July 20, 2011
7 mins read

እጅዎ ስለጤናዎ ምን ይናገራል

በሰውነታችን ጤና አንዳች እክል ሲደርስብን ሰውነታችን ይህን የጤና መታወክ የሚገልፅበት የተለያዩ መንገዶች አሉት፡፡ ለምሳሌ የሰውነት ኢንፌክሽኖች ሲያጋጥሙን በትኩሳት መልክ ስሜቱን ሊያሳይ ይችላል፡፡ አንዳንዴ ግን እነዚህ ምልክቶች ሊያዘናጉንና ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊመሩን ይችላል፡፡ በዛሬው ጽሑፋችን የእጃችን ጣቶችና መዳፋችን ከጤና አንፃር ምንን እንደሚያሳዩ እንመለከታለን፡፡ ምን ያህል የጣቶችዎ መርዘም፣ የጥፍሮችዎ ሁኔታ እንዲሁም የመዳፍዎ አቀማመጥ ስለ ወደፊቱ የጤናዎት ሁኔታ እንደሚነግሮት ያውቃሉ?
የሚያልቡ ጣቶች
ሁላችንም እንደምናውቀው ጨዋማ ምግቦች ለሰውነታችን ሙቀት በመስጠት እንዲያልበን ያደርጉናል፡፡ ይሁንና ከምንጊዜውም በተለየ መልኩ ጣቶች ቀለበት መንቀሳቀስ እስኪያቅተው ካበጡና ካላበው ሃይፖ ታይሮይድዘም /hypothyroidism/ ለተባለው በሽታ መጋለጣችንን እየነገረን ነው፡፡ ሃይፖታይሮይድዘም ማለት ሰውነታችን በጤነኛ መልኩ መንቀሳቀስና ስራ እንዲሰራ የሚያግዘው የታይሮይድ እጢ የመመራት እጥረት ሲከሰት ነው፡፡ የታይሮይድ ዕጢ ችግር የእንቅስቃሴ ችግር፣ የሰውነት ክብደት መጨመር እንዲሁም በሰውነት ውስጥ ውሃ መቋጠርን ያስከትላል፡፡ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የቆዳ ህክምና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ጀኒኪም እንደገለፁት፣ ይህን የታይሮይድ ችግር መከላከል ካልተቻለ ለአደገኛ የልብ በሽታ ከመጋለጥ አልፎ እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያደርስ ይችላል፡፡ የሚያሳክክ እንዲሁም የሚያቃጥል ቀይ መዳፍ ኤክዜማ /eczema/ ለተባለ አደገኛ የቆዳ ህመም መጋለጦትን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ታዲያ ጭንቀት ላይ ካሉ የሚብስ ነው፡፡ ይህን ሁኔታ ለመቀነስ ታዲያ ኬሚካሎችን እጆችዎን አለማስነካት እንዲሁም በሚያፀዱበት ወቅት የተለያዩ የእጅ ጓንቶችን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ካልረዳዎት ታዲያ ችግሮት ምን አልባትም ከሚያደርጉት ጌጣጌጥ የመጣ አለርጂ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው የሚያደርጉት ጌጣጌጥ ከኒኬል የተሰራ ከሆነ ነው፡፡ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች በእርግዝና ወቅት የሰውነታቸው ደም መጠን ስለሚጨምር መዳፋቸው ቀይ ከለር ሊይዝ ችላል፡፡
የገረጡ ጥፍሮች
በሳንቲያጎ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የአናቶሚ ፕሮፌሰር ዶ/ር አንቶኒ ማርቲኔዝ ጥፍሮትን በሚጫኑ ጊዜ ወደ ነጭ መቀየር አለባቸው፡፡ ሲለቁት ግን ወዲያውኑ ወደ ሮዝ መመለስ አለበት፡፡ ይሁንና ጥፍርዎትን ተጭነው ከለቀቁ ከአንድ ወይም ከሁለት ደቂቃ በላይ ነጭ ሆኖ ከቆየ ለደም ማነስና ለብረት ዕጥረት የተጋለጡ ነዎት ብለዋል፡፡
ይህ ሁኔታ ታዲያ ለከፋ የልብ ህመም ሊያጋልጥዎ እንደሚችል ተረድተው በአፋጣኝ ዶክተርዎን ቢያማክሩ መልካም ነው፡፡ ይህን ሁኔታ ለመከላከል ታዲያ የብረት ንጥረ ነገር የያዙ የምንላቸውን ምግቦች መመገብ እንዲሁም በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ተገቢ ነው፡፡
የደነዘዙና ሰማያዊ የጣት ጫፎች
ይህ ሁኔታ ለራይናውድ /Raynaud/ በሽታ መጋለጦትን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም ማለት ደም ወደ ጣቶች መምጣት ሲያቆም ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ከአምስት እስከ አስር በመቶ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት ነው፡፡ ‹‹በሴቶች ላይ በተለይ የተለመደ ሲሆን አንዳንዴ በቅዝቃዜ እና በጭንቀት ሊመጣ ይችላል›› ብለዋል ዶ/ር ማርቲኔዝ፡፡ ይህ በሽታ ዘላቂ ሊሆን የሚችል ሲሆን በአብዛኛው ግን ለሰዓታት ብቻ የሚቆይ ነው፡፡ ይህን ለመከላከል ታዲያ ሲጋራ አለማጨስ፣ ካፌን የበዛበትን ነገር አለመጠቀም እንዲሁም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
ከለር የሌላቸው ጥፍሮች
ይህ ሁኔታ ከፈንገስ የሚመጣ ሲሆን አንዳንዴ የስኳር በሽታ ምልክትም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ለመቆጣጠር ጥፍሮትን በንፅህና መያዝ፣ የሰውነት የስኳር መጠንን መቆጣጠር እንዲሁም ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገብ ተገቢ መሆኑን ዶ/ር ኪም ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተለየ መልኩ ጥፍሮት ቢጫ ወይም ግራጫማ ቀለም ከያዘ የጥርስ ማጽጂያ ሳሙናዎችን በመጠቀም ጥፍሮትን ለማፅዳት መሞከር ለችግርዎ መፍትሄ ሊሆን ይችላል፡፡
አጫጭር ጣቶች
ሴቶች ጥፍራቸው ከተገቢው መጠን አንሶ ካገኙት ለኦስትራኦ አርትራይትስ /osteoarthritis/ እንዲሁም ለፓሊሳይስቲክስ ኦቫሪያን ሲንድረም /Polycystic ovaridn syndrome/ ለተባሉ በሽታዎች መጋለጣቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እነዚህ በሽታዎች መውለድ አለመቻልን የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለልብ በሽታ የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ ይህን ለመከላከል የሰውነት ክብደትን በማስተካከል በሽታውን መከላከል ይቻላል፡፡µ

Latest from Blog

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

Go toTop