July 31, 2013
18 mins read

ስለ ኮሎኔል ታደሰ ጥቂት ልበል

ከፍል3
ይታያል የሩቅሰው
የክፍል ሁለት መጣጥፌ ያጠነጠነችው፡ የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ምላሸ በመስጠት ዙሬያ ሲሆን፡ ማሳረጊያየ፡ ለዚህ ጀግና እና እውነተኛ፡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፡ መሰወር ምክናያቱ አንድና አንድ ብቻ ነው። እሱም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ።በማለት ነበር፡፡ ወደዛሬው ምልከታየ፡ ለመግባት መንደርደሪያ የማደርገው፡ ደግሞ ተከታዩን ጥያቄ ነው።
3.1. እኛስ ስለ እሱ ምን ብለናል?
ኮሎኔል ታደሰ ሙሉለነህ፡ ከህዝብ እይታ ከተሰወረ በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም፡ ከሁለት አመት በላይ እየሆነው ይመስለኛል፡ እኛ ኢትዮጵያውያን፡ወገኖቹስ፡ የት እንዳለ ለማወቅ ወይንም ለማስፈታት ያደረግነው ጥርት ነበረ ወይ? ቢባል በጣም ጥቂት ሰዎች፡ በግል ካደረጉት ሙከራ በቀር፡ እንደህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅእነቱ፡ ታስቦበት፣ በተደራጀና በተቀናጀ፡ መልኩ የተከናወነ ነገር የለም። በተለይ አንጻራዊ ነፃነት ያለው፡ በውጭ ሃገር የሚኖረው፡ ኢትዮጵያዊ አሁንም ሆነ ቀደም ብሎ፡ ወገኖቻችን በታሰሩና በሚታሰሩ ጊዜ፡ በሰላማዊ ሰልፍ፡ የይፈቱልን ጥያቄ እንዳቀረብን ሁሉ፡ የኤርትራ መንግስት አዳመጠንም አላዳመጠን፡ ኤርትራ ሌላ ሀገር ሆናለች፡ እኛ ኢትዮጵያዊ ነን ሳንል፡ ኮሎኔል ታደሰን በተመለከተ፡ የኤርትራ ኢንባሲ በሚገኝበት ሀገር ሁሉ፡ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና፡ የኤርትራን አምባሳደሮች በማነጋገር፡ በእነሱ በኩል ለሀገሪቷ ፕሪዘዳንት፡ መልእዕክት እንዲደርስ ማድረግ፡ ስንችል አልሞከርነውም።
ጉዳዩ የኢትዮጵያውያንን ስሜት ሳይቆነጥጥና፡ በግልም ሆነ በቡድን፡ ሳይነሳ ቀርቶ ግን አይደለም፡ ኮሎሌል ታደሰ ሙሉነህ፡ከታሰረወዲህ፡በሚደረገው፡የሃሳብ ልውውጥ፡ ሁሉ ቀድሞውንም ቢሆን ሻብያ፡ ለኢትዮጵያ ነጻነት፡ አስቦ ይደግፈናል፡ ማለት ቂልነት ነው፡ የሚለው፡ ኢትዮጵያዊ በጣም ብዙ እየሆነ ነው። በዚህ ሰው መታሰር ምክናያትም፡ ኤርትራ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ፡ ግን በእሱ እስራት እጃቸው የሌለበትን፡ ተቃዋሚወች፡ ሳይቀር በጥላቻ አይን፡ የሚመለከቱና ከመደገፍ የተገቱ፡ ኢትዮጵያውያንም ጥቂት ቁጥር ያላቸው አይደሉም፡ ይህ ጥላቻ አድማሱ እየሰፋና፡ እየከፋ በመሄድ ላይ ስለሆነ በዚያች ሀገር በኩል፡ በሚሞከረው የነጻነት ትግልም ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ የሚናቅ፡ አይሆንም የሚል ስጋትም አለኝ። በኮሎኔል ታደሰ መታሰር ዙሪያ፡ በጥልቀት ከሚነጋገሩት፡ ኢትዮጵያውያን፡ ምሁራን መካከል አንዳንዶቹ፡ እንዲያውም ሻብያና ወያኔ፡ ለስልጣን እድሜ ማራዘሚያ፡ ይበጃቸው ዘንድ በሁለቱም ሀገር ህዝቦች ላይ የፖለቲካ ቁማር፡ እየተጫወቱ ነው እንጅ፡ አልተጣሉም፡፡ አሁንም ቢሆን በኤርትራ በኩል የሚንቀሳቀሱ የወያኔ ተቃዋሚዎች፡ በሰላም የሚኖሩት፡ ለወያኔ ስጋት መሆን እስካልቻሉ ድረስ ነው፡ እዚያ የሚደርሱ ከሆነ፡ የሚጠብቃቸው የእነኮሎኔል ታደሰ እጣ ፋንታ ነው። ጸባቸው ከምር ቢሆን ኖሮእማ፡ ወያኔ በባድመ ጦርነት ወቅት፡ ሻብያን መደምሰስ ከሚያስችለው ደረጃላይ ሲደርስ፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር፡ ኢትዮጵያዊ፡ ሻብያ በቀበረው ፈንጅ ላይ እንዲረማመድ በማድረግ፡ ካስጨረስ በሗላ፡ የሻብያን መሸነፍ ሲያይ፡ ውጊያው እንዲቆም ባላደረገና፡ የዚያ ሁሉ ህዝብ እልቂት ምክናያት የሆነችውን ባድመንም በድርድር ሰበብ አሳልፎ፡ ለኤርትራ ባልሰጠ ነበር፡፡
ሻብያም በፋንታው፡ ወያኔ እንዲጠፋ ቢፈልግ ኖሮ፡ በኤርትራ ውስጥ በእየቀኑ እንደዶሮ ጫጩት በመፈልፈል፡ የብሄር ጎጆ ቀልሶ የሰፈረውን፡ ተቃዋሚ ወይ ተባበሩ፣ እንቢ ከአላችሁ ደግሞ ከሃገሪ ውጡ በማለት፡ በግድም፣ በውድም ወደ አንድነት፡ እንዲመጣ አድርጎ፡ ቢያሰልፍው ወያኔ በአጭር ጊዜ ያልቅለት ነበር፡ ወ.ዘ.ተ. የሚሉ መከራከሪያወችን አጽኖት ሰጥተው ያቀርባሉ።
እኔን እንደሚመስለኝ ግን፡ የሻብያና የወያኔ ጸባቸው የእውነት ነው፡ የዛሪ መነጋገሬያችን ሻብያ ስለሆነ፡ የወያኔን አመለካክት ላቆየውና፡ በተለይም ሻብያ፡ ወያኔ እንዲወገድ ይፈልጋል፡፡ ችግሩ ግን በሻብያ እምነት፡ ከወያኔ ውድቀት በሗላ የምትመሰረተዋ፡ ኢትዮጵያ በምንም አይነት፡ መንገድ፡ ለኤርትራ ስጋት የማትሆንበትን ሁነኛ ማረጋገጫ መገኘት አለበት፡፡ ወይንም ስጋት በማትሆንበት መልክ መዋቀር መቻል አለባት። ያ እስኪረጋገጥ ግን ሻብያ፡ ከወያኔ የባሰ ጠላት እንዳይመጣበት ሰለሚፈራ እራሱ ወያኔ ባለበት ሁኔታ እንዲቆይ ይፈልጋል።
እራሴን በሻብያ ባለስልጣናት ቦታ አስቀምጨ ሳየው፡ ይህ ስሌታቸው፡ ትክክልም የሚሆንበት፡ እውነት አለው፡፡ ምክናያቱም አንድ ሀገር በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሀገር፡ ለመቀጠል ሀቀሟ የፈቀደላትን ሁሉ በማድረግ፡ የስጋት ምንጯን ማድረቅ፡ አለባት። ለኤርትራ ደግሞ ከአጎራባቾቿ ሀገራት መካከል፡ ስጋቷ ኢትዮጵያ ብቻ ነች። መንስኤውም፡ሌላ ሌላውን እንተወውና፡ የኢትዮጵያ፡ ታሪካዊይም፣ ህጋዊየም፡ አካሏ የሆነውን አሰብን፡ ያለህግ አግባብ፡ በወያኔ እንደተቸራት፡ ታውቃለች። ወሎ ይደር እንጅ ኢተዮጵያዊ ፡መንግስት በመጣ ጊዜ፡ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ የባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄን፡ ማንሳቷ የማይቀር መሆኑን፡ ኤርትራ በሚገባ ትገነዘባለች። ይህነን ስጋቷን በማያጠራጥር መልኩ ለማስወግድ፡ ግን ብዙ መስራት ስለሚጠበቅባት፡ በጥንቃቄ እየሄደችበት ነው፡ በበኩሌ ያለውን ተጨባጭ እውነታ፡ እስካሁን እያደረገችው ካለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጋር በማዛመድ፡ ሳየው ኤርትራ፡ ስለ ኢትዮጵያ ሶስት የፖሊሲ አቅጣጫዎችን፡ የምትከተል ይመስለኛል፡፡
እነሱም
1ኛ/እንደጎርቤት ሀገር ሶማልያ፡ ስራት አልበኝነት የሰፈነባት ያለመንግስት የምትኖር ሀገር እንድትሆን፡ በማድረግ፡ ስጋትነቷን ከማስወገድም ባሻገር፡ ያለከልካይ፡ በፈለገችው ጊዜና በሚያስፈለገው አካበቢ በመግባት፡ጥሪ ሃብቷንና የጥሪት ክምችቷን፡ በመውሰድ፡ ስትጠቀም መኖር።
2ኛ/ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ጠፍታ ቐንቐን መሰረት ባደረጉ፡ በርካታ መንግስታት፡ እንድትከፋፈል፡ በማድረግ፡ አሁን በወያኔ እንደሚፈጸመው፡ ለስሙ በመሪነቱ ቦታ ላይ ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩና በብሄር የተደራጁ፡ ተቃዋሚዎች እንዲቀመጡ፡ ተደርጎ፡ ቁልፍ ቦታዎች፡በሻብያ ካድሬዎች እንዲያዙና፡ ከአስመራ፡ በሚተላለፍ፡ ቀጭን ትእዕዛዝ፡በእጅ አዙር ቅኝ፡ የምትተዳደርና ለኤርትራ ስጋት እነቷ ያከተመላት፡ እንድትሆን ማድረግ፡፡
3ኛ/ ሁለቱ ካልተሳኩና የአንድነት ሃይሉ ከአየለ፡ በምንም መንገድ ይሁን፡ ተስማምቶ መልካም ጎረቤት በመሆን መኖር፡ የሚሉት ናቸው።
ስለዚህ እቅድ አንድና ሁለት፡ ተሞክረው፡ አለመስራታቸው ሳይረጋገጥ፡ እንደ እነ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ አይነት፡ በጽኑ ኢትዮጵያዊነት የሃገር ፍቅር የተጠመደ፣እንዲሁም፡ ሁለንተናዊ፡ የማድረግ አቅሙ ያለውን፡ ዜጋ ማበረታታት፡ ለዓላማቸው መሳካት የማይመች ስለሚሆን፡ ይህንን ሰው፡ ገለል እንዲል ማድረጉ፡ የሚጠበቅ ነገር ነው፡፡ ያም ቢሆን ግን ከሀገር እንዲወጣ፡ ማድረግ እንጅ፡ በፈቃድ የገባን የሌላ ሀገር ዜጋ፡ ለዚያውም
ከአንድ ሃገር ዲፕሎማት፡ የማይተናነስ ህዝባዊ እውቅና ያለውን ሰው፡ ማሰር ተገቢ አልነበረም ብቻ ሳይሆን፡ የኢትዮጵያን ህዝብ መናቅና፡ የፖለቲካ ጥበብም የጎደለው ነው ባይ ነኝ። ሌላውና የሚያሳዝነው ደግሞ፡ የጎዳኝ የእኔው ጠማማ ነው፡ አለ እንደሚባለው እንጨት፡ እንደ አለመታደል ሆኖ፡ የሻብያን የጥርጣሪ ክብሪት የጫሩትና፡ እንዳይጠፋም፡ በተከታታይ ቤንዚን በማርከፍከፍ እዚህ ደረጃ ያደረሱት፡ የእራሳችን ሰዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ነው።
ሻብያስ ቢሆን፡ እንዴት የአስተዳድርና፡ የዲፕሎማሲ ጥበብ የሚባል ነገር አይታየውም? ኮሎኔል ታደሰን፡ እኮ በምርኮ አልያዘውም፡ ለምኖና ሊያታግለው፡ ቃል ገብቶለት ነው ወደ ሀገሩ ያስገባው፡ ከገባም በሗላ ብዙ ሰዎቹን፡ በተዎጊ ጀት አብራሪነት፡ ያሰለጠነ፡ ባለውለታው ነው፡፡ እንኳን መንግስትን ያህል ተቋም ይቅርና ግለሰብ እንኳን ቃሉን ያከብራል፡ ይህ ሰው እንኳን ያላጠፋውንና ቢያጠፋና፡ ሺህ ክስ ቢቀርብብትም፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከረሁት፡ ቃል ገብቶ እንዳስገባው ሁሉ በሰላም፡ ከሃገር እንዲወጣ ይደረጋል እንጅ፡ እንዴት ይታሰራል? የኤርትራ መንግስትስ እንዴት ቃሉን ይበላል? ወደፊት ለሁለቱ ሃገር ህዝቦች፡ ግንኙነትስ እንዴት አያስብም? ነው ወይንስ ከምር ወደፊት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንዳትኖር ማድረግ እችላለሁ፡ ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶ፡ ይሆን?
ይህ ጥያቄ ሁል ጊዜ በሃሳቤ ይመላለሳል፡ በዚህ አጋጣሚ እስኪ የግል ምኞቴን ላስቀምጥ፡ ሻብያዎች 1ኛወንና 2ኛውን፡ የፖሊሲ አቅጣጫ፡ እንደ ቀን ቅዠት ቆጥረው በማለፍ፡ 3ኛው ላይ ቢያተኩሩ መልካም ነው። ምክናያቱም፡ በጦርነት ማንም ያሸንፍ ማን አሸናፌም፣ ተሸናፌም፣ የሚደርስባቸው ሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ቀላል አይሆንም፡፡ ስለዚህ ለሁላችንም የሚበጀው ሰላሙ ሰለሆነ፡ ደጋግመው ሊያስቡበት ይገባል እላለሁ።
ወደመነሻዬ ልመለስና፡ ላጠቃለው፡ በፊት የተናገረን፣ ሰው ይጠላው፡ በፊት የደረሰን ሰብል ወፍ ይበላው፡ እንዲሉ ሆኖ እነኮሎኔል ታደሰ፡ ቀድመው በመገኘታቸው፡ የችግሩ ግንባር ቀደም፡ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል። እኛ ኢትዮጵያውያንም፡ እየከፈሉ ያሉትን ዋጋ በአይናችን እያየን፣ በጆሮአችን እየሰማን፡ ብዙ ማድረግ ስንችል፡ ምንም ነገር ሳንሞክር፡ ዝም ብለን ተቀምጠናል። ለጽሁፌ፡ መግቢያ ለአደረግሁት፡ እኛስ ምን ብለናል፡ ለሚለው ጥያቄ መልሱ፡
አልናገርም እንዲያው ዝም ጥርቅም፡
ጊዜ የሚወልደው አይታወቅም።
እንዳለው ሟቹ አርቲስት ይርጋ ዱባለ፡ ዝም ጥርቅም ብለናል የሚለው ነው። ድርጊቱ በወያኔ የተፈጸመ ቢሆን እንኳ፡ ጊዜ የሚወልደውን ብንጠብቅ ጥቂትም ቢሆን ተገቢነት በኖረው ነበር፡ በሻብያ በኩል ግን ጊዜ የሚወልደው አጋጣሚ ያለ አይመስለኝም፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ ላይ ሁነን ልናከናውነው የምንችለው፡ብዙ በጣም ብዙ ነገር እያለ፡ ዝም ማለታችን፡ አሳዛኝም አሳፋሪም ነገር ነው። ለመሆኑ ለትናንት ጀግኖቻችን፡ ስራ እውቅና ካልሰጠን፡ ለዛሪ ጀግኖቻችን፡ በችግሮቻቸው ካልደረስንና፡ ገድላቸውን በመተረክ፡ አርያነታቸውን አጉልተን ለተተኪው ትውልድ ካላሳየን፣ እንዴት ነው ለወደፈት ሀገርን ከጥፋት ህዝብን ከውርደት፡ ሊታደግ የሚችል ጀግና የምናፈራው? የምንተካውስ??
ሳምንት በመሰናበቻ ቅኝቴ እስክመለስ ለዛሪን አበቃሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ አሜን!!!!
ሀምሌ ወር2005 ዓ.ም

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop