March 19, 2013
4 mins read

የአማረ ገመና ሲገለጥ!

(ከኢየሩሳሌም አ.)

አዲስ አበባ አየር ማረፊያ፣ ነሃሴ 13 ቀን 1997ዓ.ም ፣ ምሽት 2 ሰዓት…ለእረፍት መጥቶ የነበረ ጓደኛዬን ለመሸኘት በስፍራው ተገኝቻለሁ። ..እንዳጋጣሚ በቅርብ ርቀት የ<ሪፖርተር> ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊን አየሁት፤ ወደርሱ አምርቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ < ወደ አሜሪካ ለእረፍት የላከውን ልጁን ለመቀበል እንደተገኘ > ገለፀልኝ። …ከዛም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በመግባት ወሬ ቀጥልን፤ በመሃከሉ አማረ ፥ « ..ሲሳይና እስክንድር የጋዜጠኝነት ካባቸውን አውልቀው ለምን በግልፅ ፖለቲከኛ አይሆኑም? » ሲል በሹፈት አይነት ጠየቀኝ። « ምን ማለት ነው?» ስል መልሼ ጠየቅኩት፤ ..« በግልፅ የሚፅፉትን አታይም እንዴ?..የቅንጅት ዋና አቀንቃኞች ሆነዋል እኮ..» ካለ በኋላ አያያዘና « ..ይህችን አገር ልደቱና ሃይሉ ሻውል እንዲመሯት ነው የሚፈልጉት?…ልደቱ ነው አገር ለመምራት የሚቀመጠው?..» ሲል ያቺ የማውቃት የአማረ ፌዝና ሹፈት ፈገግታ በስሱ እያሳየኝ፤ …በዛ ሰሞን አማረ <አቋሙን> ይፋ አውጥቶ በቅንጅትና በጋዜጦች በተለይም በኢትኦጵና ምኒልክ ጋዜጦች ላይ በየሳምንቱ ..ለገዢው ፓርቲ የወገነ የቃላት ጦርነት የገጠመበት ወቅት ነበር።
አዳምጬው ሳበቃ እንዲህ አልኩት፥ « አማረ በምርጫው ማግስት ምን ብለህ ነበር የፃፍከው?..የሽግግር መንግስት ይቋቋም..ብለህ አልነበር?.. አሁን አቋምህን ለምን እንደቀየርክ አውቃለሁ!..» ስለው አይኑን በልጥጦ፥ « ምንድነው የምታውቀው?» አለኝ።.. < አዜብ መስፍን በቢቲ ማስታወቂያ ባለቤት ፀጋዬ በኩል አስጠርታህ ሌላ አራተኛ ሰው ጭምር ባለበት ምንድነው የተነጋገራችሁት?..አዜብ ከባለቤቷ የተላከ መልክት ነገረችህ፤ እንዲህ ስትል፥ « ሁሉም ጋዜጦችና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠራርገው እስር ቤት ይገባሉ። አንተም መግባት ትፈልጋለህ ወይ?..በማለት መለስ ንገሪው ብሎኛል፤» ብላ ነግራሃለች። ከዛም አቋምህን ቀየርክ፤ » አልኩት።...ግንባሩን አጨማዶ ገላመጠኝ። ..አያያዝኩና፥ « ደግሞስ አገሪቷን ማን ይምራ ነው የምትለው?..ሕዝብ የመረጠው ማንም ይሁን ማን…ድምፁ መከበር አለበት። አንተ ግን ካለ ሕወሐት/መለስ ሌላ ሊመራ አይችልም ..እያልክ ነው..» አላስጨረሰኝም..ጥሎኝ ሄደ። በወቅቱ ጉዳዩን በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ ፃፍኩት.. አማረ፥ ከማስታወቂያ ሚ/ር ለምን፣ እንዴትና በማን ተባረረ?...« ሪፖርተር » ጋዜጣ በመለስ ዜናዊ <ልዩ> ትእዛዝ እንደተቋቋመ ያውቃሉ?..አሁን የቲቪ ስርጭት እንዴትና በማን ትእዛዝ ሊጀምር ቻለ?…ከነደብረፂዮን ጀርባ በምስጢር የሚሰጠው ድጋፍና ለፓርቲው የሚያደርገው ስውር ተጋድሎ….በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እመለስበታለሁ።

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop