July 23, 2024
9 mins read

በግርማዊ ጃንሆይ ኃ/ሥላሴ የአፍሪቃ አባት!! በልደታቸው ቀን በጨርፍታ ሲታወሱ፤

haile selassie 2በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

ታሪክ እንደሚያወሳው ግርማዊነታቸው ዐፄ ኃ/ሥላሴ ከሕዝባቸው ጋር በመሆን ለአፍሪካ አንድነትና ነጻነት በብርቱ የታገሉና የደከሙ ታላቅ ሰው ናቸው።

ግርማዊነታቸው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን- ለጋናው የነጻነት አባት ዶ/ር ክዋሜ ንኩርማ፣ ለኬንያው የነጻነት አርበኛ ለጆሞ ኬንያታ፣ ለደበብ አፍሪቃው የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ሮሂላላ ማንዴላ፣ ለዛምቢያው ጁሊየስ ኔሬሬ፣ ለሴኔጋሉ ፓን-አፍሪካኒስት ሴዳር ሴንጎር… በአጠቃላይ በባርነትና በቅኝ ግዛት ቀምበር ስር ሆነው ሲማቅቁ ለነበሩ አፍሪቃውያም የነጻነት ተስፋ ቀንዲል ከፍ አድርገን ያሳዩ/ያሳየን ሕዝብ ነን።
ጥቂት የታሪክ አብነቶችን እናንሳ እስቲ፤

ከ60 ዓመታት በፊት የኬንያው ‹‹የማኦ ማኦ›› ሕቡዕ ነጻ አውጭ ድርጅት መሪ የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ለሰባት ዓመት ያህል በእንግሊዝ መንግሥት ታስረው ነበር፡፡ በወቅቱም የኢትዮጵያ መንግሥት ትምህርቷን በዩኒቨርሲቲ ትከታተል ለነበረችው ለጆሞ ኬንያታ ሴት ልጅ፣ በየወሩ ሁለት መቶ ሃምሳ የኬንያ ሽልንግ በኢትዮጵያ መንግሥት ጄኔራሌ ቆንሲሌ አማካይነት ይሰጣት ነበር፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ ንጉሥ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ኬንያ ላይ ደርሶ ለነበረው ረሃብ ዕርዳታ የሚውል በኬንያ የብሪታንያ ተወካይ በነበሩት በሰር ሃምፍሬይ በኩል ሁለት መቶ ሃምሳ ሺኅ ሽልንግ ለኬንያ ዕርዳታ ልግስና አድርገዋል፡፡

የኬንያው የነጻት አባት ጆሞ ኬንያታ ከእስር እንደተፈቱም፤ የሀገራችንን ውለታ በማሰብ ከሴት ልጃቸው ጋር በሀገራችን ይፋዊ ጉብኝት አድርገው ነበር፡፡ በወቅቱም በአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በቀድሞው የግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ልደት አዳራሽ ተገኝተው ባደረጉት ንግግራቸው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላደረጉላቸው ውለታ ምስጋናቸውን አቅርበው ነበር፡፡
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ለኬንያዊው የነጻነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ ብቻ ሳይሆን ለታንዛንያው የነጻነት አርበኛ ለጁለየስ ኔሬሬ ከኢትዮጵያ መንግሥት የወር ደመወዝ ተቆርጦላቸው ይከፈላቸው ነበር፡፡ ከዚህ ከንጉሡና የኢትዮጵያውያን ውለታ የተነሳም ታንዛናውያን ነጻነታቸውን ከተጎናጸፉ በኋላ የውጭ አገር ሰዎች ከታንዛንያ ሲባረሩ ስድስ መቶ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ቤተሰቦች ከኪሊማንጃሮ ተራራ አጠገብ በግብርና የመኖር መብታቸው ተጠብቆላቸው በክብር እንዲኖሩና ከአገር እንዳይወጡ ተደርጎ ነበር፡፡
በርካታ የአፍሪካ አገሮች በቅኝ ግዛት ቀምበር ስር ኾነው ይማቅቁ በነበሩበት ጊዜ ኢትዮጵያ እነዚህ አገራትና ሕዝቦቻቸው ነጻነታቸውን እንዲያገኙ በተለያዩ መንገዶች ስትረዳ ነበር፡፡ አፍሪካውያን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነጻ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ፣ የኪስ ገንዘብ እንዲሰጣቸውና በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶችም ተደልድለው እንዲያስተምሩ ዕድል ተመቻችቶላቸው እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡
በተጨማሪም አገራችን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የነጻነት ታጋዮች ወታደራዊ ሥልጠና፣ ዕርዳታና ድጋፍ በማድረግም የበኩሏን ከፍተኛ የኾነ አስተዋጽኦ አድርጋለች፡፡
ለአብነትም ያህል፤ የደቡብ አፍሪካው የነጻነት ታጋይ፣ ኔልሰን ማንዴላ፣ የዚምባቡዌው ሮበርት ሙጋቤና የበርካታ አፍሪካውያን የነጻነት ታጋዮች ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠትና አስፈላጊ የኾነውን ዕርዳታ በማድረግ አፍሪካውያን ነጻነታቸውን ዕውን ማድረግ እንዲችሉ ትልቅ ሚና ተጫውታለች፡፡ ከኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠና ጋር ተያይዞም ጄ/ል ታደሰ ብሩ፣ ኮ/ል ፈቃዱ ዋኬኔ፣ ሻምበል ጉታ ዲንቃ የመሳሰሉ ጀግኖች ኢትዮጵያውን የሚታወሱ ናቸው፡፡
በተመሳሳይም ኢትዮጵያ- የደቡብ አፍሪካው የኤ.ኤን.ሲ፣ የሞዛምቢኩ ሬናሞ፣ የናምቢያው ሰዋፖ ነጻ አውጭ ፓርቲዎች ከወታደራዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገርም በአዲስ አበባ ቢሮአቸውን እንዲከፍቱና ሕዝባቸውን መቀስቀስ እንዲችሉ የሬዲዮ ሥርጭት እንዲኖራቸው በማድረግ በአፍሪካውያን የነጻነት ትግል ውስጥ የራሷ የኾነ ደማቅና ጉልህ አሻራን ትታለች፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የአንጎላ ቅኝ ገዢ ከሆነችውና ከአገራችን ጋር የረጅም ዘመናት ግንኙነት ከነበራት ከፖርቱጊዝ መንግሥት ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እስከማቋረጥ ድረስ የሄደችው በዚሁ ለአፍሪካውያን ነጻ መውጣት ከነበራት ትልቅ ፍላጎት የተነሳ ነበር፡፡
እንዱሁም ንጉሡ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ/የኢትዮጵያ መንግሥት ናሚቢያ ነጻነቷን እንድትጎናጸፍ ከነበራቸው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳም ከላይቤሪያ ጋር በመሆን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሁለት ጠበቆችን በማቆም ዘጠኝ ዓመታት ያህል ለናምቢያውያን ነጻነት ተሟግታለች፡፡
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውን ለአፍሪካ አገራት ነጻ መውጣት ካደረጉት ትግልና ካበረከቱት ትልቅ አስተዋጽኦ ባሻገርም የተባበረችና በልጆቿ ኅብረት የጸናች አፍሪካ ዕውን እንድትሆን፣ በመሪዋ በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ፣ በእነ ጸሐፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ፣ በእነ ከተማ ይፍሩ፣ በእነ ክፍሌ ወዳጆ… በመሳሰሉ ወድ ልጆቿ አማካይነት አፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ኅብረት እንዲቋቋም ያደረገችው ታላቅ የኾነ አስተዋጽኦ በታሪክ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡
ግርማዊነታቸው ዐፄ ኃ/ሥላሴ ከሕዝባቸው/ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ለአፍሪቃና ለአፍሪቃውያን ያደረጉትን ታላቅ ውለታ ታሪክ ሁሌም የሚያስታውሰው፤ የሚዘክረው ነው!!
ሰላም!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop