በቡድን ተደራጅተው “ሲያግቱና ዝርፊያ ሲፈፅሙ ነበር” የተባሉ ተያዙ

April 13, 2020

በጎንደር ከተማ ሁለት በሕገወጥ መንገድ የተደራጀ ካምፕ ተገኝቷል ተብሏል አንድ የቴሌ ሠራተኛ ”ሦስት ሆነን ታግተን በገንዘብ ነው የተለቀቅነው” ብሏል

በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ውስጥ በሁለት መኖሪያ ቤት ከባድ መሳሪያ ጭምር ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ላይ መንግሥት እርምጃ በወሰደበት ጊዜ አንድ ነጋዴና አንድ ሹፌር በአጠቃላይ ሁለት ሰዎችከታገቱበት መለቀቃቸውን የጎንደር ከተማ ከንቲባ አስታወቁ።በተጨማሪም ቡድኑ አራት የፀጥታ አባላትንና ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን እንዲሁም አራት ሰዎች መቁሰላቸውን አያይዘው ገልፀዋል። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አንዳንድ ሰዎች መንግሥት በዚህ አሳቦ “በፋኖስም የተደራጁ ሰላማዊ ወጣቶችን ለማጥፋት ነው” የሚል ሐሳብ ቢሰነዝሩም ሌሎች ደግሞ “የለም በከተማው ነዋሪዎችን በተለይ ነጋዴዎች እና ገንዘብ አላቸው ብለው ያሰቡትን ሰዎች የሚያስጨንቁ” ናቸው በሚልአስተያየት ሰጥተዋል። እንደውም መንግሥት እርምጃ ሳይወስድ ዘግይቷል የሚሉም አሉ።

በሌላ በኩል “ሳንጃ” በሚባል አካባቢ ከታገቱ በኋላ ቤተሰቦቻቸው በከፈሉት 500 ሺህ ብር መለቀቃቸውን ከገለፁ ሦስት የኢትዮ – ቴሌኮም ሠራተኞች አንዱን አነጋግረናል።

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

 የሕብር ሬዲዮ ሚያዚያ 4/5 ቀን 2012 ዓ.ም. ፕሮግራም

Next Story

ማን አወቀው – ማንስ ለየው፣  የዛን የፅልመት ገበና ?  – አስቻለው ከበደ አበበ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop