የብሄር እኩልነት!

‘የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን’ ማክበር ጥሩ ነው። ምክንያቱም ባህሎቻችን ስናቀርብ እርስበርሳችን በደንብ እንተዋወቃለን፤ ከተዋወቅን እንከባበራለን። ከተከባበርን አንድነታችን ይጠነክራል።

ግን …
ቀን ጠብቆ፣ አብሮ መጨፈር፣ ስለ ብሄር ብሄረሰቦች መዘመር በራሱ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ማረጋገጫና ዋስትና ሊሆን አይችልም። የሁሉም ህዝቦች እኩልነት ለማረጋገጥ አብሮ ከመጨፈር ያለፈ ተግብራዊ ዉሳኔ ይሻል።

‘ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩል ናቸው’ ብለን ከተነሳን ሁሉም ብሄራቸው ግምት ዉስጥ ሳናስገባ (ምክንያቱም ሁሉም እኩል ናቸው ብለናል) በኢትዮጵያውነታቸው እንመዝናቸው። ለማንኛውም ጉዳይ (ለስራ፣ ለስልጣን …) በትምህርት ደረጃቸው ወይ ብቃታቸው ወይ ሌላ ለሁሉም በእኩል ሊያገለግል በሚችል መስፈርት እንመዝናቸው።

ሁላችን እኩል ከሆንን አንድ ሰው ለመመዘን ጉራጌነቱ፣ ኦሮሞነቱ፣ ትግራዋይነቱ፣ አማራነቱ፣ ዓፋርነቱ፣ ሶማሌነቱ፣ ጋምቤላነቱ … ማስታወስ አያስፈልገንም። ማንነቱ የራሱ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ መመዘን መቻል በቂ ነው።

ሰው ለመመዘን ብሄሩ ግምት ዉስጥ ካስገባን ግን ሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩል መሆናቸው አናምንም ማለት ነው። ሺ ግዜ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብናከብርም ሰው እንደሰው መመዘን ካልቻልን በቃ የብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩልነት አላረጋገጥንም ማለት ነው።

ይሄ የመለየየት ችግር በብሄር፣ ብሄረሰቦች ብቻ አይደለም የሚስተዋለው፤ በአንድ ብሄር ዉስጥም አለ። ለምሳሌ በትግራይ ክልል አንድ ሰው ለስራ ወይ ለሌላ ሐላፊነት ሲፈለግ የመጣበት አከባቢ ግምት ዉስጥ ይገባል። ስራ ከመሰጠቱ በፊት ከዓድዋ፣ ተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ራያ ወዘተ እየተባለ በትምህርት ደረጃውና ብቃቱ መሰረት ሳይሆን በትውልድ አከባቢው ነው የሚመደበው (የሚመዘነው)።

ሰው በመጣበት አከባቢ መሰረት ከተመዘነ እኩልነት የለም ማለት ነው። ስለዚህ እኩልነት የሚረጋገጠው በጭፈራ ሳይሆን በተግባር ነው። የሰው መብት በሕገመንግስት ስለተፃፈ ብቻ መብቱ ተከበረ፣ ተፈፀመ ማለት አይደለም። በተግባር መታየት አለበት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎሣ ፖለቲካ፣ የጎሣ ግጭቶች እና መዘዛቸው በኢትዮጵያ (በዘመነ ወያኔ)

አዎ! ሰው በብሄሩ ሳይሆን በተግባሩ መመዘን አለበት።

6 Comments

  1. አቶ አብርሃ ፡

    በጣም ግሩም አስተያየት ነዉ የሰጡት። የሰው ልጅ መመዘን ያለበት በስራዉ ነዉ።

  2. አቶ አብረሀ እንደፃፈው በስራ ነው እንጅ በጭፈራ እኩልነቱ አይረጋገጥም። አባቶቻችን እንደሚሉት ሰው ብዙ ሆይ ሆይና አሻሻ ገዳዎ ካበዛ መወደቂያው ደርሶአል ማለት ነው።

  3. the author should know that the ethno-fascist Tigre liberation front used ethnic differences as a political weapon to divide and rule. IT WAS NOT OUT OF GOOD INTENTIONS THAT THE FASCIST Tplf ethnic classification of people.

    when you apply for a job in Ethiopia, the first thing THAT IS LOOKED AT IS THE ETHNICITY OF the person. In tigraie region they even look at the viliage or the district you came from.

    You are obliged to to live and work in the ethnic kilil you have been assigned by TPlf. TPLf made it difficult for people to find work outside their own ethnic kilil.

    If people cannot work together, live together what do they have in common? NOTHING! ths is the situation being created by Tplf.

    Tplf say come to ethnicity day once in a year and dance together, and everything will be alright. what a nonesense.

  4. አብርሃ ደስታ ከመቐለ አሁን ከአማርኛ ወደትግርኛ በኋላም ወደሻቢያህወአት ቋንቋ ተርጉመው አስረዱልን በለው! *እንግዲህ ላለፉት ዓመታት ሁሉ እኛ የምንለው የተሳሳተ ከነበር አሁን ትግርኛ ተናጋሪው በራሱ ቀዬ፣ ቋንቋና ክልል ችግር እንዳለ ካመነና ከመሠከረ አልተሳሳትንም ሰውም አሳስተን አላጣላንም። እውነትም ሻቢያህወአት ለየት ያለ ፍጡር ነው ማለት ነው።….”ፊሲካል ባላንስና” “ፊዚካል ባላንስ” የጠፋበት ማን ነበር? ድሮ ልጆች ሆነን ኤርትራና ትግራይን በካርታ እነጂ በተግባር ሳንለይ በጭፋሮ ስንሽከረከር ኖርን አዞረን .. *እኛ የሞቱ ጠ/ሚ አመራር በቡድን አሉና የአድዋ ልጅና ቤተሰብ ጓደኛ አበልጅ ይዘው በሕገመንግስቱ (በማኒፌስቶአቸው) ፩ገፅ ተኩል ሥልጣን ጠቅልለው ብራስልስ ሲደርሱ ክልትው አሉ። አሁን አመራር በኅብረት(ህወአትሻቢያ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝቦች) ሆኑ የኢትዮጳያ ልጆች በለው! መሪና ተመሪው ያልታወቀ (በህብረት) የደቦ አማራር ማታ አንዱ ባለሥልጣን መሳይ ያመነውን ከሰዓት ሌላው ባለሥልጣን መሳይ ያስተባብላል፣ጭራሽ ማታ ላይ ሌላኛው ባለሥልጣን አልሰማሁም ግን አይቻለሁ ቢሆንም በፍጽም አይደረግም አላውቅም ይላል። (አቤት በሚኒስትር ማዕረግ ያለህ!) አሁን ባለው የቀድሞ አሸባሪ(ድልድይ0 ባንክ ዘረዘፊና ጎተራ ገልባጭ …አሁን ባለሀብት ኢንቨስትር በሆነበት ወቅት ዕድገትና ብልጽግና መትረፍርፍ ነበረበት! አሁንም ህፃናት በባዶ እግራቸው ይሄዳሉ፣ በባዶ ሆድ ባዶ ሜዳ ይጨፍራሉ፣ ባዶ ሜዳ ላይ እንፀዳዳስ ቢሉ ምን አለና? የአልቅት ውሃ ይጠጣሉ እሱንም በወረፋ፣ ቅማልና ትኋን ይግጣቸዋል…የውጭ ዜጋ በቁም ገዝቶአቸዋል፤የዳቦ ወረፋ ስኳር እጦት ኑሮ ውድነት፣የትምህርት ትፋት፣የጤና ቀውስ ተመረተበት ሥርዓት ለመሆኑ ለምኑ ይሆን የሚጨፍሩት? ለመሆኑ ድህነት ርሃብ ጥማት በዘር በቋንቋ በብሔር እየለየ ይመጣልን፤አይ ሞኝነት! አለመማር ድንቁርና፣ ዘለዓለም ለወጣ ለወረደው ማጎብደድ፣የበይ ተመልካች የነዋሪ አኗኗሪ መሆን! ብሔር፩ ብሔረሰብ፪ እና ሕዝቦች፫ ለለቅሶ ቀን ለቱሪስት መስዕብነት የሚጠበቅና ተከልሎ የሚኖር ተናገሪ እንስሳ! “ደፍረውናል!ንቀውናል! ተዋርደናል! አሉ።” ልብል እንጂ<

  5. mr. abraha r u ignorant, arrogant or innocent? the way u r writing these days u r going down hill. I pity u.

Comments are closed.

Share