October 27, 2023
7 mins read

የአማራ የሕልውና ትግል ላማረኛ ቋንቋ የከፈተው ትልቅ ዕድል

ሳይደግስ አይጣላም

Screen Shot 2021 09 05 at 125001 AM 600x223 1

አማረኛ ቋንቋ ማናቸውንም ነገር በቀላሉ ለመገለጽ የሚያስችል እጅግ በጣም ቀና፣ ቅን፣ ተጣጣፊና፣ በዚያ ላይ ደግሞ ውብ ቋንቋ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ደግሞ አማረኛ እንዳበጁት የሚበጅ ድንቅ ቋንቋ ነው።  ይህን እንዳበጁት የሚበጅ ድንቅ ቋንቋ በስርዓቱ በማበጃጀት፣ እንግሊዘኛን ጨምሮ ዐበይት ከሚባሉት ከማናቸው የዓለም ቋንቋወች ጋር አቻ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን እንዲበልጥም ማድረግ ይቻላል።   አማረኛ የሚበጃጀው ደግሞ የቆሸሸውን በማጽዳት፣ የተሳሳተውን በማረም፣ የተዘበራረቀውን በማደረጃጀትና አስፈላጊወቹን አዳዲስ ቃሎች በመፍጠር ነው፡፡  አስፈላጊወቹን ቃሎች ለመፍጠር ደግሞ ግእዝን የሚያህል ተቀድቶ የማያልቅ የቃላት ምንጭ አለው።

ዐረብኛን ከተለያዩ ቋንቋወች ጋር በማዳቀል ትናንት የተፈጠረው፣ የላቲን ፊደል የሚጠቀመው መናኛው የስዋሂሊ ቋንቋ የምሥራቅ አፍሪቃ ወል ቋንቋ (lingua franca) ለመሆን ሲበቃ፣ አፍሪቃዊ ፊደል ያለው፣ እንዳበጁት የሚበጀው ታላቁ የአማርኛ ቋንቋ ግን ድንበር ሊሻገር ያልቻለው፣ የጦቢያን ቢሮክራሲ ባብዛኛው የተቆጣጠሩት፣ አማረኛን እጅግ አምርረው የሚጠሉት የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን አንቀው ስለያዙት ብቻና ብቻ ነው፡፡  ከነዚህ የኦሮሞና የትግሬ አማራ ጠሎች ጋረ በመተባበር አማረኛን የሚወጉት ደግሞ ባማረኛቸው እንዲያፍሩ ተደርገው ጥራዝ ነጠቅ እንግሊዘኛ መፃፍና መናገርን ከምሁርነት የሚቆጥሩት የነ ዋለልኝ መኮንን ግርፎች ናቸው።

በደርግ ዘመን የአማረኛ ትምህርት ከዩኒቨርስቲ እንዲወገድ ያደረጉት አማራ ጠሎቹ የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃንና የነሱ አጫፋሪ አማራ ተብየወች ነበሩ፡፡  ለምሳሌ ያህል በ1976 ዓ.ም የፍልስፍና ትምህርት ባዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ባማረኛ ተሰጥቶ አመርቂ ውጤት ቢያስገኝም፣ አማራ ጠሎቹ የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን እንዲሁም አማራ ነን ባይ አጫፋሪወቻቸው  ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስተው ትምህርቱ ባማረኛ መሰጠቱ እንዲቀር አድርገዋል፡፡  በኦነግ ዘመን ደግሞ የጭራቅ አሕመድ የትምህርት ሚኒስቴር የሆነው ብርሃኑ ነጋ አማርኛ ቋንቋ በትምህርት ዐይነት ደረጃ እንኳን እንዳይሰጥ ከፍተኛ ዘመቻ ጀምሯል።  ይህን ዘመቻውን የጀመረው ደግሞ በራሱ ባማራ ክልል ውስጥ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ነው።

በሌላ በኩል ግን ሳይደግስ አይጣላምና የአማራ ሕዝብ ሊያጠፉት የተነሱትን ወያኔና ኦነግን በማጥፋት ሕልውናውን የማስጠበቅ ዘመቻውን እንደ ሰደድ እሳት አቀጣጠሎ ያያቶቹን መሬት ከፀራማሮች እያፀዳ ነጻ ማውጣት ጀምሯል።  ስለዚህም በነዚህ ነፃ በወጡ ቀጠናወች ውስጥ ሮሞ ወይም ትግሬ ይቀየማል ብሎ ሳይሰጋ ወይም ደግሞ ይሉኝታ ሳይሰማው እንግሊዘኛን ሙሉ በሙሉ ባማረኛ በመተካት ልጆቹን ሙሉ በሙሉ (ሁሉንም የትምህርት ዐይነቶች) ባማረኛ እያስተማረ እንደ ጃፓንና ኮርያ አገሩን በፍጥነት የሚያሳድግ ትውልድ በፍጥነት የመፍጠር ትልቅ ዕድል ተከፍቶለታል።  ይህ መቸም የማይገኝ ዕድል ሊያመልጠው ስለማይገባ ደግሞ እስክንድር ነጋንና ዘመነ ካሴን ጨምሮ ሁሉም ያማራ ሕዝባዊ ትግል አመራሮች በፍጥነት ሊተገብሩት ይገባል።

እንግሊዘኛ እንግሊዞች በቅኝ ወረራ ዓለም አቀፍ ቋንቋ እንዲሆን ያደረጉት፣  ውስጡ ለቄስ የሆነ፣ በግድ እንጅ በውድ ሊመረጥ የማይችል ቅጥ ያጣ ቋንቋ ነው፡፡  በተለይም ደግሞ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ለሰገል (science) እና ኪንሲን (technology) ሊያገለግል የቻለው አመቺ ሁኖ ሳይሆን በዓለም ልሂቃን ያላሰለሰ ድካም ነው፡፡  ስለዚህም የአሜሪቃ ኃያልነት ሲያከትም፣ የእንግሊዘኛም ዓለም አቀፍ ቋንቋነት እንደሚያከትም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል እንግሊዞኝ የዜሌንስኪ (Zelensky) ቀንደኛ ደጋፊወች የሆኑት ለዩክሬን ሕዝብ አስበው ሳይሆን፣ ራሺያ ድል አድርጋ የምዕራባውያንን የበላይነት ላንዴና ለመጨረሻ ከሰበረች፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲሁም የራሷ የእንግሊዝ አገር የመጨረሻው መጀመርያ (the begining of the end) መሆኑን በርግጠኝነት ስለሚያውቁ ነው፡፡

የፈረንጅ ቅጥቅጦች የሆኑት የትግሬና የኦሮሞ ልሂቃን እንግሊዘኛን አመለኩ አላመለኩ፣ የአማራን ሕዝብ የማይመለከት የነሱ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡  ባማንነቱ የሚኮራው የአማራ ሕዝብ ግን የሱ የራሱ የሆነ፣ እንዳበጁት የሚበጅ ምርጥ ቋንቋ እያለለት፣ ሳይቸግረው ጤፍ እየተበደረ፣ ፈረንሳይ ሲነግስ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝ ሲነግስ እንግሊዘኛ፣ ቻይና ሲነግስ ቻይንኛ እየተጠቀመ ከቋንቋ ቋንቋ የሚንጦለጦልበት ምንም ምክኒያት የለውም፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop