለው ትውልድ ተትካ ማለት ነው ከዛ በሆዋላ የሚታሰበው ስለ ኢትዮጵያ ሳይሆን ስለ ቀበሌ እና ጎጥ ነው። ዋናው አጀንዳቸውም ይሄው ነው።

    • Dear much I fully agree with your assement that was too what I was trying to adress for fellow Ethiopians. Many thanks

  3. It is very difficult to understand what is the main intention or goal of Ato Semere’s article wants to articulate. His focus in analyzing all the sabotages and various crimes committed against ethiopia and its people interests by SHABIA and TPLF partners is well intentioned. But, the writer seems out of step in focusing on young Eritrian refugees whose only choice in life is to exile by any available means to any country which gives them shelter and temporary safety. These young people leave Eritrea not by choice but because of Isayas’ s brutality. As a world citizen Ethiopia and its people have an international obligation to give these young people safety and temporary security. Remember most of these young people were toddlers or born after SHABIA and TPLF held power in Eritrea and ethiopia. As yourself outlined the Eritrian government is one of the most brutal regime in the world and therefore the Ethiopian people have the obligation to support these young people including by providing them education. Our struggle as Ethiopians should only focus on in establishing a democratic ethiopia which protects the country’s and its people interests not by accusing vulnerable young refugees as a whole as a danger for ethiopia and its people. I don’t have any problem if you accuse the TPLF in not protecting ethiopian interests or SHABIA always trying to weaken ethiopia. But, your focus negatively on the young Eritrian refugees to me is a bit out of order.

  4. The surprise here is where was this chauvinist for the last 20 years. You must have buried your head in the sand until you thought that it is time to shade the sand and spread your hate propaganda. You thought that the death of Meles has opened for the Amhara hegemony to stick its head once again into an open air. You are fooled buddy. The TPLF will soon implement what should have been done before. Respect the constitution and the larger Ethiopian people will respect you.

    • This is who you are. Just stop crying about Ethiopia. You are one of the nationalities out of more than 80. Just cry for your dead ended hegemonic sentiment. You got all the time and power to settle your problem with Eritrea. You didn’t use it. Now the other nations and nationalities got the power and settled every problem. Cry alot for you cannot come back again. You see you are enemy to everybody in the neighbourhood. You are against, Eritrea, Tigray, Oromia, Wolayta, Somali, everybody. You guys are still thinking that this is time to creat a country. It long gone before the traitor Menilik II was dead. Over. Oromay. Victory for all Ethiopian nations and nationalities. Down with Neftegna

      • I forgot two other countries that the Amharas are against with: 1. They started to reclaim Djibouti (you can read lots o amhara websites stating Hailesilasse’s discussion with France reclaiming Djibouti )and 2. They are denying their father ’emiye’ Minilike’s signature for the boundary with the Sudan. Just listen to them, they will claim South Africa sooner or later. Crazy people

        • Mr. An Ertrian. You preferred to be free from us, why do cry loud now? We Ethiopians are one and we know what is best for us, we don’t need any advice from you. Stay away from us and don’t write about Minilk it is not you damn business any more, as you are neighboring country.

          • Why you always cry about Eritrea then? No Eritrean sites talk about you Amharas, Eritrea has been your salt for the last 100 years. Have you heard what Donald Payne said in the above Video. It seems you are 500 years ago. We are one, dinkem ite. It is easy for any ethinicity in Ethiopia to be one with Eritrean than you Amharas. You cannot represent Ethiopians. It long gone. Don’t forget what your Emiye Minilik did to Eritreans and all Ethiopians except you adgi Amharas because as a traitor he got some modern weapons. He escaped four times from Arsi. He was the one who betrayed the true Ethiopian unifier Atse Yohannes IV.

      • Dear aha and the likes what makes u to speculate I am neftegna? Dont u think it is short sightism?

  5. At times, I do wonder who the moderator (administrator) is for comments posted on ZeHabesha. Why do you let comments that are larger than the article itself and vile and name calling comments to go through? Who benefits from such Narrow minded, Ethnically Centered comments? Make the communication clean and civil.
    On the other hand, the separation of Eritrea from Ethiopia is a failure. After so many years, nothing has changed in the Eritrean highlands. Peace with Eritrea is helpful, however it must be on equal footing among other things.

  6. When you are going to end your dream. U r so professional to dream that is not yours. Don’t forget we are WE.

  7. Yekotun awerd bla yebbtwan talech

    when you are talking about Eritrea and Eritreans, you are loosing time and energy
    for nothing. Think about tomorrows Ethiopia. what will happen ???????

  8. ante mechem helm talmaleh yagoth mekabre yabath mekaber eritra alle ante aram ante atwagam mkniatu hodam slehonk weregna shentam yeshintam lige

  9. Ato alemu semerelot min aynet yegema astesaseb yaleh sew neh.endet ethiopia wede fit teramedalech endante aynetun agases yeza ?egzabeher balehebet keneastesasebeh yatfha!!!! ethiopia ethiopia ethiopia lezalelem tenur

  10. OBSESSION not the perfuem but there are some amhara (shinfila) so obsessed with Eritrea and Eritreans more so, so infatuated with HE President Isaias Afewerqi, that ther is not a day goes with out them being thinking about Eritrea, what a nice thing but as I said before there are some amhara unclean like shinfila, no matter what you can/will never be able to clean them.

    So we let them dwell in on Eritrea.

  11. በአቶ መለስ ምንጠራ ኢትዮጵያዊ የሀገር ፍቅርና ተቆርቋሪነት አቋም ያላቸው ትግሬዎች ተነስተዉ በአብዛኛዉ ኤርትራ እና አፍቃሪ ኤርትራዉያን ቦታዉን በመያዛቸዉ የትግራይ ወንድሞቻችን ነገ ከሚመጣዉ ጥፋት እራሳቸዉን ለመከለከል ከወገናቸዉ ጋር ሰልፍ እንዲቆሙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ትላንት የትግራይ ወንድሞቻችንን ነፃ ለማዉጣት፤ የትግራይ ክልል ባድሜ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ድምበሮች እንዲከበሩ በዛ የፈሰሰዉ ደም ከንቱ ሁኖ ቀርቷል። ባድሜም ለኤርትራ ሊመለስ ዉስጥ ለዉስጥ ዲፕሎማሲዉ ተጧጡፏል ኤርትራዉያንም ያለምንም ችግር በኢትዮጵያ የቀድሞ ቦታቸዉን በመያዝ ላይ ናቸዉ። ትላንት የትግራይ ህጻናትን በቦምብ የፈጀ ሀይል ዛሬ ለትግራይ ህዝብ ወዳጂ የሚያደርገዉ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ህዝቡም አስተዳደሩም ትላንት የነበረ ነዉና። የኢትዮጵያም ህዘብ በችግሩ ጊዜ የችግሩ ተካፋይ ካልሆናችሁ የችግራችሁ ጊዜ ብቻ ድረሱልን ብትሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግነቱና እርዳታዉ ቀጣይነት ሊኖረዉ ስለማይችል ካሁኑ ማሰብ አግባብ ነዉ እላለሁ።/ሰመረ አለሙ/ ጥሩ ሀሳብ ነው ያቀረብከው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው እያንዳንዳችን ትኩረት ሰጥተን በኢትዮጵያዊነት ስሜትና አደራ ነገሮችን መከታተል አለብን፡፡

  12. ማንበብ ስጀምር፣ እንደ
    .”ትምህርት ገበያ” ላይ ስላሉት SCHLÄFER እና አለቆቻቸው መቐለ ዘንዳ፣
    .ኢትዮጵያ የሁላችን፣ “ጦጣ ግንባር” የግላችን Traumatized for the next 5.000.000.000 years፣
    .ያለንበት ዘመን ሸፍጢ Chieftains of ምርጫዎች፣ ኢሳያስ ካለዘበኞች ስለመንቀሳቀሱና ህዝቡም ለእርሱ ስላለው “ፍቅር”

    እና እንዲሁም ብዙ ሊባልባቸው የሚችሉ ነጥቦችን እያገኘሁኝ መምጣት ስጀምር፣ እኔም አስተያየቴን ለማካፈል ነጥቦችን መያዝ ተያያዝኩኝና፣ ግን በንባቤ መሃከል ላይ፣ የአርቃቂውን የጌታቸው ሃይሌ ቲፎዞ መሆኑን የሚያበስረው ነጥብ ላይ ስደርስ፣ ፍላጎቴ ሁሉ ፋሕ-ብትን(ት.) አለብኝና፣ ለካስ ኢትዮጵያን ለማዳን የሚቀርብ ስር ነቀል ትችት ሳይሆን፣ አለባብሶና ቀባብቶ የሚተሻሽ የእጅና የጓንቲ መጨባበጥ ተግባራት ላይ ነው የምገኝ ያለሁት፣ ብዬ፣ ለዛሬ ለመቆጠብ ወሰንኩኝ፣ ግን እስኪ ምናልባት ነገ፣ አለበለዚያም እንግዲህ….!

  13. ኤርትራዊያን ስደትኞች እንደማንኛውም ስደተኛ አለም አቀፍ ሕግን በጠበቀ መልኩ በሰላም የመኖር የመማር መብት አላቸው ግን ከምር ለኢትዮጲያዊ ተማሪዎች የመማር እድል ሳይሰጥ ለሌላ አገር ተወላጅ ቅድሚያ መስጠት አግባብ አይደለም የበፊቱ አይነት እሹሩሩ ውጤቱን ሁላችንም አይተነዋል (የራስዋ እያረረባት የሰው ታማስላለች እንዳይሆን የትም አገር ቅድሚያ ለዜጋ መሰለኝ.

  14. መማራችሁን ጠልተን ሳይሆን፣ ግን ዘላለማችሁን ግፈኛ ጠላትን ወደ ወዳጅ ዋሻ መርቶ በማስገባት ተግባራት ላይ እንደ የእውሮች ነጭ ብትር ሆናችሁ መሰማራታችሁን ጠላን………………….!

    እንደዚህ አይነቶቹን ደግሞ ለመታገል አገራችንን ከመውደዳችንም በተጨማሪ የሜዳው አሉላ እና የህሊናው አቡነ ጴጥሮስ ጀግኖቻችን አደራና ወገዛም አለብን::

    ” ለጠላት እንታግገዛ እንኳንስ ሰውን ምድሪቱንም አውግዣታለሁኝ…………….!”

    • Zere yakob amsgnalhu ytelatochachinen ytefat zegjit kzih belay btelakut asteyayetochi satgmet atqrem sewochu Ethiopian kalatfu enqlfe slemayiwesdachewu wegen yehone hulu leyuntun aswgedo lehageru ena andnetu ater huno meqom albet

  15. Please writer do not be scared by neighbours good relation if it will come and know the attitude of current generation, thanks to EPRDF; it showed us ETHIOPIA is much better after removal of infectious part (shabiya) and its asab used for camel drink

  16. eritrians people who r snake.All z time ty r againest ethiopia,ty wr mersineries of italia.we have 2 swep from ethio

  17. Zere yakob amsgnalhu ytelatochachinen ytefat zegjit kzih belay btelakut asteyayetochi satgmet atqrem sewochu Ethiopian kalatfu enqlfe slemayiwesdachewu wegen yehone hulu leyuntun aswgedo lehageru ena andnetu ater huno meqom albet

  18. I am so proud to be Ahmara , in every article some one are mentioning our name in negative way , but if you just think we were not in power for the last 40 years but you still intimidating and shown your inferiority complex in every comment . It is such a disease to be born with complex , hope one day the new generation will be free from this mess and have self pride not based on their ethnic back ground but for who they are. But the rest of you need lots of therapy to build or clean your complex , it is sad but true .
    From proud Ethiopian first and proud Amhara , long live for us ethiopian

Comments are closed.

Share